Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.90K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 32

2022-10-19 09:40:03 ፍራንኮ ቫሉታ የባለብዙ አደጋ ኢኮኖሚያዊ ውሳኔ ቢሆንም ላለው አነስተኛ ጥቅም ሲባል የሚተገበረው ለምን ይመስላችኋል?


ብሄራዊ ባንክ በቅርቡ የፍራንኮቫሉታ በጥቁር ገበያው ላይ እየፈጠረ ያለውን አደጋ በመረዳት በፍራንኮቫሉታ ቁሶችን ከውጪ ለማስገባት የባንክ ስቴትመንት መስፈርት የመደረግ አዝማሚያ እንዳለው ገልጿል።


ነገር ግን ፍራንኮቫሉታ የጎላ ጉዳት ቢኖረውም ውሳኔው ለኢኮኖሚው በተለይ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ጥቅም አለው በሚል እሳቤ ቀጥሏል! ታዲያ የሚታይ ጉዳት ያለው የፍራንኮ ቫሉታ ውሳኔ እንዲቀጥል የሚደረግበት መሰረታዊ ምክንያት ምን እንደሆነ ለመረዳት ይህንን ቪዲዮ

ሰርቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት፡፡
5.3K viewsWasyhun Belay, 06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 09:57:14 መኪና ከውጪ እንዳይገባ መከልከሉ ፍታዊ የሚሆነው በመንግስት ተቋማት የሚታዩ በጣም #ውድ_መኪኖችም መግባት ሲያቆሙ ነው!
6.2K viewsWasyhun Belay, 06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 08:05:10 Channel photo updated
05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 12:41:22 ኢትዮጲያ ስንዴ ወደ ውጪ የመላክ ደረጃ ላይ ነች?

የምግብ የዋጋ ንረት ከፍተኛ በሆነበት ወቅት በሀገር ውስጥ ገበያ በቂ ያልሆነ ምርት ወደ ውጪ ሀገር ገበያ የሚላክበት ምከንያት ምንድን ነው? ለአንድ ሀገር የውጪ ንግድ ጉዳይ የተወሳሰበ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲኖረው ሊያስገድድ ይችላል፡፡ ብዙ ሰዎች የኢትዮጲያ ስንዴ ወደ ውጪ ለመላክ መነሳት ምክንያታዊነት ላይ ጥያቄ አላቸው! ይህን በተመለከተ የኢኮኖሚክስ አስተምሮት ሃሳብ፤ የሃገራት ልምድ እና የኢትዮጲያ የውጪ ንግድ ባህሪ ላይ የሚከተለውን

ቪዲዮ አዘጋጅቻለሁ እስከ መጨረሻ ተከታተሉት፡፡
2.3K viewsWasyhun Belay, 09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 20:08:08 የዚህ ዓመት የመንግስት ኢኮኖሚያዊ ትኩረት የታክስ ገቢን ማሳደግ መሆኑን ገልጿል! ስለዚህ የኑሮ ጫናን በጊዚያዊነት ለማቃለል ለመንግስት ሰራተኞች በጊዚያዊነት የገቢ ግብር ቅናሽ ወይም የተወሰነ ወር የግብር እፎይታ ቢሰጥ ያልነው ምክረ ሃሳብ ተስፋ ያለው አይመስልም!
1.6K viewsWasyhun Belay, 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 10:00:50 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዲሱ የገንዘብ፤ የወርቅ እና የውጪ ምንዛሬ ክምችትን ለጠቆመ ወሮታ የሚያሰጠው መመሪያ ለጠቅላላ ኢኮኖሚው ሊኖረው የሚችለው ስጋት ወይስ መፍትሄ?


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ቪዲዮ

እስከመጨረሻው ተከታተሉት።
1.6K viewsWasyhun Belay, 07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 21:45:46 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዲሱ የገንዘብ፤ የወርቅ እና የውጪ ምንዛሬ ክምችትን ለጠቆመ ወሮታ የሚያሰጠው መመሪያ ለጠቅላላ ኢኮኖሚው ሊኖረው የሚችለው ስጋት ወይስ መፍትሄ?


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ቪዲዮ

እስከመጨረሻው ተከታተሉት።
1.5K viewsWasyhun Belay, 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 12:45:36 መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ባይሆንም ውሳኔው ግን መጥፎ አይደለም!

