Get Mystery Box with random crypto!

የነዳጅ ዋጋ ከ30% በላይ መጨመሩን ተከትሎ የሸቀጦች እና የአገልግሎት ዋጋ በስንት ይጨምራል? | The Ethiopian Economist View

የነዳጅ ዋጋ ከ30% በላይ መጨመሩን ተከትሎ የሸቀጦች እና የአገልግሎት ዋጋ በስንት ይጨምራል?


የነዳጅ ድጎማ የተለመደ በመሆኑ የድጎማው መነሳት አዝማሚያ ሲያሳይ በቅርቡ እየታየ ያለው የነዳጅ ሰልፍ እና የቦቴ መኪኖች መደበቅ በ Psychological price መርህ የሚጠበቅ ነው።


ይህ ሰልፍ እና ድበቃ የሚቆየው የሃምሌ ወር ገብቶ የነዳጅ ሸማች እና የነዳጅ አቅራቢዎች የዋጋ እና የሁኔታ Adjustment/አቀባበል እስኪያደርጉ በጊዚያዊነት ነው ብዬ አምናለሁ!


ምክንያቱም ሸማች አዲሱን ዋጋ እየተለማመደ ይመጣል በተመሳሳይ አቅራቢዎች አዲሱ ዋጋ ወደስራ መግባቱን መደበኛ አቅርቦት አድርገው መቀበላቸው አይቀርም።


በነዳጅ እና በናፍጣ ላይ በሊትር ከ10 ብር በላይ ጭማሪ ወይም ከባለፈው ወር ከ30% በላይ ጭማሪ ሲፈጠር ማዕከላዊ ገበያው ላይ ተጠባቂ የዋጋዎች መጨመር መኖሩ ግድ ነው።


#ለምሳሌ፦ በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረው ቤንዚን፤ 10 ብር ከ96 ሳንቲም ጨማሪ በማሳየት ከነገ ጀምሮ በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም ይሸጣል።


#ለምሳሌ፦ በሊትር 35.43 ብር ሲሸጥ የነበረው ነጭ ናፍጣ 13.59 ብር ጨምሮ ከዛሬ ጀምሮ በሊትር 49.02 ብር ለገበያ ይቀርባል።


የድጎማ መጥፎ ጎን ገበያው ትክክለኛ ዋጋዎችን ሳያውቅ እንዲቆይ ማድረጉ ነው። ስለዚህ የመረጃ እጥረት፤ የአቅርቦት እጥረት፤ የማምረቻ ወጪ ውድነት እና ደካማ የገበያ አመራር ያለበት ገበያ ሲሆን መተራመሱ አይቀርም።


መንግስት ድንገት የሚፈጠሩ የአቅርቦት እና የዋጋ መናጋቶችን ለመቀነስ የአቅርቦት ስርጭት እና የገበያ ቁጥጥር ስራዎችን ማከናወን አለበት።


የዋጋ ትርምሶች ዝቅተኛ ገቢ የሚያገኘውን የህብረተሰብ ክፍል ይበልጥ ስለሚጎዳ የመሰረታዊ ቁሶች አቅርቦትን መንግስት መምራት አለበት።


የዋጋ ትርምስ ፈጣን አማራጭ የማረጋጊያ ስራዎች ካልተሰሩ ነዳጅን ሰበብ አድርገው የሚፈጠሩ አዳዲስ ዋጋዎች መደበኛ ዋጋ መሆን ስለሚጀምሩ ቅድሚያ የመሰረታዊ ሸቀጦች የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት ስርዓት በማበጀት የዋጋ ጭማሪ እንዳይለመድ ማድረግ አለበት።