Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.90K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2022-11-02 19:32:46 #Digital_Economy_በኢትዮጵያ!
**
የዓለም የኢኮኖሚ ስርዓት ወደ ቴክኖሎጂ አሰራር በመሸጋገር ላይ ነው! ዲጂታል ኢኮኖሚ ማለት የምርት ስርዓትን፤ የግብይት ስርዓትን፤ የግንኙነት አይነቶች ማለትም የሰዎችን እና የድርጅቶች ግንኙነት በኢንፎርሜሽን እና በቴሌኮሚኒኬሽን አማራጮች (ICT) መጠቀም ሲጀምሩ ማለት ነው፡፡

#ለምሳሌ፡- ማሽኖችን በኢንተርኔት ታግዞ በመቆጣጠር ማምረት፤ የምርት ውጤትን በኢንተርኔት ማስተዋወቅ፤ አሰራሮችን በቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቅሞ በቀላሉ መስራት (ቀላል ምሳሌ በቀላሉ በኮምፒውተር መጻፍ፤ ፕሪንተር መጠቀም፤ በስልክ ግንኙነት ማድረግ፤ በኢንተርኔት መልዕክት መለዋወጥ፤ ገንዘብን በኢንተርኔት/በሞባይል ማንቀሳቀስ መቻል፤ ክፍያ በኢንተርኔት መፈጸም፤ ወዘተ)፡፡

ፈጣን የግብይት ስርዓት ባለበት በአሁኑ ወቅት የዲጂታሉ ስርዓት/የኢንተርኔት እገዛ በጣም መሰረታዊ ነው፡፡

#ለምሳሌ፡- የታክሲ አገልግሎት የተለመደው አሰራር፡ ታክሲ የሚፈልገው ሰው መንገድ ላይ ወጥቶ ታክሲውን ፈልጎ ማግኘት፤ ማዋራት፤ ዋጋ መደራደር፤ ወዘተ አለበት፡፡ ታክሲ ሹፌሩ ተሳፋሪ ለማግኘት መንገድ ላይ ወጥቶ ተሳፋሪ እየዞረ መፈለግ አለበት፡፡ ተሳፋሪን እና ሾፌሩን በኢንተርኔት የሚያገናኝ አሰራር ሲፈጠር ብዙ ነገሮች መቅለል ጀመሩ (በዓለም ላይ Uber እንዲሁም በኢትዮጲያ RIDE በምሳሌ መመልከት ይቻላል)፡፡

#ለምሳሌ፡- የባንኮች አገልግሎት የተለመደው አሰራር፡ ባንኮች ደንበኞቻቸውን በመስኮት ላይ ጠብቀው አገልግሎት ይሰጣሉ፤ ባንክ ተገልጋዩም ገንዘብ ለማውጣት፤ ሂሳቡን ለማየት፤ ገንዘብ ለማስተላለፍ፤ የውጪ ምንዛሬ ለመመንዘር፤ ቼክ ለማውጣት፤ ማንኛውም የባንኩን መረጃ ለመጠየቅ፤ ወዘተ በባንኩ መስኮት መገኘት አለባቸው (በባንኮቹ በስራ ቀን ላይ ብቻ!) ነገር ግን በኢንተርኔት ደንበኛው የባንክ ደጃፍን ሳይረግጥ ሁሉንም ሊያከናውነው ይችላል፡፡

ዛሬ ላይ ATM ማሽኖች (ገንዘብ ማውጣት፤ የውጪ ምንዛሬ መመንዘር፤ ቼክ መመንዘር፤ ገንዘብ ማስተላለፍ፤ የሂሳብ መረጃ ማወቅ አገልግሎት ቅርንጫፍ ሳይሄድ ይሰጣሉ)፡፡ ደንበኞች በማባይል/በኮምፕዩተር ኢንተርኔት በመጠቀም (ገንዘብ ማውጣት (የክፍያ ኤጀንቶችን ጋር በመቅረብ)፤ ገንዘብ ማስተላለፍ፤ ክፍያ መፈጸም፤ የሂሳብ መረጃ ማወቅ አገልግሎት ቅርንጫፍ ሳይሄድ ይሰጣሉ)፡፡ ይሄ በሙሉ የዲጂታል ዓለሙ ውጤት ነው፡፡

ምግብ አምራቾች ዛሬ ላይ ከማብሰያ በተጨማሪ የደንበኞች መመገቢያ ቦታ ማዘጋጀት ላያስፈልጋቸው ይችላል! ምክንያቱም የተዘጋጀውን ምግብ በኢንተርኔት ለደንበኞቻቸው አይነቱን እና ዋጋውን በማስተዋወቅ ትዛዝ ተቀብሎ ቤት ለቤት በማድረስ (Food Delivery) በኢንተርኔት ክፍያ እየተቀበሉ ሰፊ ንግድ ሊያከናውኑ ይችላሉ፡፡

አምራች ድርጅቶች ከተለመደው የሰዎችን ጉልበት ተጠቅመው ከሚያመርቱበት ዘዴ በተሻለ በኢንተርኔት ቁጥጥር ስር በሚውሉ ማሽኖች/ሮቦቶች በማምረት ከፍተኛ ምርት እና የምርት ቁጥጥር የሚያደርጉበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡

