Get Mystery Box with random crypto!

ሸማቾች አንድን ምርትም ሆነ አገልግሎት ገዝቶ ለመጠቀም የመፈለጋቸው (Willingness) እና መግ | The Ethiopian Economist View

ሸማቾች አንድን ምርትም ሆነ አገልግሎት ገዝቶ ለመጠቀም የመፈለጋቸው (Willingness) እና መግዛት የመቻላቸው (Ability) ሁኔታ፣ እንዲሁም በገበያ ያለው የምርትም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ ሰዎች ለመግዛት ከሚችሉት እና ከወሰኑት ዋጋ አንጻር ሲታይ ዝቅተኛ ከሆነ ጥሩ (ለሸማች ጤነኛ) ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ከላይ የተጠቀሰውን ልዩነት ከምናሰላበት መንገድ ዋነኛው Consumer Surplus ይባላል፡፡


#ለምሳሌ፡- አንድ አዲስ መኪና በገበያ ያለው ዋጋ 1.3 ሚሊየን (Actual price) ብር ነው ብለን ብናስብ እና ጠቅላላ የሸማች የመግዛት ፍላጎት መጠን 1 መኪና ሆኖ ነገር ግን በኪሱ ያለው ገንዘብ 500 ሺ (Maximum price willing to pay) ብር ብቻ ቢሆን፣ ሸማቹ መክፈል የሚችለው ከፍተኛ ገንዘብ መጠን 500ሺ ስለሆነ አዲሱን መኪና ገዝቶ መሄድ አይችልም፣ ነገር ግን የመኪና መግዛት ፍላጎቱ እንዲሳካ ያገለገለ መኪና በ400ሺ ብር መግዛት ቢችል:-


Consumer surplus (100ሺ) = 500ሺ- 400ሺ ሆነ ማለት ነው:: ሸማቹ የሚፈልገውን አግኝቶም 100ሺ ብር አተረፈ እንደማለት ነው፡፡


ሸማቾች ተመሳሳይ ምርትን ብዙ በተጠቀሙ ቁጥር ለተጨማሪው ምርት ለመክፈል ያላቸው ፍላጎት እየቀነሰ የሚሄደው ለምንድን ነው?


በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ውስጥ ተወዳጅ ከሆኑ ህጎች መካከል አንዱ The law of diminishing marginal utility ነው፡፡ #ለምሳሌ፡- በጣም የራበው ሰው ሳንዱች ማዘዝ ቢፈልግ የሚቀርብለትን ዋጋ ብዙም ድርድር ውስጥ ሳይከት ሊከፍል ይችላል (ምክንያቱም ከፍተኛ እርካታ የሚያገኝበት ስለሆነ) ነገር ግን ሁለተኛ ደግሞ ለማዘዝ እና ለመብላት የመጀመሪያውን ለመብላት እና ለመክፈል በወሰነው ፍጥነት ላይወስን ይችላል፣ ሶስተኛ ሳንዱች ጭራሽም ላያዝ ይችላል ማለት ነው፣ ምክንያቱም ከመራብ ስላገገመ ነው፡፡


ኢኮኖሚስቶች ሸማች እንቅልፉን የሚያጣው እርካታው ለማሳደግ ሲጥር ነው ይላሉ (Consumers are always trying to maximize their utility)፣ ይህ ሲባል ሰዎች ባላቸው ውስን ገቢ ወይም ሃብት የተወሰነ ምርትም ሆነ አገልግሎት በመጠቀም የተሻለ ደስታ ለመፍጠር ይሞክራሉ ለማለት ነው፡፡


በኢኮኖሚክስ ሰዎች ወይም ሸማቾች የደስታቸው ጣሪያ ላይ ለመድረስ እንዲችሉ በገበያ ያለው የምርትም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ መሰረታዊ ተጽኖ ፈጣሪ እና ወሳኝ ነው ይላሉ።