Get Mystery Box with random crypto!

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

የቴሌግራም ቻናል አርማ wahidcom — ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
የቴሌግራም ቻናል አርማ wahidcom — ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
የሰርጥ አድራሻ: @wahidcom
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.43K
የሰርጥ መግለጫ

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-05-02 00:15:27 ዕቅበተ ኢሥላም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥125 ወደ ጌታህ መንገድ በጥበብ እና በመልካም ግሳጼ ጥራ፡፡ ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ

"ደዕዋህ” دَعْوَة የሚለው ቃል “ደዓ” دَعَا ማለትም “ጠራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጥሪ” ማለት ነው። ይህ ጥሪ ወደ አሏህ ሲሆን ሰዎች አሏህን ብቻ እንዲያመልኩ እና በእርሱ ላይ ማንንምና ምንንም ነገር እንዳያጋሩ በማስተማር ወደ አሏህ መጣራት “ደዕዋህ” دَعْوَة ይባላል፦
16፥125 ወደ ጌታህ መንገድ በጥበብ እና በመልካም ግሳጼ ጥራ፡፡ ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ

"ደፋዒያህ" دَفَاعِيَّة የሚለው ቃል "ዳፈዐ" دَافَعَ ማለትም "መከተ" "ዐቀበ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ምከታ" "ዕቅበት" ማለት ነው፥ "ደፋዒየቱል ኢሥላም" دَفَاعِيَّة الإِسْلَام ማለት "መካቴ ኢሥላም" "ዕቅበተ ኢሥላም"Islamic apologetics" ማለት ነው።
ዕቅበተ ኢሥላም ሦስት እረድፍ አለው፦
1ኛ. አውንታዊ ትምህርት"affirmative teaching"
የኢሥላምን መልእክት ለሌሎች ማስተላለፍ፣
2ኛ. የመከላከል ትምህርት"defensive teaching"
በኢሥላም ላይ የሚሰነዘሩ ትችት መልስ መስጠት፣
3ኛ. የማጥቃት ትምህርት"offensive teaching"
የሌላ እምነት ተከታዮችን የሚያምኑበትን ነገር በማነጻጸር እውነትን መግለጥ እና ሐሰትን ማጋለጥ ነው።

ከዚህ ተነስተን ወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" የዕቅበተ ኢሥላም ሥራ ከዐማርኛ ባሻገር፦
፨በኦሮምኛ፣
፨በትግሪኛ፣
፨በጉራጊኛ፣
፨በአፋሪኛ፣
፨በሱማሊኛ፣
፨በሲዳምኛ፣
፨በስልጥኛ፣
፨በሀላቢኛ፣
፨በከንባትኛ፣
፨በወላይትኛ፣
፨በኮንሴኛ፣
፨በሀዲይኛ ለመሥራት አስበናል። ኢንሻሏህ!
ይህንን ግምት ውስጥ አስገብታችሁ ከዐማርኛ ወደ ገዛ ቋንቋችሁ የመተርጎም ክህሎት ያላችሁ ልጆች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አድሚናት በውስጥ ያነጋግሩ፦
እኅት ረምላን፦ https://t.me/REMLANEG
እኅት ሰላምን፦ http://t.me/SeuweSe
አኅት ዘሃራን፦ https://t.me/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦ http://t.me/temariwalji
እኅት ነስርያን፦ https://t.me/Nesriyaaa

ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ!

ከማኅበሩ ድኅረ ምሩቃን እና የቦርድ
5.6K views21:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 22:17:01 ጭራሽ አዳም ላይ ያሉ የአካል ክፍሎች ሁሉ ሥላሴ ላይ እንዳሉ እና በተጠቃሽነት ራስ፣ ፊት፣ ጆሮዎች፣ ዓይኖች፣ አፍንጫ፣ ከንፈር፣ እጆች፣ እግሮች እና ብብቶች እንዳሉት መጽሐፈ ሜላድ በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ አስቀምጦታል፦
መጽሐፈ ሜላድ ዘወርኃ ግንቦት ቁጥር 7
በአዳም ላይ ያለው መልክ ሁሉ በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ላይ አለ፥ ራስም ቢሆን፣ ገጽ(ፊት) ቢሆን፣ ጆሮዎች እና ዓይኖች ቢሆኑም፣ አፍንጫ እና ከንፈር ቢሆን፣ እጆች እና እግሮች፣ ብብቶች ቢሆኑ ከአብ፣ ለወልድ እና ለመንፈስ ቅዱስ ሙሉ አካል አላቸው። ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ሊቃውንት አባቶቻችን እንደተናገሩት ለእግዚአብሔር ዓይኖች፣ ጆሮዎች፣ እጆች እና እግሮች ሌሎች የቀሩት አካላት እንዳሉት እናምናለን።

