Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.90K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 29

2022-11-08 20:24:05 Channel photo updated
17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 08:30:31 በኢኮኖሚክስ #ፍፁም ትክክል የሚባል ሃሳብ የለም!

#ቀላል_ምሳሌ፦ የዋጋ ንረት የመፍትሄ ሃሳቦች የተለያዩ ናቸው! ለአንዱ ሀገር የሰራ የመፍትሄ ሃሳብ ለሌላ ሀገር የዋጋ ንረት አባባሽ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ተመሳሳይ የዋጋ ንረት የመነሻ ምክንያት (ከፍላጎት መጨመር/Demand Pull አልያም የማምረት ወጪ መጨመር/Cost Push) ቢፈጠር እና የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እውቀት ያላቸው ሰዎች የሚከተለውን ምክር ቢለግሱ.......

#የምጣኔ_ሃብት_ባለሙያ1፦ "በገበያ የገንዘብ ስርጭት እንዲጨምር ማድረግ #ከፍላጎት በሚነሳ ምክንያት አንፃር የዋጋ ንረትን ያባባብሳል! ስለዚህ የገንዘብ አቅርቦትን በመቀነስ የዋጋ ንረቱን መቀነስ ይቻላል" የሚል ምክረ ሃሳብ ቢያቀርብ።

#የምጣኔ_ሃብት_ባለሙያ2፦ በተቃራኒው "ለአምራች ሃይሉ የገንዘብ አቅርቦትን በማሳደግ #የማምረት አቅም/የግብዓት አቅርቦት እንዲሻሻል በማድረግ አቅርቦትን በመጨመር የዋጋ ንረት እንዲቀንስ ማድረግ ይቻላል" የሚል ምክረ ሃሳብ ቢያቀርብ።

የሁለቱም ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ በመርህ ደረጃ ስህተት የለበትም! ማንኛቸውም ባለሙያ የሰጠሁት የመፍትሔ ሃሳብ ፍፁም ትክክለኛውን ነው በሚል መኩራራትም አይችልም! የመፍትሔ ሃሳቦች ሲተገበሩ የመንሻፈፍ አጋጣሚዎቻቸው ብዙ ናቸው። ለዚህ ነው ታዋቂ የኢኮኖሚክስ Assumption መላምቶች (Other Things Remaining Constant) በሚል የሚጀምሩት።

#ለምሳሌ፦ በ1930 በአሜሪካ የተከሰተው ኢኮኖሚያዊ ቀውስ (Great Depression) በዋናነት መነሻው ምክንያት የአምራች ክፍሉ ያመረተውን ከፍተኛ መጠን ምርት መግዛት የሚገባው የሸማች ክፍሉ በበቂ ሁኔታ መሸመት ባለመቻሉ አምራቾች የተመረቱ ምርቶች ገበያ ካጡ ተጨማሪ ምርት ከማምረት በመቆጠብ ሰራተኛ በማሰናበታቸው በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛው የስራ አጥነት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል።

#ለምሳሌ፦ በአሜሪካ በ1929 ስራ አጥነቱ 3.2% ነበር፤ በዓመቱ  6 ሚሊየን አሜሪካዊያን ስራ በማጣታቸው በ1930 የስራ አጥነቱ ቁጥር 19.4% ደረሰ በ1933 ስራ አጥነቱ 25% አልፎ ነበር፡፡

ይህ ችግር እንዲቀረፍ ብዙ ኢኮኖሚስቶች ተሞክረው በመጨረሻ እንግሊዛዊው ኢኮኖሚስት ጆን ሜሬድ ኬነስ "የገንዘብ አቅርቦትን ባለመቀነስ የሸማች ክፍሉን አቅም በማሳደግ ችግሩን መቅረፍ ይቻላል" የሚለው ሃሳብ በLogic አደገኛ በመሆኑ ከብዙ ክርክር በኋላ "እስቲ ይሞከር!" በሚል ነበር የተተገበረው! ነገር ግን ችግሩ ለመቀረፍ 10ዓመት ቢፈጅም ምክረ ሃሳቡ መፍትሄ መሆን በመቻሉ መማሪያ ሆኖ Keynesian Theory በሚል ተመዝግቧል።

