Get Mystery Box with random crypto!

#ጤነኛ_መግለጫ_ነው? የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ፦ 'በመዲናዋ የመንግሥት ሠራተኞችን #የኑሮ_ | The Ethiopian Economist View

#ጤነኛ_መግለጫ_ነው?

የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ፦ "በመዲናዋ የመንግሥት ሠራተኞችን #የኑሮ_ውድነት_ጫና ለማቃለል 6 ነጥብ 8 ሚሊየን ሊትር ዘይት እና 3 ሺህ 500 ኩንታል ስኳር በተያዘው ሰኔ ወር ስርጭት ለማካሄድ ታቅዷል"፡፡ የሚል ዜና አየሁ!


የእውነት የዚህ አይነት መግለጫ የኑሮ ውድነት ትርጓሜን ካለመረዳት የሚነሳ መሆን አለበት እንጂ ለአንድ ወር በሸማቾች ዋጋ #በኮታ ዘይት እና ስኳር ማቅረብ እንደ ኑሮ ውድነት ጫና ማቃላያ መጋነኑ ልክ አይመስልም።

#ለምሳሌ፦ የአንድ ኪሎ ስኳር ዋጋም 42 ብር ከ16 ሳንቲም እንደሆነ መረጃው ያመላክታል፡፡


በሸማቾች በኩል ምርቶችን ለመንግሥት ሰራተኛው ማቅረብ መጥፎ አይደለም ነገር ግን ጊዚያዊ (Nominal) ድጋፍን እንደ ኑሮ ጫና የማቃለል እርምጃ ማቅረብ የኑሮ ውድነት ትርጓሜን ያቀጭጫል።