Get Mystery Box with random crypto!

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

የቴሌግራም ቻናል አርማ wahidcom — ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
የቴሌግራም ቻናል አርማ wahidcom — ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
የሰርጥ አድራሻ: @wahidcom
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.43K
የሰርጥ መግለጫ

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-04 15:32:59 ማሞት እና መሞት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

25፥58 በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ

"የሺህ ፍልጥ ማሰሪያው አንድ ልጥ" በሚል ብሒል ተነስተን ዐላዋቂ ሳሚዎች፦ "አሏህ እንሞታለን" ብሏል" ብለው የማያውቁትን ሲለቀልቁ ምናልባት ምንተ አፍታቸውን እንዲያውቁ እና ሌላው ትምህርት እንዲያገኝበት ብለን መልስ ሰተንበታል። አሏህ ሕያው የሚያደርግ እና የሚያሞት ነው፦
15፥23 እኛም ሕያው የምናደርግ እና የምናሞት እኛው ብቻ ነን፡፡ وَإِنَّا لَنَحْنُ نُحْيِي وَنُمِيتُ
50፥43 በእርግጥ እኛው ሕያው እናደርጋለን፡፡ እናሞታለንም፡፡ መመለሻም ወደ እኛ ብቻ ነው፡፡ إِنَّا نَحْنُ نُحْيِي وَنُمِيتُ وَإِلَيْنَا الْمَصِيرُ

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "ሕያው እናደርጋለን" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው ቃል "ኑሕዪ" نُحْيِي ሲሆን ፋዒል ነው። "ፋዒል" فَاعِل ማለት "አድራጊ"active" ማለት ነው፥ በተመሳሳይ "እናሞታለን" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው ቃል "ኑሚቱ" نُمِيتُ ሲሆን "ፋዒል ነው።
"መፍዑል" مَفْعول ማለት "ተደራጊ"passive" ማለት ሲሆን "ሕያው የምንሆን" ለሚለው የግሥ መደብ የሚገባው "ነሕያ" نَحْيَا ነው፥ "የምንሞት" ለሚለው የግሥ መደብ ደግሞ "ነሙቱ" نَمُوتُ ነው፦
45፥24 አሉ፦ "እርሷም ሕይወት የቅርቢቱ ሕይወታችን እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ "እንሞታለን"፤ ሕያውም እንኾናለን"፡፡ وَقَالُوا مَا هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا الدُّنْيَا نَمُوتُ وَنَحْيَا

አሏህ፦ "ኑሚቱ" نُمِيتُ የሚለውን "ነሙቱ" نَمُوتُ አድርጎ በማጣመም ሙግት ማደራጀት እጅግ ሲበዛ ነውር ነው። ኑን ዶማህ "ኑ" نُ እና "ኑ ፈትሓህ "ነ" نَ ለይቶ ከማያውቅ እና ከማይረዳ ሰው የመጣ ጥያቄ ነው፥ ከመነሻው ጥያቄው ጥራዝ ነጠቅ ጥያቄ እንጂ ጥራዝ ጠለቅ ጥያቄ አይደለም። በባለቤት ቦታ ተሳቢ እያረጉ ማንበብ ኢብራሂም፦ "የሚያሞተኝ" የሚለውን "የማሞተው" እንዲሁ "ሕያው የሚያደርገኝ" የሚለውን "ሕያው የየማደርገው" ብሎ እንደመረዳት ነው፦
26፥81 ያም የሚያሞተኝ ከዚያም ሕያው የሚያደርገኝ ነው፡፡ وَالَّذِي يُمِيتُنِي ثُمَّ يُحْيِينِ

"ዩሕዪ" يُحْيِي እና "ዩሚቱ" يُمِيتُ በሦስተኛ መደብ ባለቤት አድራጊ ነው፥ በመጀመሪያ መደብ ባለቤት አድራጊ ደግሞ "ኑሕዪ" نُحْيِي እና "ኑሚቱ" نُمِيتُ ነው፦
36፥12 በእርግጥ እኛ ሙታንን ሕያው እናደርጋለን፡፡ إِنَّا نَحْنُ نُحْيِي الْمَوْتَىٰ

"ሙታንን" ሕያው የሚያደርግ እና "ሕያዋንን" የሚያሞት አሏህ ነው፥ እርሱ አሟች ሲሆን ፍጡራን ሟች ናቸው፦
30፥40 አላህ ያ የፈጠራችሁ፣ ከዚያም ሲሳይን የሰጣችሁ፣ ከዚያም የሚያሞታችሁ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ነው፡፡ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَكُمْ ثُمَّ رَزَقَكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ
45፥26 «አላህ ሕያው ያደርጋችኋል፤ ከዚያም ያሞታችኋል፣ ከዚያም ወደ ትንሣኤ ቀን ይሰበስባችኋል፡፡ በእርሱ ጥርጥር የለበትም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም» በላቸው፡፡ قُلِ اللَّهُ يُحْيِيكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يَجْمَعُكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