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ

ኢትዮጵያዊያን በግለሰብ ደረጃ ከ100 ሺህ ብር በላይ ለድርጅቶች ደግሞ ከ200 ሺህ ብር በላይ ቤት ውስጥ ማስቀመጥ የተከለከለ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸወል።

ገንዘብ በባንክ መቀመጥ አለበት ፤ የግብይት ስርዓትም በባንክ ማካሄድ ይቻላል።

መመሪያው ከሚፈቅደው የገንዘብ መጠን በላይ አስቀምጦ የተገኘን አካል #የጠቆመ ግለሰብ 15 በመቶ የወረታ ክፍያ ይከፈለዋል።

በውጭ አገራት ገንዘብ ግብይት መፈጸምም ሆነ በህገወጥ መንገድ ይዞ መገኘት አይቻልም።

ወርቅን በህገወጥ መልኩ ቤት ውስጥ ማከማቸት የማይቻል ሲሆን በህገወጥ መልኩ ወርቅን ያከማቸ ግለሰብ ለጠቆመ ግለሰብ ባንኩ በወቅቱ ባለው ግብይት የ15 በመቶ ወረታ ይከፈለዋል።

በህገወጥ የሃዋላ የውጭ አገራት የተሰማሩ አካላትን ለጠቆመም እስከ 25 ሺህ ብር ወረታ ይከፈለዋል።

በህገወጥ ገንዘብ ህትመት የተሰማሩ አካላትን ያጋለጠም ከ20 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወረታ ይከፈለዋል።

ጠቋሚዎች ወረታውና ሽልማቱ የሚበረከትላቸው #ደህንነታቸው እና #ሚስጥራዊነታቸው በተጠበቀ መልኩ ነው።
3.0K viewsWasyhun Belay, edited  09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 19:34:19 መሰረታዊ የኢኮኖሚ ችግር የሆነውን የዋጋ ንረትን በደንብ መረዳት ተገቢ ነው! የዋጋ ንረት ማለት በተደጋጋሚ የቁሳቁስም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ መጨመር ሲከሰት እና እሱን ተከትሎ የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ሲጀምር ነው። በቀላል ቋንቋ ብዙ ገንዘብ ይዞ ጥቂት ብቻ መሸመት መቻል ማለት ነው!


የዋጋ ንረት አሁን ላይ በሀገራችን የደረሰበት ደረጃ ላይ ለመድረስ የተጓዘባቸውን እና ወደፊት የሚጓዝባቸውን ደረጃዎች እንመልከት! የዋጋ ንረት አይነት እና ደረጃዎች......


#Creeping_Inflation፦ የዋጋ ንረት መሆን የሚገባው ተፈጥሯዊ ደረጃ አለ እሱም በዓመት ዋጋ ከ3% ባልበለጠ መልኩ በዝግታ እየጨመረ ሲሄድ የአምራች ክፍሉ ስለሚበረታታ ጤነኛ የዋጋ ንረት (Moderate Inflation) ደረጃ ይባላል።


#ለምሳሌ፦ የዛሬ አመት መስከረም ወር 100 ብር ይሸጥ የነበረ ቁስ ዘንድሮ በመስከረም ወር ቢያንስ አማካይ ዋጋው እስከ 3 ብር ጨምሮ 103 ብር ቢሸጥ እንደማለት ነው።


#Walking_Inflation፦ ጤነኛ የነበረው የዋጋ መጨመር በሂደት ከፍ እያለ በዓመት በአማካኝ ቢያንስ ከ3% እስከ 9% በዝግመት መጨመር ሲጀምር የዋጋ ግሽበት ጥንቃቄ መደሚፈልግበት ደረጃ ደርሷል ይባላል።


#ለምሳሌ፦ የዛሬ አመት መስከረም ወር 100 ብር ይሸጥ የነበረ ቁስ ዘንድሮ በመስከረም ወር ቢያንስ አማካይ ዋጋው በ9 ብር ጨምሮ 109 ብር ቢሸጥ እንደማለት ነው።