መልአክ ሥላሴ የተባለው የኦርቶዶክስ መጽሐፍ ሥላሴ "ደም" "ወርች" "ጎን" "ከርስ" "ኩላሊት" "ወገብ" "አብራክ" "ተረከዝ" "ጫማ" "ጥፍር" "ጣት" እንዳላቸው ይናገራል፦
"ደም"
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ! "ስርየተ ደማችሁ" ስርየተ ኃጢኣት ነውና የነፍሴን ቤት መቃን በስርየት "ደማችሁ" እርጩት።

"ወርች"
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የአዳምን ወርች ላጸና መለኮታዊ "ወርቾቻችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ጎን"
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የወርቅ አስፈላጊያቸው ላይደለ መለኮታዊ "ጎኖቻችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ከርስ"
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የፍጡራንን ሆድ ለፈጠረ ለማይመረመር "ከርሳችሁ" ሰላምታ ይገባል።”

"ኩላሊት"
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! በህላዌ አካል ትክክል ለሚሆኑ "ኩላሊታችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ወገብ"
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! መታጠቂያው የቸርነት ሰቅ ለሆነው "ወገባችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"አብራክ"
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የፍጥረት ሁሉ አብራክ ለሚያሰግድ "አብራካችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ተረከዝ"
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ብርሃናት ለተጎናፀፈው "ተረከዛችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ጫማ"
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ለሚራመድ "ጫማችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ጥፍር"
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! "ከጥፍሮቻችሁ" ጋር ያለመነጣጠል ተባብረው ተመሳስለው ላሉ "ጣቶቻችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ወርች" ማለት ለከብት "የፊት እግር" ሲሆን ለሰው "ባት" ነው፣ "ከርስ" ማለት "ማኅፀን" ወይም "ሆድ" ማለት ነው፣ "አብራክ" ማለት ተራክቦ የሚደረግበት "የዘር ከረጢት ነው። "ደም" እና "ኩላሊት" ሥጋ ነው፥ ሌሎቹ ይሁኑ እሺ! "ከርስ" ምን ያረግላቸዋል? ምግብ ይበላሉ ወይስ ያረግዛሉ? "አብራክ" ምን ያረግላቸዋል? ተራክቦ ያረጋሉ? የእኛን ዓሣ ስትጎረጉሩ የእናንተን ዘንዶ አወጣንባችሁ።
አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
6.7K views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 22:16:19 የእግዚአብሔር አካል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

42፥11 የሚመስለው ምንም "ነገር" የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

አምላካችን አሏህ ከፍጡራኑ ጋር የማይመሳሰል የራሱ ባሕርያት አሉት፥ እርሱን የሚመስል ምንም ነገር የለም፦
42፥11 የሚመስለው ምንም "ነገር" የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሚስል" مِثْل በሚለው ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የገባው "ከ" كَ የሚል መስተዋድድ "በጭራሽ" ማለት ነው፥ "ነገር" በሚለው ቃል ውስጥ ሁሉም ፍጡራን የሚካተቱ ሲሆኑ ከፍጡራን መካከል እርሱን የሚመስል ብጤ በጭራሽ የለም። እዚሁ አንቀጽ ላይ አሏህ "ሰሚ እና ተመልካች" እንደሆነ ተገልጿል፥ ሰውም "ሰሚ እና ተመልካች" እንደሆነ ሌላ አንቀጽ ላይ ተገልጿል፦
76፥2 እኛ ሰውን በሕግ ግዳጅ የምንፈትነው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ ሰሚ ተመልካችም አደረግነው*፡፡ إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا

የአሏህ መስማት እና ማየት ከፍጡራን ጋር እንደማይመሳሰል እና እንደማይነጻጸር ሁሉ የፈጣሪ ባሕርዮት ከፍጡራን ባሕርዮት ጋር አይመሳሰለም አይነጻጸርም።
በኢሥላም ያለውን የአሏህ ሲፋት በመጠኑ እዚህ ድረስ ካየን ዘንዳ በባይብል እግዚአብሔር የአካል ክፍል የሆኑት ከንፈር እና ምላስ አለው፦
ኢሳይያስ 30፥27 "ከንፈሮቹም" ቍጣን የሞሉ ናቸው፥ "ምላሱም" እንደምትበላ እሳት ናት።

"ከንፈሮች" የሚለው "ከንፈር" ለሚል ብዙ ቁጥር ሲሆን የላይኛው ከንፈር እና የታችኛው ከንፈር ያመለክታል፥ ምላስ ግን በነጠላ ስለሆነ አንድ ብቻ ይመስላል። "ባት" ሲባል ደንግጠህ "የግድ ሥጋ መሆን አለበት" ካልክ ከንፈር እና ምላስ የግድ ሥጋ መሆን አለበት ብዬ እሞግትካለው፥ በሰፈሩት ቁና መሰፈር ግድ ነውና። እግዚአብሔር የአካል ክፍሎች የሆኑት ዓይኖች፣ ቅንድቦች እና ጆሮዎች አሉት፦
መዝሙር 11፥4 "ዓይኖቹ" ወደ ድሃ ይመለከታሉ፥ "ቅንድቦቹም" የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
1 ጴጥሮስ 3፥12 የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ "ጆሮዎቹም" ለጸሎታቸው ተከፍተዋል።