በወቅቱ ከኬይነስ በፊት ከቀረቡ የመፍትሄ ሃሳቦች መካከል "የሰራተኛውን ክፍያን በመቀነስ እና የአምራች ክፍሉ የሚከፍለውን የወለድ መጠን በመቀነስ ወጪን በመቆጠብ ስራ አጥነቱ እናዲቃለል ማድረግ ይቻላል" የሚለው ሲሆን ኬይነስ በበኩሉ "የሰራተኛውን ክፍያ ከመቀነሰ ይልቅ የሰራተኛው ክፍል የመሸመት አቅም እንዲጨምር በማድረግ ሸማች እንዲሆን ማድረግ ይቻላል"፤ ይህንን ተከትሎ የአምራች ክፍሉ የማምረት መጠን እየጨመረ ይሄዳል የሚል ነበር፡፡ በተግባርም አስተሳሰቡ ውጤት አምጥቷል፡፡

በሀገራችን ኢኮኖሚክስን የተማሩ ሰዎች በአብዛኛው ለጊዚያዊ ችግሮች የመፍትሄ ሃሳብ እና የኢኮኖሚያዊ ችግሮች መነሻ ምክንያትን ሲያስቀምጡ ሃሳቦቹ የተለያዩ ናቸው። ይህ ማለት ባለሙያዎቹ ሙሉ ለሙሉ ስህተቶች ናቸው እና ትክክለኛው መፍትሄ እና ምክንያት የቱ እንደሆነ አልታወቀም አያስብልም።

አስር የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ለምን የከፋ ድህነት ውስጥ ለመኖር ተገደደች? ተብለው ቢጠየቁ። ስምንት አልያም አስር የተለያዩ ምክንያቶችን ሊያቀርቡ ይችላሉ። ስለዚህ ኢትዮጵያ ከድህነት እንድትወጣ ምን ይደረግ? ቢባሉም ስምንት አልያም አስር የተለያዩ ከችግር መውጫ መንገዶችን በምክንያትነት ሊያቀርቡ ይችላሉ።

ለዚህ አይነቱ ችግር የባለሙያዎች ስብስብ በመፍጠር የሃሳቦችን እድል እና ስጋት በመወያየት ወደ ዋና መሰረታዊ (Significant) ነጥብ እንዲደርሱ ማድረግ ይቻላል! ደግሞም መንግስታት ይህንን ዘዴ ይጠቀማሉ።

#ለምሳሌ፦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ቤት ውስጥ ያሉ ኢኮኖሚስቶች የጥሬ ገንዘብ ገደብ ይቀመጥ! የሚለው ውሳኔ ላይ በተናጥል የተለያየ ምልከታ እንደሚኖራቸው እገምታለሁ። ነገር ግን እንደማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳዳሪነታቸው በጋራ ከየልዩነታቸው ወደ ተመሳሳይ ውሳኔ እንደደረሱ መገመት ይቻላል። በተመሳሳይ የገንዘብ ሚኒስትር፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ አማካሪ ቡድኑ፤ ወዘተ ውስጥ በምክንያት እና መፍትሄ ላይ የሚኖረው ሁኔታ በተናጥል እና በቡድን ሃሳቦቻቸው የተለያዩ ነው የሚሆኑት።

በሀገራችን ብዙ ሰዎች ኢኮኖሚክስን በብዙ ጥልቀት በትምህርት እና በስራ ልምድ እንደሚያውቁት ግልፅ ነው! ስለዚህ የሚሰማቸውን ስሜት ለማጋራት ግዴታ ጥቂት ሰዎች ብቻ በየቀኑ የሚያቀርቡትን ሚዲያዎች መፈለግ አይጠበቅባቸውም፤ ሃሳቦቻቸው ለፖሊሲ አውጪዎች እንዲደርስ መፈለግ የለባቸውም፤ ሃሳቦች ትክክል እና ስህተት መሆናቸውን የሚመዝን አካል ስለመኖሩ ማሰብ የለባቸውም፤ ወዘተ። ስለዚህ የተማሩትን እና የሚያውቁትን ብቻ ያንጸባርቃሉ፡፡

#ለምሳሌ፦ በሀገራችንን የምጣኔ ሃብት ዙሪያ አስተያየት ለመስጠት በተለያዩ ሚዲያዎች የሚቀርቡት እንዲሁም ሚዲያዎች የሚያቀርቧቸው ሰዎች ጥቂት እና ተመሳሳይ ናቸው (ከጥቂት ጊዚያት ወዲህ እኔንም ይጨምራል!) ይህ ሁኔታ የሃሳብ ተዋፅኦን ይቀንሳል!