"ኩም" كُمْ የሚለው ተሳቢ ፍጡራንን የሚያመለክት ሲሆን እነርሱ የሚሞቱ እና ሕያው የሚሆኑ ናቸው፥ አሏህ ግን የሚያሞትም እና ሕያው የሚያደርግ ባለቤት እንደሆነ ከላይ ያቀረብነው የሙግት አሰላለፍ እና አሰነዛዘር ከበቂ በላይ ጉልኅ ማሳያ ነው። አሏህ በሕያውነቱ ሞት የሌለበት አምላክ ነው፦
25፥58 በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ

አፈሙዝ ከመያዝ ይልቅ አፍን ከፍቶ፦ "ያዙኝ ልቀቁኝ፥ ደግፉኝ ጣሉኝ" ለሚል በአንድ መጣጥፍ ማስተንፈስ እንዲህ ይቻላል፥ ሕሊናችሁን በመቅጠፍ እያቆሸሻችሁ መኖር ግን እንዴት አስቻላችሁ? የማይለውን እንደሚል አድርጎ ሙግት ማዋቀር እኮ ቁልመማዊ ሕፀፅ"strawman fallacy" ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
2.2K viewsedited  12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 04:56:33 አጅር ፈላጊ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥2 በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ

አሠላሙ ዐለይኩም ያ ሙሥሊሙን ወሙሥሊማት!
እንደሚታወቀው ከቤት የሚባረሩ ሠለምቴዎችን ለስድስት ወር ያክል ጊዜያዊ መቆያ ለቤት ክራይ፣ ለቀለብ እና ለትራንስፓርት የሚሆን ወጪ ወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር እና አሜሪካ መቀመጫ ያደረገው የጥሪያችን ጀመዓህ በአጋርነት ሆነው በአሳብ፣ በጉልበት እና በንዋይ እየሠሩ ይገኛል።

ያ ከመሆኑ ጋር እነዚህ ከቤት የሚባረሩት ሠለምቴዎች እራሳቸውን እንዲችሉ ለመቋቋሚያ አንዳንድ ሰዎች እነርሱን(ሠለምቴዎች) መርዳት ጀምረዋል፥ ሙሥሊም ወንድሞች እና እኅቶች ሆይ! እነዚህን ሠለምቴዎች መደበኛ ሥራ ለድርጅት ወይም ለተቋም መቅጠር እና ማስቀጠር የምትችሉ እና በቀጥታ ሠለምቴዎችን አግኝታችሁ እራሳቸውን እንዲችሉ የዘካህ ገንዘብ መስጠት የምትፈልጉ አዲስ አበባ መሬት"ground" ላይ ያሉትን ወንድሞች በቴሌ ግራም አናግሩ፦
1. ወንድም ዐብዱ ራሕማን https://t.me/Abi_Abik
2. ወንድም አቡ ኑዓይም https://t.me/arhmanu
3. ወንድም ልጅ ነጃ https://t.me/hubi1aqsua2

በተሻለ አቅም በየግሩፑ፣ በየፔጁ፣ በቤታችሁ እና በየኮሜንት መስጫ ሥር ሼር አድርጉት!

አሏህ ኸይር ሥራችሁ በኢኽላስ ይቀበላችሁ።
1.2K views01:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 13:51:15 ምንዳው ያለ ግምት የሆነው አስታራቂ ብቻ ሳይሆን ተበድሎ ይቅር ያለ ሰውም ጭምር ነው። ጀነት ከሰዎችም ይቅርባዮች ለኾኑት ተደግሳለች፦
3፥134 ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት ተደግሳለች፡፡  ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ فِى ٱلسَّرَّآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَٱلْكَٰظِمِينَ ٱلْغَيْظَ وَٱلْعَافِينَ عَنِ ٱلنَّاسِ
42፥37 ለእነዚያም የኀጢኣትን ታላላቆች እና ጠያፎችን የሚርቁ በተቆጡም ጊዜ እነርሱ ይቅር የሚሉ ለኾኑት፡፡ وَٱلَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلْإِثْمِ وَٱلْفَوَٰحِشَ وَإِذَا مَا غَضِبُوا۟ هُمْ يَغْفِرُونَ

የተጣላ ሰውም አስታራቂ መጥቶ "ታረቁ" ሲል መታረቅ አለብን፥ መታረቅ መልካም ነው። የበደለንን ይቅርታ ሲጠይቅ ይቅር ማለት አሏህ ወንጀላችንን ይቅር ይለናል፦
4፥128 መታረቅ መልካም ነው፡፡ وَالصُّلْحُ خَيْرٌ
4፥149 ደግ ነገርን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት ወይም "ከበደል ይቅርታ ብታደርጉ" አላህ ይቅር ባይ ኃያል ነው፡፡ إِن تُبْدُوا۟ خَيْرًا أَوْ تُخْفُوهُ أَوْ تَعْفُوا۟ عَن سُوٓءٍۢ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَفُوًّۭا قَدِيرًا
2፥263 መልካም ንግግር እና ይቅርባይነት ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው፡፡ አላህም ተብቃቂ ታጋሽ ነው፡፡ قَوْلٌۭ مَّعْرُوفٌۭ وَمَغْفِرَةٌ خَيْرٌۭ مِّن صَدَقَةٍۢ يَتْبَعُهَآ أَذًۭى ۗ وَٱللَّهُ غَنِىٌّ حَلِيمٌۭ