"ዓይኖች" "ቅንድቦች" እና "ጆሮዎች" የተባሉት "ዓይን" "ቅንድብ" "ጆሮ" ለሚሉት ብዙ ቁጥር ስለሆነ ቢያንስ ከአንድ በላይ ዓይኖች፣ ቅንድቦች እና ጆሮዎች አሉት፥ ሰው ላይ ያየሁት ዓይኖች፣ ቅንድቦች እና ጆሮዎች ሥጋ ስለሆኑ "የእግዚአብሔር ዓይኖች፣ ቅንድቦች እና ጆሮዎች ሥጋ ናቸው" ብዬ ደረቅ ንትርክ መነታረክ አላቃተኝም። እግዚአብሔር የአካል ክፍሎች የሆኑት አፍንጫ እና አፍ አሉት፦
ዘጸአት 15፥8 "በአፍንጫህ" እስትንፋስ ውኆች ተከመሩ።
መዝሙር 33፥6 ሠራዊታቸውም ሁሉ "በአፉ" እስትንፋስ።

ሰው የሚተነፍስበት አፍንጫ እና አፍ ሥጋ ስለሆነ "እግዚአብሔር የሚተነፍስበት አፍንጫ እና አፍ ሥጋ ነው" ብዬ ጉንጭ አልፋ ንትርክ መነታረክ አላቃተኝም። እግዚአብሔር የአካል ክፍሎች የሆኑት ክንድ፣ ብብት፣ እግሮች፣ እጆች፣ ጣቶች አሉት፦
ኢሳይያስ 40፥11 ጠቦቶቹን "በክንዱ" ሰብስቦ "በብብቱ" ይሸከማል።
መዝሙር 132፥7 "እግሮቹ" በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን።
መዝሙር 119፥73 "እጆችህ" ሠሩኝ አበጃጁኝም።
መዝሙር 8፥3 "የጣቶችህን" ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥

ባሻዬ እኔ የማውቀው ክንድ፣ ብብት፣ እግሮች፣ እጆች፣ ጣቶች ሥጋ ናቸው፥ እና እግዚአብሔር ልክ እንደ ሰው ክንድ፣ ብብት፣ እግሮች፣ እጆች፣ ጣቶች አሉትን? "አይ ክንድ፣ ብብት፣ እግሮች፣ እጆች፣ ጣቶች፣ አፍንጫ፣ አፍ፣ ዓይኖች፣ ቅንድቦች፣ ጆሮዎች፣ ምላስ፣ ከንፈሮች ትርጉም አላቸው" ካላችሁ በጥቅስ መሞገት እንጂ ከኪስ እየመዘዙ እንቶ ፈንቶ ማውራት ውኃ የማያነሳ እና የማይቋጥር ሙግት ነው። ምክንያቱም እነዚህ የአካል ክፍሎች ትርጉም መስጠት ሠለስቱ ምዕት ከልክለዋል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 19 ቁጥር 33
“ለእግዚአብሔር ዓይኖች እና ጆሮዎች እንዳሉት መጽሐፍት የተናገሩት እና የቀሩት እንዳሉት ስለ እግዚአብሔር የተነገረው ሁሉ የታመነ እውነተኛ እንደሆነ እናምናለን፥ ነገር ግን አይመረመርም አይታሰብም”።

"ሠለስቱ ምዕት" ማለት በ 325 ድኅረ ልደት በኒቂያ ጉባኤ የተሰበሰቡት 318 ሊቃውንት ናቸው፥ እነርሱ፦ "የቀሩት" ያሉት ከዓይኖች እና ከጆሮዎች ሌላ የተገለጹትን የአካል ክፍሎች ነው፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 28 ቁጥር 30
“ለእግዚአብሔር ዓይን፣ ጆሮ፣ እጅ፣ እግር እንዳለው የተነገረው ሁሉ ስለ እግዚአብሔር በከበሩ መጻሕፍት የተጻፈ ሁሉ የታመነ የተረዳ ነው፥ የተናገርነው ሁሉ አለው። ነገር ግን አይመረመርም አይታወቅም”።

እርማችሁን አውጡ! ጆሮ፣ እጅ፣ እግር እንዳለ እንቅጩን ፍርጥ አርገው ተናግረዋል። ለእግዚአብሔር እጅ፣ ጥፍር፣ እግር እንዳለው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ተናግሯል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 1 ቁጥር 62
“እግዚአብሔር እጆች እና ክንድ፣ ጥፍር እንዳለው ዕወቁ”።
5.3K views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 10:12:06
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ሙሥሊም ወንድሞቼ እና እኅቶቼ እንዲሁ ክርስቲያን ወገኖች ሰላም ብያለው!