ኢኮኖሚክስን የተማረ ሰው ልኩን ብቻ ሳይሆን ልክ ነው ብሎ የሚያምንበትን እና የሚያውቀውን ሃሳብ ነው ማጋራት ያለበት! (ለብዙ ጉዳዬች ፍፁም ልክ የሚል ሳይሆን የመሳካት እድላቸው ከፍ ያለ ሃሳቦች ናቸው የኢኮኖሚክስ አስተምሮትን የሞሉት)።


#ለምሳሌ፦ ከውጪ ለሚገቡ ውስን ምርቶች የLC ክልከላ መደረግ ልክ የሚሆነውም ልክ የማይሆነውም በሚቀርቡት አመክንዮ ብዛት እና ጥንካሬ እንጂ በደፈናው መከልከሉ ፍፁም ትክክል ወይም አለመከልከል ለቀጣይ ኢኮኖሚው ፍፁም ወሳኝ ነው የሚባል አይሆንም። ምክንያቱም ኢኮኖሚክስ ያላለቀ እና ከተለዋዋጭ ነባሪያዊ ሁኔታዎች ጋር ጥገኛ ነው።

ስለዚህ ሀገር ኢኮኖሚክስን ያስተማረቻቸውን እንዲሁም በራሳቸው ያዳበሩትን እውቀት ባገኙት አጋጣሚ (በማህበራዊ ሚዲያ፤ በህትመት ሚዲያ፤ በራዲዮ፤ በቲቪ፤ ወዘተ) ማጋራት ተገቢ ነው። ኢኮኖሚያዊ መረጃ እና ሃሳብ ለመንግስት፤ ለሚዲያዎች፤ ለተማሪዎች፤ ለመደበኛው ሰው፤ ወዘተ በጣም አስፈላጊ ነው።


YouTube፦ https://youtube.com/channel/UCzc8ISpZJ6RskJmd_DEx7WQ
1.7K viewsWasyhun Belay, 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 19:07:47 ዳታ በቀላሉ በStata እንዴት ይተነተናል ?/ How to interpret descriptive data results in Stata?

ከዚህ በፊት ዳታ ወደ SPSS እንዴት ማስገባት እንደሚቻል፤ እንዴት መተንተን እንደሚቻል እና እንዴት ቻርት ማውጣት እንደሚቻል አቅርቤላችሁ የነበረ ቢሆንም ዛሬ በቀላሉ በStata እንዴት Descriptive ውጤት እና ግራፍ ማውጣት እንደሚቻል ይህንን

አጭር ቪዲዮ ሰርቻለሁ፡፡

የዚህ ቪዲዮ ዓላማ ሰዎች እንደመነሻ እንዲወስዱት እና ተጨማሪ ሌሎች መጽሃፍትን እና ቪዲዮችን በመመልከት ጥናታቸውን በቀላሉ በአቅማቸው ልክ መስራት እንደሚችሉ ለማስረዳት ያህል ነው፡፡ ከዚህ በፊት በSPSS እንዴት ዳታ ማስገባት እና መተንተን እንደሚቻል የሰራሁትን ቪዲዮ ለምትፈልጉ ከታች ያለው ሊንክ ተጠቀሙ፡፡









2.7K viewsWasyhun Belay, 16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 16:44:26 ዛሬ ሽንኩርት ለመግዛት ትልቅ አትክልት ቤት ቆሜ ስመለከት 2 አይነት ሽንኩርት ተቀምጧል ዋጋቸው በኪሎ 25ብር እና 40ብር ነው።

የሁለቱን ሽንኩርት ልዩነት ንገረኝ አልኩት! "ብዙም ልዩነት የላቸውም" አለኝ። ነገር ግን የተወሰኑ ሰዎች ከተለጠፈው ዋጋ አንፃር ከ40 ብሩ አድርግልኝ እያሉ ሲወስዱ አየሁ።