ሃኪሞች በህክምና ተቋም ሳይገኙ የቀዶ ጥገና ስራ ላይ ተሳታፊ ሊሆነ ይችላሉ (Tele-Medicine)፤ ተማሪዎችም ሆኑ አስተማሪዎች በክፍል ውስጥ ሳይገናኙ በኢንተርኔት ትምህርት ሊማማሩ ይችላሉ፡፡

የዜና ጣቢያዎች የተገነባ ማሰራጫ ጣቢያ ሳይኖራቸው በኢንተርኔት (ማለትም YouTube; Facebook, Twitter) በመጠቀም መደበኛ ስራዎቻቸውን ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ የግብርና ባለሙያዎች ማሳ ላይ ሳይገኙ Drone በመጠቀም የእጽዋት እንክብካቤ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

የዲጂታሉ ኢኮኖሚ ስርዓት ስጋቶችም አሉበት! ከነዚህ መካከል የመረጃ መጠለፍ እና መዘረፍ ችግር ሊገጥም ይችላል (መረጃዎችን ከችግር መጠበቅ (Cyber Security) ከፍተኛ ወጪ እና ስራ ይጠይቃል)፤ ስራ አጥነትን ሊያስፋፋ ይችላል (#ለምሳሌ፦ ሮቦቶች የሰውን ስራ ሊቀሙ ይችላሉ!)፤ የዲጂታል ስርዓት ግንባታ ጠንካራ መሰረተ ልማት መጠየቁ ወጪን የማብዛት አደጋ ይፈጥራል፡፡

በዚህ በዲጂታል የቢዝነስ ዓለም በሶሻል ሚዲያ አንድ ሚሊየን ተከታይ ይዘው ወደ ውጤት እና ገንዘብነት መለወጥ ከተቸገሩ በሚሊየን ብር የመስሪያ ካፒታል ምንም እንዳልሰሩበት ሊቆጥሩት ይገባል!፤ ድርጅቶች/መንግስትን ጨምሮ ለዲጂታሉ አሰራር ትኩረት ባለመስጠት የአሰራር ሽግግር ማድረግ ካልጀመሩ መጪው ጊዚ ከእጃቸው እየወጣ ነው የሚመጣው፡፡

በእኛ ሀገር የዲጂታል ኢኮኖሚ እየተነቃቃ ቢሆንም ብዙ ማደግ ይጠበቅበታል! ከመሰረተ ልማት ጀምሮ (በቅርቡ የተሰራው የኢትዮጵያ የሳይንስ ሙዚየም ተስፋ ሰጪ ነው)፤ ከግለሰቦች እና ተቋማት ንቃት ጀምሮ፤ የዲጂታሉ ስርዓት ቁጥጥር መላላት ጀምሮ፤ የፖሊሲ አማራጭ ከመጥበቡ ጀምሮ (በኢትዮጰያ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ወደ ገንዘብ ዝውውር እንዲገቡ መፈቀዱ ጥሩ ጅምር ነው)፤ ከትምህርት ተቋማት ስትራቴጂክ ካለመሆን ጀምሮ፤ የቴክኖሎጂ ፈጠራን በበቂ ሁኔታ ካለማበረታታት ጀምሮ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ብዙ አሉ፡፡

                                                                                                    Subscribe      


YouTube፦ https://youtube.com/channel/UCzc8ISpZJ6RskJmd_DEx7WQ
2.1K viewsWasyhun Belay, edited  16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 20:00:38 ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት ወይም GDP የሚሰላው ጠቅላላ ኢኮኖሚ ውስጥ በአንድ ዓመት ውስጥ የተንቀሳቀሰ ገንዘብ መጠን ማለትም ግለሰቦች በዓመት ውስጥ የሸመቷቸው ወጪዎች (ምግብ የገዙበት፤ የተዝናኑበት፤ የታከሙበት፤ ቤት የገዙበት፤ ወዘተ የወጣ ወጪ)፤ በዓመት ውስጥ ለኢንቨስትመንት የተደረጉ ወጪዎች (ለመሬት፤ ለግብዓት፤ ወዘተ የወጣ ወጪ)፤ በዓመት ውስጥ የመንግስት ወጪዎች (ለመሰረተ ልማት ግንባታ፤ ለድጎማዎች፤ ለመከላከያ፤ ወዘተ የወጣ ወጪ) በአብዛኛው ይህ የመንግስት ወጪ የጠቅላላ ምርቱን ሰፊ ድርሻ ይይዛል፤ እንዲሁም በውጪ ንግዱ የገቡ ገቢዎች (Export)  ከወጡ ወጪዎች (Import) በመቀነስ የሚገኝ ገንዘቦች በማቀናነስ የተገኘውን የገንዘብ መጠን በመውሰድ ነው፡፡


ለመገበያያ የሚቀርበው የገንዘብ አይነት በተለያየ ሀገር ገንዘብ ቢሆንም በዶላር ተመን እየተሰላ ሊቀመጥ ይችላል! (የአንድ ሀገር GDP ሲጠቀስ የዚህን ያህል ዶላር የሚባለው ለዛ ነው! በሀገር ውስጥ የተንቀሳቀሰው ገንዘብ ከውጪ ንግዱ ውጪ በአብዛኛው በኢትዮጲያ ብር ቢሆንም የአቻ ተመኑ ተወስዶ በዶላር ሪፖርት የመሰራት ልምድ አለ እንደማለት ነው! ነገር ግን በብር አቻ ተተምኖም ሊቀመጥ ይችላል)፡፡


#ለምሳሌ፦ የዜጎች ሸመታ እና የመንግስት ወጪ በብር ቢሆንም ከውጪ ንግዱ የሚገኘው ዶላር ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሲጠቃለል ብሩን ወደ እለቱ የዶላር ዋጋ ወይም ዶላሩን ወደ እለቱ የብር ምንዛሬ ተመን ለውጡ በብር ወይም በዶላር የዚህን ያህል ተብሎ ይቀርባል።


ነገር ግን #ያገለገሉ_እቃዎች ሽያጭ ገንዘብ GDP ስሌት ውስጥ አይጠቃለልም! ለምን ይመስላችኋል?


