Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View T
የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View
የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.32K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 36

2022-08-12 19:01:41 #ብዝሃ_ዋና_ከተሞች!

በቀላሉ አዲስ አበባ እና የክልል ከተሞች እንዲሁም አዲስ አበባ እና በዙሪያዋ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚኖሩ መንደሮች፤ የክልል ዋና ከተሞች እና ሌሎች የዞን ከተሞች መካከል ያለውን የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ልዩነት ተመልከቱ!

ኢትዮጲያ ለአዲስ አበባ አቻ ተቀራራቢ #ኢኮኖሚያዊ ደረጃ ያለው ከተማ የላትም! ኦሮሚያ ውስጥ የአዳማ አቻ ከተማ ለማግኘት ከባድ ነው፤ ባህርዳር ከተማ ላይ ለመድረስ የክልሉ ከተሞች ገና ብዙ ይቀራቸዋል፤ ድሬዳዋ እና ሀረርም አይቀራረቡም፤ ደቡብ ክልል ከተሞች በጥቂቱ ነው ነባሪያዊ የእድገት ቅርርብ ያላቸው፤ በትግራይ ክልል ከተሞች የመቀሌን ያህል አይደሉም፤ አፋርም ሶማሌም ከክልል መቀመጫ ከተሞቹ ውጪ ያሉ ከተሞቻቸው የተፎካካሪነት አቅማቸው ገና ነው (በተለያየ አጋጣሚ አብዛኛዎቹን ክልል እና ከተሞች የመመልከት እድል ነበረኝ)፡

የወረዳ ነዋሪ ወደ ዞን፤ የዞን ነዋሪ ወደ ክልል መቀመጫ፤ የክፍለ ሀገር ነዋሪ ወደ አዲስ አበባ ለመዘዋወር ከሚቀመጡ መሰረታዊ ምክንያቶች መካከል አንዱ ከተሞች ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እድሎቻቸው የተራራቀ በመሆኑ ነው፡፡

የሀገራት ኢኮኖሚ በተለይ በታዳጊ ሀገራት ሁለት መልክ አለው (Dual Economy)! አንደኛው ገጠሩ (Traditional Sector)፤ በግብርና ዘርፍ የሚተዳደረው፤ ደካማ የተቋማት እና የቴክኖሎጂ ለውጥ የሌለው ሲሆን ሁለተኛው ከተሜው (Modern Sector)፤ ኢንዱስትሪ መዳረሻ ያለበት እና የቴክኖሎጂ እገዛ ተጋሪ የሆነው ማለት ነው፡፡ የኢኮኖሚ እድገት በፍጥነት መሄድ ካስፈለገው የገጠሩ ክፍለ ኢኮኖሚ ከምርታማነት ሳይቀንስ ከተሜነትን በማስፋፋት እድገትን ማስቀጠል ይገባል/ይቻላል፡፡

ከተሜነት በተወሰኑ ቦታዎች በሚስፋፉበት ወቅት የገጠሩ የሰው ሃይል ወደ ከተሞች ሲፈልስ በአብዛኛው በጉልበት ስራ ላይ ስለሚሰማሩ ኢኮኖሚው በፈጠራ ከመሞላት ይልቅ ነዋሪዎች የከተሞችን ማህበራዊ አገልግሎት ወደ ማጣበብ/መሻማት ይሄዳሉ፡፡

በሀገራችን የትልልቅ ከተሞች አሁናዊ ሁኔታ ከዚህ ሃሳብ የተለየ አይደለም! ገጠሩ ክፍለ ኢኮኖሚ የመሬት ባለቤትነት፤ የመሰረተ ልማት አቅርቦት፤ የምርታማነት መቀነስ፤ የሰዎች ጉልበት መባከን (የመሬት መጠን ማነስ ብዙ የቤተሰብ አባላት አነስተኛ መሬት ላይ እንዲሰሩ ስለሚያደርግ ከአቅም በታች መስራት መገለጫው ነው)፡፡