ለምን የ15 ብር ልዩነት ያለውን ተመሳሳይ ምርት በ25ብር መውሰድ ትታችሁ በ40ብር ትገዛላችሁ ስላቸው! "መጠኑ ትንሽ ተለቅ ስለሚል እና ዋጋው ጥራቱን ያሳያል ብለን ነው!" የሚል አይነት መልስ ሰጡኝ።

ሻጩን ለምን የሁለቱ ሽንኩርቶች ዋጋ ተለያየ? ስለው "ባለ 40ብሩ ሽንኩርት ከሩቅ ቦታ ስለሚመጣ ነው! የተወደደው" አለኝ።

ዋጋ የሚወሰነው በምርት ወቅት የነበረው የግብዓት ወጪ መጠን እና ወደ ገበያ የሚመጣበት የትራንስፖርት ወጪ እንዲሁም የሚሸጥበት ቦታ ሁኔታ (ውድ የኪራይ ቦታ ከሆነ ዋጋ ላይ ሊደመር ይችላል!) ተደማምረው ነው።

በተወሰነ መልኩ ሁለቱ ሽንኩርቶች ለመመረት ያለባቸው የግብዓት ወጪ ተቀራራቢ ነው የሚሆነው! ስለዚህ የምርቱ የትራንስፖርት ወጪ ነው ዋጋው ላይ ልዩነት የፈጠረው።

በሀገራችን ውድ ነገር ጥሩ ነው የሚል ልምድ አለ! ነገር ግን ተመሳሳይ ነገር ለመግዛት የዋጋ ልዩነት ሲገጥማችሁ የተፈጠረው የዋጋ ልዩነት ምክንያታዊ መሆኑን ማረጋገጥ ግድ ነው።

ተመሳሳይ ምርት ከሩቅ ስለመጣ ውድ ሆነ ማለት በሸማች አስተሳሰብ በዋጋ ውድ የሆነው የተሻለ ቢሆን ነው በሚል ነባር የሸመታ ልምድ መሸመት እንደመሸወድ ነው የሚቆጠረው።

እኔ ለሸመታው ምክንያታዊ ለመሆን ሻጩንም ሲሸምቱ የነበሩ ሰዎችን ጠየኩ በቂ መረጃ የሌለው ሸማች ሊያደርግ እንደሚችለው ሸማች አወዳደርኩ እና ባለ 25ብሩ ሽንኩርት ገዛሁ።

#ለምሳሌ፦ በተለያዩ ሽንኩርቶች መካከል የአይነት መሰረታዊ ልዩነት ሊኖር ይችላል! የሚጣፍጥ፤ ቶሎ የሚበስል፤ ሳይበላሽ የሚቆይ፤ ወዘተ ነገር ግን እኔ በተገኘሁበት የነበረው ምርት ይህ ልዩነት እንዳለው ሻጭም ሸማቾችም አላወቁም ግን ውዱን መግዛት መርጠዋል።

ዋጋ ብቻውን የጥራት ማሳያ አይደለም! ለምትከፍሉት የዋጋ ልዩነት ተጨማሪ ምክንያት መፈለግ መለመድ አለበት።
2.5K viewsWasyhun Belay, edited  13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 19:43:50 የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ላለፉት ሁለት ዓመታት ለሶስተኛ ዙር ጦርነት ውስጥ ነው፡፡ የጦርነቱ ባህሪ በአንድ ሀገር ውስጥ ከመከናወኑ በተጨማሪ ሰፊ ቦታን የሸፈነ ነው፡፡ ሰፊ ቦታን የሸፈነ ማለት ብዙ ሞት፤ ብዙ መፈናቀል፤ ብዙ መሰረተ ልማት መውደም፤ ብዙ ወጪ፤ ብዙ እዳ፤ ብዙ ጫና ያለበት ነው ማለት ነው፡፡

በየትም ሀገር ጦርነት ለኢኮኖሚ ጫናው ከባድ ነው፡፡ በተለይ ለእንደኛ ዓይነቱ ድሃ ሃገር ጫናው ከሃገር ውስጥ ወደ ውጪም የሚዘልቅ ነው፡፡ ለዚህ ማሳያ ከአግዋ ከመሰረዝ እስከ የውጪ እርዳታ እና ብድር መቀነስ እና ዲፕሎማሲያዊ ጫናን ጨምሯል፡፡

