Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View T
የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View
የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.32K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-28 07:20:12 ኢድ ሙባረክ!

እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል አድሀ(አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!
5.4K viewsWasyhun Belay, 04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 20:41:19 28 ግራም ወርቅ 35 ዶላር የሚመነዘርበት ወቅት! በዓለም ላይ የወርቅ ክምችት እንደምንዛሬ የሚቆጠርበት ጊዜ እና ወርቅ በዶላር የመቀየር ልምምድ| "Bancor" የተባለው ዓለም አቀፍ ገንዘብ በዶላር የመሸነፍ ሚስጥር| ዶላርን የዓለም ዘዋሪ ገንዘብ ያደረገው አጋጣሚ!


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን

ትንታኔ ይመልከቱ! ለሌሎችም እንዲማሩበት አጋሩት!
5.7K viewsWasyhun Belay, edited  17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 19:26:09 የንብረት ታክስ በመንግስት፤ በንብረቱ ባለቤት እና በተከራይ እይታ ሊኖረው የሚችለው ኢኮኖሚያዊ ተቃርኖ! #ለምሳሌ፡- መንደር ውስጥ ገባ ብሎ ያለ አንድ ህንጻ (የመሸጫም ሆነ የኪራይ ዋጋው ገባ ከማለቱ ጋር ቀጥተኛ ይገናኛል!) በህንጻው አጠገብ የአስፓልት መንገድ ቢወጣ ህንጻው መንገድ ዳር በመሆኑ ብቻ Land Value መጨመሩ አይቀርም! (የመሸጫም ሆነ የኪራይ ዋጋው መንገድ ዳር ከመሆኑ ጋር ቀጥተኛ ይገናኛል!)፡፡


ህንጻው መንገድ ዳር በመሆኑ ብቻ የሽያጭም ሆነ የኪራይ ዋጋው ለመጨመሩ የህንጻው ባለቤት ሚና ዜሮ ሲሆን (ግብር ከፋይ ከሆነ የተመጠነ አስተዋጾ ሊኖረው ይችላል!) ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ እና ፕሮጀክቱን ያሰራው መንግስት ብቻ ነው ዋና ሚና የሚኖራቸው!፡፡


የንብረት ታክስ ሰብሳቢው አካል ህንጻውን ከመንገድ ገባ ብሎ በነበረበት ወቅት ከሚያስከፍለው፡ መንገድ ዳር መሆኑን ተከትሎ የደረጃ ለውጥ በማምጣቱ ብቻ ተጨማሪ የክፍያ መጠን ማስቀመጡ አይቀርም (የንብረት ታክስ ህንጻው ያለበትን ቦታ፤ ህንጻው እየሰጠ ያለውን አገልግሎት፤ የህንጻው ይዞታ ስፋት፤ ወዘተ ከግምት ይከታል)፡፡


ጉዳዩ መንግስት ለተለያዩ አገልግሎቶች በሚል በዘረጋው የአስፓልት መንገድ በአካባቢው ያሉ ህንጻዎችን ተፈላጊነት ያሳድጋል! የህንጻው ባለቤቶች ከነሱ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ምክንያት ህንጻቸው ዋጋው አድጓል፡፡ መንግስት በሚያለማው መሰረተ ልማት እና የህግ ማሻሻያ ምክንያት በመሬት እና መሬት ነክ ንብረቶች እሴታቸው (Value) ሊጨምር ይችላል!