እውን ኢየሱስ የባሕርይ አምላክ ነውን? የሚለው ይህ መጽሐፌ አዲስ አበባ በለገሃር እና በሜክሲኮ መካከል ኮሜርስ ወይም ከጃፋር መጽሐፍ መደብር በስተቀኝ "ኮሜርስ የመጽሐፍ መደብር" በሚባለው ውስጥ ይገኛል። ለበለጠ መረጃ 0920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ!

ሌሎቻችሁ ተደራሽነት እንዲኖረው በየታይም ላይናችሁ፣ በየጉሩፑ፣ በየፔጁ፣ በየቻናሉ፣ በየኮሜንቱ ሼር እና ፓስት በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!
8.3K views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 10:11:06 የባሕርይ እናት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥36 «እኔም እርስዋን እና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

የመርየም እናት፦ "እርስዋን እና ዝርያዋን" በማለቷ ዒሣ የመርየም ዘር እንደሆነ ቁርኣን አስረግጦ እና ረግጦ ያሳያል፦
3፥36 «እኔም እርስዋን እና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

"ዙሪያህ" ذُرِّيَّة ማለት "ዘር"offspring" ማለት ሲሆን "ዙሪያህ" ذُرِّيَّة በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ "ሃ" هَا የሚለው አንስታይ አገናዛቢ ተውላጠ ስም መርየምን አመላካች ስለሆነ ዒሣ የመርየም ዘር መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል። "ባሕርይ" ማለት "ምንነት" ማለት ሲሆን ለምሳሌ፦ የእኔ እናት ለእኔ የባሕርይ እናት ናት፥ ምክንያቱም የእኔ መገኛ እናቴ ስለሆነች እና እርሷን አህዬ እና መስዬ ከማንነቷ ማንነት ከምንነቷ ምንነት ወስጃለው፥ በተመሳሳይ የኢየሱስ መገኛው እናቱ ማርያም ስለሆነች ከእርሷ ምንነት ምንነት ወስዶ እና ከእርሷ ማንነት ማንነት ወስዶ ሰው ሆኗል።
ይህ ሆኖ ሳለ በዐበይት ክርስትና ኢየሱስ "ከአብ ባሕርይ ባሕርይን እንዲሁ ከአካሉ አካልን ወስዶ የተገኘ አምላክ" ተብሎ ይታመናል፦
ሃይማኖተ አበው 74፥8 "ከባሕርይ አምላክ የተገኘ የባሕርይ አምላክ"።
ሃይማኖተ አበው 70፥17 "ከአብ ባሕርይ የተገኘ አምላክ"።
ሃይማኖተ አበው 78፥8 "አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ የተወለደው ልደት የማይመረመር ነው"።
ሃይማኖተ አበው 121፥10 "ከአብ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ተወልዶ የመጣ አምላክ"።

ኢየሱስ ከአብ ተገኘ ሲባል ምን ማለት ነው? የሚለውን ጥያቄ ርዕስ እንዳያስቀይስ ሙግቱን አጥበበነው እውን ማርያም ለመለኮት የባሕርይ እናቱ ናትን? መለኮት ከማርያም ለሁለተኛ ጊዜ ተገኝቷልን? ይህንን ነጥብ እስቲ እንመልከት፦
ሃይማኖተ አበው 74፥13 "የመለኮት መገኘት ከድንግል አይደለም፥ ከአብ ከተወለደ በኃላ ለመለኮት ሁለተኛ ልደት አይሻምና"።

ስለዚህ ከማርያም ተፀንሶ የተወለደው ሰው ብቻ እና ብቻ ነው፥ ማርያም መለኮትን ከወለደች ሁለተኛ ልደት አይሆንምን? መለኮትን ካልወለደች እና መለኮት ከእርሷ ካልተገኘ የአምላክ እናት አይደለችም ማለት ነው። ወይም ማርያም ለመለኮት የጸጋ እናት እንጂ የባሕርይ እናቱ አይደለች ይሆን? ውስብስብ ትምህርት ነው፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘእሑድ ምዕራፍ 8 ቁጥር 73
"በመለኮት እናት በድንግል ማርያም"።