ጦርነት በቀጥታ ከሚታዩ የወጪ መጠን ብዛት እና የመሰረተ ልማት ውድመት በተጨማሪ የዜጎች በኢኮኖሚው ላይ ያላቸው መተማመን/Public Confidence ይሸረሽራል፡፡ ምክንያቱም ጦርነት በረዘመ ቁጥር ብርም ዶላርም መብላቱ ስለማይቀር በማዕከላዊ ባንክ የሚኖርን የውጪ ምንዛሬ መንካቱ ስለማይቀር የጥቁር ገበያው ከፍተኛ ሸማቾች እንዲኖሩት ያደርጋል፡፡ የዜጎች መተማመን መቀነስ ኢኮኖሚውን ከቤተሰብ እስከ ጠቅላላ ኢኮኖሚ ድረስ ተጽኖ እንዲፈጠርበት ያደርጋል፡፡


#ለምሳሌ፡- የኢኮኖሚክ ትሬዲንግ መረጃ ብንመለከት ላለፉት አራት ወራት የዋጋ ንረቱ በሰኔ ወር 38.1%፤ በሃምሌ ወር 35.5%፤ በነሃሴ ወር 32.5%፤ በመስከረም/ጥቅምት ወር ወደ 30.7% ከመቶ ዝቅ ብሏል (ከአፍሪካ ሃገራት ኢትዮጲያ ዝምባብዌ፤ ሱዳን እና ጋናን በመከተል አራተኛዋ ባለከፍተኛ የዋጋ ንረት ሀገር ነች)! ለማነጻጸር ያህል የዓለም የገንዘብ ድርጅት ትንበያ የሚያሳየው ኢትዮጲያ ውስጥ ጠቅላላ የዓመቱ የዋጋ ንረት በቀጣይ ዓመት ወደ 28.6% ዝቅ ሊል ይችላል የሚል ትንበያ ሰጥቷል (የሰላም ስምምነቱን ሳያውቅ በፊት የሰጠው ትንበያ ነው ደምሩ ቀንሱበት!)፡፡

ስለዚህ በአንጻራዊነት በሂደት እየወረደ ያለ የዋጋ ንረት ባለበት የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ውስጥ የጥቁር ገበያ የውጪ ምንዛሬ ፍላጎት እና የቋሚ ቁሶች (መሬት እና ቤት) ግዢ ፍላጎት የሚንረው ዜጎች የገንዘብን የመግዛት አቅም በቀጣይ ይቀዛቀዛል የሚለው ግምታቸው ጠንካራ በመሆኑ ብራቸውን ወደ ንብረት ለማዞር ከመፈለግ ስጋት ጋር የተገናኘ ነው (ስጋትን ከሚፈጥረው መሰረታዊ ምክንያት አንዱ ጦርነት ነው)፡፡

የውጪ ምንዛሬ አጠቃቀም መመሪያ እና የውጪ ምንዛሬ ጥያቄ ላልተወሰነ ጊዜ በተወሰኑ ቁሶች ላይ ክልከላ መደረግ (የዓለም የገንዘብ ድርጅት በዚህ ወቅት የኢትዮጲያ የውጪ ምንዛሬ ክምችት ለ21 ቀን የሚያሸምት ነው የሚለው ሪፖርት) የሚያሳዩት የውጪ ምንዛሬ ወጪ ሰፊ እንደነበር እና የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት መሳሳት ምክንያት መካከል ቀጥታ ጦርነት እና ጦርነቱን ምክንያት በማድረግ ያሉ ዓለም አቀፍ ጫናዎች የታከሉበት መሆኑ አይቀርም፡፡

በሀገራችን ያለው ጦርነት ባህሪ ለየት ያለ ኢኮኖሚዊ ተጽኖ ያለበት ነው! አንዴት? ለጦርነት የሚሆነው ወጪም ሆነ በጦርነት የወደሙትን መሰረተ ልማቶች የመገንባት ወጪም ከአንድ የኢኮኖሚ ቋት ላይ መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ኢኮኖሚው ሲዋጋም ያወደመውን መልሶ ሲገነባም ባለ ብዙ ወጪ መሆኑ አይቀርም፡፡

