Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.90K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2023-03-21 07:49:21 መንግስት ከወር በላይ የኢንተርኔት ገደብ መጣሉ እየፈጠረበት ያለው #Opportunity_Cost ዝቀተኛ ከሆነ የማናውቀው ብዙ ነገር አለ ማለት ነው!
3.0K viewsWasyhun Belay, 04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 11:47:37 በተለያዩ ምክንያቶች የቁሳቁስም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ አንዴ ከፍ ካለ በጊዚያዊነት አቅርቦት ቢሻሻልም የጨመረ ዋጋ ወደ ነበረበት ለመመለስ ለምን ይቸገራል?


የዚህ ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው ብዬ የማምንባቸውን 4ቱን

ቪዲዮ ለመግለጽ ያህል።
866 viewsWasyhun Belay, 08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 20:33:19 አንዳንድ ወጣቶች "ስራ የማይጠፋበትና የሚያበላ ዘርፍ ምንድን ነው?" ብለው ይጠይቃሉ። በርግጥ የሚያበላም ሆነ በፍጥነት ስራ የሚገኝበት ስለሚባል የትምህርት መስክ ዛሬ ላይ መወሰን ከባድ ነው።



ልጅ ሆናችሁ በምትመኟቸው ዘርፎች ተመርቀው ለለት ፍጆታ ትግል ውስጥ ያሉ ብዙ ናቸው። ከዚህ ዩኒቨርስቲ መመረቅ እድል ነው ትሉባቸው ከነበሩ ተቋማት ወጥተው የሰራተኛው ገበያው ያልወሰዳቸው ብዙ ናቸው።  ምርጫቸውን ሰፊ ለማድረግ ከአንድ በላይ ድግሪ ይዘው በአንዱም ያልተቀጠሩ ትንሽ አይደሉም።


ኮሌጅ አልሄድም ብለው ብዙዎችን ቀጣሪ የሆኑ ብዙ ናቸው! ኢኮኖሚ ውስጥ አንዳንድ ከፍተኛ ገቢ እየተገኘባቸው ያሉ መስኮች የኮሌጅ ድግሪ ግዴታ የሆነባቸው አይደሉም።


ስለዚህ ለመማር ዛሬ ላይ ስትወስኑ ወቅታዊው የሰራተኛ ገበያ፤ የኢኮኖሚ፤ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ እስከምርቃታችሁ እንደሚዘልቅ እርግጠኛ አትሁኑ።


የሰራተኛ ገበያው እና የቢዝነስ አዝማሚያው የሚወሰነው በጥረታችሁ እና ለሁኔታዎች ባላችሁ ተለዋዋጭ እይታ በመሆኑ ነባር መመዘኛዎችን በሂደት እየመረመሩ መሄድ ግድ ነው።
246 viewsWasyhun Belay, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 20:18:55 የመሰረታዊ ፍጆታ ገንዘብ ያለው ተከራይ እና የመሰረታዊ ፍጆታ እጥረት ያለበት የቤት ባለቤት መካከል ያለው ልዩነት #ተስፋ ብቻ ነው?


50% የሚሆኑ ዜጎቻቸውን የቤት ባለቤት ማድረግ ያልቻሉ የበለፀጉ ሃገራት አመክንዮ ምንድን ነው?


የዓለም መረጃ

2.4K viewsWasyhun Belay, 17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 17:29:40 የቤት ባለቤትነት የፋይናንስ ነፃነት ላያመጣ ይችላል! እንዴት?


የመሰረታዊ ፍጆታ ገንዘብ ያለው ተከራይ እና የመሰረታዊ ፍጆታ እጥረት ያለበት የቤት ባለቤት መካከል ያለው ልዩነት #ተስፋ ብቻ ነው?


50% የሚሆኑ ዜጎቻቸውን የቤት ባለቤት ማድረግ ያልቻሉ የበለፀጉ ሃገራት አመክንዮ ምንድን ነው?


የዓለም መረጃ

2.8K viewsWasyhun Belay, 14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 19:57:42 ስለ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በጥልቀት ለማወቅ ፍላጎት ላላቸው በሙሉ የተከፈተ ቻናል!
If you are passionate about Economics, This page is for you!