#Running_Inflation፦ የዋጋ ንረት ፈጠን ያለ ዝግመት በጀመረበት ወቅት ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ባለማድረግ ሁኔታው እየተባባሰ ከመጣ የዋጋ ጭማሪ ወደ ሩጫ ይዘዋወራል። ማለትም በዓመት ቢያንስ ከ10% እስከ 20% ሲጨምር ማለት ነው። የዋጋ ንረት ከወጣ በኋላ ለመቆጣጠር ከመሞከር ይልቅ መጀመሪያ አካባቢ የሚታዩ የዋጋ መጨመርን በጥንቃቄ መቆጣጠር ካልተቻለ የዋጋ ንረት በፍጥነት ከጨመረ በኋላ ዝቅ ማድረግ አስቸጋሪ እና ፈታኝ ነው።


#ለምሳሌ፦ የዛሬ አመት መስከረም ወር 100 ብር ይሸጥ የነበረ ቁስ ዘንድሮ በመስከረም ወር ቢያንስ አማካይ ዋጋው 20 ብር ጨምሮ 120 ብር ቢሸጥ እንደማለት ነው።


#Hyper_inflation፦ የዋጋ ንረት የመጨረሻ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ እና ኢኮኖሚውን በሚያሽመደምድ ደረጃ ላይ ሲደርስ ማለት ሲሆን በዚህ ወቅት የቁሳቁስም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ አማካይ ወራዊ ጭማሪ ከ50% በላይ ሲደርስ ነው።


#ለምሳሌ፦ የዛሬ አመት መስከረም ወር 100 ብር ይሸጥ የነበረ ቁስ ዘንድሮ በመስከረም ወር ቢያንስ ከ50 ብር በላይ ጨምሮ ከ150 ብር በላይ ቢሸጥ እንደማለት ነው። ሀገራችን በተለይ በውስን ቁሶች ለዚህ አይነቱ የዋጋ ንረት እየተቃረበች ነው።


በዓለም ላይ ከተከሰቱ ከፍተኛ የዋጋ ንረቶች የምንማረው! አብዛኛው ከፍተኛ የዋጋ ንረት Hyperinflation ተፈጥሮባቸው የነበሩ ሀገራት ስንመለከት በጦርነት ወቅት እና ከጦርነት ማግስት ባሉት የመጀመሪያዎቹ 3 ዓመታት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አስተናግደው ነበር! ምክንያቱም ከጦርነት ለማገገም ከፍተኛ የበጀት ጉድለቱ የሚሞላበት መንገድ ዋጋ ንረትን አቀጣጣይ በመሆኑ ነው፡፡


#ለምሳሌ፡- በዓለም ላይ ከተከሰቱ ከፍተኛ የዋጋ ንረቶች መካከል…..


#ሀንጋሪ፦ 1946 (የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማለቂያ ላይ) የዋጋ ንረቱ በወር 41.9 ኳድሪሊየን % የነበረ ሲሆን (41,900,000,000,000,000%) በየ15 ሰዓቱ የዋጋ ንረቱ ራሱን እጥፍ ያደርግ ነበር።


#ዝምባዋብዌ፦ 2008 (የዓለም የፋይናንስ ቀውስ በተፈጠረበት እና የነጮችን መሬት በመቀማት ለጥቁሮች ማደል በተጀመሩበት ወቅት) የዋጋ ንረቱ በወር 79 ቢሊየን ወይም 79,600,000,000%% የነበረ ሲሆን በየ 24 ሰዓቱ የዋጋ ንረቱ ራሱን እጥፍ ያደርግ ነበር።


በዚህ ወቅት ዜጎች ቁሳቁስ ለመግዛት ገንዘብ መሸከም ዋጋ ቢስ ከመሆኑ የተነሳ በአንድ ወረቀት እስከ 100ትሪሊን ኖት ለማተም ተገደው የነበረ ሲሆን በመጨረሻ መገበያያ ገንዘባቸውን ወደ አሜሪካ ዶላር ለውጠው ነበር።


#ይጎዝላቪያ፦ 1994 (ጦርነት እና መከፋፈልን በነበረበት ወቅት) የዋጋ ንረቱ በወር 313 ሚሊየን % የነበረ ሲሆን በየ 1 ቀን ከግማሽ የዋጋ ንረቱ ራሱን እጥፍ ያደርግ ነበር (ዓመታዊ የዋጋ ንረቱ 116 ትርሊዮን ወይም 116,545,906,563,330% ደርሶ ነበር)።