#ጥያቄው፡- የተሰራው አስፓልት መንገድ እንደ ታክስ መጨመሪያ ምክንያት ወይስ የተሰራው አስፓልት እንደ የቋሚ ንብረቶች ተፈላጊነት ደረጃ ወይም የመሸጫ እና የማከራያ ዋጋ ጭማሪ ይቆጥሩታል የሚለው ነው? (ከመሬት ፖሊሲው ጋር ቆይቶም ቢሆን መዛመዱ አይቀርም)፡፡


መሬት የግለሰብ በሆነባቸው ሃገራት የመንግስት መሰረተ ልማት በአካባቢው ሲሰራ በቋሚ ንብረት ሽያጭ ወቅት በሚኖራቸው የዋጋ ድርድር ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያገኙ በማሰብ ደስተኛ ይሆናሉ! በሀገራችን የመሰረተ ልማት መኖር የቋሚ ንብረቶችን ዋጋ በተዘዋዋሪ ስለሚጨምር እና የንብረት ታክስን አብሮ መጨመሩ ስለሚጠበቅ መሰረተ ልማቱን በቀጣይ ወቅቶች አንዴት እያዩት የሚሄዱ ይመስላችኋል? (በኢትዮጲያ ለልማት የተፈለገ የግል ይዞታ በባለቤት በኩል ያለው የዋጋ ድርድር አቅም የተገደበ ነው!)፡፡


የመንግስት መከራከሪያ ከግብር ከሰበሰብኩት ገቢ ወጪ አውጥቼ የሰራውት አስፓልት መንገድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከህንጻው ታገኙ የነበረውን ገቢ በማሳደጉ ልካስ ይገባል አይነት ነው፡፡


ህንጻው ገባ ብሎ በነበረበት ወቅት ተከራይቶ የነበረ የህንጻ ተከራይ ህንጻው በአስፓልቱ መንገድ ምክንያት ዋጋው (Land Value) በመጨመሩ ወደ ንግድ ተቋሙ በርካታ ሸማች ሊመጣ መቻሉን እና በአስፓልቱ መንገዱ ምክንያት የጨመረበትን የቤት ኪራይ ዋጋ እንዴት ያወዳድራል?


በመንግስት መሰረተ ልማት እና የንብረት ባለቤቶች መካከል፤ በንብረት ባለቤቶች እና ተከራዮች መካከል እዲሁም በተከራዮች እና በመጨረሻ ሸማቾች መካከል የመሰረተ ልማት መሰራት የሚፈጥረውን ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ መተላለፍን እንዴት ማስታመም ይቻላል?
6.4K viewsWasyhun Belay, 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 18:09:25 በዋጋ ንረት (Inflation) እና በዋጋ ዝቅጠት (Deflation) መካከል ያለ የአደጋ ልዩነት! የዓለም ልምድ እና የማቃለያ መላዎች!

ዋጋ ንረት (Inflation)፡- በተከታታይ የአገልግሎት እና የቁሳቁስ ዋጋ መጨመር ሲሆን ምክንያቱ የምርት እጥረት እና የፍላጎት መጠን መጨመር ናቸው፡፡

ለምሳሌ በታሪክ ከፍተኛው የዋጋ ንረት…..

ሀንጋሪ፦ 1946 የዋጋ ንረቱ በወር 41.9 ኳድሪሊየን ከመቶ።

ዝምባዋብዌ፦ 2008 የዋጋ ንረቱ በወር 79 ቢሊየን ከመቶ።

ይጎዝላቪያ፦ 1994 የዋጋ ንረቱ በወር 313 ሚሊየን ከመቶ።

ጀርመን፦ 1923 የዋጋ ንረቱ በወር 29ሺ ከመቶ፡፡

ግሪክ፦ 1944 የዋጋ ንረቱ በወር 14ሺ% ከመቶ።

የዋጋ ዝቅጠት (Deflation)፡- በተከታታይ የአገልግሎት እና የቁሳቁስ ዋጋ መቀነስ ወይም ዋጋ ንረት ከዜሮ በታች ሲሆን ማለት ሆኖ ምክንያቱ የምርት መጠን ከፍተኛ መሆን እና የፍላጎት መጠን ማነስ፡፡ በተጨማሪም ከፍተኛ ስራ አጥነት፤ የገንዘብ እጥረት እና የውጪ ምርት ጥገኝነት ሲኖር ነው፡፡

ለምሳሌ በታሪክ ከፍተኛው የዋጋ ዝቅተት…..

