Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View T
የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View
የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.32K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-05-17 14:28:09 ነጻ ገበያ ስለሆነ ከፈለክ ግዛ ካልፈለህ ትተህ ሂድ፤ ከፈለኩ እሸጣለሁ ከፈለኩ አልሸጥም፤ በገዛ ንብረቴ ዋጋ መወሰን እችላለሁ፤ ነጻ ገበያ ስለሆነ ጣልቃ መግባት አንችልም፤ ወዘተ ማለት ነጻ ገበያ ማለት አይደለም፡፡ የገበያ ህግን ማስከበር አለመቻልም ሆነ በገበያ ህግ አለመገዛት ሁሉ የነጻ ገበያነት አመክንዮ አይደለም!

2.5K viewsWasyhun Belay, 11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 16:19:04 የዋጋ ንረት እና ልጆች የመውለድ መጠን ምን ግንኙንት አላቸው? Does inflation determine fertility rate?


2022 ላይ በቱርክ በተደረገ አንድ ጥናት የዋጋ ንረት በአንድ ከመቶ ሲጨምር የወሊድ መጠን በ0.035% ይቀንሳል (ተቃራኒ ግንኙነት አላቸው ማለት ነው)። ወላጆች የመኖሪያ ወጪ ሲጨምርባቸው ተጨማሪ ልጆች ለመውለድ ያላቸው ፍላጎት ይቀንሳል እንደማለት ነው።


የቤተሰብ ቁጥር ከገቢ መጠን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ብዙ ጥናቶች አሉ (ቤተሰቦች ገቢያቸው እያደገ ሲሄድ የቤተሰብ ቁጥራቸውን ለመጨመር ይወስናሉ ለማለት ሲሆን ውስን ተቃራኒያዊ ውጤት የሚታይበትም ጥናትም አለ)።


በኢትዮጵያ የዋጋ ንረት ለረጅም  ዓመታት የመጨመር ባህሪ አለው! ለምሳሌ ያህል ብናይ የህዝብ ቁጥር እድገት ከ2018 እስከ 2022 ድረስ በአማካይ ከ2.5 እስከ 2.7 የደረሰ በማደግ መለዋወጥ እንዳለው Projection ቢሆንም የህዝብ ትሬንድ ላይ ያሳያል! ከዚህ በመነሳት  በኢትዮጵያ የዋጋ ንረት የህዝብ ቁጥር እድገት ሁኔታ ላይ ተፅዕኖው ደካማ ነው የሚል Hypothesis ለማስቀመጥ ያስደፍራል? (ለውይይት ያህል ነው!)።


ሌላው Hypothesis እንደ ግለሰብ እና ቤተሰብ በመጪው ጊዜ የኢኮኖሚ ሁኔታ ለውጥ ላይ መተማመን ሲቀንስ የአሁንን ሃይል በማሰብ የቤተሰብ ቁጥር መጨመርን ከዋጋ ንረት ጋር ያለማጣበቅ ባህሪ ሊኖር ይችላል።



ጥሩ የጥናት ሃሳብ የሚሆን ይመስለኛል! የዋጋ ንረት እና የህዝብ ቁጥር እድገት ግንኙነቱን በTime series መረጋገጥ ቢቻልም የመጨመርም ሆነ የመቀነስ ምክንያቱን በDescriptive ማወቅ የሚቻል ይመስለኛል።



በኢትዮጵያ የዋጋ ንረት (ለረጅም ጊዜ ቀጣይነት ይዞ የሚያድግ ነው) እና የውልደት መጠን/የህዝብ ቁጥር እድገት ያላቸው ግንኙነት ምን ይመስላችኋል? ከትዝብቶቻችሁ ተነስታችሁ ያለው Rationality ምን ይመስላችኋል?
4.5K viewsWasyhun Belay, 13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 21:10:38 ብሄራዊ ባንክ ለሳፋሪኮም የሞባይል ባንኪንግ (#ኤም_ፔሳ) ፍቃድ መስጠቱ የማይጠበቅ አይደለም! ኢትዮ ቴሌኮም ልምድ እንዲያገኝ የተሰጠውን አድቫንቴጅ ተጠቅሞ ያስተዋወቀው #ቴሌ_ብር እየሰጠ ካለው አገልግሎት ጋር ኤም ፔሳ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የገንዘብ እንቅስቃሴን የሚያፋጥን እድል ነው።
1.8K viewsWasyhun Belay, edited  18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 19:56:36 የኑሮ ውድነት = የዋጋ መጨመር + የገቢ አለማደግ ነው! ስለዚህ የልጆች የትምህርት ቤት ክፍያ በአንዴ በ70% ጨምሮ የወላጆች ገቢ በነበረበት ከቆመ የኑሮ ውድነት ትክክለኛ ትርጉሙን ያገኛል!።