ምክንያቱም ምርቱ በተመረተበት ዓመት ላይ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት ወይም GDP ውስጥ ስለተመዘገበ ካገለገለ በኋላ ለገበያ ወጥቶ ሲሸጥ ገንዘቡ ቢመዘገብ ለሁለተኛ ጊዜ ስለሚሆን ካገለገለ በኋላ በሚኖረው ሽያጭ አይመዘገብም (ስሌቱ የሚያዘው ህግ ነው)፡፡


#ለምሳሌ፡- አንድ ቁምሳጥን የዛሬ አራት ዓመት በ4ሺ ብር ወጪ ቢመረት እና ቢሸጥ የዛሬ አራት ዓመት በነበረው ጠቅላላ ሃገራዊ ምርት ምዝገባ ውስጥ 4ሺ ብሩ ይመዘገባል፡፡ ነገር ግን ከአራት ዓመት በኋላ ዘንድሮ ባለቤቱ ያገለገለውን ቁምሳጥን በ4ሺ ብር ቢሸጠው (በፈለገው ዋጋ) በዚህ ዓመት ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት ወይም GDP ሂሳብ ውስጥ 4ሺ ብሩ አይጠቃለልም እንደማለት ነው፡፡


ነገር ግን እንደኛ ባለ ሀገር በዓመት ውስጥ የሚደረጉ ሽያጮች እና የገንዘብ እንቅስቃሴዎች #ባለሰነድ የመሆን እድላቸው ዝቅተኛ ካለመሆናቸው አንጻር መሸዋወድ አይቀርም! ምን ማለት ነው? የዛሬ አራት ዓመት ቁምሳጥኑ ሲመረት የወጣው የግብዓት ወጪ፤ የሰራተኞች ደሞዝ፤ ወዘተ መንግስት የማያውቀው ሊሆን ይችላል እንደማለት ነው (የተቋማት አሰራር መዳከም እና የገበያ አሻጥር መብዛት ትክክለኛውን የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት/GDP መጠን አንዲዛባ ያደርጋል)፡፡

                 Subscribe      
             

YouTube፦ https://youtube.com/channel/UCzc8ISpZJ6RskJmd_DEx7WQ
1.6K viewsWasyhun Belay, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 19:31:19 የውጪ እርዳታ አፍሪካን ድህነት ውስጥ ከቷታል! "Aid is not working in Africa"


#Dambisa_Moyo (ዳምቢሳ ሞዮ).......


"አፍሪካ ለአጭር ጊዜ ከውጪ እርዳታ ብትላቀቅ ኢኮኖሚዋ ያድጋል!"


"ላለፉት 70 ዓመታት ለአፍሪካ ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የውጪ እርዳታ ቢሰጥም በድህነት ውስጥ የሚኖረው አፍሪካዊ ህዝብ ብዛት ከ11% ወደ 66% አድጓል"።


"ለአፍሪካ ከሚሰጠው የውጪ እርዳታ ውስጥ 85% ላልታለመለት ዓላማ ይውላል እንዲሁም ይዘረፋል"።


"#Dead_aid" በሚለው የዳምቢሳ ሞዮ ድንቅ መፅሃፍ ውስጥ ስለተጠቀሱ አመክንዮዎች ይህንን

የመፅሃፍ ዳሰሳ ቪዲዮ ሰርቻለሁ እስከመጨረሻው ይመልከቱት።
2.3K viewsWasyhun Belay, 16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 13:31:22 ዶላር ለምን የዓለም ጠንካራ መገበያያ እና የክምችት ገንዘብ ሆነ? ሀገራት ለምን የአሜሪካንን ዶላር ያከማቻሉ? ዶላር ለምን እስከአሁን በሌሎች ገንዘቦች አልተተካም? በቅርብ ዶላር መተካት ይችላል? ሰዎች እና ሀገራት በእጃቸው ያለውን ዶላር ለምን ይተማመኑበታል?