ይቅርባይነት ማስከፋት ከሚከተላት ሶደቃህ በላጭ ነው። ቂም፣ ቁርሾ እና በቀል ልብ ውስጥ ሲቀመጥ ግን የሚጎዳው በቂም ያቄምንበትን፣ በቁርሾ ያቀረሸንበት፣ በበቀል የምንበቀለውን ሰው ብቻ ሳይሆን እራሳችንንም ጭምር ነው። ቂም፣ ቁርሾ እና በቀል በልብ ውስጥ ማስቀመጥ ኪሳራ እና ጉዳት እንጂ ትርፍ እና ጥቅም የለውም፦
35፥10 እነዚያም መጥፎ ሥራዎችን የሚዶልቱ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው፡፡ የእነዚያም ተንኮል እርሱ ይጠፋል፡፡ وَٱلَّذِينَ يَمْكُرُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ لَهُمْ عَذَابٌۭ شَدِيدٌۭ ۖ وَمَكْرُ أُو۟لَٰٓئِكَ هُوَ يَبُورُ

ነገርን በማብረድ ከማስታረቅ ይልቅ በማንደድ ሰዎችን የሚያነካክሱ እና የሚያባሉ አጥፊዎች ናቸው። እነዚህ ወሬ የሚያዋስዱ ሰዎች ወንጀሉ ከፍተኛ ስለሆነ ጀነት አይገቡም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1 ሐዲስ 196
ሑዘይፋህ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቶ አስተላልፏል፦ "ነገር አዋሳጅ ጀነት አይገባም"።  فَقَالَ حُذَيْفَةُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ لاَ يَدْخُلُ الْجَنَّةَ نَمَّامٌ ‏"‏

አምላካችን አሏህ ወሬ አዋሳጆች ከመሆን ይጠብቀን! አታራቂዎች እና ይቅርባዮች ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
1.2K views10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 13:51:06 ማስታረቅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

49፥10 ምእመናን ወንድማማቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ! ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

"ኢስላሕ" إِصْلَاح የሚለው ቃል "አስለሐ" أَصْلَحَ‎ ማለትም "አስታረቀ" "አስማማ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማስታረቅ" "ማስማማት" ማለት ነው፦
4፥114 ከውይይታቸው በምጽዋት ወይም በበጎ ሥራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውስጥ ደግ ነገር የለበትም፡፡ የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ይህንን የሚሠራ ሰው ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን፡፡ لَّا خَيْرَ فِي كَثِيرٍ مِّن نَّجْوَاهُمْ إِلَّا مَنْ أَمَرَ بِصَدَقَةٍ أَوْ مَعْرُوفٍ أَوْ إِصْلَاحٍ بَيْنَ النَّاسِ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ فَسَوْفَ نُؤْتِيهِ أَجْرًا عَظِيمًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ማስታረቅ" ለሚለው የገባው ቃል "ኢሥላሕ" إِصْلَاح ሲሆን የአሏህ ውዴታ ለመፈለግ የሚያስታርቅ ሰው ታላቅ ምንዳ አለው። የማስታረቅ ምንዳ ከሶላት፣ ከሲያም እና ከሶደቃህ በላጭ ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 147
አቢ አድ-ደርዳህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከሶላት፣ ከሲያም እና ከሶደቃህ ደረጃ በላጭ ነገር አልነግራችሁምን? ሶሓባዎችም፦ "እንዴታ" አሉ። እርሳቸውም፦ "በሰዎች መካካል ማስታረቅ ነው፥ በሰዎች መካከል የሚያበላሹ(የሚያጣሉ) ግን አጥፊዎች ናቸው" አሉ"። عَنْ أَبِي الدَّرْدَاءِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ أَلاَ أُخْبِرُكُمْ بِأَفْضَلَ مِنْ دَرَجَةِ الصِّيَامِ وَالصَّلاَةِ وَالصَّدَقَةِ ‏"‏ ‏.‏ قَالُوا بَلَى ‏.‏ قَالَ ‏"‏ إِصْلاَحُ ذَاتِ الْبَيْنِ وَفَسَادُ ذَاتِ الْبَيْنِ الْحَالِقَةُ ‏"‏ ‏.‏

