Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View T
የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View
የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.32K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-15 11:02:22 ማለፍ ለሚችል ፍላጎት/ፍጆታ ብላችሁ ብድር ውስጥ ላለመግባት ሞክሩ! የዚህ አይነት ልምድ ከፋይናንስ ነፃነት ማጣት እስከ ነባር ልምዶችን መቀየር የደረሰ ውሳኔን የሚጠይቅ ነው።
1.4K viewsWasyhun Belay, 08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 20:19:01 #ዋጋ_እንዴት_ይወጣል?


ቢዝነስ ለመጀመርም ሆነ በቢዝነስ ውስጥ ለመቆየት አስቸጋሪ ከሆኑ ነገሮች መካከል ዋነኛው ለሚያቀርቡት ምርት ትክክለኛውን ዋጋ እንዴት ማስቀመጥ እንደሚቻል አለማወቅ ነው፡፡ ትክክለኛውን መስፈርት ጠብቆ ዋጋን መተመን አለመቻል ጠቅላላ የቢዝነስ እንቅስቃሴን ህልውና ያናጋል፡፡


የዋጋ ተመን የሸማችን ሁኔታ በቀጥታ ይነካል፤ ምክንያቱም ሸማች ከምንም በላይ ለሸመታ ውሳኔው ዋጋን በተመለከተ ስሜታዊ ነው (Price Sensitivity) ይህ ሁኔታ ደግሞ አምራች እና ሻጮችን ስለ ዋጋ ሁኔታ እንቅልፍ እንዲያጡ ያደርጋል (የእኛ ሃገርን ሁኔን ገላጭ ባይሆንም)፡፡ የምርትም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ በተለመደ መልኩ ወይም ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ሊወሰን ይችላል፡፡ ነገር ግን ዋጋን ለመወሰን ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶች መሰረታዊ መስፈርቶች ናቸው፡፡


ሸማች ለሚሸምተው ነገር በአብዛኛው በቂ መረጃ አለው ተብሎ ይታሰባል! ስለዚህ ጊዜው እና ገንዘቡ የሚመጥነውን ዋጋ በራሱ በማስላት እርካታውን ለመጠበቅ ይጥራል፡፡ ስለዚህ አምራቾች እና ሻጮች ትክክለኛውን ሸማች ማወቅ እና ለሚያቀርቡት ምርት እስከ ስንት ድረስ የመክፈል ፍላጎት እንዳለው (Willing to Pay) ማወቅ በሳይንስ (Pricing Strategy) መመራት ያለበት የገበያ ጥናት አካል ነው፡፡


የዋጋ ሁኔታን ለመወሰን ከቢዝነሱ አይነት (ኢንዱስትሪ፤ ግብርና፤ አገልግሎት፤ ቴክኖሎጂ፤ ወዘተ)፤ ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ከሚሸምተው እና ከሚጠቀመው ደንበኛ አንጻር (Ideal Target Customers)፤ ምርቱ ወይም አገልግሎቱ ካስወጣው ወጪ አንጻር እንዲሁም ከተመሳሳይ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ካላቸው የዋጋ ንጽጽር አንጻር (Competitive Markets/Pricing) ከግምት መከተት አለባቸው፡፡


#ለምሳሌ፡ የችርቻሮ ሻጮች የዋጋ ተመን ከአምራቾች እኩል አሳሳቢ እና ሳይንሳዊ ለመሆን ላይገደድ ይችላል፡፡


አንድ ምርት ለመመረት ያስወጣውን ወጪ በጠቅላላ ደምሮ ይገባኛል የሚሉትን የትርፍ መጠን (Profit Margin) ጨምሮ ዋጋ ማውጣት በጣም ቀላሉ ነው (Cost-Plus Pricing):: ነገር ግን አምራቾችም ሆኑ ሻጮች ዋጋን አንዴ የሚወስኑት ጉዳይ ብቻ መሆን አይችልም! ምክንያቱም የሚያስቀምጡት ዋጋ የቢዝነሳቸውን ዘላቂነት የሚነካ መሆኑን ማወቅ ግድ ነው፡፡