የትምህርት ቤቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ወላጆችን ብቻ ሳይሆን ወላጅ በሆኑ አከራዬች፤ የአገልግሎት እና ሸቀጥ አቅራቢዎች በኩል ወላጅ ያልሆነውም የዋጋ ጭማሪው ንዝረት ይደርሰዋል።


ስለዚህ ስለ ፍትሃዊነት ማሰብ እና እንዲታሰብ ማድረግ ግድ ነው!
3.4K viewsWasyhun Belay, 16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 09:16:23 የጃፓን ኢኮኖሚ በዓለም ላይ ቀደምት ጠንካራ ኢኮኖሚ ነበር ነገር ግን ከ1990 እስከ 2012 ለ 22 ዓመታት ኢኮኖሚው እድገቱ ቆሞ! በጃፓን የህዝብ እድገት ቆመ፤ የዋጋ ጭማሪ ቆመ፤ የኢኮኖሚ እድገት ቆመ! ዓለም እድገት ጫፍ ደርሶ እንደሚቆም ያየው በጃፓን ነው!


ጃፓን በ20 ዓመት ውስጥ የኢኮኖሚ ደረጃዋን በቻይና በእጥፍ ተበለጠች። ሽንዞ አቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲመረጡ እድገቱ የቆመ ሀገር ነበር የተረከቡት! ነገር ግን ለማምጣት በሞከሩት 3 የለውጥ እርምጃዎች (Monetary, fiscal and structural reform) በስማቸው "አቤኖሚክስ" የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።



የአቤ ለውጦች ውጤት በግማሽ እንደተሞላ ብርጭቆ ነው ቢባልም ጥሩ መማሪያ ይሆናል።




3.9K viewsWasyhun Belay, 06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 22:12:27 የጃፓን ኢኮኖሚ በዓለም ላይ ቀደምት ጠንካራ ኢኮኖሚ ነበር ነገር ግን ከ1990 እስከ 2012 ለ 22 ዓመታት ኢኮኖሚው እድገቱ ቆሞ! በጃፓን የህዝብ እድገት ቆመ፤ የዋጋ ጭማሪ ቆመ፤ የኢኮኖሚ እድገት ቆመ! ዓለም እድገት ጫፍ ደርሶ እንደሚቆም ያየው በጃፓን ነው!


ጃፓን በ20 ዓመት ውስጥ የኢኮኖሚ ደረጃዋን በቻይና በእጥፍ ተበለጠች። ሽንዞ አቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲመረጡ እድገቱ የቆመ ሀገር ነበር የተረከቡት! ነገር ግን ለማምጣት በሞከሩት 3 የለውጥ እርምጃዎች (Monetary, fiscal and structural reform) በስማቸው "አቤኖሚክስ" የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።



የአቤ ለውጦች ውጤት በግማሽ እንደተሞላ ብርጭቆ ነው ቢባልም ጥሩ መማሪያ ይሆናል።




3.9K viewsWasyhun Belay, 19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 13:11:45 ስለሚከተሉት ጉዳዮች ማለትም ስለ ማንኛውም ጉዳይ የእጥረት ሁኔታ (Scarcity)፤ ስለምንም አይነት አቅርቦት እና ፍላጎት (Supply & Demand)፤ ስለ ተግባራቶቻችሁ ወጪ እና ትርፍ (Costs & Benefits) እና በእንቅስቃሴዎቻች በሙሉ ስለሚኖሩ እድሎች (Incentives) ማሰብ እና መጨነቅ ከያዛችሁ ኢኮኖሚክስን እየኖራችሁት ነው!
4.7K viewsWasyhun Belay, 10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 15:37:23 #Kicking_Away_the_Ladder!