ማስታረቅ ብዙዎች የዘነጋነው ኸይር ሥራ ነው። ሙእሚን የሆኑ ሁለት ወንድሞቻችን ቢቀያየሙ ማስታረቅ ፈርድ ነው፦
49፥10 ምእመናን ወንድማማቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ! ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አስታርቁ" ለሚለው ትእዛዛዊ ግሥ የገባው ቃል "አስሊሑ" أَصْلِحُوا መሆኑ በራሱ ማስታረቅ ፈርድ ነው። ከወንድማማችነት በላይ ሁለት ጭፍሮች ቢጋደሉ በመካከላቸው ማስታረቅ ፈርድ ነው፦
49፥9 ከምእምናን የኾኑ ሁለት ጭፍሮች ቢጋደሉ በመካከላቸው አስታርቁ፡፡ ከሁለቱ አንደኛይቱም በሌላይቱ ላይ ወሰን ብታልፍ ያችን ወሰን የምታልፈውን ወደ አላህ ትዕዛዝ እስከምትመለስ ድረስ ተጋደሉ፡፡ وَإِن طَائِفَتَانِ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ اقْتَتَلُوا فَأَصْلِحُوا بَيْنَهُمَا ۖ فَإِن بَغَتْ إِحْدَاهُمَا عَلَى الْأُخْرَىٰ فَقَاتِلُوا الَّتِي تَبْغِي حَتَّىٰ تَفِيءَ إِلَىٰ أَمْرِ اللَّهِ

"ወሰን አትለፉ" ወደሚለው ወደ አሏህ ትእዛዝ ከተመለሱ ስናስታርቅ ሳናዳላ በፍትሕ ማስታረቅ አለብን፦
49፥9 ብትመለስም በመካከላቸው በትክክል አስታርቁ፡፡ በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና፡፡ فَإِن فَاءَتْ فَأَصْلِحُوا بَيْنَهُمَا بِالْعَدْلِ وَأَقْسِطُوا ۖ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ትክክል" ለሚለው የገባው ቃል "ዐድል" عَدْل ሲሆን በነገሩ ሁሉ በፍትሕ ማስተካከል ግዴታ ነው፥ አሏህ አስተካካዮችን ይወዳልና። ያስታረቀ ሰው አሏህ ዘንድ ምንዳው ያለ ግምት ነው፦
42፥40 ይቅርም ያለ እና ያስታረቀ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ
1.2K views10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 15:07:36 ተዋዱዕ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

22፥34 ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ

"ተዋዱዕ تَوَاضُع የሚለው ቃል "ተዋደዐ" تَوَاضَعَ ማለትም "ተናነሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መተናነስ"humility" ወይም "ትህትና"humbles" ማለት ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 135
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሶደቃህ ሀብትን አይቀንስም፣ አሏህ አንድን ሰው ይቅርታ በማለቱ ክብርን እንጂ ሌላን አይጨምርለትም፣ አሏህ ከፍ የሚደርገው ቢሆን እንጂ ለአሏህ ራሱን የሚተናነስ የለም"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَا نَقَصَتْ صَدَقَةٌ مِنْ مَالٍ وَمَا زَادَ اللَّهُ رَجُلاً بِعَفْوٍ إِلاَّ عِزًّا وَمَا تَوَاضَعَ أَحَدٌ لِلَّهِ إِلاَّ رَفَعَهُ اللَّهُ ‏"‏ ‏.‏

እዚህ ሐዲስ ላይ "የሚተናነስ" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው ቃል "ተዋደዐ" تَوَاضَعَ ሲሆን ተዋዱዕ የሌለው ልብ ላይ ነቢያችን"ﷺ" ኢሥቲዓዛ አርገዋል፦
ሡነን አን-ነሣኢ መጽሐፍ 50, ሐዲስ 15
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ከአራት ነገር በአሏህ ይጠበቁ ነበር፥ እነርሱም ከማይጠቅም ዕውቀት፣ ከማይተናነስ ልብ፣ ከማይሰማ ዱዓእ እና ከማትረካ ነፍስ ናቸው"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَتَعَوَّذُ مِنْ أَرْبَعٍ مِنْ عِلْمٍ لاَ يَنْفَعُ وَمِنْ قَلْبٍ لاَ يَخْشَعُ وَدُعَاءٍ لاَ يُسْمَعُ وَنَفْسٍ لاَ تَشْبَعُ ‏.‏

እዚህ ሐዲስ ላይ "ማይተናነስ" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው ቃል "ላ የኽሸዑ" لاَ يَخْشَعُ ሲሆን የስም መደቡ "ኹሹዕ" خُشُوع ነው፥ ኹሹዕ ያለው በሶላት ላይ የሚቆም የአሏህ ባሪያ "ኻሺዕ" خَاشِع ይባላል፦
2፥45 በትእግስት እና በሶላትም ተረዱ! እርሷም ሶላት በ-"ፈሪዎች" ላይ እንጂ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፡፡ وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ
23፥2 እነዚያ እነርሱ በሶላታቸው ውስጥ አሏህን "ፈሪዎች" የሆኑት፡፡ الَّذِينَ هُمْ فِي صَلَاتِهِمْ خَاشِعُونَ