ጦርነቱ የምርት ሁኔታን መጉዳቱ፤ አምራች ክፍሉን ለሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት መዳረጉ፤ የቱሪዝም ሴክተሩን ማዳከሙ፤ የማህበራዊ እና የገንዘብ እንቅስቃሴን መቀነሱ (በመብራት፤ በቴሌኮም፤ በመንገድ፤ ወዘተ ሊጠቀስ ይችላል)፤ መሰረተ ልማቶችን ማውደሙ፤ የመንግስት እና የማህበረሰብ ወጪን ምርታም ላልሆነ ሴክተር/ጦርነት ማስወጣቱ፤ ወዘተ የታወቀ ነው፡፡

ስለዚህ በዚህ ወቅት በመርህ ደረጃ ሰላም ለማውረድ የተደረገው ስምምነት በራሱ ሊኖረው የሚችለው እድል ምንድን ነው? እንዲሁም የሰላም ስምምነቱን በአግባቡ ወደ መሬት በማውረድ ሲተገበር በኢኮኖሚው ላይ ሊኖረው የሚችለው እድል ምንድን ነው?

በመጀመሪያ ጦርነት አውዳሚ ከሆነ ሰላም መጥፎ ሊሆን አይችልም! ስለዚህ ሰላም ለማውረድ የተጀመረ የመጀመሪያ ስምምነት በጣም ጥሩ ነው! እኔ የሰላም ስምምነት መደረጉ ብቻ በመጀመሪያው ደረጃ ለኢኮኖሚው የሚከተሉት ዋና ዋና ጠቀሜታዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ ይሰማኛል፡፡

1. በተወሰነ መልኩ በቀጥታ ለጦርነት የሚደረጉ ወጪዎች እንዲቀንሱ ሊያግዝ ይችላል፡፡ እንዲሁም በቀጣይ የሚጠበቀው የሰብዓዊ እና የመልሶ ግንባታ ወጪዎች ማደጋቸው ባይቀርም የረጅም ጊዜ ውጤቶችን መሰረት በማድረግ የማህበረሰብ ተሳትፎ እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ትብብርን መሰረት በማድረግ ወደ ተረጋጋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ክልሎችን (በዋናነት ትግራይ፤ አፋር እና አማራ) ወደ ተሻለ ሁኔታ ለመመለስ እድል ሊሰጥ ይችላል፡፡

2. የማህበረሰብ መተማመን/Public Confidence እንዲሻሻል ሊያደርግ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ጦርነት የመጪው ጊዚያት ላይ ያለን መተማመን ካጠፋ፡ የሰላም አዝማሚያ ደግሞ ሰዎች በመጪው ጊዜ ላይ የሚኖራቸው መተማመን እንዲጠናከር ያደርጋል (የስልክ፤ የመብራት እና የባንክ አገልግሎት መጀመር ብቻውን ለዜጎች ብዙ ማለት ነው!) የማምረት እና የመሸመት (ማከማቸትን ጨምሮ) ውሳኔ ከመጪው ጊዜ ሀኔታ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው! ስለዚህ ሰላም ይወርዳል የሚለው ስሜት ዜጎች የተረጋጉ ጊዜዎች እና ገበያዎች ሊኖሩ ይችላሉ በሚል ትንበያ በተወሰነ መልኩ የተረጋጋ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ሊያደርግ ይችላል፡፡

3. የውጪ ሀገራት እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ጫና በተወሰነ መልኩ ሊላላ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ጦርነቱን ተከትሎ የውጪ ሃገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኢኮኖሚያዊ ጫና ቀላል አልነበረም! ስለዚህ የሰላም አዝማሚያን ተከትሎ የኢኮኖሚ ጫና መቀነስ (ብድር እና እርዳታን ጨምሮ) እንዲሁም የሰብዓዊ ድጋፍ መጨመር ሊኖር ስለሚችል የተሻለ የውጪ ንግድ እና የውጪ ምንዛሬ ምንጮችን ለመፍጠር ያግዛል ብዬ አስባለሁ፡፡