#ለምሳሌ፡- የሚቀመጠው ዋጋ ወድ ሆኖ ሸማቾች የሚችሉት/የሚመርጡት ካልሆነ ከገበያ መውጣት ሊከሰት ይችላል በተቃራኒው ከመሰረታዊ ወጪ በታች ዝቅተኛ ዋጋ በማስቀመጥም በገበያው በቀጣይ ለመቆየት መቸገር ሊመጣ ይችላል፡፡ በርግጥ ሸማችን እና በገበያው የሚኖርን ዘለቄታዊ ቆይታ በማሰብ በውስን ክስረት መሸጥ ሊኖር ይችላል ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ አካሄድ ነው፡፡


አንዳንዴ አምራቾች ነባር ደንበኞቻቸውን መሰረት በማድረግ የተጨማሪን ዋጋ ሁኔታ መመርመር ይቻላሉ! ይህ የሸማችን የመግዛት አቅም እና ምክንያታዊነት ለማወቅ ይረዳል፡፡


ዋጋ ለማስቀመጥ የሚከተሉትን መስፈርቶች መከተል ተገቢ ነው እነሱም…..


1. ምርቱ ለመመረት ያስወጣውን ጠቅላላ ወጪ ማወቅ (Variable Costs)፡- አምራች ከሆኑ ለማምረት ያወጡት የግብዓት ወጪ፤ የሰራተኛ ወጪ፤ የማጓጓዝ ወጪ እና የስራ ማስኬጃ ወጪዎችን በመውሰድ እና የምርቱን መጠን ደምሮ ማስላት ማለት ነው:: እያንዳንዱ ምርት ተመርቶ ለመውጣት የፈጀው ሰዓት እንደወጪ ዝርዝር ይካተታል፡፡


#ለምሳሌ፡- አንድ ኪሎ ቲማቲም ለማምረት የግብዓት ወጪ 10 ብር ቢሆን፤ ለማምረት የፈጀው ጊዜ ወደ ገንዘብ ሲቀየር በኪሎ 2 ቢሆን፤ ተለቅሞ የሚሰበሰብበትን ሳጥን ለመግዛት የወጣው ወጪ በኪሎ 2 ብር ቢሆን፤ ምንአልባት ለማስተዋወቅ (ባነርም ቢሆን) ያስወጣው ወጪ በኪሎ 1ብር ቢደርስ፤ ቲማቲሙን ወደ ገበያ ለማድረስ ያስወጣው ወጪ በኪሎ 3 ብር ቢደርስ፤ ጫኝና አውራጆች የሚጠይቁት በኪሎ 1 ብር ቢደርስ፤ (ህጋዊም ሆነ ህገወጥ ቀረጥ እና ግብር ኖሮ) 1 ብር ቢያስወጣ……..አንድ ኪሎ ቲማቲም ገበያ ለመድረስ ያስወጣው ወጪ (Per-Product Cost) 20 ብር ደረሰ ማለት ነው፡፡


2.ቋሚ ወጪዎችን ማጠቃለል (Fixed Costs)፡- በማምረት ወቅት የቋሚ ንብረቶች ወጪ መታሰብ አለበት (የመሬት፤ የግንባታ፤ የማሽኖች፤ የመኪኖች፤ ወዘተ) ምክንያቱም ግንባታ ገንብቶ እና ማሽን ገዝቶ የሚያመርት አምራች በሂደት ወጪውን ማካካስ የሚችለው ከሚሸጠው ምርት ነው፡፡


#ለምሳሌ፡- በ10 ሚሊየን ብር ግንባታ ሰርቶ ቲማቲም ለማምረት ቢዝነስ የጀመረ አምራች የሚሸጡ ቲማቲሞች ላይ የቋሚ ንብረቶችን ወጪ መደመር አለበት ነገር ግን በነጠላ እያንዳንዱ ቲማቲም ላይ ለመደመር ሊያስቸግር ይችላል (ዋጋ ሳይንስ ነው የሚባለው ለዚህ ነው! ከጠቅላላው 10 ሚሊየን ብር ውስጥ አንዷ ቲማቲም ምን ያህል ብር ድርሻ ትያዝ?)