ማርያም ለመለኮት የባሕርይ እናቱ ናትን? መለኮትስ ለማርያም የባሕርይ ልጇ ነውን? "አዎ" ካላችሁን መለኮትነቱን አስገኝታለችን? እርሱስ መለኮትነቱ ከእርሷ ተገኝቷልን?
እሺ ይሁን እንበልና መለኮት አንድ ከሆነ ማርያም የሥላሴን መለኮት ወልዳለችን? ወይስ የወለደችው የወልድን መለኮት ብቻ ነው? የአብ እና የመንፈስ ቅዱስ መለኮትነት ካልወለደች ስንት መለኮት ሊኖር ነው? ማርያም "ቴዎቶኮስ" ናትን? "ቴዎቶኮስ" Θεοτόκος የሚለው ቃል "ቴዎስ" Θεός እና "ቶኮስ" τόκος ከሚል ሁለት ቃላት የተዋቀረ ሲሆን "ወላዲተ መለኮት" "የመለኮት ወላጅ" ማለት ነው፥ መለኮት ከእሷ ሳይገኝ እንዴት ወልዳ እናቱ ትሆናለች? በነገራችን ላይ "መለኮት" ማለት በቀላሉ "አምላክ" ማለት ነው።

የቁስጥንጥንያው ኤጲስ ቆጶስ ንስጥሮስ "ማርያም የወለደች ሰው ብቻ ነው" ብሎ ኢየሱስን ምንታዌ ከማድረግ ባሻገር ከማርያም ተፀንሶ የተወለደውን ሰው የሥላሴ አራተኛ አባል አርጎ ሲያርፈው ይህንን የሥላሴን ርባቤ "እንፈታለን" ብሎ የእስክንድርያው ኤጲስ ቆጶስ ቄርሎስ ሁለት አካላት የአብ ልጅ መለኮታዊ አካል እና የማርያም ልጅ ሰዋዊ አካል አንድ አካል ሆኑ በማለት ማርያምን "ቴዎቶኮስ" ብሏታል፦
ሃይማኖተ አበው 49፥15 "ቅድስት ሥላሴን እንዴት አራተኛ አካል ያደርጋሉ? እንዲህ ያለ የተነቀፈ ነገር ሊነገር አይገባውም"።

ንስጥሮስ እና ፕሮቴስታንት፣ የይሆዋ ምስክር፣ ሰባተኛው ቀን የመገለጣውያን ቤተክርስቲያን"The Seventh-day Adventist Church" የሚባሉ አንጃዎች "ማርያም "ኽሪስቶቶኮስ" ብቻ ናት" ብለው ያምናሉ፥ "ኽሪስቶቶኮስ" Χριστοτόκος የሚለው ቃል "ኽሪስቶስ" χρῑστός እና "ቶኮስ" τόκος ከሚል ሁለት ቃላት የተዋቀረ ሲሆን "ወላዲተ ክርስቶስ" "የክርስቶስ ወላጅ" ማለት ነው። ክርስቶስ ደግሞ የአምላክ እንጂ አምላክ አይደለም፦
1ኛ ቆሮንቶስ 3፥23 ክርስቶስ የአምላክ ነው። Χριστὸς δὲ Θεοῦ.
ሉቃስ 9፥20 እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ፦ "የአምላክ ክርስቶስ ነህ" አለ። εἶπεν δὲ αὐτοῖς Ὑμεῖς δὲ τίνα με λέγετε εἶναι; Πέτρος δὲ ἀποκριθεὶς εἶπεν Τὸν Χριστὸν τοῦ Θεοῦ.

በእርግጥም ማርያም የክርስቶስ ኢየሱስ የባሕርይ እናቱ ናት። መለኮት ግን አስገኝ እንጂ ከፍጡር ሆነ ከመለኮት የሚገኝ አይደለም፥ መለኮት መነሻ፣ ምንጭ እና መገኛ ካለው መለኮት እንዴት ይባላል? መነሻ እና ጅማሮ ያለው እኮ ፍጡር ብቻ ነው።
አምላካችን ሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
7.4K viewsedited  07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 04:34:21 የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ

በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 7ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ!

"ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በእሥልምና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ-መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው።

፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ-አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
በሥላሴ"trinity" እሳቤ፣
በነገረ-ክርስቶስ ጥናት"Christology"፣
በነገረ-ማርያም ጥናት"Mariology"፣
በነገረ-መላእክት ጥናት"angelology"፣
በነገረ-ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው።

፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
በአህሉል ኪታብ"People of the Book"፣
በመጽሐፍት"scriptures"፣
በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation"፣
በመጽሐፍት ልኬት"Standardization"፣
በባይብል ግጭት"Contradiction"፣
በኦሪት"Torah"፣
በወንጌል"Gospel" ላይ ነው።

አባሪ ኮርሶች፦
1. ሥነ-አመክንዮ"logic"
2. ሥነ-ልቦና"psychology"
3. ሥነ-ቋንቋ"linguistics" ናቸው።

ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት የቦርዱ አካላት በውስጥ ያናግሩ!
እኅት ረምላን፦https://t.me/REMLANEG
እኅት ሰላምን፦ http://t.me/SeuweSe
አኅት ዘሃራን፦ https://t.me/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦http://t.me/temariwalji
እኅት ነስርያን፦ https://t.me/Nesriyaaa

