Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View T
የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View
የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.32K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-06 15:15:37 የ2016 በጀት 801.6 ቢሊየን ብር ከባለፈው ዓመት (786.6 ቢሊየን ብር) አንጻር የ1.9 ከመቶ ብቻ ጭማሪ ያለው በጀት በመሆኑ ብዙ እድል እና ጥቂት ስጋት ያለው በጀት ነው፡፡
2.8K viewsWasyhun Belay, edited  12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 19:06:40 ከዚህ ቀደም በጤናና በሕግ የትምህርት መስኮች ለሚመረቁ ተማሪዎች ብቻ የመውጫ ፈተና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ዘንድሮ 240ሺ የሚደርሱ ተመራቂዎች በመንግሥትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ይታወቃል!


በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ ውጤት ሐምሌ 10 ቀን የሚገልጽ ይሆናል።


የተማሪዎችን ምረቃ በተመለከተ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ማካሄድ የሚቻል መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ ናቸው ብሏል።


በቀሪ ጊዚያችሁ....


1. የመውጫ ፈተናው አስፈላጊ መሆኑን አምኖ መቀበል (ልምድ እንዳላችሁ አለመርሳት ወደ ኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲ ለመግባት ተፈትናችሁ ያለፋችሁ ናችሁ (10ኛ እና 12ኛ ክፍል)፡፡ የመውጫ ፈተናውን በአይምሮ ደረጃ አምኖ አለመቀበል ጊዚያችሁን ይበላል፡፡


2. ለፈተና ይጠቅማል ብላችሁ ያሰባችሁበትን ክፍል ለይታችሁ መከለስ! ያላጣራችሁት ቦታ ካለ በደንብ ለፈተና በሚሆን መልኩ ማንበብ/መከለስ (በእያንዳንዱ የኮሌጅ ቆይታ ወቅት ለፈተና  አንብባችሁ ሊሆን ስለሚችል ምን አልባት ክለሳ ማድረግ ሊበቃ ይችላል)፡፡


3. ከፈተናው ሁኔታ (ፎርማት) ጋር ፈጥኖ ለመግባባት መሞከር (ኦን ላይን ከሆነ መልመድ፤ ፈተናው ስለሚዳስሰው ነጥብ ማወቅ፤ ልምምድ ማድረግ፤ ሞዴል ፈተናዎችን በትኩረት መስራት፤ የጥያቄዎቹን ይዘት ለማወቅ መሞከር፡፡


4. የሚዘጋጁ የናሙና ፈተናዎችን በትኩረት መፈተን እና በደንብ መለማመድ የቀደመ የህግ እና የጤና መውጫ ፈተና ይዘቶችን ጠይቆ ልምዶችን መውሰድ፤ ምን አልባት ኦን ላይን ያሉ ናሙናዎችን እንደ መለማመጃ መውሰድ፡፡


5. የጊዜ መርሃ ግብር ማውጣት፤ በአንዴ ብዙ ለመሸፈን መሞከር ትኩረት ስለሚያሳጣ ቀሪ ጊዚያችሁን በጥብቅ ፕሮግራም መምራት (ከማህበራዊ ሚዲያ መቀነስ፤ ከጨዋታ መቀነስ፤ ከእንቅልፍ መቀነስ (በቀሪው ጊዜ ተቸግራችሁ ከቁጭት መዳን ትችላላችሁ) እና ለዚህ ፈተና የመጨረሻ አቅማችሁን መጠቀም፡፡


6. በዚህ ወቅቱ በቡድን ማጥናት፤ ሙከራዎችን መስራት፤ ሊያስረዷችሁ የሚችሉ ሰዎችን መፍጠር ያስፈልጋል፤ በከበዳችሁ ክፍል ላይ ጊዜ በማጥፋት ወደ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንዳትገቡ የሌሎችን እርዳታ ለመቀበል ክፍት መሆን አስፈላጊ ነው፡፡


7. ከወዲሁ እና በፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት ሊፈጠሩ የሚችሉ ስህተቶችን ቀንሱ የኮምፒዊተር አጠቃቀም፤ የማርፈድ፤ ጥሩ ስሜት ያለመፈጠር፤ የድካም፤ የመጨናነቅ፤ ወዘተ፡፡


አስታውሱ በማንኛውም መለኪያ ፈተናውን ማለፍ በእናንተ ጥረት እና ዝግጅት ልክ ነው የሚወሰነው! ሳያጠኑ ለማለፍ መመኘትም ሆነ ሳያጠኑ ወድቆ ቅር መሰኘት አዋጪ Rational አይሆንም!


@The Ethiopian Economist View

3.7K viewsWasyhun Belay, 16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 20:08:21 If you look around carefully, you will see that #scarcity is a fact of life!
4.2K viewsWasyhun Belay, 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 08:07:56 ዘንድሮ ለ240ሺ የመንግስት እና የግል ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች ከሃምሌ 3-8 ድረስ የመውጫ ፈተና "Exit Exam" እንደሚሰጣቸው ይታወቃል! ስለሆነም በቀሪ ቀናት የሚከተሉትን 7 ምክረ ሃሳቦች በመተግበር የተሻለ ውጤት ማምጣት ትችላላችሁ!