 ይህንን በተመለከተ በመረጃ የተደገፈ ሰፊ ትንታኔ አቅርቢያለሁ እስከ መጨረሻ ተከታተሉት።



2.9K viewsWasyhun Belay, 10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 15:05:49 ክፍል 2

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ ሃገራት ጠንካራ ኢኮኖሚ እየፈጠሩ መምጣት፤ ያደጉ ሀገራት ብድር የመውሰድ ፍላጎት መቀነስ፤ የሀገራት የንግድ ትብብር መጠናከር መጀመር፤ የአሜሪካን ጫና ላለመቀበል መወሰን መጀመሩ፤ ወዘተ ተደማምሮ ጠንካራ ገንዘቦች መፈጠር ጀምረዋል፡፡

#ለምሳሌ፡-  ብዙ ሀገራት የአውሮፓ ህብረት የሚጠቀመውን #ይሮን ለመገበያያ ማከማቸት እንዲሁም ከይሮ ዞን የተወሰዱ ብድሮችን ለመክፈል እንዲረዳ በብሄራዊ ባንኮቻቸው ይሮን ማከማቸት ጀምረዋል (ኢትዮጲያ ውስጥ ይሮ ከዶላር በላይ የምንዛሬ ዋጋ አለው!)፡፡ ማለትም ብዙ ዓለም አቀፍ የንግድ ደንበኞች በግብይት ወቅት ይሮን መቀባበል መጀመር ማለት ነው፡፡


በአንድ ወቅት የአረብ ሀገራት ነዳጅን በዶላር ለመሸጥ በነበራቸው ስምምነት የዓለም ሀገራት ለነዳጅ ፍላጎቶቻቸው ሲሉ ብቻ ከአረብ ሀገራት ነዳጅ ለመግዛት እንዲችሉ ዶላርን ባገኙት አጋጣሚ በሙሉ ለማከማቸት ተገደዋል፡፡

አሁን ላይ ለነዳጇ ሲባል ከፍተኛ ፍላጎት ያለባት ኪዌት አርቴፊሻል በሆነ መልኩ ገንዘቧን/ዲናር ከዶላር በላይ አድርጋለች (አንድ የኪዌት ዲናር ከ3 ዶላር በላይ ይመነዘራል)።

ብዙ ጥናቶችን ስንመለከት ወደፊትም የአሜሪካ ዶላር የዓለም መሪ ዓለም አቀፍ መገበያያ ሆኖ ሊቀጥል እንደሚችል ያስረዳሉ፡፡ ነገር ግን ቻይና እና ሩስያ ዓለም እራሱን ከአሜሪካ ጫና ለማላቀቅ አዲስ የዓለም መገበያያ እና የክምችት ገንዘብ ለመፍጠር ጥረት እንዲያደርግ እየሞከሩ ነው።


የBRICS አባል ሀገራት ማለትም ብራዚል፤ ሩስያ፤ ህንድ፤ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ በቀጣይ ሳውዲን በመቀላቀል በግብይት ዘርፍ ዶላር/አሜሪካ ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር እየሞከሩ ነው (ለምሳሌ፦ አሁን ላይ ቻይና እና ሩስያ እርስ በርስ ግብይት ሲያከናውኑ በአብዛኛው ዶላር ላለመጠቀም ወስነዋል)፡፡

#ለምሳሌ፡- በ2018 አሜሪካ/ትራንፕ ኢራን ላይ የኢኮኖሚ መአቀብ በመጣሉ የኢራን የነዳጅ ሽያጭ ተጽኖ ውስጥ በወደቀ ጊዜ ፈረንሳይ፤ እንግሊዝ እና ጀርመን ከዶላር ውጪ (Dollar Free System) ከኢራን ጋር ግብይት ለማከናወን ስምምነት አድርገዋል ቀጥለዋል፡፡

በዓለም ላይ ከ1.8 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ተሰራጭቷል እንዲሁም ከ75% በላይ የ100 ዶላር ኖት እና ከ50% በላይ ባለ 50 ኖት ዶላር ተሰራጭቶ የሚገኘው ከአሜሪካ ውጪ ባሉ የዓለም ሀገራት ነው (ኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አጠገብ የሚመነዝሩት ልጆች እጅ ሳይቀር ባለ 100 እና ባለ 50 ዶላር አለ ማለት ነው!)።

ሙሉውን በድንቅ ትንታኔ ለመመልከት

3.5K viewsWasyhun Belay, 12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 10:50:31 ዶላር ለምን የዓለም ጠንካራ ገንዘብ ሆነ? ከአሜሪካ ውጪ ያሉ ሀገራት ለምን ዶላርን ያከማቻሉ? ዶላር መተካት የሚችል ገንዘብ ነው?

ክፍል 1

ከ1940ዎቹ በፊት የዓለም ሀገራት ለዓለም አቀፍ ግብይት የወርቅ ክምችትን እንደ ዋስትና ይይዙ ነበር፡፡ ምን ማለት ነው? አንድ ግራም ወርቅ ያለው ሀገር ምን ያህል ገንዘብ አቻ እንዳለው ልኬት ይቀመጣል፡፡ ይህ አሰራር Gold Standard ይባል ነበር፡፡

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቂያ ላይ (ማለትም 1944) የዓለማችን 44 ሀገራት ተሰባስበው በወርቅ የሚኖረው የአቻ ተመን ወደ አንድ ጠንካራ ወደሚባል ገንዘብ እንዲለወጥ እና ዓለም አቀፍ ግብይት ለማከናወን ጥቅም ላይ እንዲውል ሃሳብ አመጡ፡፡ በወቅቱ በሁለቱም የዓለም ጦርነቶች ያልተዳከመችው እና ከአውሮፓ ሀገራት የተሻለ የተረጋጋ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ የነበራት አሜሪካ ስለነበረች በስምምነት ዶላር የዓለም አቀፍ መገበያያ ወርቅን ወክሎ እንዲመነዘር ወሰኑ ይህ ስምምነት Bretton Woods Agreement ይባላል፡፡