በቀጣይ ሁኔታዎችን በአንጻራዊነት ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ማምጣት ከተቻለ የግብርና፤ የኢንዱስትሪ፤ የቱሪዝም ሴክተሮች መነቃቃት፤ የሰዎች እንቅስቃሴ ከገደብ መውጣት፤ የገቢ መጠን መሻሻል፤ የስራ እድል መነቃቃት፤ የልማት ትኩረት መሻሻል፤ ወዘተ ሊኖር መቻሉ አይቀርም! ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚኖረው አብዛኛውን ያስማማ እና ዘላቂነት ያለው ሰላም የማስፈን ፍላጎት እና ተግባር ሲኖር ነው፡፡




3.2K viewsWasyhun Belay, 16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 17:48:29 ጦርነትን ለማቆም የተደረገው የመጀመሪያ ደረጃ የሰላም ስምምነት በመፈረሙ ብቻ ለኢኮኖሚው ሊኖረው የሚችለው ፈጣን ጠቀሜታዎች.......


ይህንን በተመለከተ ዝርዝር ትንታኔውን ከሚመለከተው ቪዲዮ እስከመጨረሻው ተከታተሉት!

3.3K viewsWasyhun Belay, 14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 21:00:00
ናይጄሪያ የባለ 200,500 እና 1,000 የገንዘብ ኖቷን/ናይራ ልትለውጥ ነው። ምክንያቱ 85% የሚሆነው ብሯ (ከጠቅላላው ካላት 3.23 ትሪሊዮን ናይራ መካከል 2.73 ትሪሊዮን  ናይራ)ከባንክ ስርዓት ውጪ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ በመታወቁ ነው!


ናይጄሪያ ላለፉት 20 ዓመታት ተመሳሳይ የገንዘብ ኖት ነው የምትጠቀመው። ትልልቅ መጠን ያላቸው የብር ኖቶች በሰዎች እጅ በጣም ተፈላጊ እና ለስወራ ስለሚቀሉ ተመራጭ ናቸው! ለዚህም ሲባል ሀገራት ባለ ትልቅ ኖት ብር ለማሳተም ፍላጎት አያሳዩም!


በኢትዮጵያ ብር ሲለወጥ አንዱ ምክንያት ከ113ቢሊየን ብር በላይ ከባንክ ስርዓት ውጪ በመኖሩ ነበር! አሁን ላይ ብር ከተለወጠ ረጅም ጊዜ ባይሆንም ጥሬ ገንዘብ የሚወደው ገበያ ምን ያህሉን ብር ከባንክ ያስወጣው ይመስላችኋል?


ሀገራት ተመሳሳይ የገንዘብ ኖቶችን ሳይለውጡ ከ10 ዓመት በላይ እንዳይቆዩ ይመከራል።
1.7K viewsWasyhun Belay, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 19:37:58 SPSS ላይ ዳታ እንዴት ማስገባት ይቻላል?

ጥናት ለማካሄድ የተሰበሰበ መረጃ ወደ ሶፍትዌር መግባት እንዳለበት ይታወቃል፡፡

ስለዚህ....

1. ወደ SPSS እንዴት ዳታ ማስገባት እንደሚቻል፤

2. ከExcel እና ከStata እንዴት ዳታና ወደ SPSS ማምጣት እንደሚቻል፤

3. ከSPSS ወደ Excel እና Stata ዳታን ማዛወር/ Export እንደሚቻል፤

ጠቃሚ ቪዲዮ ጭኛለሁ! እስከመጨረሻው በመመልከት ጥናቶን በቀላል የመስሪያ ግንዛቤ ያግኙ!


2.1K viewsWasyhun Belay, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 14:24:58
ጠለቅ ያለ የኢኮኖሚ ሃሳቦች ትንታኔዎች፤ የኢኮኖሚ መጽሃፎች ዳሰሳ እና የዓለም ድንቅ ኢኮኖሚስቶችን አስተምሮት ለመከታተል የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! ለሌሎች እንዲደርስ ያጋሩ!

Subscribe

https://youtube.com/channel/UCzc8ISpZJ6RskJmd_DEx7WQ
2.7K viewsWasyhun Belay, 11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 20:19:31 ሰላም = ተስፋ = ኢኮኖሚ
1.9K viewsWasyhun Belay, 17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