Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View T
የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View
የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.32K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-27 19:57:58 ከመካከለኛው አፍሪካ 6 ሀገራት እና በምዕራብ አፍሪካ 8 ሀገራት ወጥ የሆነ XAF እና XOF የሚባሉ ተመሳሳይ ገንዘብ በጋራ እንደሚጠቀሙ ያውቃሉ? በሁለቱ ዞኖች 27 ሀገራት ያሉ ሲሆን 14ቱ ላላፉት 78 ዓመታት የአንድ ገንዘብ ተጠቃሚ ናቸው!




5.9K viewsWasyhun Belay, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 13:42:50 ከመካከለኛው አፍሪካ 6 ሀገራት እና በምዕራብ አፍሪካ 8 ሀገራት ወጥ የሆነ XAF እና XOF የሚባሉ ተመሳሳይ ገንዘብ በጋራ እንደሚጠቀሙ ያውቃሉ? በሁለቱ ዞኖች 27 ሀገራት ያሉ ሲሆን 14ቱ ላላፉት 78 ዓመታት የአንድ ገንዘብ ተጠቃሚ ናቸው!




6.1K viewsWasyhun Belay, 10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 19:45:45 የአዲስ አበባ ከተማ #የቤት_ግብር ተመን!
10.3K viewsWasyhun Belay, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-24 19:50:11 እንደ ኢትዮጲያ ከሞላ ጎደል Progressive Capitalism (ማለትም በመንግስት፤ የግል ሴክተሩ እና የምርምር ተቋማት በመቀናጀት ስትራቴጂክ የሆነ አቅም በመፍጠር አቅርቦት እና ፍላጎትን ማቀራረብ ላይ ያነጣጠረ) ስርዓት ለመተግበር በምትሞክር ሃገር ውስጥ ነጻ ገበያ በመሆኑ ማሰገደድ አንችልም የሚሉ መግለጫዎች፤ ነጻ ገበያ በመሆኑ መብታችን ነው ተባልን የሚሉ ሸማቾች እና ነጻ ገበያ በመሆኑ ዋጋ ተማኝ ነን የሚሉ አምርቾች/ሻጮች፤ መስማት በጣም  እንግዳ ነገር ነው፡፡

ነጻ ገበያ ማለት በጥቂት የመንግስት ጣልቃ ገብነት ወይም ያለ መንግስት ጣልቃ ገብነት ገበያውን አቅርቦት እና ፍላጎትን ተከትሎ እንዲመራ መፍቀድ ማለት ነው (ነጻ ገበያ ስለዋጋ ያለ ጉዳይ ብቻ ማለትም አይደለም)፡፡

ነጻ ገበያ የኢኮኖሚ ዋና ተዋናይ የሆኑት ሸማቾች እና አምራቾች/ሻጮች ሌላው ተዋናይ መንግስት ተቀንሶ ገበያው ላይ የመወሰን መብት እዲወስዱ የተሰጠ የውክልና አካሄድ ነው፡፡ በዜጎች መካከል ያለው የሃብት ክፍፍል ሲዛነፍም ሆነ ፍታዊነትን ለመጠበቅ ሲባል ገበያን ለብዙሃን ምቹነት ሲባል በመንግስት መጎብኘቱ አይቀርም! ምክንያቱም ነጻ ገበያን ይዞ ብቅ ካለው አዳም ስሚዝ (1723-1790) ጀምሮ ላለፉት 250 ዓመታት በወረቀት እንጂ በተግባር አሟልቶ መተግበር የቻለ አንድም ሃገር የለም፡፡

በዓለም የኢኮኖሚ ታሪክ ውስጥ ነጻ ገበያ ስርዓት ምናባዊ ነው ተብሎ የሚተችበት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ መተግበር አለመቻሉ ነው፡፡ ምክንያቱም መንግስታት በጥቂቱም ቢሆን ገበያውን ማየት አለመቻላቸው የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ጣልቃ መግባታቸው ወደው ሳይሆን ተገደው ነው::

ሃገራት በተለይ ፖለቲከኞች ነጻ ገበያ ላይ ገደብ ለማስቀመጥ የሚደፍሩበት መሰረታዊ ምክንያት የሚመነጨው ለፖለቲካል ኢኮኖሚው ደህንነት፤ ፍታዊነትን ለመጠበቅ እና የህዝብ የጋራ መጠቀሚያ ሃብቶችን ለመፍጠር ሲባል ነው፡፡ ገበያ ቸል በተባለ ቁጥር የጥቁር ገበያ መጠንከር፤ የብቸኛ አምራች እና አቅራቢነት ባህሪ መፈጠር እንዲሁም ወደ ኢኮኖሚው ስርዓት መግባትን ከባድ የማድረግ ልምምድ ስለሚፈጠር ነው፡፡