አሁን ላይ በኢኮኖሚ ብልጽግና ላይ ደርሰዋል ተብለው የሚገለጹ ሀገራት በማደግ ላይ ባሉበት ወቅት የተቋማትን ነጻነት የሚጠብቁ አልነበሩም! ምክንያቱም በፍጥነት ለማደግ ተቋማትን ከገበያ ጣልቃ ገብነት ለመጠበቅ አስቸጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ በኢኮኖሚ ያደጉ ሀገራት በማደግ ላይ ያሉ ድሃ ሀገራት ለማደግ በሚሞኩሩበት ወቅት የተቋማትን ነጻነት ማረጋገጥ አለባችሁ በሚል ጫና ከፈጣን እድገታቸው ለመገደብ ዘወትር ይጥራሉ፡፡


የዛሬ 20 ዓመት በHa-Joon Chang የተጻፈው እና ያደጉ ሀገራት እነሱ ባደጉበት መንገድ ታዳጊ ሀገራት እንዲሄዱ አይፈቅዱም! ያደጉበትን መንገድ ለመከተል የሚፈልጉትን በተለያየ ዘዴ ያከላክላሉ Kicking Away the Ladder "መንሰላሉን ገፍቶ መጣል" ወይም ያደጉበትን ትክክለኛ ሚስጥር ይደብቃሉ ይላል፡፡


አሜሪካ ለማደግ በሄደችባቸው ወቅቶች በገበያ ጣልቃ በመግባት የግሉን ሴክተር ትደግፍ ነበር፤ ጠበቅ ያሉ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን ትጠቀም ነበር፤ ክልከላዎችን ታደርግ ነበር፤ ወዘተ ነገር ግን አሁን ላይ በማደግ ላይ ያሉ ድሃ ሀገራት ከዓለም ባንክ፤ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት እና ከሌሎች ተቋማት ብድር እና እርዳታ ለማግኘት ማሟላት አለባቸው በሚል ያዘጋጀቸውን (Washington Consensus) ማለትም ነጻ ገበያ መፍጠር፤ የገበያ ጣልቃ ገብነትን መቀነስ፤ ሰብአዊ መብት ማክበር፤ ክልከላዎችን ማንሳት፤ ወዘተ ይከበር የሚለው ህጓን ድሮም አሁንም በተገቢ መልኩ በራሷ ሀገር የማይተገበሩትን ታዳጊ ሀገራት ላይ አሳሪ በማድረግ አውጥታለች ይላል፡፡


የሰዎችን ጉልበት ብዝበዛ፤ የተፈጥሮ ሃብቶችን በገፍ መጠቀም፤ የአየር ብክለት፤ የውሃ ብክለት፤ መርዛማ ኬሚካል መጠቀም፤ ደን መጨፍጨፍ፤ ወዘተ ለማደግ ሲሞክሩ አንደልባቸው የተጠቀሙት መንገድ ነበር! ነገር ግን አሁን ላይ ለማደግ የሚሞክሩ ሀገራት እነዚህን ተግባራት እንዲያደርጉ በተለያየ ዘዴ አይፈቅዱም፡፡


በኢንዱስትሪ አብዮት ወቅት እንግሊዝም፤ ጀርመንም፤ አሜሪካም በባሪያ ንግድ የተወሰዱ ሰዎችን እና ህጻናትን ሳይቀር ለምርት ሲጠቀሙ ነበር! ነገር ግን እነሱ ለማደግ ሲሉ ያለፉበትን ይህን አካሄድ አሁን ላይ ለየትኛው ሀገር የሰብሃዊ መብት ጠባቂ ነን በሚል ምክንያት ይህ እንዲሆን አይፈቅዱም!