#ለምሳሌ፦ አንድ አባወራ ከቤተሰቡ 1 ሄክታር ወርሶ ይኖር ከነበረ እና በሂደት 8 ልጆች ወልዶ እድሜያቸው በደረሱ ቁጥር ከመሬቱ እየቀነሰ ቢሰጥ አልያም ብቻውን ያርሰው የነበረ መሬት ከልጆቹ ጋር 9 ሆነው ቢያርሱት የ8ቱ ሰዎቹ ጉልበት በማሳው ላይ ሚናው (Marginal effect) ዜሮ ነው! ስለዚህ ልጆቹ ስራ ፍለጋ ወደ ከተሞች/ኢንዱስትሪ አካባቢዎች መጓዛቸው አይቀርም (የገጠሩ ነዋሪ በአብዛኛው ለከፍተኛ ትምህርት ሩቅ በመሆኑ ከተሜው ለገጠሬው የሚያቀርበው ስራ የጉልበት ስራ/ የቤት ሰራተኝነት የመሆን እድሉ ሰፊ ነው)፡፡

የተመጣጠነ የኢኮኖሚ እድገት መንገዶችን በገጠር እና ከተማ ለመፍጠር የመቶ ዓመታት ጊዜ ሊወስድም ይችላል! አንዳንድ ሀገራት በኢኮኖሚ ሚናቸው የፈረጠሙ ከተሞችን በመፍጠር ኢኮኖሚያቸው ወጥ እንዲሆን ማድረግ እየቻሉ ነው። #ለምሳሌ፦ 3 ዓመት በሞላው አንድ ጥናት ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ክልሎች በሙሉ 50% GDP ድርሻ የላቸውም።

በከተሞች እና ገጠር መካከል ያለው የተለያየ የኢኮኖሚ እድገት ሁኔታ ገጠሩን በሴክተር ተዋፅዎ ወደ ከተሜነት በማሳደግ፤ የምርታማነት ደረጃን የሚያሻሽሉ ስራዎችን በመስራት፤ የሃብት ክፍፍልን ጤናማ በማድረግ፤ ወዘተ ዘላቂ ሁኔታው የተስተካከል እንዲሆን የፖሊሲ እገዛ ያስፈልገዋል፡፡

ትምህርት ለሁሉም በሚለው ፖሊሲ የአርሶ አደሩ ልጆች እንዲማሩ ጥረት ሲደረግ በመርህ ደረጃ የሚያገኙትን ከፍተኛ ትምህርት በመጠቀም አዳዲስ አሰራሮች እና ግብዓቶችን በመጠቀም በቤተሰቦቻቸው ማሳ ላይ ምርታማነት ደረጃዎችን ያሳድጋሉ የሚል ነው (ምክንያቱም የግሉም የመንግስትም ሴክተር በቋሚነት ቀጥሮ የሚጨርሰው ሃይል ስለማይሆን፣ የሀብት መሰረት የሆነው መሬት ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ግድ ነው፡፡

ነገር ግን በዋናነት ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ የአርሶ አደሩ ልጆች ዘመናዊ የትምህርት ማስረጃ ይዘው ግብርናው ላይ ከሚሳተፉ የወረዳ፤ ዞን፤ ክልል እና ፌደራል ከተሞች ላይ ዝቅተኛ ደሞዝ እያገኙ ተቀጥረው ለመስራት ከገጠር ወደ ከተማ ስደትን ይመርጣሉ (ይህ ጉዳይ በአጭሩ የሚቆም አይደለም!)፡፡ ስለዚህ የገጠር ክፍለ ኢኮኖሚው የሚታይበት መነጽር እና የከተሜነት መስፋፋት ስትራቴጂ የተናበበ አንዲሆን ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ለከተሞች ማደግ ከሚነረዱ መንገዶች አንዱ የመንግስት አስተዳደር መቀመጫ መሆን እና የመሰረተ ልማት መስፋፋት በመሆኑ የመንግስት መቀመጫዎችን የነዋሪን እንግልት በማይፈጥር መልኩ የተለያዩ ከተሞች ላይ በማድረግ ተመጣጣኝ እንዲሆኑ እና አንዱ ከተማ በሌሎች ከተሞች ጫና ሳይፈጠርበት እንዲኖር በማድረግ የተሻለ ፖለቲካል እና ኢኮኖሚካል ውጤት ማምጣት ይቻላል፡፡
5.0K viewsWasyhun Belay, edited  16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 21:26:03 ይህ ክረምት የኢትዮጲያን ኢኮኖሚ ሊያቀዛቅዝ ይችላል!!

