Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንድ ወጣቶች 'ስራ የማይጠፋበትና የሚያበላ ዘርፍ ምንድን ነው?' ብለው ይጠይቃሉ። በርግጥ የሚ | The Ethiopian Economist View

አንዳንድ ወጣቶች "ስራ የማይጠፋበትና የሚያበላ ዘርፍ ምንድን ነው?" ብለው ይጠይቃሉ። በርግጥ የሚያበላም ሆነ በፍጥነት ስራ የሚገኝበት ስለሚባል የትምህርት መስክ ዛሬ ላይ መወሰን ከባድ ነው።



ልጅ ሆናችሁ በምትመኟቸው ዘርፎች ተመርቀው ለለት ፍጆታ ትግል ውስጥ ያሉ ብዙ ናቸው። ከዚህ ዩኒቨርስቲ መመረቅ እድል ነው ትሉባቸው ከነበሩ ተቋማት ወጥተው የሰራተኛው ገበያው ያልወሰዳቸው ብዙ ናቸው።  ምርጫቸውን ሰፊ ለማድረግ ከአንድ በላይ ድግሪ ይዘው በአንዱም ያልተቀጠሩ ትንሽ አይደሉም።


ኮሌጅ አልሄድም ብለው ብዙዎችን ቀጣሪ የሆኑ ብዙ ናቸው! ኢኮኖሚ ውስጥ አንዳንድ ከፍተኛ ገቢ እየተገኘባቸው ያሉ መስኮች የኮሌጅ ድግሪ ግዴታ የሆነባቸው አይደሉም።


ስለዚህ ለመማር ዛሬ ላይ ስትወስኑ ወቅታዊው የሰራተኛ ገበያ፤ የኢኮኖሚ፤ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ እስከምርቃታችሁ እንደሚዘልቅ እርግጠኛ አትሁኑ።


የሰራተኛ ገበያው እና የቢዝነስ አዝማሚያው የሚወሰነው በጥረታችሁ እና ለሁኔታዎች ባላችሁ ተለዋዋጭ እይታ በመሆኑ ነባር መመዘኛዎችን በሂደት እየመረመሩ መሄድ ግድ ነው።