አንዳንድ ኢኮኖሚስቶች በወቅቱ የአሜሪካው ዶላር ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት ጠንካራ የነበረውን የእንግሊዙን ገንዘብ ማለትም ፓውንድን ቀምቶታል ይላሉ፡፡

ዶላር የወርቅ ተመን ማውጫ ሆኖ እንዲያገለግል የሚፈቅደውን ስምምነት እንዲያስፈጽሙ ከተቋቋሙት ተቋማት መካከል የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF)፤ የዓለም ባንክ (World Bank)፤ የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO)፤ ወዘተ ስራቸውን ጀመሩ፡፡
#ለምሳሌ፡- ከ1944 እስከ 1970 ድረስ አንድ የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት አንድ ሀገር 28 ግራም ወርቅ ማቅረብ አለባት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የወርቅ ልኬቱ 28 ግራም አንድ ዶላር በሚል ይሆናል ማለት ነው፡፡

በወቅቱ አሜሪካ በተለይ ከአሜሪካ ውጪ በተለያዩ ሀገራት የብሄራዊ ባንኮች የሚከማቸው ዶላር አቻ ወርቅ መሸፈን ሲያቅታት የወርቅ ክምችትን ከዶላር አቻ ጋር እያነጻጸሩ መገበያየት 1971 በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ኒክሰን አማካኝነት የአሜሪካ ዶላር ስንት ግራም ወርቅ ይሁን የሚለው ቀርቶ የሌሎች ሀገራት ገንዘብ ከራሱ ከዶላር ጋር ያላቸው ተመን እንዲሰራ ወሰኑ፡፡

ማለትም 28 ግራም ወርቅ አንድ ዶላር የሚለው ልኬት ቀርቶ በቀላል ቋንቋ አንድ የእንግሊዝ ፓውንድ በስንት ዶላር ይመነዘራል ወደማለት ተዛወረ፡፡ ወይም አንድ ዶላር ስንት የኢትዮጲያ ብር ነው እንደማለት ነው፡፡

በወቅቱ የዓለም ጠንካራ ኢኮኖሚ አቅም ባለቤት የሆነችው አሜሪካ ያላት የንግድ ትስስር ከፍተኛ በመሆኑ (ከፍተኛ ላኪ እና ከፍተኛ ሸማች በመሆኗ) ሀገራት በዶላር ለሚኖር ዓለም አቀፍ ግብይት እንዲረዳቸው ዶላርን ባገኙት አጋጣሚ በሙሉ በብሄራዊ ባንኮቻቸው ማከማቸት ጀመሩ፡፡ ምን ማለት ነው Foreign Reserve Currency መፈጠር ጀመረ ማለት ነው፡፡

ሀገራት ዶላርን የሚያገኙት ምርትን እና አገልግሎትን ወደ ሌሎች ሀገራት ይልኩ (Export) እና ክፍያውን በዶላር ይቀበላሉ፤ የሌሎች ሀገራት ባለሃብቶች በሀገራቸው ሲመጡ (FDI) የሚደረግን ክፍያ በዶላር ያደርጉ እና ይቀበላሉ፤ ቱሪስት ወደ ሃገራቸው ሲመጣ ዶላር እንዲከፍል እያስገደዱ ያከማቻሉ፤ ወዘተ፡፡
#ለምሳሌ፡- በቅርቡ ኢትዮጲያ ያላት የውጪ ምንዛሬ ክምችት የ21 ቀን ፍጆታ ብቻ ነው የሚል ትንበያ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እንደወጣው ማለት ነው፡፡

የዶላር ክምችቱ የሚያስፈልገው በዋናነት ዓለም አቀፍ ግብይት ለማከናወን እና እዳ ለመክፈል ሲባል ነው፡፡ በቀላል አነጋገር ህንድ ከጃፓን እቃ ለመግዛት ብታስብ የምትከፍለው የህንድን ገንዘብ/ሩፒ ሳይሆን የአሜሪካ ዶላር ይሆናል ወይም ጃፓን እቃውን ለህንድ ለመሸጥ ህንድን የምታስከፍላት በጃፓን የን ወይም በህንድ ሩፒ ሳይሆን በአሜሪካ ዶላር ነው፡፡ ለምን?

ጃፓን ምንም ቁስ ከሌሎች ሀገራት ለመሸመት የምትጠየቀው ዶላር በመሆኑ በራሷ ገንዘብ ግብይት ልታደርግ አትችልም ወይም ብራዚል ከኮርያ ብድር ብትወስድ ልትከፍል የምትችለው በዶላር ነው! ምክንያቱም ብራዚል የሆነ እቃ ከቱርክ ለመሸመት ብታስብ የምትጠየቀው ዶላር በመሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም አሁንም ድረስ ጠንካራ የወለድ ምጣኔ፤ ዝቅተኛ የዋጋ ንረት፤ ጠንካራ ኢኮኖሚ አቅም ያለው ሀገር ገንዘብ መሪ ነው! እሱ ደግሞ የአሜሪካው ዶላር ነው፡፡