YouTube፦



Facebook፦ https://www.facebook.com/EconomistWasyhun/?modal=admin_todo_tour
3.3K viewsWasyhun Belay, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 19:43:35 ዋጋ ንረት/Inflation ምንነት፤ ምክንያት፤ ደረጃ፤ ስጋት እና እድል!


ዋጋ ንረት/Inflation ሰፊ ትርጉም፤ የዋጋ ንረት የሚከሰትበት ምክንያት እና ተፅዕኖ፤ የዋጋ ንረት ሊኖረው የሚችለው እድል፤ የሚመከር የዋጋ ንረት ደረጃ፤ ከፍተኛ የዋጋ ንረት የተከሰተበት ወቅት፤ የዋጋ ንረት መከላከያ መንገድ፤ ወዘተ ላይ ጠለቅ ያለ ትንተና ተመልከቱ።

2.0K viewsWasyhun Belay, 16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 08:42:12
የዓለም ባንክ በዛሬ መረጃ (https://www.facebook.com/worldbank) መረጃው ወቅታዊ ዋጋን (Nominal) መሰረት ያደረገ ነው ይላል)!

በዓለም ላይ የምግብ ዋጋ ንረት ከፍተኛ ሆኗል! ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ምግብ በ94.1% ሲንር፤ ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ምግብ በ86% ንሯል እንዲሁም ከፍተኛ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ምግብ በ93% ዋጋው ንሯል፡፡

የምግብ ዋጋ ንረት በ264% በዝምባብዌ እና በ139% በሊባኖስ ከፍተኛ ሲሆን ኢትዮጲያ ከ30% በላይ የምግብ የዋጋ ንረት ካለባቸው ውስን ሃገራት መካከል አንዷ ነች ይላል፡፡ ከምግብ እህል መካከል በ2ዓመት ውስጥ በቆሎ በ24% የጨመረ ሲሆን ስንዴ በ7% ዋጋቸው ጨምሯል፡፡

በስጋት የተሞላው የዓለም የግብርና ገበያ እና የራሽያ እና የዩክሬን ጦርነት አለመብረዱ ችግሩን ካባባሱት መካከል መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

በኢትዮጲያ ያለውን የስንዴ እና የጤፍ የዋጋ መጨመርን ነዋሪ በቀላሉ ሊተነትነው ይችላል፡፡
3.0K viewsWasyhun Belay, edited  05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 08:40:24 በሀገራችን የባንክ ወለድን በመጨመር የዋጋ ንረቱን መቀነስ ይቻላል?


በርካታ የዓለም ሀገራት እየተፈጠረ ያለውን ከፍተኛ #የዋጋ_ንረት ለመቋቋም በባንኮች ያለውን #የወለድ_መጠን በመጨመር ላይ ናቸው! ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተመሳሳይ ምክረ ሃሳብ ከኢኮኖሚስቶች እየተሰጠ ነው! እውነት በኢትዮጵያ የባንክ ወለድን በመጨመር በፍጥነት እየጨመረ ያለውን የዋጋ ንረት ማረጋጋት ይቻላል?


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን

ቪዲዮ ሰርቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት።
2.2K viewsWasyhun Belay, 05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 19:47:54 #በድሃ እና #ከድህነት_ወለል_በታች በሚኖር መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?


በኢትዮጵያ በቀን ስንት ብር የሚያገኝ ወይም ምን ያህል ካሎሪ ያለው ምግብ የሚመገብ ነው ከድህነት ወለል በታች የሚካተተው?



በዓለም ላይ ወጥ በሆነ መልኩ የድህነት ወለል የለም! ያደጉ ሃገራት የድህነት ወለል ላላደጉ ሀገራት ከጣሪያ በላይ ነው! ለምን?


ለድህነት ወለል መሰረታዊ ነጥቦች.......


1. ገቢ/ወጪ፤
2. የቤተሰብ ብዛት፤
3. እድሜ፤
4. የሚኖሩበት አካባቢ፤
5. የምግብ አይነት፤


እንዴት ተፅዕኖ እንደሚፈጥሩ

በዝርዝር ቀርቧል።
1.5K viewsWasyhun Belay, 16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