Get Mystery Box with random crypto!

የንብረት ታክስ በመንግስት፤ በንብረቱ ባለቤት እና በተከራይ እይታ ሊኖረው የሚችለው ኢኮኖሚያዊ ተቃ | The Ethiopian Economist View

የንብረት ታክስ በመንግስት፤ በንብረቱ ባለቤት እና በተከራይ እይታ ሊኖረው የሚችለው ኢኮኖሚያዊ ተቃርኖ! #ለምሳሌ፡- መንደር ውስጥ ገባ ብሎ ያለ አንድ ህንጻ (የመሸጫም ሆነ የኪራይ ዋጋው ገባ ከማለቱ ጋር ቀጥተኛ ይገናኛል!) በህንጻው አጠገብ የአስፓልት መንገድ ቢወጣ ህንጻው መንገድ ዳር በመሆኑ ብቻ Land Value መጨመሩ አይቀርም! (የመሸጫም ሆነ የኪራይ ዋጋው መንገድ ዳር ከመሆኑ ጋር ቀጥተኛ ይገናኛል!)፡፡


ህንጻው መንገድ ዳር በመሆኑ ብቻ የሽያጭም ሆነ የኪራይ ዋጋው ለመጨመሩ የህንጻው ባለቤት ሚና ዜሮ ሲሆን (ግብር ከፋይ ከሆነ የተመጠነ አስተዋጾ ሊኖረው ይችላል!) ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ እና ፕሮጀክቱን ያሰራው መንግስት ብቻ ነው ዋና ሚና የሚኖራቸው!፡፡


የንብረት ታክስ ሰብሳቢው አካል ህንጻውን ከመንገድ ገባ ብሎ በነበረበት ወቅት ከሚያስከፍለው፡ መንገድ ዳር መሆኑን ተከትሎ የደረጃ ለውጥ በማምጣቱ ብቻ ተጨማሪ የክፍያ መጠን ማስቀመጡ አይቀርም (የንብረት ታክስ ህንጻው ያለበትን ቦታ፤ ህንጻው እየሰጠ ያለውን አገልግሎት፤ የህንጻው ይዞታ ስፋት፤ ወዘተ ከግምት ይከታል)፡፡


ጉዳዩ መንግስት ለተለያዩ አገልግሎቶች በሚል በዘረጋው የአስፓልት መንገድ በአካባቢው ያሉ ህንጻዎችን ተፈላጊነት ያሳድጋል! የህንጻው ባለቤቶች ከነሱ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ምክንያት ህንጻቸው ዋጋው አድጓል፡፡ መንግስት በሚያለማው መሰረተ ልማት እና የህግ ማሻሻያ ምክንያት በመሬት እና መሬት ነክ ንብረቶች እሴታቸው (Value) ሊጨምር ይችላል!


#ጥያቄው፡- የተሰራው አስፓልት መንገድ እንደ ታክስ መጨመሪያ ምክንያት ወይስ የተሰራው አስፓልት እንደ የቋሚ ንብረቶች ተፈላጊነት ደረጃ ወይም የመሸጫ እና የማከራያ ዋጋ ጭማሪ ይቆጥሩታል የሚለው ነው? (ከመሬት ፖሊሲው ጋር ቆይቶም ቢሆን መዛመዱ አይቀርም)፡፡


መሬት የግለሰብ በሆነባቸው ሃገራት የመንግስት መሰረተ ልማት በአካባቢው ሲሰራ በቋሚ ንብረት ሽያጭ ወቅት በሚኖራቸው የዋጋ ድርድር ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያገኙ በማሰብ ደስተኛ ይሆናሉ! በሀገራችን የመሰረተ ልማት መኖር የቋሚ ንብረቶችን ዋጋ በተዘዋዋሪ ስለሚጨምር እና የንብረት ታክስን አብሮ መጨመሩ ስለሚጠበቅ መሰረተ ልማቱን በቀጣይ ወቅቶች አንዴት እያዩት የሚሄዱ ይመስላችኋል? (በኢትዮጲያ ለልማት የተፈለገ የግል ይዞታ በባለቤት በኩል ያለው የዋጋ ድርድር አቅም የተገደበ ነው!)፡፡


የመንግስት መከራከሪያ ከግብር ከሰበሰብኩት ገቢ ወጪ አውጥቼ የሰራውት አስፓልት መንገድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከህንጻው ታገኙ የነበረውን ገቢ በማሳደጉ ልካስ ይገባል አይነት ነው፡፡


ህንጻው ገባ ብሎ በነበረበት ወቅት ተከራይቶ የነበረ የህንጻ ተከራይ ህንጻው በአስፓልቱ መንገድ ምክንያት ዋጋው (Land Value) በመጨመሩ ወደ ንግድ ተቋሙ በርካታ ሸማች ሊመጣ መቻሉን እና በአስፓልቱ መንገዱ ምክንያት የጨመረበትን የቤት ኪራይ ዋጋ እንዴት ያወዳድራል?


በመንግስት መሰረተ ልማት እና የንብረት ባለቤቶች መካከል፤ በንብረት ባለቤቶች እና ተከራዮች መካከል እዲሁም በተከራዮች እና በመጨረሻ ሸማቾች መካከል የመሰረተ ልማት መሰራት የሚፈጥረውን ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ መተላለፍን እንዴት ማስታመም ይቻላል?