እነዚህ አናቀጽ ላይ "ፈሪዎች" ለሚለው የገባው ቃል "ኻሺዒን" خَاشِعِين ሲሆን "ትሁታን" "ተናናሾች" "ተዋራጆች" ማለት ነው፥ ሶላት ላይ ለመቆም ቀላል የሚያደርገው ለአሏህ መተናነስን፣ መጎባደድን፣ ዝቅ ማድረግን፣ መዋረድን ነው። መተናነስ ለአሏህ ተብሎ የሚደረግ ዒባደቱል ቀልቢያ ነው፦
7፥55 ጌታችሁን "ተዋርዳችሁ" በድብቅም ለምኑት፡፡ ادْعُوا رَبَّكُمْ تَضَرُّعًا وَخُفْيَةً
2፥150 አትፍሩዋቸውም፤ ፍሩኝም። فَلَا تَخْشَوْهُمْ وَاخْشَوْنِي

አምላካችን አሏህ "ኢኽሸውኒ" خْشَوْنِي ማለቱ በራሱ መተናነስ የአምልኮ ክፍል መሆኑን ያሳያል። መተናነስ ከትህትና ወደ ልዕልና፣ ከዕርደት ወደ ዕርገት፣ ከቀንበር ወደ መንበር አሸጋግሮ ለጀነት የሚያስበስር ነው፦
22፥34 ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ
21፥90 ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ፡፡ وَكَانُوا لَنَا خَاشِعِينَ

ሌላው ለሰው የምንተናነሰው መተናነስ ትህትና ሲሆን "ኸፍድ" ነው፥ "ኸፍድ" خَفْض የሚለው ቃል "ኸፈደ" خَفَضَ ማለትም "ዝቅ አለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ዝቅታ"lowliness" ማለት ነው፦
17፥24 ለሁለቱም(ለወላጆች) ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው፡፡ وَاخْفِضْ لَهُمَا جَنَاحَ الذُّلِّ مِنَ الرَّحْمَةِ
26፥215 ከምእምናንም ለተከተሉህ ሰዎች ክንፍህን ዝቅ አድርግ፡፡ وَاخْفِضْ جَنَاحَكَ لِمَنِ اتَّبَعَكَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ

እነዚህ አናቀጽ ላይ "ዝቅ አርግ" ለሚለው የገባው ትእዛዛዊ ግሥ "ኢኽፊድ" اخْفِضْ ነው፥ ኸፍድ የተዋዱዕ ክፍል ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 123
ዒያድ ኢብኑ ሒማር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ ወደ እኔ፦ "ተናነሱ፣ አንዱ ሌላውን አይጨቁን፣ አንዱ በሌላው ላይ አይኩራ"የሚለውን ገልጧል"። عَنْ عِيَاضِ بْنِ حِمَارٍ، أَنَّهُ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ أَوْحَى إِلَىَّ أَنْ تَوَاضَعُوا حَتَّى لاَ يَبْغِيَ أَحَدٌ عَلَى أَحَدٍ وَلاَ يَفْخَرَ أَحَدٌ عَلَى أَحَدٍ ‏"‏ ‏.‏

አምላካችን አሏህ በተዋዱዕ ኻሺዒን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
1.5K views12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 19:55:01 መጥፎ ሥራ የሚያሠራን ከልብ የተቀመጠው እውነተኛ ድህነት ነው፥ መልካም ሥራ የሚያሠራን ከልብ የተቀመጠው እውነኛው ሀብት ነው። አምላካችን አሏህ የሚመለከተው ልባችንን እና ሥራችንን እንጂ ቅርጻችንን እና ገንዘባችንን አይደለም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 42
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ ወደ ቅርጻችሁ እና ገንዘባችሁ አይመለከትም፥ ነገር ግን ወደ ልባችሁ እና ሥራችሁ ይመለከታል"፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ لاَ يَنْظُرُ إِلَى صُوَرِكُمْ وَأَمْوَالِكُمْ وَلَكِنْ يَنْظُرُ إِلَى قُلُوبِكُمْ وَأَعْمَالِكُمْ ‏"‏

ልብ የምንነይትበት የኒያህ መቀመጫ ነው፥ ሥራ የሚለካው በኒያህ ስለሆነ ሥራችን የልባችን ውጤት ነው። ጽድቅ መልካም ሥነ ምግባር"ethics" ሲሆን በግልጠተ መለኮት በኩል ከሥነ መለኮት የሚመጣ ነው፥ በተቃራኒው ኃጢአት በልብህ ውስጥ የሚሸረብ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ, 45, ሐዲስ 16
አን ነዋሥ ኢብኑ ሠዕማል አል አንሷሪይ እንደተረከው፦ "እኔም "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ስለ ጽድቅ እና ኃጢአት ጠየኳቸው፥ እርሳቸውም፦ "ጽድቅ መልካም ሥነ ምግባር ነው፥ ኃጢአት በልብህ ውስጥ የሚሸረብ ነው" አሉ"። عَنِ النَّوَّاسِ بْنِ سَمْعَانَ الأَنْصَارِيِّ، قَالَ سَأَلْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنِ الْبِرِّ وَالإِثْمِ فَقَالَ ‏ "‏ الْبِرُّ حُسْنُ الْخُلُقِ وَالإِثْمُ مَا حَاكَ فِي صَدْرِكَ ‏"‏ ‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ, 45, ሐዲስ 17
አን ነዋሥ ኢብኑ ሠዕማል አል አንሷሪይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ጽድቅ መልካም ሥነ ምግባር ነው፥ ኃጢአት በነፍስ ውስጥ የሚሸረብ ነው"። عَنِ النَّوَّاسِ بْنِ سَمْعَانَ الأَنْصَارِيِّ، قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الْبِرُّ حُسْنُ الْخُلُقِ وَالإِثْمُ مَا حَاكَ فِي نَفْسِكَ ‏"‏ ‏