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!
ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ!
4.3K viewsedited  01:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 15:53:13 በእርግጥም "ሦስት ለሚሆን አምላክ፣ ሦስት ቅዱስ፣ ሦስት ልዑላን፣ ሦስት ጌቶች፣ ሦስት ነገሥታት፣ ሦስት ገዢዎች" ብላችሁ ካስተማራችሁ በግልጽ መድብለ አማልክታውያን ናችሁ፦
፨ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 22-23
“ሦስት ልዑላን ገዢዎች፥ ሦስት ጌቶች ናቸው”።
፨ ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 26
“ሦስት ነገሥታት አንድ አገዛዝ ናቸው”።
፨ ሰይፈ ሥላሴ ዘረቡዕ ምዕራፍ 4 ቁጥር 52
“እነዚህ ገዢዎች በገጽ ሦስት በፈቃድ አንድ ናቸው”።

"ገጽ" ማለት "ፊት" ማለት ነው፥ ባለ ሦስት ፊት አምላክ የዐረማውያን እንጂ የአብርሃም አምላክ በፍጹም አይደለም፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 24
"ሦስት ገጽ አንድ አመለካከት ናቸው"።

ሥላሴ አካላቸው የተለያዩ ከሆኑ አካላቸው አንድ ዓይነት ወይስ የተለያየ? አንድ ዓይነት ከሆነ ምን ዓይነት አንድ ዓይነት? ከተለየስ ምን ዓይነት የተለየ አካል ነው? ገጽታቸውን ሦስት አርጎ ያለያየ ምን ዓይነት ገጽታ ይሆን? "መለኮት ሦስትም አንድም ነው" ማለት የጤና አይደለም፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘቀዳሚት ምዕራፍ 7 ቁጥር 68
"ለመለኮት ሦስትነት ምስጋና ይገባል"።
ሰይፈ ሥላሴ ዘቀዳሚት ምዕራፍ 7 ቁጥር 69
"ለመለኮት አንድነት ምስጋና ይገባል"።
ገድለ ተክለ ሃይማኖት 60(61)፥12
"የመለኮት ሦስትነት መቆፈሪያ ልቡን በኮሰተረው እና በቆፈረው ጊዜ"።

በምድር ላይ ያለው እያንዳንዱ ሰው የራሱ ገጽ ያለው ሲሆን በስም፣ በአካል፣ በግብር ስምንት ቢልዮን ነው፥ ግን የሁሉም ምንነት አንድ ምንነት ስለሆነ ስምንት ቢልዮን ሰው አንድ ሰው አይባልም። ስምንት ቢልዮን ሰዎች ያሰኘው በማንነት እከሌ እየተባለ ስለሚለያይ ነው፥ አምላክ በማንነት እከሌ እየተባለ በስም፣ በአካል፣ በግብር ከተለያየ አንድ ሳይሆን ብዙ ነው። በሦስት ፊቶች የተለያየ መለኮት፣ ጌታ፣ ንጉሥ፣ አምላክ እና ፈጣሪ መድብለ አማልክት እንጂ ሌላ አይደለም፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘእሑድ ምዕራፍ 8 ቁጥር 41
"ሥስት የምትሆን ጌታዬ፣ ንጉሤ፣ አምላኬ፣ ፈጣሪዬ ሆይ! ለአዳራሽህ መብራት ለመመላለሻህም ፀሐይ አትፈልግም"።
መልክአ ሥላሴ ቁጥር 39
“ሥሉስ ቅዱስ ሆይ! የአደም እና የሔዋን "ፈጣሪዎቻቸው" እንደመሆናችሁ የምርኮኞች ነጻ አውጪ የሆነ ኃይላችሁ የጣዖታትን ሐሰተኝነት አጋለጠ"።

ሥላሴ "ፈጣሪዎች" ከተባሉ ስንት ፈጣሪ ሊኖር ነው? እነርሱም በድፍረት፦ "ኤሎሂም" ማለት "አማልክት" ማለት ነውና "አማልክት" የተባለው ሥላሴን አምልካች ነው" በማለታቸው ሥላሴ "አማልክት" መሆናቸው በግልጽ ነግረውናል። ሳያቅማሙም "ሦስት በአንድ የሆነ አምላክ"Triune God" ይሉታል፣ በአገራችን "ሥላሴ" ማለት "ሦስትነት" ማለት ነው፣ በዐረብ ክርስቲያኖች ዘንድ "ተሥሊስ" تَسْلِيث‎ ይሉታል። በፕሮቴስታንት ዘንድ ደግሞ፦ "አብ እራሱን የቻለ አእምሮ፣ ፈቃድ እና ስሜት አለው፣ ወልድ እራሱን የቻለ አእምሮ፣ ፈቃድ እና ስሜት አለው፣ መንፈስ ቅዱስ እራሱን የቻለ አእምሮ፣ ፈቃድ እና ስሜት አለው" ይላሉ፥ ይህ በኦርቶዶክስ ሦስት አማልክት ነው፦
መጽሐፈ ሜላድ 6፥38 ሦስት ልብ፣ ሦስት ቃል፣ ሦስት እስትንፋስ የሚል ግን ሦስት አማልክት አመለከ"።