ለነጻ ገበያ የቀረበ የኢኮኖሚ ስርዓት አመክንዬ ያላቸው ሃገራት ነጻ ገበያን የግለሰቦችን ሃብት የመፍጠር ነጻነት እና የግለሰቦችን መብት ማክበር ድረስ ነው የሚተገብሩት ምክንያቱም ነጻ ገበያ የመንግስት ቁጥጥር ብቻ ሳይሆን የመንግስት ድጎማንም ማስቀረት አለበት ስለሚል ነው፡፡ በአይነትም ሆነ በፖሊሲ ባልተደጎመ አርሶ አደር በተመጣጣኝ ዋጋ እና በገፍ ሰብል ወደ ገበያ ለማቅረብ ላደጉም ሃገራት ቀላል አይደለም፡፡

ስለ ካፒታሊዝም በተለይ የነፃ ገበያ አቀንቃኞች የማይነግሩን 23 ቁልፍ ጉዳዮች! በሚለው ድንቅ መጽሃፉ ፕሮፌሰር ሃ ጁን ቻንግ እንደሚለው በእውነት ነፃ ገበያ የሚባል ነገር የለም There is Really No Such Thing as a Free Market ወይም ብዙ ኢኮኖሚስቶች እንደሚስማሙት No Pure Free Market Economies Actually Exist, and All Markets Are in Some Ways Constrained):: ይህ ከኢትዮጰያ እስከ አሜሪካ ገበያ ያለ ሃቅ ነው፡፡

አስታውሱ የነጻ ገበያ መስፈርቶች በሙሉ ተተገበሩ ማለት መንግስት የገበያ ቁጥጥር ብቻ ሳይሆን ድጎማንም ማስቀረት አለበት ማለት ነው፡፡ በተለያየ መልኩ በድጎማ ስርዓት ውስጥ የማያልፍ አምራች እና ሻጭ ለማግኘት ከባድ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በሚደጎም ነዳጅ፤ በሚደጎም ውሃ፤ በሚደጎም መብራት፤ በሚደጎም የህዝብ መገልገያ እየተጠቀሙ የሚያመርቱ አምራቾች ሸማቾችን መግፋት መብታቸው ሊሆን አይችልም፡፡

ነጻ ገበያ ነው ከፈለክ ግዛ ካልፈለህ ትተህ ሂድ፤ ከፈለኩ እሸጣለሁ ካልፈለኩ አልሸጥም፤ በገዛ ንብረቴ ዋጋ መወሰን እችላለሁ፤ ወዘተ ማለት ነጻ ገበያ ማለት አይደለም፡፡ ህግን ማስከበር ባለመቻል የሚመጡትም ሆነ በህግ ያለመገዛት አዝማሚያዎች ሁሉ የነጻ ገበያነት መገለጫ አይደሉም፡
8.4K viewsWasyhun Belay, 16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-22 20:52:58 በከባዱ የኢኮኖሚክስ ዘርፍ የመጀመሪያውን የኖቤል ሽልማት ያገኘችዋ ብርቱ ሴት Elinor Ostrom! የኢትዮጵያ ፖለቲካ ብዙ ሊማርበት የሚችለው Economic Governance ፈጣሪ!




8.0K viewsWasyhun Belay, 17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 13:30:24
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፦ "የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚን ለመገንባት የመንግሥት ወጭ ቅነሳ ላይ ትኩረት ይደረጋል"።


ትኩረቱን አንገብጋቢ ያልሆኑ የመንግስት ፕሮጀክቶችን ከማቆየት ቢጀምር አይቀለውም?
8.6K viewsWasyhun Belay, 10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 20:03:29 #ኤክሳይዝ_ታክስ ማን ይከፍላል? ኤክሳይዝ ታክስ በተወሰኑ የምርት እና የአገልግሎት ባህሪ ባላቸው ቁሳቁሶች እና አገልግሎቶች ላይ በዋናነት በአምራቾች እና አስመጪዎች ላይ የሚጣል ቀጥተኛ ያልሆነ የታክስ አይነት ቢሆንም እንደአለመታደል ሆኖ ከዋጋ ጋር ለሸማች አውርደው ይሰጡታል!


ጥያቄው ነባር ኤክሳይዝ ታክስ ሲቀነስ ከነባር ዋጋ መውረድ ያለመደው ገበያ (ገደብ የሌለው የትርፍ ጣሪያ ጭማሪ ፍላጎት) ባለበት የሸማች ጫና ይቀንሳል ወይ የሚለው ነው!


ታክስ ሊጨመርም ሊቀነስም ይችላል! ለምሳሌ ሀገራት ታክስ ለመጨመር ሲወስኑ የሚከተለው አመክንዮ ሊኖራቸው ይችላል ሊቀንሱ ሲያስቡም በተቃራኒው.....