"ልብ" እና "ነፍስ" በአንድ ዐውድ ላይ ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ መምጣቱ በራሱ ነፍስ ውሳጣዊ ልብን ያመለክታል፥ ልብ ይህን ያክል በሰው ሕይወት ላይ አውንታዊ ሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ አለው። ጀነት ወደ አሏህ በንጹሕ ልብ ለመጣ ትቀረባለች፥ ለምሳሌ፦ ኢብራሂም ወደ ጌታው በንጹሕ ልብ የመጣ ሰው ነው፦
50፥33 አልረሕማንን በሩቁ ኾኖ ለፈራ እና "በ-ንጹሕ ልብ" ለመጣ ትቀረባለች፡፡ مَّنْ خَشِيَ الرَّحْمَـٰنَ بِالْغَيْبِ وَجَاءَ بِقَلْبٍ مُّنِيبٍ
37፥84 ወደ ጌታው "በ-ንጹሕ ልብ” በመጣ ጊዜ የኾነውን አስታውስ፡፡፡ إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
26፥89 ወደ አላህ "በ-ንጹሕ ልብ" የመጣ ሰው ቢኾን እንጂ፡፡ إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ንጹሕ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሠሊም" سَلِيم ነው፥ አንድ በኢሥላም ልቡን ሢያሠልም ልቡ ውስጥ "ሠላም" سَلَام ስላለ ልቡ ሠሊም ስትሆን እርሱ ደግሞ "ሣሊም" سَالِم‎ ይሆናል፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 17027
ዐምር ኢብኑ ዐባሣህ እንደተረከው፦ "አንድ ሰው የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ሆይ! ኢሥላም ምንድን ነው? ብሎ ጠየቀ፥ እርሳቸውም"ﷺ"፦ "ልብህን ለአሏህ ዐዘ ወጀል ማሥለም ነው" አሉት"። عَنْ عَمْرِو بْنِ عَبَسَةَ قَالَ قَالَ رَجُلٌ يَا رَسُولَ اللَّهِ مَا الْإِسْلَامُ قَالَ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنْ يُسْلِمَ قَلْبُكَ لِلَّهِ عَزَّ وَجَلَّ

አንድ ሰው ልቡን ለአሏህ ካሠለመ ጀነት ይገባል፥ ልቡን ለአሏህ ያሠለመ ሰው ከጀሀነም ይድናል፦
አል አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 260
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለው፥ እስካልሠለማችሁ ድረስ ጀነት አትገቡም"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لاَ تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ حَتَّى تُسْلِمُوا
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 12, ሐዲስ 163
ዐምር ኢብኑ አል ዓስ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሠለመ ዳነ"። عَنْ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ قَدْ أَفْلَحَ مَنْ أَسْلَمَ ‏"‏ ‏.‏

አምላካችን አሏህ በልባችን ውስጥ ያለውን እውነተኛ ሀብት እንድንጠቀም ይርዳን! በሠሊም ቀልብ ወደ እርሱ የምንመጣ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
1.2K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 19:54:38 ቀልብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

37፥84 ወደ ጌታው "በ-ንጹሕ ልብ” በመጣ ጊዜ የኾነውን አስታውስ፡፡፡ إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ

"ቀልብ" قَلْب የሚለው ቃል "ቀለበ" قَلَبَ ማለትም "ለበወ" "ኀለየ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ልብ" "ኃልዮ" ማለት ነው፥ "ልብ" የሚለው የግዕዝ ቃል "ለበወ" ማለትም "አጤነ" "አስተዋለ" "አመዛዘነ" "ዐወቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማጤኛ" "ማስተዋያ" "ማመዛዘኛ" "ማወቂያ" የሚል ፍቺ አለው። "ፉአድ" فُؤَاد ስሜትን"emotion" የያዘ የውስጥ ክፍል ሲሆን "ዐቅል" عَقْل ደግሞ አመክንዮን"intellect" የያዘ የውስጥ ክፍል ነው፥ ፉኣድን እና ዐቅልን አመዛዝኖ የሚይዝ ውሳጣዊ ክፍል "ቀልብ" قَلْب ነው። "ቁሉብ" قُلُوب ደግሞ የቀልብ ብዙ ቁጥር ሲሆን "ልቦች" ማለት ነው፦
15፥51 አላህም "በልቦቻችሁ" ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ አላህም ዐዋቂ ታጋሽ ነው፡፡ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا فِي قُلُوبِكُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَلِيمًا

"ነፍሥ" نَفْس ማለት "እራስነት"own self" ማለት ሲሆን አንፉሥ" أَنْفُس የነፍሥ ብዙ ቁጥር ነው፥ ነፍሥ በሰው ውስጥ ያለውን ልብ ለማመልከት ይመጣል፦
2፥284 በ"ነፍሶቻችሁ" ውስጥ ያለውን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት አላህ በእርሱ ይቆጣጠራችኋል"፡፡ وَإِن تُبْدُوا مَا فِي أَنفُسِكُمْ أَوْ تُخْفُوهُ يُحَاسِبْكُم بِهِ اللَّهُ ۖ

"ቁሉቢኩም" قُلُوبِكُمْ የሚለው "አንፉሢኩም" أَنفُسِكُمْ በሚል ተለዋዋጭ ከመጣ ዘንዳ ቀልብ ወይም ነፍስ ውስጥ ያለው ሀብት እውነተኛ ሀብት ሲሆን ይህም ውሳጣዊ ሀብት ነው፦
ሶሒሕ ኢብኑ ሒባን መጽሐፍ 1 ሐዲስ 3055
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሀብት በውጪ አይኖርም፥ እውነተኛ ሀብት የነፍሥ ሀብት ብቻ ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ عَنْ رَسُولِ اللهِ صَلى الله عَلَيه وسَلم أَنَّهُ قَالَ لَيْسَ الْغِنَى عَنْ ظَهْرٍ إِنَّمَا الْغِنَى غِنَى النَّفْسِ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 35
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ "ሀብት ማለት መጠነ ሰፊ ንብረት መያዝ አይደለም፥ ነገር ግን ሀብት ማለት የነፍሥ ሀብት ነው። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لَيْسَ الْغِنَى عَنْ كَثْرَةِ الْعَرَضِ، وَلَكِنَّ الْغِنَى غِنَى النَّفْسِ ‏”‌‏.‏

የውስጥ ሀብት እምነት፣ እሳቤ፣ አሳብ፣ የአስተሳሰብ ቅኝነት፣ ጥልቅ አመለካከት፣ ዕውቀት ነው፥ የውስጥ ድህነት ክህደት፣ ጭፍንነት፣ ጸለምተኝነት፣ ድንቁርና፣ መሃይምነት ነው። እውነተኛ ሀብትም ሆነ ድህነት በልብ ውስጥ ያለ ነው፦
አል-ሙዕጀመል ከቢር መጽሐፍ 4, ሐዲስ 154
አቢ ዘር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አቢ ዘር ሆይ! "የተትረፈረፈ ገንዘብ ሀብት ነው" ትላለህን? እኔም፦ "አዎ" አልኩኝ፥ እርሳቸውም፦ "የገንዘብ አለመኖር ድህነት ነው" ትላለህን? እኔም፦ "አዎ" አልኩኝ፥ እርሳቸውም ይህንን ሦስት ጊዜ ደጋገሙት። ከዚያም "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ"፦ "ሀብት በልብ ውስጥ ነው፥ ድህነትም በልብ ውስጥ ነው" አሉ"። عن أبي ذر قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَا أَبَا ذَرٍّ تَقُولُ كَثْرَةُ الْمَالِ الْغِنَى قُلْتُ نَعَمْ قَالَ تَقُولُ قِلَّةُ الْمَالِ الْفَقْرُ قُلْتُ نَعَمْ قَالَ ذَلِكَ ثَلاثًا ثُمَّ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ الْغِنَى فِي الْقَلْبِ وَالْفَقْرُ فِي الْقَلْبِ.
1.3K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 10:57:27 የተባረከ ወር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥185 የረመዷን ወር በእርሱ ውስጥ ቁርኣን ለሰዎች መሪ፣ የመመሪያ ግልጽ ማስረጃ እና ፉርቃን ሲሆን የተወረደበት ነው። شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ

አምላካችን አሏህ በቁርኣን ከተገለጹት ስሞቹ አንዱ "አል-ከሪም" الْكَرِيم ሲሆን ትርጉሙ "ቸሩ" "ለጋሱ" ማለት ነው፦
82፥6 አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ? يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ الْكَرِيمِ
27፥40 እርሱ ዘንድ ረግቶ ባየውም ጊዜ «ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው፥ የማመሰግን ወይም የምክድ መኾኔን ሊፈትነኝ ቸረልኝ፡፡ ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ነው፥ የካደም ሰው ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ ቸር ነው» አለ፡፡ فَلَمَّا رَآهُ مُسْتَقِرًّا عِندَهُ قَالَ هَـٰذَا مِن فَضْلِ رَبِّي لِيَبْلُوَنِي أَأَشْكُرُ أَمْ أَكْفُرُ ۖ وَمَن شَكَرَ فَإِنَّمَا يَشْكُرُ لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ رَبِّي غَنِيٌّ كَرِيمٌ