ዶላር የዓለም መገበያያ መሆኑን ተከትሎ አሜሪካ በቀላሉ ለተለያዩ የዓለም ሀገራት ብድር እና ቦንድ በማቅርብ ከፍተኛ ሃብት እንድታካብት ከማድረጉ በተጨማሪ የዶላርን ጉዳይ የፖለቲካ ጫና መፍጠሪያ በማድረግ ትጠቀማለች (የፖለቲካ ቅራኔ የፈጠረችባቸውን ሀገራት የዶላር ክምችት ሃብት ማንቀሳቀስ አትችሉም እስከሚል ክልከላ ድረስ ማለት ነው!)፡፡

የየሃገራት ኢኮኖሚ አቅም የአሜሪካን አቅም ተገዳዳሪ አለመሆን፤ አሜሪካ በብዙ ሀገራት ያላት ወዳጅነት እና ጣልቃ ገብነት ከፍተኛ መሆን፤ የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ ገንዘቡን/ዶላርን ለማስተዳደር የሚወስደው የወለድ ማሻሻያ እና የዋጋ ንረትን ተቆጣጥሮ ለማቆየት ባላቸው ጥረት ዶላር አሁንም ድረስ በጣም ተፈላጊ የገንዘብ አይነት ሆኖ ቆይቷል፡፡

በዓለም ላይ የዶላር አጠቃቀም ሶስት ባህሪ ይዟል፡፡ አንደኛ፡- ዶላርን እንደ ገንዘባቸው አቻ አድርገው የሚጠቀሙ ሀገራት (ከ65 ሀገራት በላይ) አሉ! (ማለትም አንድ የራሳቸው ገንዘብ አንድ ዶላር እንደማለት ነው) ስለዚህ በገበያቸው ዶላርን ቀጥተኛ መገበያያ አድርገው ይጠቀማሉ፡፡ #ለምሳሌ፡- ፖርተሪኮ፤ ኢኳዶር፤ ፓናማ፤ ዝምባብዌ፤ ወዘተ ዶላርን ገንዘባቸው አድርገው ይጠቀማሉ፡፡ ለዚህ ዋናው ምክንያት የሀገራቸው ገንዘብ አቅም በጣም ደካማ ከመሆኑ የተነሳ የሚፈጠርን ከፍተኛ የዋጋ ንረት ለመቋቋም ሲባል ነው፡፡
ሁለተኛ፡- ዶላርን ከሀገራቸው ገንዘብ ጎን ለጎን እንደ ህጋዊ መገበያያ የሚጠቀሙ ሀገራትም (Quasi-Currency of Exchange) አሉ #ለምሳሌ፡- አብዛኛው የካሪቢያን ወይም የላቲን አሜሪካ ሀገራት ይጠቀሳሉ፡፡ #ለምሳሌ፡- ካናዳ እና ሜክሲኮ አንድ የየትኛውም ሀገር ቱሪስት ቢሄድ በዶላር እየከፈለ በቀጥታ መጠቀም ይችላል፡፡

ሶስተኛ፡- ሀገራት ደግሞ ልክ እንደ ኦትዮጲያ ዶላር በብሄራዊ ወይም በባንኮች እየተመነዘረ እንጂ ገበያ ውስጥ ዶላር ከፍሎ መጠቀም የማይፈቅዱ ሀገራት አሉ፡፡ #ለምሳሌ፡- ኢትዮጲያ ውስጥ የሚመጣ ቱሪስት ታክሲ ለመያዝ ዶላር ሳይሆን የሚከፍለው በባንክ ሄዱ በእለቱ ምንዛሬ ዶላሩን መንዝሮ ነው የኢትዮጲያ ብርን ይዞ የሚጠቀመው፡፡


የፅሁፉ ክፍል 2 ይቀጥላል..... (ቴሌግራም ላይ ረጅም ፅሁፍ በአንድ ገፅ ማድረግ ስለማይቻል ሁለት ቦታ አድርጌዋለሁ! በሰፊው ሙለውን በቪዲዬ

ማየት ይቻላል)።
3.4K viewsWasyhun Belay, 07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 07:47:36 ዶላር ለምን የዓለም ጠንካራ መገበያያ እና የክምችት ገንዘብ ሆነ? ሀገራት ለምን የአሜሪካንን ዶላር ያከማቻሉ? ዶላር ለምን እስከአሁን በሌሎች ገንዘቦች አልተተካም? በቅርብ ዶላር መተካት ይችላል? ሰዎች እና ሀገራት በእጃቸው ያለውን ዶላር ለምን ይተማመኑበታል?

 ይህንን በተመለከተ በመረጃ የተደገፈ ሰፊ ትንታኔ አቅርቢያለሁ እስከ መጨረሻ ተከታተሉት።



3.4K viewsWasyhun Belay, 04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-29 14:05:28 በሀገራችን በሆነ ምክንያት ዋጋ ከፍ ካለ ወደ ቦታው ለመመለስም ሆነ ለመቀነስ በጣም ከባድ ነው! ለምን?


በተለያዩ ምክንያቶች የቁሳቁስም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ አንዴ ከፍ ካለ በጊዚያዊነት አቅርቦት ቢሻሻልም የጨመረ ዋጋ ወደ ነበረበት ለመመለስ ሲችል አንመለከትም! የዚህ ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው ብዬ የማምንባቸውን አራቱን በዚህ

ቪዲዮ ለመግለጽ ሞክሪያለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት።


የንግድ ሰንሰለቱ ረዥም እና በርካታ ተዋናዮች ያሉበት መሆኑ፤ ደካማ የመረጃ ተደራሽነት ያለው ገበያ መሆኑ፤ አቅርቦት ዘላቂ እድገት ያለማሳየቱ እና ገበያው የሚመራበት ስትራቴጂ ደካማ መሆን የሚጠቀሱ ምክያቶች ናቸው።
4.1K viewsWasyhun Belay, 11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 19:30:43 #Cost_Disease?

