Get Mystery Box with random crypto!

የአንዱ ሴክተር ወይም ሀገር መዳከም አልያም መነቃቃት ለሌላው ሴክተር ወይም ሀገር ላይ ያለው ቀጥተ | The Ethiopian Economist View

የአንዱ ሴክተር ወይም ሀገር መዳከም አልያም መነቃቃት ለሌላው ሴክተር ወይም ሀገር ላይ ያለው ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ ተጽኖ/Spillover Effect ይባላል፡፡ በተለምዶ Spillover Effect ለአሉታዊ ተጽኖ (Negative Spillover Effect) መግለጫ ሆኖ የሚቀርብ ቢሆንም ለአዎንታዊ ተጽኖም (Positive Spillover Effect) መገለጫ ይሆናል፡፡

#ለምሳሌ፡- ራሽያ እና ዩክሬን በዓለም ገበያ ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ጦርነት ውስጥ በመግባታቸው እና ማዕቀብ ውስጥ በመግባታቸው በዓለም ውስጥ ያላቸው ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ በመቀነሱ በዋናነት ሰፊ የንግድ አጋርነት ያላቸው ሀገራት ተጽኖ ውስጥ ገብተዋል፡፡ የዚህ አይነቱ ሁኔታ ሌሎች ሀገራት በሁለቱ ሀገራት ጦርነት ምክንያት Negative Spillover Effect ደረሰባቸው ይባላል፡፡

#ለምሳሌ፡- ራሽያ የዓለም ማዕቀብ ስለተጣለባት ህንድን አጋር ሀገር በማለት በርካሽ ነዳጅ ብታቀርብላት እና የህንድ ኢኮኖሚ መነቃቃት ቢያሳይ በራሽያ ጦርነት ሰበብ ህንድ Positive Spillover Effect ደረሰባት ሊባል ይችላል (ናይጄሪያ ጦርነቱን ተከትሎ የነዳጅ ገበያዋ ደርቷል ይህም በተመሳሳይ አወንታዊ ተጽኖ ሊባል ይችላል!)፡፡

ቀጥተኛ የትርፍም ሆነ የኪሳራ ተካፋይ የማይሆን ነገር ግን ተዘዋዋሪ ተጽኖ የሚጋሩ የኢኮኖሚ ክፍሎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ #ለምሳሌ፡- ራሽያ እና ዩክሬን ጦርነት ውስጥ መግባታቸውን መሰረት በማድረግ ራሽያ ላይ ማዕቀብ በመጣሉ በሶስተኛ ሀገራት ላይ የሚፈጠር ከራሽያ መሸመት ያለመቻል ችግር Externalities Spillover Effect ሊባል ይችላል፡፡

#ለምሳሌ፡- የአትክልት ማሳዎች ምርታምነት ቢሻሻል ለአግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ አወንታዊ ተጽኖ ሊፈጠርለት ይችላል፤ አፋር ክልል ችግር ውስጥ ቢገባ ሌላው ክልል በጨው አቅርቦት እጥረት አሉታዊ ተጽኖ ሊፈጠርበት ይችላል፤ በሀገር ውስጥ ለቻይና ተቋራጭ ፕሮጀክት መስጠት የእውቀት ሽግግር ቢፈጠር አዎንታዊ ተጽኖ ሊፈጠር ይችላል፤ የሶሻል ሚዲያ መምጣት ለጥቂቶች ገንዘብ መስሪያ ለብዙዎች የወጪ ምክንያት ሆኗል! ወዘተ ማለት ነው፡፡

በዚህ ወቅት የዓለም ሀገራት ኢኮኖሚ በጣም የተሳሰረ ከመሆኑ የተነሳ የአንዱ ሀገር ኢኮኖሚያዊ መቀዛቀዝም ሆነ በፍጥነት ማደግ ሌሎች ሀገራት ላይ ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ተጽኖ መፍጠሩ አይቀርም ይሁ ሁሉ Spillover Effect ይባላል፡፡