የዚህ ክረምት ወቅት የምርት ማምረቻ ሂደት እንጂ ምርት ወደ ገበያ የሚመጣበት አለመሆኑ፤ የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ በመደረጉ ከውጪ በየብስ ትራንስፖርት ተጓጉዞ የሚመጡ የውጪ ምርቶች ለማስገባት የዋጋ መጨመር መኖር፤ የመንግስት የበጀት በቀላሉ የሚለቀቅበት ወቅት ያለመሆኑ እና ክረምት ወቅትን ተከትሎ አንዳንድ ሴክተሮች ስራቸው መቀዛቀዙ ጠቅላላ የስራ እድልን እና የዋጋ ሁኔታን ሊለውጠው ስለሚችል የተለመደ የነበረውን የክረምት ወቅት የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ የባሰ ያደርገዋል በሚል ይህንን

ቪዲዮ አዘጋጅቻለሁ ተመልከቱት፡፡
1.4K viewsWasyhun Belay, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 08:20:09
3.5K viewsWasyhun Belay, 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:46:58 የነዳጅ ዋጋ ከ30% በላይ መጨመሩን ተከትሎ የሸቀጦች እና የአገልግሎት ዋጋ በስንት ይጨምራል?


የነዳጅ ድጎማ የተለመደ በመሆኑ የድጎማው መነሳት አዝማሚያ ሲያሳይ በቅርቡ እየታየ ያለው የነዳጅ ሰልፍ እና የቦቴ መኪኖች መደበቅ በ Psychological price መርህ የሚጠበቅ ነው።


ይህ ሰልፍ እና ድበቃ የሚቆየው የሃምሌ ወር ገብቶ የነዳጅ ሸማች እና የነዳጅ አቅራቢዎች የዋጋ እና የሁኔታ Adjustment/አቀባበል እስኪያደርጉ በጊዚያዊነት ነው ብዬ አምናለሁ!


ምክንያቱም ሸማች አዲሱን ዋጋ እየተለማመደ ይመጣል በተመሳሳይ አቅራቢዎች አዲሱ ዋጋ ወደስራ መግባቱን መደበኛ አቅርቦት አድርገው መቀበላቸው አይቀርም።


በነዳጅ እና በናፍጣ ላይ በሊትር ከ10 ብር በላይ ጭማሪ ወይም ከባለፈው ወር ከ30% በላይ ጭማሪ ሲፈጠር ማዕከላዊ ገበያው ላይ ተጠባቂ የዋጋዎች መጨመር መኖሩ ግድ ነው።


#ለምሳሌ፦ በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረው ቤንዚን፤ 10 ብር ከ96 ሳንቲም ጨማሪ በማሳየት ከነገ ጀምሮ በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም ይሸጣል።


#ለምሳሌ፦ በሊትር 35.43 ብር ሲሸጥ የነበረው ነጭ ናፍጣ 13.59 ብር ጨምሮ ከዛሬ ጀምሮ በሊትር 49.02 ብር ለገበያ ይቀርባል።


የድጎማ መጥፎ ጎን ገበያው ትክክለኛ ዋጋዎችን ሳያውቅ እንዲቆይ ማድረጉ ነው። ስለዚህ የመረጃ እጥረት፤ የአቅርቦት እጥረት፤ የማምረቻ ወጪ ውድነት እና ደካማ የገበያ አመራር ያለበት ገበያ ሲሆን መተራመሱ አይቀርም።


መንግስት ድንገት የሚፈጠሩ የአቅርቦት እና የዋጋ መናጋቶችን ለመቀነስ የአቅርቦት ስርጭት እና የገበያ ቁጥጥር ስራዎችን ማከናወን አለበት።