የዛሬ 40 ዓመት ጥርስ የሚነቀልበት ሂደት ብዙም ሳይለወጥ ጥርስ የማስነቂያ ዋጋ አሁን ላይ እጅግ ውድ የሆነው ለምን ይመስላችኋል? በትምህርት ጥራት እየቀነሱ ነገር ግን በዋጋ ውድ እየሆኑ ያሉ ኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲዎች ምክንያታቸው ምን ይመስላችኋል?

ከ1970ዎቹ እስከ 2014 ድረስ ተመሳሳይ ዘፈን በየመድረኩ የዘፈነ ዘፋኝ ተመሳሳይ ስራ እየሰራ የሚከፈለው ክፍያ ለምን የጨመረ ይመስላችኋል? የዛሬ 25 ዓመት በተመሳሳይ የሰርግ ዘፈን የዳረ ዘፋኝ ዘንድሮ ያንኑ ዘፍኖ በብዙ እጥፍ ክፈሉኝ ለምን የሚል ይመስላችኋል? የዛሬ 20 ዓመት የነበሩ የግል ትምህርት ቤቶች የማስተማሪያ ዘዲያቸው ብዙም ሳይለውጡ እና ነባር አስተማሪዎቻቸው እየተጠቀሙ የዛሬ 20 ዓመት ከሚጠይቁት ክፍያ በከፍተኛ ሁኔታ ያስወደዱት ለምን ይመስላችኋል?

በጥራትም ሆነ በአዋጪነት ደካማ መሆናቸው እየታወቀ ለትምህርት ሴክተር፤ ለጤናው ሴክተር፤ ለደህንንት ተቋማት፤ ወዘተ ለምን ከፍተኛውን የመንግስታትን በጀት ድርሻ የሚወስዱ ይመስላችኋል?

ከላይ በዘመናት መካከል የአገልግሎት ዋጋዎች በከፍተኛ ደረጃ እየጨመሩ የመጡበትን ምክንያት እኔም እናንተ ልትገምቱ ከምትችሉት የዘለለ ምክንያት አላቸው ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ ነገር ግን የአሜሪካዊውን ኢኮኖሚስት William Baumol ወሳኝ አርቲክል ማለትም #Cost_Disease (Baumol effect) የሚለውን ሳነብ በቀጣይ የአለም የኢኮኖሚ አካሄድ ባህሪ ልብ ሳይባል እየተለወጠ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡

William Baumol በ1960ዎቹ የሚሰሩ ሙዚቀኞች የተለየ ፈጠራን ሳይጨምሩ (Low productivity) ተመሳሳይ ስራዎች በመስራት የሚያገኙት ገቢ ግን በፍጥነት እያደገ መሄዱን አየ! ከዛ የ100 ዓመት መረጃዎችን (1865 እስከ 1965) ሲያጠና ተጨማሪ ፈጠራ ሳይኖራቸው ዘፋኞች በየመድረኩ የሚያስከፍሉት ክፍያ እየጨመረ ነበር፡፡

ስለዚህ "ሁለት አይነት ሴክተር በኢኮኖሚ ውስጥ አለ" አለ! በጣም የቴክኖሎጂ ፈጠራቸው እያደግ ያሉ እና በተጨማሪ የማምረት አቅም (Productivity) የደረጁት የአምራች/Manufacture ክፍሉ እና ብዙም የተለየ ፈጠራ እና የማምረት አቅማቸው እያደገ ያልሆኑት (Stagnant productivity) የአገልግሎት/Service ክፍል ናቸው ይላል፡፡

የአምራች ክፍሉ ዋጋ እና የአገልግሎት ክፍሉ ዋጋ ያላቸው ልዩነት ከፍተኛ ነው! የጫማ ዋጋ ከሚጨምረው በላይ የትምህርት ቤት ክፍያ ያድጋል፤ የአዳዲስ ዘመናዊ መኪኖች ዋጋ ከሚጨምረው በላይ ለህክምና የሚጠየቀው ዋጋ ውድ ነው፤ በየዘመኑ ለመጡ ለፈርኒቸር ውጤቶች ከሚጠየቀው ዋጋ በላይ ልጅ ለማስተማር የሚጠየቀው ዋጋ ውድ ነው፤ ወዘተ፡፡

በአምራች ክፍሉ ያለው ምርታማነት ማደግ ሰዎች ከፍተኛ ገቢ እንዲያገኙ ስለሚያደርግ የመክፈል አቅም አላቸው (This is because the economy's constantly growing productivity simultaneously increases the community's overall purchasing power) የሚለው እሳቤ ለአገልግሎት የሚቀርቡ ሰዎችን ዋጋ እያናረው መጥቷል። እንዲሁም ሰዎች በተቻለ መጠን ወደ አምራች ክፍሉ የስራ ዘርፍ ሊኖራቸው የሚችልን መዛወር ለመቋቋም በአገልግሎቱ ሴክተር ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን እዳይለቁ ለማባበል ሲባል የሚከፈላቸው ክፍያ እያደገ ሲሄድ ለአገልግሎቱ የሚያስከፍሉት እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

በሀገራችን ከሆቴል ማናጀር ወይም ዋና ሼፍ እና ከጫማ ፋብሪካ ማናጀር በደሞዝ የሚሻለው ማን ነው?