እንግሊዝ፡- 1921 (ከዜሮ በታች 10 ከመቶ)፣ 1922 (ከዜሮ በታች 14ከመቶ)፣1930 (ከዜሮ በታች 5 ከመቶ)፤

አሜሪካ፡- 1930-1933 (ከዜሮ በታች 7 ከመቶ)፤

ግሪክ፡- (2013-2015)፤

ኦንግ ኮንግ፡- (1997-2004)፤

ጃፓን፡- (1999-2009)፤

አይርላንድ፡- (1933) 0.1ከመቶ፤

ደቡብ ሱዳን (2022) 12.7ከመቶ (የገንዘብ እጥረት እና የውጪ ምርት ጥገኝነት)

የአንድ ሃገር ኢኮኖሚ ግዴታ ከሆነ ከዋጋ ዝቅጠት ይልቅ የዋጋ መጋሸብን ሊመርጥ ይችላል! ምክንያቱም ለማስታመም ግሽበት የዝቅጠት የተሻለ እድል ስላለው ነው፡፡

እንዴት?

በዋጋ ግሽበት ወቅት አምራቾች በግብዓት እጥረት ሲፈተኑ፤ ሸማቾች በመሸመቻ ዋጋ ይፈተናሉ! ጠቅላላ ኢኮኖሚው በሸመታ መቀዛቀዝ እና በምርት መቀነስ ወደ ፈተና ይገባል! (የሸማች ቁጥር እና መጠን መቀነስን ተከትሎ የምርት መጠን መቀነሱ አይቀርም! ምርት መጠንን በመቀነስ ሰበብ ሰራተኛ መበተን ወይም ግሽበትን ተከትሎ ክፍያን ማሳደግ ተፈጥሮ ዋጋ ንረቱ እንዲደጋገም ሊያደርግ ይችላል!)፡፡

በዋጋ መዝቀጥ ወቅት አምራቾች ያመረቱበትን ወጪ መተካት በመቸገር ሰራተኛ የመበተን ችግር እንዲሁም ሰራተኛ በመበተን ከጠቅላላ ምርት መጠናቸው ሲወርዱ የሃገር ውስጥ ግብር መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡

ሁለቱም ችግሮች ገንዘብን ወደ ገበያ በመልቀቅ ሊፈቱ ቢችሉም ገንዘብን ወደ ገበያ መልቀቅ ጥናት ከሌለው ሁለቱንም ችግሮች ይበልጥ ሊያባብሳቸው ይችላል፡፡



የኢኮኖሚ ግንዛቤዎን ለመጨመር

6.6K viewsWasyhun Belay, 15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 20:28:35 በዋጋ ንረት (Inflation) እና በዋጋ ዝቅጠት (Deflation) መካከል ያለ የአደጋ ልዩነት! የዓለም ልምድ እና የማቃለያ መላዎች!


የኢኮኖሚ ግንዛቤዎን ለመጨመር

6.3K viewsWasyhun Belay, 17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 13:54:05 የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ታሪክ ለመረመረ ኢትዮጵያ ሶስቱንም የኢኮኖሚ አማራጮች (ከፊል ነፃ ገበያ፤ ኮሚኒስት እና ጣልቃ ገብ አስተዳደር) በተለያየ ጊዚያት ተጠቅማለች አሁንም እያፈራረቀች በመጠቀም ላይ ነች!  ታዲያ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሶስቱም ርዕዮቶች ድህነትን የሚያስተናግደው ለምን ይመስላችኋል?


የርዕዮቱን ልዩነት ትንታኔ ለማየት ለምትፈልጉ

6.6K viewsWasyhun Belay, 10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 19:31:27 ላለፉት 250 ዓመታት የዓለም የኢኮኖሚ ቅርጽ አፈጣጠር (ይህንን ማወቅ ጠቃሚ ነው!) በአለም ታሪክ ውስጥ በጣም ተደማጭነት የነበራቸው የሶስቱ የኢኮኖሚክስ ሊቃውንት የሃሳብ ጦርነት "The Big Three in Economics" ። አዳም ስሚዝ (ነጻ ገበያ ሲወክል)፤ ካርል ማርክስ፤ (አክራሪ ሶሻሊስት ሞዴልን ያንጸባርቃል እንዲሁም ጆን ሜይናርድ ኬይንስ (በገበያ የመንግስት ሚናን ያመለክታል፡፡ የእያንዳንዳቸው አመለካከት ዘመናዊውን ዓለም በመቅረጽ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡

#አዳም_ስሚዝ (ከ1723-1790)
አዳም ስሚዝ በ1776 የኢኮኖሚ አብዮት አወጀ! አዳም ስሚዝ አጠቃላይ መርሆዎች፡ የኢኮኖሚክስ ክላሲካል ሞዴል ሆነው ያገለግላሉ እነሱም….
ነፃነት፡- ግለሰቦች እንደፈለጉት ምርት፣ ጉልበት እና ካፒታል የማምረት እና የመለዋወጥ መብት አላቸው።

ውድድር፡- ግለሰቦች በሸቀጦችና አገልግሎቶች ምርትና ልውውጥ ላይ የመወዳደር መብት አላቸው።

ፍትህ፡ የግለሰቦች ተግባር በህብረተሰቡ ህግ መሰረት ፍትሃዊ እና ታማኝ መሆን አለበት።

ቆጣቢነት፣ ጠንክሮ መሥራት፣ የግል ጥቅምን ማጎልበት እና ለዜጎች ቸርነት በጎነት ናቸው እናም ሊበረታቱ ይገባል።

መንግሥት በኢኮኖሚው ሊኖረው የሚገባው ሚና ፍትህን ማስፈን፣ የግል ንብረት መብቶችን ማስከበር፣ በአንዳንድ ህዝባዊ ሥራዎች ላይ መሰማራት እና ሀገርን ከጥቃት መከላከል መሆን አለበት (ነፃ ንግድ፣ ዝቅተኛ ግብር፣ አነስተኛ ቢሮክራሲ፣ ወዘተ)።

የወርቅ/ብር ክምችት ስታንዳርድ መንግስት የመገበያያ ገንዘቡን እንዳይቀንስ ያግዘዋል።

#ካርል_ማርክስ (ከ1818-1883)
ካርል ሄንሪች ማርክስ ጀርመናዊ ፈላስፋ፣ ኢኮኖሚስት፣ የታሪክ ምሁር፣ ሶሺዮሎጂስት፣ የፖለቲካ ቲዎሪስት፣ ጋዜጠኛ፣ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ተቺ እና የሶሻሊስት አብዮተኛ ነበር። በጣም የታወቀው በ1848ቱ የኮሚኒስት ማኒፌስቶ ነው። ነጻ ገበያ ላይ አቢዮት ያስነሳ ነው፡፡

በስሚዝ እና በማርክስ መካከል ያለው “ዋና ልዩነት” የሚከተለው ነው።
ስሚዝ የግለሰቡ የግል ጥቅምን ማሳደድ ለሁሉም የሚጠቅም ውጤት እንደሚያስገኝ ተከራክሯል፣ ማርክስ ግን የራስን ጥቅም ማሳደድ ወደ አለመረጋጋት፣ ቀውስ እና የግል ንብረት መበተን ያስከትላል ሲል ተከራክሯል። ካርል በካፒታሊዝም ስርዓት ላይ አብዮት ነው ያስነሳው።

ማርክስ የራሱን የአስተሳሰብ ትምህርት ቤት፣ በራሱ ዘዴ እና ልዩ ቋንቋ ያቋቋመ የመጀመሪያው ኢኮኖሚስት ሳይሆን አይቀርም። ከማርክስ ጀምሮ ኢኮኖሚክስ አንድ አይነት ሆኖ አያውቅም።

ማርክስ ሲከራከር የካፒታሊዝም ቀውስ ወጭ መቀነስ፣ የትርፍ ማሽቆልቆል፣ የብቸኝነት ሃይል (Monopolistic Power)፣ የፍጆታ መቀነስ (Under-Consumption)፣ ከፍተኛ ስራ አጥነት፤ ወዘተ ሲሆን እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች የመንፈስ ጭንቀት ያስከትላሉ ይላል፡፡