የዋጋ ትርምሶች ዝቅተኛ ገቢ የሚያገኘውን የህብረተሰብ ክፍል ይበልጥ ስለሚጎዳ የመሰረታዊ ቁሶች አቅርቦትን መንግስት መምራት አለበት።


የዋጋ ትርምስ ፈጣን አማራጭ የማረጋጊያ ስራዎች ካልተሰሩ ነዳጅን ሰበብ አድርገው የሚፈጠሩ አዳዲስ ዋጋዎች መደበኛ ዋጋ መሆን ስለሚጀምሩ ቅድሚያ የመሰረታዊ ሸቀጦች የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት ስርዓት በማበጀት የዋጋ ጭማሪ እንዳይለመድ ማድረግ አለበት።

3.3K viewsWasyhun Belay, 04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:46:57
3.0K viewsWasyhun Belay, 04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 19:40:57 ሸማቾች አንድን ምርትም ሆነ አገልግሎት ገዝቶ ለመጠቀም የመፈለጋቸው (Willingness) እና መግዛት የመቻላቸው (Ability) ሁኔታ፣ እንዲሁም በገበያ ያለው የምርትም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ ሰዎች ለመግዛት ከሚችሉት እና ከወሰኑት ዋጋ አንጻር ሲታይ ዝቅተኛ ከሆነ ጥሩ (ለሸማች ጤነኛ) ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ከላይ የተጠቀሰውን ልዩነት ከምናሰላበት መንገድ ዋነኛው Consumer Surplus ይባላል፡፡


#ለምሳሌ፡- አንድ አዲስ መኪና በገበያ ያለው ዋጋ 1.3 ሚሊየን (Actual price) ብር ነው ብለን ብናስብ እና ጠቅላላ የሸማች የመግዛት ፍላጎት መጠን 1 መኪና ሆኖ ነገር ግን በኪሱ ያለው ገንዘብ 500 ሺ (Maximum price willing to pay) ብር ብቻ ቢሆን፣ ሸማቹ መክፈል የሚችለው ከፍተኛ ገንዘብ መጠን 500ሺ ስለሆነ አዲሱን መኪና ገዝቶ መሄድ አይችልም፣ ነገር ግን የመኪና መግዛት ፍላጎቱ እንዲሳካ ያገለገለ መኪና በ400ሺ ብር መግዛት ቢችል:-


Consumer surplus (100ሺ) = 500ሺ- 400ሺ ሆነ ማለት ነው:: ሸማቹ የሚፈልገውን አግኝቶም 100ሺ ብር አተረፈ እንደማለት ነው፡፡


ሸማቾች ተመሳሳይ ምርትን ብዙ በተጠቀሙ ቁጥር ለተጨማሪው ምርት ለመክፈል ያላቸው ፍላጎት እየቀነሰ የሚሄደው ለምንድን ነው?


በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ውስጥ ተወዳጅ ከሆኑ ህጎች መካከል አንዱ The law of diminishing marginal utility ነው፡፡ #ለምሳሌ፡- በጣም የራበው ሰው ሳንዱች ማዘዝ ቢፈልግ የሚቀርብለትን ዋጋ ብዙም ድርድር ውስጥ ሳይከት ሊከፍል ይችላል (ምክንያቱም ከፍተኛ እርካታ የሚያገኝበት ስለሆነ) ነገር ግን ሁለተኛ ደግሞ ለማዘዝ እና ለመብላት የመጀመሪያውን ለመብላት እና ለመክፈል በወሰነው ፍጥነት ላይወስን ይችላል፣ ሶስተኛ ሳንዱች ጭራሽም ላያዝ ይችላል ማለት ነው፣ ምክንያቱም ከመራብ ስላገገመ ነው፡፡


ኢኮኖሚስቶች ሸማች እንቅልፉን የሚያጣው እርካታው ለማሳደግ ሲጥር ነው ይላሉ (Consumers are always trying to maximize their utility)፣ ይህ ሲባል ሰዎች ባላቸው ውስን ገቢ ወይም ሃብት የተወሰነ ምርትም ሆነ አገልግሎት በመጠቀም የተሻለ ደስታ ለመፍጠር ይሞክራሉ ለማለት ነው፡፡