#ጀርመን፦ 1923 (የአንደኛው የዓለም ጦርነት በ1918 ከተጠናቀቀ በኋላ) የዋጋ ንረቱ በወር 29ሺ% የነበረ ሲሆን በየ3 ቀን የዋጋ ንረቱ ራሱን እጥፍ ያደርግ ነበር።


#ግሪክ፦ 1944 (በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት) የዋጋ ንረቱ በወር 14ሺ% የነበረ ሲሆን በየ4 ቀኑ የዋጋ ንረቱ ራሱን እጥፍ ያደርግ ነበር።


በ2022 በዓለማችን ከፍተኛ የዋጋ ንረት ካላባቸው 10 ሃገራት መካከል ኢትዮጲያ አንዷ ነች (ቬንዙዬላ በ1200% ዓመታዊ የዋጋ ንረት ቀዳሚዋ ሀገር ነች)፡፡


#ማሳሰቢያ፦ የዋጋ ንረቱ መነሻ የፍላጎት መናር (Demand-Pull Inflation) ወይም የማምረቻ ወጪ በመጨመሩ (Cost-Push Inflation) ምክንያት ሊሆን ይችላል። አማካይ የዋጋ ንረት የሚሰላው የብዙ ቁሶች የመሸጫ ዋጋ ይሰበሰብ እና ለእያንዳንዱ ቁሳቁስ ከተሰጠው ክብደት አንፃር ተሰልቶ የሚሰራ ስለሚሆን በገበያው ከተቀመጠው ዋጋ የሚጨምርም የሚቀንስም ይኖራል።


#ለምሳሌ፦ የዋጋ ንረት 20% ሆኗል ሲባል ሁሉም ቁሳቁስ የጨመረው 20% ብቻ ነው ማለት ሳይሆን የተወሰኑት ከ20% በታች የተወሰኑት ከ50% በላይ ጨምረው ሊሆን ይችላል።


በሀገራችን ያለው የዋጋ ንረት ተደራራቢ ነባር እና አዳዲስ ምክንያቶችን እየጨመረ የሚሄድ በመሆኑ ለአጭር ጊዜ ከውጪ አጋር ሀገራት የፍጆታ ብድርችን በማፈላለግ መሰረታዊ ቁሶች ሸመታ ማከናወን (መሰረታዊ ቁሶች ላይ የተፈቀደው የፍራንኮ ቫሎታ እድል የግንባታ ቁሶችን ቢያጠቃልል መጥፎ አይደለም!)፤ በድጎማ የሚገቡ ምርቶችን የገበያ ስርጭትን መከታተል፤ የምርት ስራዎች ላይ ርብርብ ማድረግ፤ ከውጪ በሚገቡ ምርቶች ላይ ቁጥጥር እና ክልከላ ማካሄድ፤ አዳዲስ ብር ማተምን ማቆም ወይም መቀነስ………..


የመንግስት የገቢ አማራጮችን ማስፋት (መሬቶች፤ ቤቶች፤ ማዕድኖች፤ ወዘተ ለሽያጭ ማቅረብ ሊሆን ይችላል!) ግብር ከፋዩ ቀድሞ የሚከፍል ከሆነ አበረታች የግብር ቅናሽ በማቅረብ አሁን ላይ የመንግስት ገቢን ማሳደግ፤ #ለምሳሌ፦ በዓመት 100 ሚሊየን ብር ግብር የሚከፍል ተቋም ቀድሞ 85 ሚሊየን ብር ቢከፍል እና የ15 ሚሊየን ብር ቅናሽ እንደሚያገኝ ድርድር ቢፈጠር ያልተለመደ ወይም የማይሰራ አካሄድ አይደለም!፤ የመንግስትን ወጪ ምክንያታዊ ማድረግ እንዲሁም ከሁሉም በላይ #የጸጥታ ሁኔታውን ማረጋጋት ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አስባለሁ፡፡
1.7K viewsWasyhun Belay, 16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 20:49:45 የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት አስፈሪው Hyperinflation ደረጃ ላይ ደርሷል?


የኑሮ ውድነቱን ጣራ ያደረሰው የዋጋ ንረት ምክንያት እና ያለበት ደረጃ ከዓለም ሀገራት አንፃር ምን ይመስላል? በዚህ ዙሪያ ይህንን

ትንታኔ ተመልከቱ።
1.6K viewsWasyhun Belay, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