በ19ኛው ክፍለዘመን የአውሮፓ ሀገራት በተለይ እንግሊዛዊ የሌሎች ሀገራት ዜጎች የፈጠራ መብት እንደራሱ አድርጎ የመጠቀም በህግ መብት ነበራቸው፤ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ምርጫ ለሴቶች በአውሮፓ ሀገራት አይፈቀድም ነበር እንዲሁም ህፃናትን ከጉልበት ስራ የሚጠብቅ ህግ አልነበራቸውም (በወቅቱ በአሜሪካ 50% የሚሆነው የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ሰራተኛ እድሜው ከ16ዓመት በታች ነበር!፤ ወዘተ።


ግን በ21ኛው ክፍለ ዘመን አሜሪካ የቻይና ምርቶች የህጻናትን እና እስረኞችን ጉልበት ተጠቅማ ነው የምታመርተው (ሰብዓዊ መብት ረገጠች) ስለዚህ በተመረጡ ቁሶች ላይ ማዕቀብ ሊጣልበት ይገባል የሚል ዛቻ በተደጋጋሚ ታነሳለች (የኢኮኖሚ ተፎካካሪነትን ለመቀነስ ነው!)፡፡


ያደጉ ሀገራት ለሃይል ግብዓት ዩራኒየምን አበልጽገው ከኒዩክሌር ሃይል ይጠቀማሉ (መሳሪያም አድርገው ይታጠቃሉ)! ነገር ግን ታዳጊ ሀገራት የሃይል ምርጫቸውን ኒዩክሌር ለማድረግ ቢያስቡ ጫናው ከባድ ነው (ኢራን እና ሰሜን ኮርያ ተመሳሳይ ጫና ውስጥ ናቸው)፡፡ በምድር ላይ የመጀመሪያውንም ሆነ የመጨረሻውን አቶሚክ ቦምብ ጃፓን ላይ የሞከረችው ሀገር አሜሪካ ብቻ ነች፡፡


በዚህ ወቅት ለማደግ እየሞከሩ ያሉ ድሃ ሀገራት አሁን ላይ ያደጉ ሀገራት ለማደግ ይሞክሩ በነበረበት ወቅት ከነበራቸው የተሻለ ተቋማዊ አደረጃጀት አላቸው! ነገር ግን የበለፀጉ ሀገራት ለማደግ ሲሉ ማንኛውንም ጤናማ ያልሆነ አካሄድ ሞክረዋል (በወቅቱ ቁጥጥር ያደርግባቸው የነበረ አካል አልነበረም) ድሃ ሀገራት በዚህ ፍትሃዊነት በጎደለው ቁጥጥር በበዛበት ጊዜ እንደምንም ብሎ ማደግን እንዴት ያሳኩታል?
5.8K viewsWasyhun Belay, 12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 12:06:16 የበለፀጉ ሀገራት ለኢኮኖሚ እድገት የተጠሙበትን መንገድ አሁን ላይ ለማደግ እየሞከሩ ያሉ ሀገራት በፍፁም እንዲከተሉ የማይፈቅዱበት ስልት እና ምክንያት ምንድን ነው?


በ Kicking away the ladder ላይ የተጠቀሱ የ7ቱንም ምዕራፍ ጭብጦች እና ምሳሌዎች ከምክንያቶቹ ጋር

አቅርቤላችኋለሁ እስከመጨረሻው ተመልከቱ እና ተማሩበት ለሌሎችም የዓለምን እውነታ እንዲረዱ አጋሩት።
1.9K viewsWasyhun Belay, 09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 19:35:53 የበለፀጉ ሀገራት ለኢኮኖሚ እድገት የተጠሙበትን መንገድ አሁን ላይ ለማደግ እየሞከሩ ያሉ ሀገራት በፍፁም እንዲከተሉ የማይፈቅዱበት ስልት እና ምክንያት ምንድን ነው?


በ Kicking away the ladder ላይ የተጠቀሱ የ7ቱንም ምዕራፍ ጭብጦች እና ምሳሌዎች ከምክንያቶቹ ጋር

አቅርቤላችኋለሁ እስከመጨረሻው ተመልከቱ እና ተማሩበት ለሌሎችም የዓለምን እውነታ እንዲረዱ አጋሩት።
2.7K viewsWasyhun Belay, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