Get Mystery Box with random crypto!

ከዚህ ቀደም በጤናና በሕግ የትምህርት መስኮች ለሚመረቁ ተማሪዎች ብቻ የመውጫ ፈተና ሲሰጥ ቆይቷል፡ | The Ethiopian Economist View

ከዚህ ቀደም በጤናና በሕግ የትምህርት መስኮች ለሚመረቁ ተማሪዎች ብቻ የመውጫ ፈተና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ዘንድሮ 240ሺ የሚደርሱ ተመራቂዎች በመንግሥትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ይታወቃል!


በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ ውጤት ሐምሌ 10 ቀን የሚገልጽ ይሆናል።


የተማሪዎችን ምረቃ በተመለከተ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ማካሄድ የሚቻል መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ ናቸው ብሏል።


በቀሪ ጊዚያችሁ....


1. የመውጫ ፈተናው አስፈላጊ መሆኑን አምኖ መቀበል (ልምድ እንዳላችሁ አለመርሳት ወደ ኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲ ለመግባት ተፈትናችሁ ያለፋችሁ ናችሁ (10ኛ እና 12ኛ ክፍል)፡፡ የመውጫ ፈተናውን በአይምሮ ደረጃ አምኖ አለመቀበል ጊዚያችሁን ይበላል፡፡


2. ለፈተና ይጠቅማል ብላችሁ ያሰባችሁበትን ክፍል ለይታችሁ መከለስ! ያላጣራችሁት ቦታ ካለ በደንብ ለፈተና በሚሆን መልኩ ማንበብ/መከለስ (በእያንዳንዱ የኮሌጅ ቆይታ ወቅት ለፈተና  አንብባችሁ ሊሆን ስለሚችል ምን አልባት ክለሳ ማድረግ ሊበቃ ይችላል)፡፡


3. ከፈተናው ሁኔታ (ፎርማት) ጋር ፈጥኖ ለመግባባት መሞከር (ኦን ላይን ከሆነ መልመድ፤ ፈተናው ስለሚዳስሰው ነጥብ ማወቅ፤ ልምምድ ማድረግ፤ ሞዴል ፈተናዎችን በትኩረት መስራት፤ የጥያቄዎቹን ይዘት ለማወቅ መሞከር፡፡


4. የሚዘጋጁ የናሙና ፈተናዎችን በትኩረት መፈተን እና በደንብ መለማመድ የቀደመ የህግ እና የጤና መውጫ ፈተና ይዘቶችን ጠይቆ ልምዶችን መውሰድ፤ ምን አልባት ኦን ላይን ያሉ ናሙናዎችን እንደ መለማመጃ መውሰድ፡፡


5. የጊዜ መርሃ ግብር ማውጣት፤ በአንዴ ብዙ ለመሸፈን መሞከር ትኩረት ስለሚያሳጣ ቀሪ ጊዚያችሁን በጥብቅ ፕሮግራም መምራት (ከማህበራዊ ሚዲያ መቀነስ፤ ከጨዋታ መቀነስ፤ ከእንቅልፍ መቀነስ (በቀሪው ጊዜ ተቸግራችሁ ከቁጭት መዳን ትችላላችሁ) እና ለዚህ ፈተና የመጨረሻ አቅማችሁን መጠቀም፡፡


6. በዚህ ወቅቱ በቡድን ማጥናት፤ ሙከራዎችን መስራት፤ ሊያስረዷችሁ የሚችሉ ሰዎችን መፍጠር ያስፈልጋል፤ በከበዳችሁ ክፍል ላይ ጊዜ በማጥፋት ወደ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንዳትገቡ የሌሎችን እርዳታ ለመቀበል ክፍት መሆን አስፈላጊ ነው፡፡


7. ከወዲሁ እና በፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት ሊፈጠሩ የሚችሉ ስህተቶችን ቀንሱ የኮምፒዊተር አጠቃቀም፤ የማርፈድ፤ ጥሩ ስሜት ያለመፈጠር፤ የድካም፤ የመጨናነቅ፤ ወዘተ፡፡


አስታውሱ በማንኛውም መለኪያ ፈተናውን ማለፍ በእናንተ ጥረት እና ዝግጅት ልክ ነው የሚወሰነው! ሳያጠኑ ለማለፍ መመኘትም ሆነ ሳያጠኑ ወድቆ ቅር መሰኘት አዋጪ Rational አይሆንም!


@The Ethiopian Economist View