ማርክስ እና ኢንግልስ ባለ አስር ​​ነጥብ የኮሚኒስት ማኒፌስቶ አውጥተዋል እነሱም…

ሁሉንም የመሬት ሃብት እና ኪራይ ለሕዝብ ጥቅም ማዋል፣ አዳጊ የገቢ ግብር መጠን መጣል፣ የውርስ መብትን በሙሉ መሰረዝ፣ የሁሉም ስደተኞች እና አመጸኞች ንብረት መውረስ፤ የብድር አቅርቦትን በመንግስት እጅ ውስጥ ማድረግ፤ የመገናኛ እና የመጓጓዣ መንገዶችን በመንግስት እጅ ማድረግ፤ በመንግስት ባለቤትነት የተያዙ ፋብሪካዎች እና የማምረቻ መሳሪያዎች ማራዘም፤ ቆሻሻ መሬቶችን ወደ ልማት ማምጣት፤ ሁሉም ላይ የመሥራት እኩል ግዴታ መጣል፤ ግብርና ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ጥምረት፤ በከተማ እና በአገር መካከል ያለውን ልዩነት ቀስ በቀስ ማጥፋት፣ በአገሪቱ ላይ የበለጠ ፍትሃዊ የህዝብ ስርጭት መፍጠ፤ በሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ላሉ ልጆች ትምህርት በነጻ ማቅረብ፤ በፋብሪካ የሕፃናት የጉልበት ሥራ ማስወገድ፤ ትምህርትን ከኢንዱስትሪ ጋር ማጣመር፤ ወዘተ፡፡

የማርከስ ትንበያ ያልተሳኩ ያስመሰሉት እውነቶች!
በካፒታሊዝም ስር የትርፉ መጠን ማሽቆልቆል አልቻለም፡፡

የሰራተኛ መደብ ከበለጠ እና ከከፋ መከራ ውስጥ አልገባም፤ የደመወዝ ክፍያ ከኑሮ ደረጃው በላይ ጨምሯል፤ በኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ አገሮች በአማካይ ሠራተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ በሚያስደንቅ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል፤ መካከለኛው ክፍል አልጠፋም እንዲያውም ተስፋፍቷል.

የሶሻሊስት ማህበረሰቦች እንደታሰበው አላደጉም፡፡

ምንም እንኳን አልፎ አልፎ ከፍተኛ የመንፈስ ጭንቀት ቢኖርም ካፒታሊዝም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እያደገ የመጣ ይመስላል፡፡

#ጆን_ሜይንራድ_ኬይነስ (ከ1883-1946)
ኬይነስ የጀመረው አዳም ስሚዝን ስውሩ እጅ (Invisible Hand Doctrine) ከመተቸት ነው! ኬይንስ የካፒታሊዝም አዳኝ ተብሎ ተመስግኗል፡፡ ነገር ግን የእሱ ሞዴል እና የፖሊሲ ምክሮች በብዙ መልኩ በአዳም ስሚዝ ነጻ ገበያ ስርዓት ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ነበሩ። አዳም ስሚዝ “ግለሰቦች በኢኮኖሚ ተግባራቸው ውስጥ የተፈጥሮ ነፃነት (Self-Interest) አላቸው“ የሚለው ሃሳብ እውነት አይደለም ይልና ልምዱ የሚያሳየው ግለሰቦች፣ ማሕበራዊ ጥምረት ሲፈጥሩ፣ ሁልጊዜም ተለያይተው ከሚሰሩበት ጊዜ ይልቅ የማየት ችሎታቸው ያነሰ ነው” ይላል።