6.0K viewsWasyhun Belay, 05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 21:28:29 ዘንድሮ ለ240ሺ የመንግስት እና የግል ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች ከሃምሌ 3-8 ድረስ የመውጫ ፈተና "Exit Exam" እንደሚሰጣቸው ይታወቃል! ስለሆነም በቀሪ ቀናት የሚከተሉትን 7 ምክረ ሃሳቦች በመተግበር የተሻለ ውጤት ማምጣት ትችላላችሁ!




8.4K viewsWasyhun Belay, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 08:31:36 "Currency Peg" ሆን ብለው በውሳኔ የሃገራቸውን ገንዘብ ከዶላር እና ከይሮ አንፃር አዳክመው ለመያዝ አደገኛ ውሳኔ የወሰኑ 22 ሀገራት። የትኞቹ ሀገራት በምን ምክንያት እንደወሰኑ እና ያገኙትን ውጤት ተመልከቱ።


ምንዛሬን በውሳኔ ማስቀመጥ "Currency Peg" ይባላል።



6.5K viewsWasyhun Belay, 05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 21:05:40 "Currency Peg" ሆን ብለው በውሳኔ የሃገራቸውን ገንዘብ ከዶላር እና ከይሮ አንፃር አዳክመው ለመያዝ አደገኛ ውሳኔ የወሰኑ 22 ሀገራት። የትኞቹ ሀገራት በምን ምክንያት እንደወሰኑ እና ያገኙትን ውጤት ተመልከቱ።


ምንዛሬን በውሳኔ ማስቀመጥ "Currency Peg" ይባላል።



6.4K viewsWasyhun Belay, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 14:50:38 ፍራንኮ ቫሉታ የባለብዙ አደጋ ውሳኔ.......! The impact of Franco Valuta in Ethiopia!


ምርቶቹ በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ በመፈቀዱ ባለፉት አስር ወራት ብቻ መንግስት በታክስ መልክ ማግኘት የነበረበትን ከ10 ቢሊየን ብር በላይ አጥቷል! ነገር ግን የምርቶቹ ዋጋ ከመቀነስ ይልቅ በየጊዜው ሲጨምር እንደሚታይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ድኤታ አቶ ተሻለ በልሁ ተናግረዋል (ጭማሪው እየታየ ያለዉ በአለም ላይ ዋጋቸው ቀንሶ ባለበት ወቅት ጭምር ነው ብለዋል) የሚል ዜና (ሸገር ኤፍ ኤም 102.1) ላይ ሳይ የዛሬ 10 ወር የፍራንኮ ቫሉታ የባለብዙ አደጋ ውሳኔነነት የጻፍኩት ትዝ አለኝ፡፡

የኢትዮጲያ መንግስት የውጪ ምንዛሬ ያላቸው ሰዎች በማሳወቅ ብቻ ከውጪ የተወሰኑ መሰረታዊ ቁሳቁሶችን በማስመጣት እንዲሸጡ ፍቃድ መሰጠቱ ይታወቃል! ነገር ግን ይህ ውሳኔ የጎላ ጉዳት ቢኖረውም ውሳኔው ለኢኮኖሚው በተለይ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ጥቅም አለው በሚል እሳቤ ቀጥሏል! ታዲያ የሚታይ ጉዳት ያለው የፍራንኮ ቫሉታ ውሳኔ እንዲቀጥል የሚደረግበት መሰረታዊ ምክንያት ምን እንደሆነ ለመረዳት ይህንን

ቪዲዮ ተከታተሉት፡፡
6.7K viewsWasyhun Belay, 11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 20:33:48 የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት፦ "ለመጪው የ2016 ዓ/ም ወደ ሃገር ለማስገባት ለታቀደው 4.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ 4.4 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል!"

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ጠቅላላ የኤክስፖርት ገቢ መጠን 4.41 ቢሊየን ዶላር ነው! ስለዚህ ገቢው ካልተሻሻለ ነዳጅ ብቻ ነው መግዛት የሚችለው!


ለግንዛቤ ስለ የውጪ ምንዛሬ ምንጮች፦ #ከኤክስፖርት (ምርቶች ወደ ውጪ ተልከው)፤ ከአገልግሎት ሽያጭ (ለምሳሌ የአየር መንገድ እና የቴሌኮም ገቢ)፤ ከቱሪዝም (ለምሳሌ ከስብሰባ ተሳታፊዎች እና ቱሪስቶች)፤ ከሬሚታንስ (ውጪ ሃገር ያሉ ዜጎች የሚልኩት)፤ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (የውጪ ባለሃብቶች ሲገቡ) እና ከእርዳታ እና ከብድር ነው።
7.0K viewsWasyhun Belay, edited  17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 19:55:10 አሜሪካዊቷ Elinor Ostrom (ሊን) በ2009 በኢኮኖሚክስ ዘርፍ ኖቤል ሽልማት ያገኘች የመጀመሪያዋ ሴት የፖለቲካ ሳይንቲስት ነች:: በርግጥ ከኢኮኖሚስቱ Oliver Williamson ጋር በጋራ ነው የተቀበሉት (ከሷ በመቀጠል በ2019 ድህነት ቅነሳ ላይ በሰራችው ስራ በኢኮኖሚክስ ዘርፍ ኖቤል የወሰደችው ሁለተኛዋ ሴት የ46 ዓመት ሴት ፈረንሳዊቷ Esther Duflo ስትሆን በMIT መምህር ናት)::