3.የትርፍ ጣሪያ (Profit Margin)፡- አምራች ማትረፍ የሚፈልገውን የትርፍ መጠን ለማስላት ሁለት ነገር ታሳቢ ማድረግ አለበት፡፡ የመጀመሪያው ለቋሚ ንብረቶች (የመሬት፤ የግንባታ፤ የማሽኖች፤ የመኪኖች፤ ወዘተ) ያወጣው ወጪ እዚህ ላይ መደመር የለበትም ሁለተኛው የሚያጠቃልለው የትርፍ ጣሪያ ጭማሪ ምርቱ መጨረሻ ላይ ሲሸጥ ተቀባይነት ከሚኖራቸው ዋጋዎች በጣም የራቀ እንዳያደርገው መጠንቀቅ አለበት፡፡


#ለምሳሌ፡ ጠቅላላ የምርት ወጪው እና ለቋሚ ንብረት የወጣበት ወጪ ተደምር አንድ ምርት ገበያ ለመድረስ 20 ብር ቢያስወጣ እና አምራቹ የትርፍ መጠኑ 20%  እዲሆን ቢወስን በቀላል ስሌት/Profit Margin Calculator (20 ብር/1-20% (0.2) = 20/0.8 = 25 ብር ሊሸጥ ይችላል) ስለዚህ ምርቱ ያስወጣው ወጪ 20 ብር ሆኖ የምርቱ የመሸጫ ዋጋ 25ብር ደረሰ ማለት ሲሆን የአምራቹ ትርፍ ደግሞ 5 ብር ሆነ ማለት ነው፡፡


ከላይ የተጠቀሱ ሶስቱም መስፈርቶች በሙሉ ታሳቢ ቢደረጉም በመጨረሻ ግን ሸማች ለመሸመት የሚፈቅድበት የዋጋ መጠን (Willing to Pay) ከግምት ካልገባ ዋጋ የለውም፡፡
1.8K viewsWasyhun Belay, 17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 19:51:27 በ 10 ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ከተመረተ የቲማቲም ማሳ ላይ አንዷ ቲማቲም ተመርታ ስትሸጥ ከ10 ሚሊዮን ብሩ ጠቅላላ የኢንቨስትመንት ወጪ ላይ ስንት ይድረስባት?


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ቪዲዮ

ተመልከቱ፤ ተጠቀሙበት እና ለሌሎች እንዲጠቀሙበት አጋሩት፡፡
1.7K viewsWasyhun Belay, 16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 15:16:32 አምራቾች፤ ነጋዴዎች፤ የቢዝነስ አዋጪነት ጥናት አዘጋጆች እና የቢዝነስ ፕላን ጥናት ገምጋሚዎች የመሸጫ እና የአገልግሎት መስጫ ዋጋ ለማውጣት የሚከተሉትን መስፈርቶች መከተል ተገቢ ነው...

1. ምርቱ ለመመረት ያስወጣውን ጠቅላላ ወጪ (Variable Costs)
2. ለቋሚ ንብረቶች የወጣ ወጪ (Fixed Costs)
3. የትርፍ ጣሪያ (Profit Margin)

ሸማች ለሚሸምተው ነገር በአብዛኛው በቂ መረጃ አለው ተብሎ ይታሰባል! ስለዚህ ጊዜው እና ገንዘቡ የሚመጥነውን ዋጋ በራሱ በማስላት እርካታውን ለመጠበቅ ይጥራል፡፡ ስለዚህ አምራቾች እና ሻጮች ትክክለኛውን ሸማች ማወቅ እና ለሚያቀርቡት ምርት እስከ ስንት ድረስ የመክፈል ፍላጎት እንዳለው (Willing to Pay) ለማወቅ፤ የወሰኑት ዋጋ ቢዝነሳቸው በትርፋማነት ለረጅም ጊዜ እንዲዘልቅ የሚያደርግ ዋጋ መሆኑን ለማወቅ በሳይንስ (Pricing Strategy) መመራት ያለበት የገበያ ጥናት አካል ነው፡፡

ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ቪዲዮ

ተመልከቱ፤ ተጠቀሙበት እና ለሌሎች እንዲጠቀሙበት አጋሩት፡፡
2.5K viewsWasyhun Belay, 12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 20:31:37 ወቅት እየጠበቁ እስከ 30% ቅናሽ አድርገናል የሚሉ አምራቾች እና ሻጮች እውነታቸውን ከሆነ ከዚህ በፊት የነበራቸው የትርፍ ጣሪያ/Profit Margin ስንት ይሆን?
2.3K viewsWasyhun Belay, 17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 21:37:06 የኢኮኖሚክስ አስተምሮት በሁለት መሰረታዊ አመክንዮዎች የተከፈለ ነው፦ እነሱም በ18ኛው እና በ19ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ አካባቢ የተጀመረው የክላሲካል(Classical Economics) እና ከ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ  ጀምሮ አዳዲስ ልምዶች እና ሃሳቦች በተጨመሩበት የኒዮክላሲካል (Neoclassical Economics) እውነቶች ነው።


የሁለቱ አስተምሮቶች ምንድን ነው? ልዩነታቸው የሚመነጨው ከየትኛው እውነት ተነስቶ ነው? አሁን ላይ የዓለም ሀገራት ከሁለቱም አስተምሮቶች እየቀላቀሉ የሚጠቀሙባቸው የትኞቹን ነው?


