Get Mystery Box with random crypto!

በተሻሻለው ኤክሳይዝ ታክስ . . አዲስ የተጨመሩ ፦ - የሞባይል አገልግሎቶች (ኢንተርኔት ፣ የ | The Ethiopian Economist View

በተሻሻለው ኤክሳይዝ ታክስ . . አዲስ የተጨመሩ ፦

- የሞባይል አገልግሎቶች (ኢንተርኔት ፣ የድምፅና የፅሁፍ መልዕክት)፣  የገመድ አልባ ስልክ አገልግሎት፣ የገመድም ሆነ ገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎቶች የማስከፈያ ምጣኔ 5 %

የኤክሳይዝ ታክስ ማስከፈያ ዋጋቸው የቀነሰ ፦

ስኳር ለህክምና ከሚውለው በስተቀር
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 20 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 10 %

ማስቲካ
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 20 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 10 %

በቀጥታ ለምግብነት እንዲውል የተዘጋጀ ቸኮሌት እና ጣፋጭ ከረሜላዎች
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 20 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 10 %

ባህሪው ያልተለወጠ ኢቴል አልኮል
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 60 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 10 %

ጨው
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 25 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 10 %

ኬሮሲን፣ ቤንዚን እና ናፍጣ ነዳጆች
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 30 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 15 %

ጨርቅና ልብስ
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 8 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 5 %

ምንጣፎች፣ ከጨርቃ ጨርቅ የተሰሩ የወለል መሸፈኛዎች
- በፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 30 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 15 %

በአዲሱ አዋጅ ነፃ የሆኑ የማይመለከታቸው ፦

ቪድዮ መቅረጫ ወይም ማባዣ መሳሪያዎች፣ የቴሌቪዥን ስርጭት መቀበያዎች፣ ፎቶ ወይም ቪድዮ ካሜራ ነፃ (ነባሩ ማስከፈያ ምጣኔ 10 % ነበር)

ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ የሆኑ ዕቃዎች ፦

የሚከተሉት የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ ተደርገዋል፡፡

1. አውሮፕላን በዓለምዐቀፍ ትራፊክ እንቅስቃሴ ውስጥ ባለበት ጊዜ ተሳፋሪ መንገደኞች እና የአውሮፕላኑ ሠራተኞች በጉዞ ወቅት የሚጠቀሙባቸው በነፃ የሚሰጡ ዕቃዎች፤

2. የዲፕሎማቲክ ወይም ኮንሱለር ሚሲዮኖች ወይም ዲፕሎማቶች አና ቆንስላዎች ወይም በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ የዲፕሎማቱ እና የቆንስላው ቤተሰቦች ወደአገር የሚያስገቧቸው ወይም ከአገር ውስጥ የሚገዟቸው በዲፕሎማቶች መብትና ጥቅም ደንብ የተፈቀዱ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች፣

3. በመንግሥት ጥሪ መሰረት በአደጋ የተጎዱ ሰዎችን ለመርጃ እንዲውሉ ወደአገር የሚገቡ ዕቃዎች፣

4. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ወይም የፌዴራልና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ወደአገር የሚያስገቧቸው ወይም ከአገር ውስጥ የሚገዙዋቸው በሚኒስትሩ በሚወጣ መመሪያ የተፈቀዱ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች፤

5. ከተሽከርካሪ በስተቀር ወደአገር የሚገቡ መንገደኞች ይዘዋቸው የሚመጡ አግባብ ባለው ሕግ የተፈቀዱ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች፤