Get Mystery Box with random crypto!

አምራቾች፤ ነጋዴዎች፤ የቢዝነስ አዋጪነት ጥናት አዘጋጆች እና የቢዝነስ ፕላን ጥናት ገምጋሚዎች የመ | The Ethiopian Economist View

አምራቾች፤ ነጋዴዎች፤ የቢዝነስ አዋጪነት ጥናት አዘጋጆች እና የቢዝነስ ፕላን ጥናት ገምጋሚዎች የመሸጫ እና የአገልግሎት መስጫ ዋጋ ለማውጣት የሚከተሉትን መስፈርቶች መከተል ተገቢ ነው...

1. ምርቱ ለመመረት ያስወጣውን ጠቅላላ ወጪ (Variable Costs)
2. ለቋሚ ንብረቶች የወጣ ወጪ (Fixed Costs)
3. የትርፍ ጣሪያ (Profit Margin)

ሸማች ለሚሸምተው ነገር በአብዛኛው በቂ መረጃ አለው ተብሎ ይታሰባል! ስለዚህ ጊዜው እና ገንዘቡ የሚመጥነውን ዋጋ በራሱ በማስላት እርካታውን ለመጠበቅ ይጥራል፡፡ ስለዚህ አምራቾች እና ሻጮች ትክክለኛውን ሸማች ማወቅ እና ለሚያቀርቡት ምርት እስከ ስንት ድረስ የመክፈል ፍላጎት እንዳለው (Willing to Pay) ለማወቅ፤ የወሰኑት ዋጋ ቢዝነሳቸው በትርፋማነት ለረጅም ጊዜ እንዲዘልቅ የሚያደርግ ዋጋ መሆኑን ለማወቅ በሳይንስ (Pricing Strategy) መመራት ያለበት የገበያ ጥናት አካል ነው፡፡

ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ቪዲዮ

ተመልከቱ፤ ተጠቀሙበት እና ለሌሎች እንዲጠቀሙበት አጋሩት፡፡