Get Mystery Box with random crypto!

በዋጋ ንረት (Inflation) እና በዋጋ ዝቅጠት (Deflation) መካከል ያለ የአደጋ ልዩነት! | The Ethiopian Economist View

በዋጋ ንረት (Inflation) እና በዋጋ ዝቅጠት (Deflation) መካከል ያለ የአደጋ ልዩነት! የዓለም ልምድ እና የማቃለያ መላዎች!

ዋጋ ንረት (Inflation)፡- በተከታታይ የአገልግሎት እና የቁሳቁስ ዋጋ መጨመር ሲሆን ምክንያቱ የምርት እጥረት እና የፍላጎት መጠን መጨመር ናቸው፡፡

ለምሳሌ በታሪክ ከፍተኛው የዋጋ ንረት…..

ሀንጋሪ፦ 1946 የዋጋ ንረቱ በወር 41.9 ኳድሪሊየን ከመቶ።

ዝምባዋብዌ፦ 2008 የዋጋ ንረቱ በወር 79 ቢሊየን ከመቶ።

ይጎዝላቪያ፦ 1994 የዋጋ ንረቱ በወር 313 ሚሊየን ከመቶ።

ጀርመን፦ 1923 የዋጋ ንረቱ በወር 29ሺ ከመቶ፡፡

ግሪክ፦ 1944 የዋጋ ንረቱ በወር 14ሺ% ከመቶ።

የዋጋ ዝቅጠት (Deflation)፡- በተከታታይ የአገልግሎት እና የቁሳቁስ ዋጋ መቀነስ ወይም ዋጋ ንረት ከዜሮ በታች ሲሆን ማለት ሆኖ ምክንያቱ የምርት መጠን ከፍተኛ መሆን እና የፍላጎት መጠን ማነስ፡፡ በተጨማሪም ከፍተኛ ስራ አጥነት፤ የገንዘብ እጥረት እና የውጪ ምርት ጥገኝነት ሲኖር ነው፡፡

ለምሳሌ በታሪክ ከፍተኛው የዋጋ ዝቅተት…..

እንግሊዝ፡- 1921 (ከዜሮ በታች 10 ከመቶ)፣ 1922 (ከዜሮ በታች 14ከመቶ)፣1930 (ከዜሮ በታች 5 ከመቶ)፤

አሜሪካ፡- 1930-1933 (ከዜሮ በታች 7 ከመቶ)፤

ግሪክ፡- (2013-2015)፤

ኦንግ ኮንግ፡- (1997-2004)፤

ጃፓን፡- (1999-2009)፤

አይርላንድ፡- (1933) 0.1ከመቶ፤

ደቡብ ሱዳን (2022) 12.7ከመቶ (የገንዘብ እጥረት እና የውጪ ምርት ጥገኝነት)

የአንድ ሃገር ኢኮኖሚ ግዴታ ከሆነ ከዋጋ ዝቅጠት ይልቅ የዋጋ መጋሸብን ሊመርጥ ይችላል! ምክንያቱም ለማስታመም ግሽበት የዝቅጠት የተሻለ እድል ስላለው ነው፡፡

እንዴት?

በዋጋ ግሽበት ወቅት አምራቾች በግብዓት እጥረት ሲፈተኑ፤ ሸማቾች በመሸመቻ ዋጋ ይፈተናሉ! ጠቅላላ ኢኮኖሚው በሸመታ መቀዛቀዝ እና በምርት መቀነስ ወደ ፈተና ይገባል! (የሸማች ቁጥር እና መጠን መቀነስን ተከትሎ የምርት መጠን መቀነሱ አይቀርም! ምርት መጠንን በመቀነስ ሰበብ ሰራተኛ መበተን ወይም ግሽበትን ተከትሎ ክፍያን ማሳደግ ተፈጥሮ ዋጋ ንረቱ እንዲደጋገም ሊያደርግ ይችላል!)፡፡

በዋጋ መዝቀጥ ወቅት አምራቾች ያመረቱበትን ወጪ መተካት በመቸገር ሰራተኛ የመበተን ችግር እንዲሁም ሰራተኛ በመበተን ከጠቅላላ ምርት መጠናቸው ሲወርዱ የሃገር ውስጥ ግብር መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡

ሁለቱም ችግሮች ገንዘብን ወደ ገበያ በመልቀቅ ሊፈቱ ቢችሉም ገንዘብን ወደ ገበያ መልቀቅ ጥናት ከሌለው ሁለቱንም ችግሮች ይበልጥ ሊያባብሳቸው ይችላል፡፡



የኢኮኖሚ ግንዛቤዎን ለመጨመር