Get Mystery Box with random crypto!

በርካታ ሰዎችን መንግስት የሚያቀርበውን #የዋጋ_ንረት ቁጥር እንደሚያምኑ ስጠይቃቸው፡ ሁሉም በተመሳ | The Ethiopian Economist View

በርካታ ሰዎችን መንግስት የሚያቀርበውን #የዋጋ_ንረት ቁጥር እንደሚያምኑ ስጠይቃቸው፡ ሁሉም በተመሳሳይ ገበያ ውስጥ የሚገጥማቸው የዋጋ ግነት እና መንግስት የእቃ ዋጋ 36% ነው የጨመረው የሚለው አይታመንም አሉኝ።


እርግጥ የመንግስት ወራዊ እና አመታዊ የዋጋ ንረት ቁጥሮች በማህበረሰብ እይታ አጠራጣሪ የሚሆኑበትን አሳማኝ አመክንዬ ልንገራችሁ።


1. የዜጎች የሸመታ አይነት መረጃ የቆየ መሆን። ሃገራት ከ3 እስከ 5 ዓመት የተወሰኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ናሙና በመውሰድ በአብዛኛው ሰዎች ምን ምን በብዛት እንደሚሸምቱ (Household consumption survey) መረጃ ይሰበሰባል። ስለዚህ የዛሬ አምስት አመት በቤተሰቦች የሚዘወተር ሸመታ ዘንድሮ እንደቀጠለ ያስባል።


በተመሳሳይ የዛሬ ከ3 እስከ 5 ዓመት አንድ ቤተሰብ ለወራዊ እና አመታዊ ለፍጆታ የሚያወጣው ወጪ (Households expenditure survay) ዘንድሮም እኩል እንደሆነ ያስባል።


#ለምሳሌ፦ የዘንድሮ ዋጋን ለማነፃፀር የዛሬ 5 ዓመቱን መነሻ (Base year) አድርጎ መውሰድ ማለት ነው።


#ለምሳሌ፦ የዛሬ 5 ዓመት ስጋ በቤተሰብ ደረጃ በተደጋጋሚ የሚሸመት ከሆነ ትልቅ የወጪ ክብደት (Weight) የተሰጠ ቢሆን እና አሁን ላይ በወር አንዴም ስጋ ለማይገዛ ቤተሰብ ስጋ ትልቅ ክብደት ተሰጥቶ ቁጥሩ ይሰላል።


በተመሳሳይ የወጪም ሆነ የሸመታ ዝርዝር ተሰብስቦ የሚቀርበው አማካይ ቁጥር ከጎንደር ጥግ እስከ ጂግጂጋ ጥግ ተመሳሳይ ተደርጎ መቅረቡ በየቦታው ልዩነት ቁጥሩ ያወዛግባል።


2. የዋጋ ንረት ዓመቱን ሙሉ የተለዋወጠ ዋጋን ሲወስድ የሚሰበሰበው ዋጋ ከ150 በላይ ቁሶችን ጨፍልቆ ስለሚያሰላ የቀነሰውንም እጥፍ የጨመረውን ጠቅልሎ ስለሚይዝ ሰዎች በተደጋጋሚ የሚፈልጓቸው ቁሶች ዋጋ እጥፍ ቢጨምሩም የ150 ቁስ አማካይ ሲሰራ ቁጥሩ አይዋጥም።


#ለምሳሌ፦ አንድ ቤተሰብ ዋናው ወጪው የቤት ኪራይ፤ ጤፍ፤ ዘይት፤ ሽንኩርት፤ ቲማቲም፤ ወዘተ ተሰብስበው ዋና ዋናዎቹ 10 ሊሆኑ ይችላሉ! እነዚህ 10 አስቤዛዎች ከአምናው ሁሉም 100% ዋጋቸው ቢጨምር ይህንን ቤተሰብ የሸቀጦች ዋጋ ንረት በ36% የጨመረው ቢባል ሊቀበል ይችላል?


#ለምሳሌ፦ በኢትዮጵያ ከጠቅላላ የዋጋ ንረት ድርሻ ውስጥ 56% ከምግብ ነክ የሚነሳ ሲሆን 44% ምግብ ካልሆኑ ቁሶች ይነሳል።


ተወደደም ተጠላም ዓለም የዋጋ ንረትን ለማስላት የሚመራበት ስሌት ከላይ ባስቀመጥኳቸው መርሆዎች ነው።


አንዳንድ ሀገራት የሸመታ እና የወጪ መረጃን ከ3-5 ከመጠበቅ በየዓመቱ እንዲሆን ያደርጋሉ። በተመሳሳይ የዋጋ ንረት አሃዙን በየከተሞቹ በመሰነጣጠቅ ያቀርባሉ።


#ለምሳሌ፦ በኢትዮጵያ አንዳንድ ክልሎች ከአዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተሞች በላይ ዋጋ ንረት እንዳለባቸው የCSA ሪፖርት ያሳያል።


የዋጋ ንረት ሲሰላ ቁጥሩን ፖለቲካሊ መነካካት ሊኖር ይችል ይሆናል! ነገር ግን የስሌት አካሄዱ በተለይ የመሰረታዊ ቁሶች ዋጋ ከፍተኛ በሆነበት ወቅት ቁጥሩ ብዙዎችን አያሳምንም።