William Baumol የመኪና አምራች ክፍሉ በጣም ዘመናዊ መኪኖችን እያመረተ ነው! ስለዚህ ፈጠራው ጨምሮ በሹፍርና ዘርፍ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰዎች በራሱ መንቀሳቀስ የሚችል (Automated) መኪና ሲፈጠር ስራቸውን ያጣሉ! ነገር ግን ምንም ዘመናዊነት ቢያድግ ሰዎች ሃኪም፤ አስተማሪ እና ጸጉር ቆራጮችን በማሽን ሊተኳቸው አልያም እነዚህ የአገልግሎት ሴክተር ሰራተኞች ስራችንን ልናጣ እንችላለን ስለማይሉ የአገልግሎት ሴክተሩ ተሳትፎ እያደገ ይሄዳል ይላል፡፡

ረቦቶች/ማሽኖች እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች እያደጉ መምጣታቸውን ተከትሎ በማምረቻ ተቋማት ያለው የሰራተኛ ቁጥር የመጨመር ሳይሆን የመቀነስ አዝማሚያ እያሳየ ነው፡፡ ነገር ግን በአገልግሎት ሴክተሩ ያለው ሰራተኛ በእጅጉ እያደገ ነው፡፡ ምን ማለት ነው? በቀጣይ የዓለም ኢኮኖሚ ከአምራች ወደ አገልግሎት ሴክተር እየተዛወረ መሄዱ ጤነኛ የሚባል አይሆንም ይላል ምክንያቱም በአገልግሎት ሴክተሩ የሚከፈለው ከፍተኛ ክፍያ በአምራች ዘርፉ ያሉ ሰራተኞችን ማስኮብለሉ አይቀርም ነው፡፡

የመንግስታት የጤና እና የትምህርት ወጪ/በጀት እያደገ ሲሄድ ለሴክተሩ በተሰጠ ትኩረት ብቻ ይመስላቸዋል! ነገር ግን ሴክተሩ የሚጠይቀው ዋጋ እና ወጪ በፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ ነው፡፡

ከፍተኛ የማምረት አቅም ያላቸው የአምራች ክፍሎች/ፋብሪካዎች የሚጠቀሟቸው ማሽኖች የምርትን ጠቅላላ ወጪ ስለቀነሱት የምርቶች ዋጋ መቀነስ እያሳየ ነው ነገር ግን ከፍተኛ የማምረት አቅም የማይስተዋልበት የአገልግሎት ዘርፉ ከፍተኛ ፈላጊ በመያዝ የአገልግሎት ወጪውም ክፍያውም ውድ እየሆነ ነው፡፡

#ለምሳሌ፡- ደሞዝ በማይከፈላቸው ረቦቶች የሚያመርት ካምፓኒ የማምረቻ ወጪው በሂደት እየቀነሰለት ነው የሚሄደው ስለዚህ የምርቱ ዋጋ እየቀነሰ ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ቀጥታ ተሳትፎ የሚያደርጉበት ሴክተር (labor-intensive services) ውድ መሆናቸው ቀጥለዋል፡፡

ነገር ግን በሀገራችን ሁኔታው ይህንን ባህሪ ይይዛል ለማለት ከባድ ነው፡፡ የማምረቻ ዘርፉ የምርታማነት መጠን በሚፈለገው ልክ ሳያድግ/ኢኮኖሚው በአብዛኛው ለፍጆታው የሚያስፈልገውን የኢንዱስትሪ ውጤቶች ከውጪ ሸምቶ አስገቢ ሆኖ/ የግል ሴክተሩ ለትምህርት፤ ለጤና፤ ወዘተ የሚጠየቀው ክፍያ William Baumol በሚለው በተመሳሳዩ እያደገ ነው! ስለዚህ ኢኮኖሚያዊ መሰረት ጠንካራ መሆን የሚገባው በአምራች እና በአገልግሎት ሴክተሩ መካከል ሊኖር የሚገባው እሽቅድድም ጤነኛ ሲያረግ ነው፡፡

የኢኮኖሚክስ ትምህርት እንዲወደድ የሚያደርገው ዋናው ምክንያት አለማለቁ ነው! ሁሌም ከሁኔታዎች አንጻር አመክንዮዎቹ ይቀነሳሉ! ይጨመራሉ! ዛሬ ላቀርብላችሁ የሞከርኩት ሃሳብ ትንሽ ግር የሚል ቢመስልም ዓለም ምርጥ የሚለው የኢኮኖሚክስ ሃሳብ ነው! በጽሁፍ ለመግለጽ የማያመቹ ቢሆኑም የተወሰነ ሞክሪያለሁ ተጨማሪ በማንበብ በደንብ መረዳት አልያም ማዳበር የምትፈልጉ ሰዎች ልትጨምሩበት ትችላላችሁ፡፡

YouTube፦ https://youtube.com/channel/UCzc8ISpZJ6RskJmd_DEx7WQ


Facebook፦ https://www.facebook.com/EconomistWasyhun/?modal=admin_todo_tour
4.4K viewsWasyhun Belay, edited  16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