የትኛውም ሀገር ከሁለቱ አስተምሮቶች ውጪ አይደለም! ለምን? የሚከተለውን ቪዲዮ

ተመልከቱ ኢኮኖሚክስ ይበልጥ በማወቅ በእውነታዎቹ ይገረሙ።
3.3K viewsWasyhun Belay, 18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 11:41:31 የኢኮኖሚክስ አስተምሮት በሁለት መሰረታዊ አመክንዮዎች የተከፈለ ነው፦ እነሱም በ18ኛው እና በ19ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ አካባቢ የተጀመረው የክላሲካል(Classical Economics) እና ከ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ  ጀምሮ አዳዲስ ልምዶች እና ሃሳቦች በተጨመሩበት የኒዮክላሲካል (Neoclassical Economics) እውነቶች ነው።


የሁለቱ አስተምሮቶች ምንድን ነው? ልዩነታቸው የሚመነጨው ከየትኛው እውነት ተነስቶ ነው? አሁን ላይ የዓለም ሀገራት ከሁለቱም አስተምሮቶች እየቀላቀሉ የሚጠቀሙባቸው የትኞቹን ነው?


የትኛውም ሀገር ከሁለቱ አስተምሮቶች ውጪ አይደለም! ለምን? የሚከተለውን ቪዲዮ

ተመልከቱ ኢኮኖሚክስ ይበልጥ በማወቅ በእውነታዎቹ ይገረሙ።
718 viewsWasyhun Belay, 08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 09:53:48 የጥናት ፕሮፖዛል (Research Proposal) መስፈርቶች

1. Title

2. Summary/Abstract

3. Introduction

4. Background

5. Statement of the Problem

6. Conceptual Framework

7. Research Objectives (Main and Specific)

8. Research Questions/Research Hypotheses

9. Significance

10. Scope, Thematic

11. Description of the Study Area

12. Research Methods and Procedures (Research Design (Research Paradigm)

#Research Approach (Deductive, Inductive, Exploratory, Explanatory, Qualitative, Quantitative, Mixed).

#Research Type (Descriptive, Analytical, Evaluative, etc.)

#Research Strategy (Experiment, Survey, Case Study, Grounded Theory, Ethnography, Action Research, etc.)

#Time Dimension (Cross sectional, Longitudinal (time series), panel) 

#Method of Data Collection (Type of Data, Instrumentation (Questionnaire, Interview, Focus Group Discussion, Document Review, Observation Etc.)

#Sampling Methods (Sampling Technique, target population, Sampling Frame, Sampling Unit, Sample Size)

#Operationalization Framework (Variables and Description, Measurement Type, Expected Sign etc.). 

#Method of Data Analysis: Data quality assurance (Validity, Reliability, etc.)

13. Limitations

14. Ethical Considerations

15. Organization of the Paper

16. Work Plan 

17. Budget

18. References

19. Appendices (Questionnaire, Schedule of Interview, FGD questions for etc.)


በቪዲዮ በዝርዝር ከነምሳሌው ለምትፈልጉ

2.5K viewsWasyhun Belay, 06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 10:01:09 የተሟላ ምርጥ የጥናት ፕሮፖዛል አዘገጃጀት (ከሀ እስከ ፐ) (How to Write an Excellent Research Proposal?)

3.4K viewsWasyhun Belay, 07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 11:00:23 የተሟላ ምርጥ የጥናት ፕሮፖዛል አዘገጃጀት (ከሀ እስከ ፐ) (How to Write an Excellent Research Proposal?) የተሟላ የጥናት ፕሮፖዛል ለማዘጋጀት በመሰረታዊነት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ መከተል ያለባችሁ መስፈርቶች እና ጠለቅ ያለ መግለጫ/ትንታኔ የያዘ ቪዲዮ

አዘጋጅቻለሁ ስለዚህ #የምትፈልጉ ሰዎች ተጠቀሙበት ሌሎች መጠቀም ለሚፈልጉ ሰዎችም እዲማሩበት አጋሩት!
3.9K viewsWasyhun Belay, 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