በኢኮኖሚክስ ሰዎች ወይም ሸማቾች የደስታቸው ጣሪያ ላይ ለመድረስ እንዲችሉ በገበያ ያለው የምርትም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ መሰረታዊ ተጽኖ ፈጣሪ እና ወሳኝ ነው ይላሉ።
3.9K viewsWasyhun Belay, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 15:49:26 ይህ ወቅት ለአዲስ ተመራቂዎች ስራ ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው! ስለዚህ ከተለመደው የተለየ የስራ አፈላለግ ዘዴ፤ የስራ ቦታ እና አይነት ምርጫ እና በራስ ስራ የመጀመር ውሳኔዎችን ይጠይቃል፡፡ ኢኮኖሚው ለፍቶ ያስተማራቸውን ሰዎች እውቀት በአግባቡ በመጠቀሙ የሚያተርፈው እራሱ ጠቅላላ ኢኮኖሚው ነው፡፡ በተመሳሳይ ጥቂቶች ብቻ በትግል በሚያሸንፉበት የሰራተኛ እና የቢዝነስ ገበያ ተፎካካሪ እና ተመራጭ ሆኖ መገኘት ከፍተኛ ጥረት ይጠይቃል፡፡ ይህንን በተመለከተ ለአዳዲስ ተመራቂዎች ማስታወሻ እና ማንቂያ እንዲሆን ይህንን

ቪዲዮ አዘጋጅቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት፡፡
3.9K viewsWasyhun Belay, 12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 16:30:40 የጥናት ውጤት ለማቅረብ የትኞቹ ነጥቦች ላይ ትኩረት ማድረግ አለባችሁ?

ብዙ ተማሪዎች የጥናት ውጤታቸውን ለማቅረብ በጣም እንደሚጨነቁ ይታወቃል! ነገር ግን የተወሰኑ ጉዳዮችን ቅድሚያ በማስተካከል በቀላሉ የሰሩትን ጥናት በማስረዳት የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንዲችሉ የሚያግዝ: ጥሩ ጥናት በደካማ አቀራረብ ሊወድቅ ስለሚችል ጥሩ ጥናት ብታዘጋጁም አቀራረባችሁ ሳቢ እንዲሆን ይህንን

ቪዲዮ አዘጋጅቻለሁ እስከመጨረሻ ተከታተሉት፡፡
5.7K viewsWasyhun Belay, 13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 20:42:02 በሀገራችን በሆነ ምክንያት ዋጋ ከፍ ካለ ወደ ቦታው ለመመለስም ሆነ ለመቀነስ በጣም ከባድ ነው! ለምን?


በተለያዩ ምክንያቶች የቁሳቁስም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ አንዴ ከፍ ካለ በጊዚያዊነት አቅርቦት ቢሻሻልም የጨመረ ዋጋ ወደ ነበረበት ለመመለስ ሲችል አንመለከትም! የዚህ ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው ብዬ የማምንባቸውን አራቱን በዚህ

ቪዲዮ ለመግለጽ ሞክሪያለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት።


የንግድ ሰንሰለቱ ረዥም እና በርካታ ተዋናዮች ያሉበት መሆኑ፤ ደካማ የመረጃ ተደራሽነት ያለው ገበያ መሆኑ፤ አቅርቦት ዘላቂ እድገት ያለማሳየቱ እና ገበያው የሚመራበት ስትራቴጂ ደካማ መሆን የሚጠቀሱ ምክያቶች ናቸው።
7.2K viewsWasyhun Belay, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 13:03:58 ብር ከዶላር አንፃር ስንት መሆን ነበረበት? ለሚለው ጥያቄ መልስ ከብሔራዊ ባንክ በተሻለ ፈጣን ምላሽ እየሰጠ ያለው ጥቁር ገበያው ነው! ጉዳዩ በጥቁር ገበያው እና በብሔራዊ ባንክ ተመን መካከል ያለው #Equilibrium_point ስንት ብር ሲደርስ ይሆን? የሚለው ነው።
6.4K viewsWasyhun Belay, 10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