ነገር ግን በ#Economic_Governance ማለትም የጋራ ኢኮኖሚያዊ ሃብቶችን ስለማስተዳደር በሰራችው ጥናት ዓለም የሚያከብራት ታላቅ ኢኮኖሚስት Elinor Ostrom ለዓለም ያስተዋወቀችው ዋናው ሃሳብ በማህበረሰብ ውስጥ የጋራ የምንላቸው መገልገያዎች እንዳሉ ይታወቃል::

ኦስትሮም እንደምትለው የጋራ መገልገያዎችን ሰዎች በፍታዊነት እንዲጠቀሙበት ከተፈቀደ (ከማንም ጣልቃ ገብነት ውጪ ማለቷ ነው) የማስተዳደሪያ ህጎችን አውጥተው በመጠቀም በገቢም ተጠቃሚ ሆነው አካባቢያቸውንም በዘላቂነት እንዲንከባከቡ ያግዛል ትላለች::


#ለምሳሌ:- ወንዞች፤ የግጦሽ መሬት እንዲሁም ደኖች የወል/የጋራ (Common Resources) መገልገያ እንደሚባሉ ይታወቃል:: ነገር ግን እነዚህን የጋራ መገልገያዎች እንዴት በጋራ በፍታዊነት መጠቀም እንደሚቻል የሚያስረዳ ታላቅ ሃሳብ ነው፡፡

ለዚህ አካሄድ ያዋጣል ያለችውን 8 መንገዶች አስተዋውቃለች፡፡ እነሱም….

1.የጋራ ሃብቶችን በአግባቡ መከለል እና ተጠቃሚዎችን መለየት፤

2.አካባቢያዊ የአጠቃቀም ደንቦች እና ህጎች ማውጣት፤

3.ሁሉንም አካላት ውሳኔዎች ላይ ተሳታፊ ማድረግ፤

4.የአጠቃቀምን ፍታዊነት የመከታተል እና የመቆጣጠር ስራ መስራት፤

5.ህጎችን የሚጥሱ አካላትን ማስጠንቀቅ እና መቅጣት፤

6.በባህላዊ መንገድ ግጭቶች ሲከሰቱ በአፋጣኝ መፍታት፤

7.የበላይ አለቆች ባህላዊውን አስተዳደር እውቅና መስጠት አለባቸው እና

8.አጎራባች ክልሎችን የሚነኩ ሃብቶችን በጋራ ከክልሎች ጋር በመወያየት መጠቀም የሚሉ ናቸው።


በሀገራችን የጋራ የሆኑ ሀብቶችን በመጠቀም ዙሪያ መልካም ማህበራዊ አስተዳደር ቢኖርም የተፈጥሮ ሀብቶች እየገጠማቸው በመጣው እጥረት ምክንያት ሀብቶችን በጋራ በመጠቀም ዙሪያ በርካታ ግጭቶች ይፈጠራሉ (የሚነሱት የጥቅም ይገባኛል ግጭቶች፦ ነዋሪዎች የሚሞቱባቸው፤ ሀብቶች የሚወድምባቸው እንዲሁም  ሰዎች የሚፈናቀሉባቸው ናቸው)።


የክልል አወቃቀር ባለበት የሀገራችን የመንግስት አስተዳደር በክልሎች መካከል፤ በዞኖች መካከል፤ በወረዳዎች መካከል፤ በቀበሌዎች መካከል፤ በጎጦች እና በመንደሮች መካከል በርካታ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ የጋራ ሀብቶች እንዳሉ ይታወቃል!(ጎረቤት ሀገራት ደግሞ እንደ ሀገር ከሀገራችን ጋር የሚጋሩት የአባይ ወንዝ ምሳሌ መሆን ይችላል!)።

የጋራ ሀብቶችን በእኩል ተጠቃሚነት እና ባለቤትነት ስርዓት ለማስተዳደር መቸገር፣ ሀብቱ መስጠት የሚገባውን ጥቅም ለማህበረሰቡ በዘላቂነት እንዳይሰጥ ምክንያት ይሆናል!


ይህ የሊን አስተሳሰብ ከሚነሱበት ትችቶች መካከል ስብጥር ማህበረሰብ ባለበት አካባቢ በአንድ መጠቀሚያ ሃብተ ላይ ስለፍታዊነት ለመስማማት እና ህብረት ለመፍጠር መቻላቸው አስቸጋሪ ስለመሆኑ እና የጥቅም ግጭት ሲፈጠር ሁኔታውን ለማስተካከል ምን ማድረግ እንዳለባቸው አስገዳጅ መፍትሄ አልጠቆመችም ይሏታል።


በ2013 በካንሰር ህመም ምክንያት ህይወቷ አልፏል።
6.2K viewsWasyhun Belay, 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