"ለበወ" ማለት "አወቀ" ማለት ከሆነ ሦስቱ ማንንነቶች የየራሳቸው ዕውቀት ካላቸው እና እርስ በእርስ የሚነጋገሩ ከሆነ ሦስት ልብ ይሆናል፥ በፕሮቴስታንት ልክ እንደ አርጌናሳውያን አብ ወልድን እና መንፈስ ቅዱስን የሚገዛቸው አስተዳዳሪያቸው ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥28 አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማብራሪያ፦ "ወልድ ለአብ የሚገዛው በአስተዳደር ረገድ ሲሆን..በሥላሴ አካላት መካከል አብ የበላይ አስተዳዳሪ ነው"

እንግዲህ ሥላሴ ሰው በማመኑ የሚድንበት እና በመካዱ የሚጠፋበት አንቀጸ እምነት ቢሆን ኖሮ ነቢያት እና ሐዋርያት በግልጽ ልክ እንደ ተውሒድ ያስቀምጡልን ነበር። ነገር ግን በግልጠተ መለኮት ውስጥ የሥላሴ አሳቡ ስለሌለ «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛን ጽናቱን ይስጠን! አሚን። 

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
5.4K viewsedited  12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 15:53:01 ተሥሊስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

"መለኮት" ማለት "አምላክነት" ማለት ነው፥ "እግዚአብሔር" የሚለው ቃል ደግሞ በግሪክ "ቴዎስ" θεός ሲሆን "አምላክ"God" ማለት ነው። በጥቅሉ "መለኮት" "እግዚአብሔር" "አምላክ" ተመሳሳይ ነገር ለማሳየት የመጣ ሲሆን በሥላሴ እሳቤ፦
1. ወላዲ ማንነት አምላክ፣
2. ተወላዲ ማንነት አምላክ፣
3. ሰራጺ ማንነት አምላክ
ከሆነ ወላዲ አምላክ፣ ተወላዲ አምላክ፣ ሰራጺ አምላክ አለ ማለት ነው፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘሰኞ ምዕራፍ 2 ቁጥር 42
"በጽርሐ አርያም ለሚኖር ልዩ ሦስት ለሚሆን አምላክ ሰላምታ ይገባል"

"ልዩ ሦስት ለሚሆን አምላክ" የሚለው ይሰመርበት! "ሦስት ለሚሆን አምላክ" በግዕዙ "ሥሉስ አምላክ" ነው። ወላዲ አምላክ "አብ" ተወላዲ አምላክ እና ሰራጺ አምላክ ካልሆነ፣ ተወላዲ አምላክ "ወልድ" ወላዲ አምላክ እና ሰራጺ አምላክ ካልሆነ፣ ሰራጺ አምላክ "መንፈስ ቅዱስ" ወላዲ አምላክ እና ተወላዲ አምላክ ካልሆነ ስንት አምላክ አለ? መልሱ ሦስት አምላክ ይሆናል። ምክንያቱም ወላዲ አምላክ፣ ተወላዲ አምላክ፣ ሰራጺ አምላክ ሦስት ነው፥ እነርሱም፦ በግዕዙ "ሦሉስ አምላክ" ሲሉ ትርጉሙ "ሦስት አምላክ" ማለት ነው፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘረቡዕ ምዕራፍ 4 ቁጥር 31
“መለኮት በአካል ሦስት ሲሆን በባሕርይ አንድ ነው”።

"መለኮት በአካል ሦስት ሲሆን" የሚለው ይሰመርበት! "መለኮት በአካል ሦስት ነው" ማለት የጤንነት ነውን? አምላክ አባት(እግዚአብሔር አብ)፣ አምላክ ልጅ(እግዚአብሔር ወልድ)፣ አምላክ መንፈስ ቅዱስ(እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ) የሚባሉ በአካል ሦስት አምላክ"tritheism" ናቸው። አምላክነት ሦስቱ አካላት የሚጋሩት ባሕርይ እንጂ "ማንነት ነው" ብለው አያምኑም፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 17
"ሦስት የእሳት ባሕርይ ነገር ግን አንድ ብርሃን ነው"።

"ሦስት የእሳት ባሕርይ" የሚለው ይሰመርበት! "ሦስት የእሳት ባሕርይ" ካለ አንድ ብርሃን ሳይሆን ሦስት ብርሃናት ናቸው፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 10 ቁጥር 6
"ዕውቀትን የሚገልጹ ብርሃናት ናቸው"።

