Get Mystery Box with random crypto!

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቂያ ወቅት ማለትም 1944 የዓለማችን 40 ሀገራት 730 ተወካዮቻ | The Ethiopian Economist View

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቂያ ወቅት ማለትም 1944 የዓለማችን 40 ሀገራት 730 ተወካዮቻቸውን በመላክ አሜሪካ ውስጥ የወርቅ ክምችትን እንደ ጠንካራ የዓለም የምንዛሬ ተመን ለመጠቀም ሶስት ሳምንታት የፈጀ ውይይት በማድረግ ስምምነት ላይ ደረሱ ስምምነቱ በአካባቢው ስያሜ Bretton Woods Agreement ይባላል፡፡


የምንዛሬ ተመኑ ዓላማ በፉክክር ምክንያት የሚፈጠር የገንዘብን የመግዛት አቅም የማዳከም አደጋን የመቀነስ እና ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገትን የመፍጠር ነበር፡፡ ዋናዎቹ የስምምነቱ ተዋናዮች አሜሪካ፤ ካናዳ፤ የምዕራብ አውሮፓ ሀገራት፤ አውስትራሊያ እና ጃፓንን የያዘ ነበር፡፡


ወርቅን እንደ ጠንካራ የዓለም የምንዛሬ ተመን የመጠቀም ስምምነት ሁለት ጠንካራ የዓለም ተቋማትን ፈጠረ እነሱም ምንዛሬን ለመቆጣጠር እና ገንዘብ ነክ የአስተዳደር ድጋፎችን ለማድረግ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የልማት ብድር እና ድጋፍ ለማድረግ የዓለም ባንክ (World Bank) ናቸው (ሁለቱ ዓለም አቀፍ ተቋማት እስከ አሁን ድረስ 190 አባል ሃገራትን ይዘው ቀጥለዋል)፡፡


የዚህ ስምምነት የረጅም ዓመታት አጠንጣኞች ታዋቂው እንግሊዛዊው ኢኮኖሚስት ጆን ሜይራንድ ኬይነስ ከአሜሪካዊው ኢኮኖሚስት ሃሪ ዲክሰር ጋር በመሆን ነበር፡፡


የጆን ሜይራንድ ኬይነስ ዓላማ ለዓለም ጠንካራ ማዕከላዊ ባንክ (የታሰበው መጠሪያ Clearing Union ነበር) ለመፍጠር እና ጠንካራ የዓለም መገበያያ ገንዘብ (የታሰበው መጠሪያ Bancor ነበር) ለመፍጠር ነበር፡፡ ነገር ግን አሜሪካዊው ኢኮኖሚስት በወቅቱ ጠንካራ የነበረው የአሜሪካ ዶላር እንዲመረጥ ሃሳብ በማቅረቡ አዲሱ ብር ሳይሳካ ቀረ፡፡


ወርቅን መገበያያ ምንዛሬ አድርጎ የመጠቀሙ ስምምነት በተግባር ከባድ ስለነበር እስከ 1958 በአግባቡ ለመተግበር አልቻለም! ነገር ግን 28 ግራም ወርቅ የ35 ዶላር ዋጋ እዲኖረው ወስነው ሲመነዝሩ ነበር፡፡ አካሄዱ ሌሎች ሃገራት ዶላር ለማግኘት ወርቅ የመሰብሰብ ግዴታ ውስጥ ሲገቡ አሜሪካ በዶላሯ ወርቅ የመሰብሰብ እድል አግኝታ ነበር፡፡


ሁኔታው የተለወጠው በ1971 በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ኒክሰን አሜሪካ ዶላርን በወርቅ መተመን እንደማትፈልግ በመግለጻቸው ወርቅን መገበያያ ምንዛሬ አድርጎ የመጠቀሙ ስምምነት ከተቋቋመ ከ20ዓመታት በኋላ ፈረሰ፡፡ በወቅቱ ሀገራት ጠንካራ ዓለም አቀፍ ገንዘብ ለመፍጠር የነበራቸው ህልም በመክሸፉ በወቅቱ ጠንካራ የነበረውን የአሜሪካ ዶላር እንደ ዓለም አቀፍ መገበያያ ተመን አድርገው መውሰድ ጀመሩ፡፡ እስካሁንም ዶላር ዓለምን ዘዋሪ ሆኖ ዘልቋል፡፡