መንግስታት በሁለት መንገድ ታክስን ሊጨምሩ ይችላሉ፤ አንደኛው የገቢ መጠናቸውን በመጨመር ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ለማዋል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የገንዘብ አቅርቦትን እና ፍላጎትን ለመቆጣጠር በሚያስቡበት ወቅት ነው፤ #ለምሳሌ የገንዘብ አቅርቦት በሰዎች እጅ ሲበዛ በታክስ ሰበብ መሰብሰብ የተለመደ አሰራር ነው፤ የገንዘብ አቅርቦትን ለመጨመር ታክስ መቀነስ ሌላው አሰራር ነው (ታክስ ተቀነሰ ማለት ሰዎች ለመንግስት ይከፍሉት የነበረው ገንዘብ እጃቸው ላይ ይቆያል ማለት ነው)።


በተጨማሪም ከውጪ በሚገቡ ቁሳቁሶች ላይ የሚጣል ታክስ የውጪ ምንዛሬን አቅርቦት መሰረት ያደረገ መሆን ስለሚኖርበት ሀገራት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ  እጥረት ሲገጥማቸው ከውጪ በሚገቡ እና መሰረታዊ በማይባሉ ቁሶች ላይ ተጨማሪ ታክስ ይጥላሉ::
8.5K viewsWasyhun Belay, edited  17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 16:03:32 በተሻሻለው ኤክሳይዝ ታክስ . . አዲስ የተጨመሩ ፦

- የሞባይል አገልግሎቶች (ኢንተርኔት ፣ የድምፅና የፅሁፍ መልዕክት)፣  የገመድ አልባ ስልክ አገልግሎት፣ የገመድም ሆነ ገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎቶች የማስከፈያ ምጣኔ 5 %

የኤክሳይዝ ታክስ ማስከፈያ ዋጋቸው የቀነሰ ፦

ስኳር ለህክምና ከሚውለው በስተቀር
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 20 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 10 %

ማስቲካ
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 20 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 10 %

በቀጥታ ለምግብነት እንዲውል የተዘጋጀ ቸኮሌት እና ጣፋጭ ከረሜላዎች
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 20 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 10 %

ባህሪው ያልተለወጠ ኢቴል አልኮል
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 60 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 10 %

ጨው
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 25 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 10 %

ኬሮሲን፣ ቤንዚን እና ናፍጣ ነዳጆች
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 30 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 15 %

ጨርቅና ልብስ
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 8 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 5 %

ምንጣፎች፣ ከጨርቃ ጨርቅ የተሰሩ የወለል መሸፈኛዎች
- በፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 30 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 15 %

በአዲሱ አዋጅ ነፃ የሆኑ የማይመለከታቸው ፦

ቪድዮ መቅረጫ ወይም ማባዣ መሳሪያዎች፣ የቴሌቪዥን ስርጭት መቀበያዎች፣ ፎቶ ወይም ቪድዮ ካሜራ ነፃ (ነባሩ ማስከፈያ ምጣኔ 10 % ነበር)

ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ የሆኑ ዕቃዎች ፦

የሚከተሉት የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ ተደርገዋል፡፡

1. አውሮፕላን በዓለምዐቀፍ ትራፊክ እንቅስቃሴ ውስጥ ባለበት ጊዜ ተሳፋሪ መንገደኞች እና የአውሮፕላኑ ሠራተኞች በጉዞ ወቅት የሚጠቀሙባቸው በነፃ የሚሰጡ ዕቃዎች፤

2. የዲፕሎማቲክ ወይም ኮንሱለር ሚሲዮኖች ወይም ዲፕሎማቶች አና ቆንስላዎች ወይም በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ የዲፕሎማቱ እና የቆንስላው ቤተሰቦች ወደአገር የሚያስገቧቸው ወይም ከአገር ውስጥ የሚገዟቸው በዲፕሎማቶች መብትና ጥቅም ደንብ የተፈቀዱ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች፣

3. በመንግሥት ጥሪ መሰረት በአደጋ የተጎዱ ሰዎችን ለመርጃ እንዲውሉ ወደአገር የሚገቡ ዕቃዎች፣

4. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ወይም የፌዴራልና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ወደአገር የሚያስገቧቸው ወይም ከአገር ውስጥ የሚገዙዋቸው በሚኒስትሩ በሚወጣ መመሪያ የተፈቀዱ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች፤

5. ከተሽከርካሪ በስተቀር ወደአገር የሚገቡ መንገደኞች ይዘዋቸው የሚመጡ አግባብ ባለው ሕግ የተፈቀዱ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች፤
8.3K viewsWasyhun Belay, 13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 15:29:06 የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል! አዲስ ወደ ኤክሳይዝ ታክስ የተጨመረ እንዲሁም ከታክስ የተቀነሰ የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ የተደረገባቸው የቁሳቁስ ዝርዝሮች።
5.9K viewsWasyhun Belay, 12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 19:32:23 ነጻ ገበያ ስለሆነ ከፈለክ ግዛ ካልፈለህ ትተህ ሂድ፤ ከፈለኩ እሸጣለሁ ከፈለኩ አልሸጥም፤ በገዛ ንብረቴ ዋጋ መወሰን እችላለሁ፤ ነጻ ገበያ ስለሆነ ጣልቃ መግባት አንችልም፤ ወዘተ ማለት ነጻ ገበያ ማለት አይደለም፡፡ የገበያ ህግን ማስከበር አለመቻልም ሆነ በገበያ ህግ አለመገዛት ሁሉ የነጻ ገበያነት አመክንዮ አይደለም!

1.6K viewsWasyhun Belay, 16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