"ብርሃናት" የብርሃን ብዙ ቁጥር ነው፥ አንዱ ብርሃን አብ ሁለቱ ብርሃናትን ወልድ እና መንፈስ ቅዱስን አስገኘ ማለት የጤንነት አይደለም፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 10 ቁጥር 12
"አብ ብርሃን ነው፣ ከአብ የተወለደ ቃሉ ወልድ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው፣ እንዲሁ ከአብ የሠረፀ መንፈስ ቅዱስም ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው"።

ከአንዱ ብርሃን ከአብ ወልድ የሚባል ብርሃን በመወለድ ተገኘ እና ከአንዱ ብርሃን ከአብ መንፈስ ቅዱስ የሚባል ብርሃን በመሥረፅ ተገኘ የሚል ትምህርት በግልጽ "ሦስት ፀሐይ" ብለው አስቀምጠዋል፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘረቡዕ ምዕራፍ 4 ቁጥር 21
"ሦስት ፀሐይ አንድ ብርሃን.. ነው"።
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 21
"ሦስት የብርሃን አዕማድ በመጠን ግን..አንድ ነው"።

ዶክተር ዛኪር፣ ዶክተር ቢላል እና ዶክተር ፊሊፕ ሦስት ዶክተር እንጂ አንድ ዶክተር አይደሉም፥ ግን አንድ ዶክትሬት ይጋራሉ። በተመሳዳይ እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ እና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሦስት እግዚአብሔር እንጂ አንድ እግዚአብሔር አይደሉም፥ ግን አንድ እግዚአብሔርነትን ይጋራሉ፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘማክሰኞ ምዕራፍ 3 ቁጥር 21
"ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር ሦስት ሲሆን አንድ፥ አንድ ሲሆን ሦስት የሚሆን እርሱ አንድ ቅዱስ ነው"።

"እግዚአብሔር ሦስት ሲሆን" የሚለው ይሰመርበት! "አንድ ቅዱስ ነው" ካላችሁ በኃላ "ሥሉስ ቅዱስ" ማለትም "ሦስት ቅዱስ" ማለታችሁ የጤና ነውን? "ቅድስት ሥላሴ" ማለትም "ቅዱሶች ሦስነት" ለምን ትላላችሁ? በነገራችን ላይ "ቅድስት" የሚለው ቃል "ቅዱሳን" "ቅዱሶች" የሚለውን ለመተካት የሚጠቀሙበት ነው፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 82 ቁጥር 14
"ሥሉስ ቅዱስ ያልተፈጠሩ ናቸው"

"ሦስት ቅዱስ" "አንድ ቅዱስ" እርስ በእርሱ ይጋጫል። እንደ እናንተ ትምህርት አምላክ ከማርያም ሲወለድ የተወለደው አንዱ አምላክ ነው ወይስ ሁለተኛው ልጅ የሆነ አምላክ? አንዱ አምላክ ከሆነ አብ እና መንፈስ ቅዱስ አብረው ተወልደዋል? ምክንያቱም ማርያም የመለኮት እናት ናት ስለሚል፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘእሑድ ምዕራፍ 8 ቁጥር 73
"በመለኮት እናት በድንግል ማርያም"።

ሁለተኛው ልጅ የሆነው አምላክ ከሆነ ያልተወለዱ ሁለት አባት እና መንፈስ ቅዱስ የሆኑ አምላክ አሉን? ከማርያም የተነሳው ሥጋ መለኮትን ገንዘብ ሲያደርግ ሙሉ መለኮትን ነው ወይስ የአብ ተወላዲ መለኮትን?
ያለው አማራጭ ሦስት አምላክ ስለሆነ በግልጽ "አምላካችን ያለ መለየት ሦስት ነው" ብለው አርፈውታል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 99 ቁጥር 11
“አምላካችን ያለ መለየት ሦስት ነው”።

"ኡሲያ" οὐσία የሚለው ቃል "ሃልዎት" "ኑባሬ" "ህላዌ"essence" የሚል ትርጉም አለው፥ "በአካል ሦስት ህላዌ" ማለት የጤንነት አይደለም፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 3ር ቁጥር 22
“በአካል ሦስት "ህላዌ" በመለኮት አንድ ህላዌ ነው”።
5.1K viewsedited  12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 21:21:18 ስለ ሸዋል ይህንን ያንብቡ እና ለሌሎች ወንድሞች እና እኅቶች ሼር ያርጉ፦ https://t.me/Wahidcom/2757
1.5K viewsedited  18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 21:08:10
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ!

እንኳን የዒዱል ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ!
ተናፍቆ የሚመጣ እና ሳይጠገብ የሚሄድ ብቸኛው ወር የረመዷን ወር ነው።

አሏህ ከእኛም ከእናንተ መልካም ሥራዎችን ይቀበል! አሚን።

ዒድ ሙባረክ!
1.8K views18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