ኬይንስ የሚከተሉትን መርሆች አቅርቧል…..
የቁጠባ መጨመር ገቢን ሊቀንስ እና የኢኮኖሚ እድገትን ሊቀንስ ይችላል. ኢንቨስትመንትን ከማበረታታት ይልቅ ፍጆታ ከማምረት የበለጠ ጠቃሚ ነው፣ ስለዚህ የሳይ ህግን “ፍላጎት የራሱን አቅርቦት ይፈጥራል” መቀየር።

ኢኮኖሚ እየወደቀ ሲመጣ የፌደራል መንግስት በጀት ሆን ተብሎ ሚዛናዊ ባልሆነ ሁኔታ (የበጀት ጉድለት) ውስጥ መቀመጥ አለበት፤ የፊስካል እና የገንዘብ ፖሊሲ ​​በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋት አለበት እና የወለድ ተመኖች በቋሚነት ዝቅተኛ መሆን አለባቸው።

መንግስት የነጻ ገበያ ፖሊሲውን ትቶ በገበያው ውስጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ጣልቃ መግባት።

ኢኮኖሚን ለማረጋጋት የወርቅ ስታንዳርድ ጉድለት ያለበት ነው (የመለጠጥ አቅም የለውም) ስለዚህ የወረቀት ገንዘብ ይመረጣል።

ኬይንስ እንደሚለው በነጻ ገበያ ውስጥ የምንቆይ ከሆነ በረጅም ጊዜ ውስጥ ሁላችንም ሟቾች ነን ይላል “In the Long Run We Are All Dead”፡፡
7.0K viewsWasyhun Belay, edited  16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-21 19:35:32 "The Big Three in Economics" የዓለም ታሪክን የቀረጹ የሶስቱ የኢኮኖሚክስ ሊቃውንት የሃሳብ ጦርነት!

1. አዳም ስሚዝ (1723-1790) ነጻ ገበያ የሚወክል

2. ካርል ማርክስ (1818-1883) አክራሪ ሶሻሊስት ሞዴልን የሚያንፀባርቅ

3. ጆን ሜይናርድ ኬይንስ (1883-1946) የመንግስትን የጣልቃ ገብነት ሚና የሚያመለክት

የእያንዳንዳቸው አመለካከት ዘመናዊውን ዓለም በመቅረጽ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል! ሁላችሁም ይህንን

ማወቅ አለባችሁ!
6.0K viewsWasyhun Belay, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-21 08:04:26 "The Big Three in Economics" የዓለም ታሪክን የቀረጹ የሶስቱ የኢኮኖሚክስ ሊቃውንት የሃሳብ ጦርነት!

1. አዳም ስሚዝ (1723-1790) ነጻ ገበያ የሚወክል

2. ካርል ማርክስ (1818-1883) አክራሪ ሶሻሊስት ሞዴልን የሚያንፀባርቅ

3. ጆን ሜይናርድ ኬይንስ (1883-1946) የመንግስትን የጣልቃ ገብነት ሚና የሚያመለክት

የእያንዳንዳቸው አመለካከት ዘመናዊውን ዓለም በመቅረጽ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል! ሁላችሁም ይህንን

ማወቅ አለባችሁ!
6.0K viewsWasyhun Belay, edited  05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 20:43:30 2016 በጀት ልዩ ባህሪያት.....


1. የ2016 በጀት 801.6 ቢሊየን ብር ከ2015 (786.6 ቢሊየን ብር) አንጻር የ1.9 ከመቶ ብቻ ጭማሪ ያለው በጀት መሆኑ.......


2. በ2016 የካፒታል ወጪ ብር 218.11 ቢሊየን ከ2015 አንፃር ወደ 203.9 ቢሊዮን (6.51% ቅናሽ) ማድረጉ......


2. የ2016 በጀት 27% የዋጋ ንረትን ከግምት ቢከት ወደ 1 ትሪሊየን ብር ሊደርስ ይችል ነበር......


የኢትዮጵያ በጀት በ3 ዓመት ውስጥ (ከ2014 እስከ 2016 ዓ/ም) የሚፈጥረው ለውጥ ምንን አመላካች ነው? ንፅፅሩን ተመልከቱ።



1.4K viewsWasyhun Belay, 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