"ከሪም" كَرِيم የሚለው ቃል እንደየ ዐውዱ ዘርፈ ብዙ እና መጠነ ሰፊ ትርጉም አለው፥ "የተባረከ" "የተከበረ" "ቅዱስ" "ክቡር" "ብፁዕ" "ንኡድ" "ውዱስ" "ስቡህ" "እኩት" "እጹብ" የሚል ፍቺ አለው። ለምሳሌ፦ መልአኩ ጂብሪል "ከሪም" كَرِيم ተብሏል፦
81፥19 እርሱ የ-"ክቡር" መልእክተኛ ቃል ነው፡፡ إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ

እዚህ ዐውድ ላይ ጂብሪል "ክቡር" ለተባለበት የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم ሲሆን "ንኡድ"noble" ለማለት እንጂ "ለጋሽ" "ቸር" ለማለት ተፈልጎ አይደለም፥ በተመሳሳይ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ "ከሪም" كَرِيم ተብለዋል፦
69፥40 እርሱ የ-"ተከበረ" መልእክተኛ ቃል ነው፡፡ إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ

እዚህ ዐውድ ላይ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" "ክቡር" ለተባሉበት የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم ሲሆን "ንኡድ"noble" ለማለት እንጂ "ለጋሽ" "ቸር" ለማለት ተፈልጎ አይደለም። ስለዚህ አንድ ምንነት ወይም ማንነት "ከሪም" كَرِيم ስለተባለ አሏህ ከተወሰፈበትን ወስፍ ጋር ማምታታት አግባብ አይደለም። ቁርኣን "ከሪም" كَرِيم ተብሏል፦
56፥77 እርሱ "የከበረ" ቁርኣን ነው። إِنَّهُۥ لَقُرْءَانٌۭ كَرِيمٌۭ

እዚህ አንቀጽ ላይ ቁርኣን "የተከበረ" ለተባለበት የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم ሲሆን ሌላ አንቀጽ ላይ በተለዋዋጭ ቃል "ሙባረክ" مُّبَارَك ተብሏል፦
6፥155 ይህም ያወረድነው የኾነ "የተባረከ" መጽሐፍ ነው፡፡ وَهَـٰذَا كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ مُبَارَكٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ ቁርኣን "የተባረከ" ለተባለበት የገባው ቃል "ሙባረክ" مُّبَارَك ሲሆን "ሙባረክ" እና "ከሪም" የቃላት ልዩነት እንጂ የአሳብ ልዩነት የላቸውም። አትክልቶችን እና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ የሚበቅልበት ውኃ "ሙባረክ" مُّبَارَك ተብሏል፦
50፥9 ከሰማይም "ቡሩክን" ውኃ አወረድን፡፡ በእርሱም አትክልቶችን እና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ አበቀልን፡፡ وَنَزَّلْنَا مِنَ السَّمَاءِ مَاءً مُّبَارَكًا فَأَنبَتْنَا بِهِ جَنَّاتٍ وَحَبَّ الْحَصِيدِ

እዚህ አንቀጽ ላይ ውኃ "ቡሩክ(የተባረከ) ለተባለበት የገባው ቃል "ሙባረክ" مُّبَارَك ሲሆን ሌላ አንቀጽ ላይ በተለዋዋጭ ቃል "ከሪም" كَرِيم ተብሏል፦
79፥30 ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا
79፥31 ውኃን እና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ፡፡ أَخْرَجَ مِنْهَا مَاءَهَا وَمَرْعَاهَا
26፥7 ወደ ምድርም በውስጧ "ከ"መልካም" በቃይ ሁሉ ብዙን እንዳበቀልን አላዩምን?፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا إِلَى الْأَرْضِ كَمْ أَنبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍ كَرِيمٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መልካም" ለሚለው የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم እንደሆነ ልብ አድርግ! "ሙባረክ" እና "ከሪም" ተለዋዋጭ ቃላት እንደሆኑ ለመረዳት ከላይ የቀረቡት ናሙናዎች በቂ ማሳያ ናቸው። እዚህ ድረስ ከተግባባን የረመዷን ወር ቁርኣን የወረደበት ወር ነው፦
2፥185 የረመዷን ወር በእርሱ ውስጥ ቁርኣን ለሰዎች መሪ፣ የመመሪያ ግልጽ ማስረጃ እና ፉርቃን ሲሆን የተወረደበት ነው። شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ

"ፉርቃን" فُرْقَان ማለት "እውነት ከሐሰት፣ ትክክሉን ከስህተት፣ መልካሙን ከክፉ የሚለይ ሚዛን" ማለት ነው። "ሸህሩ ረመዷን" شَهْرُ رَمَضَان ማለት "የረመዳን ወር" ማለት ነው፥ "ረመዷን" رَمَضَان ደግሞ የዘጠነኛው ወር ስም ነው። "ረመዷን" የወር ስም እንጂ የጦም ስም አይደለም፥ ነገር ግን ይህ ወር ቁርኣን የተወረደበት ወር በመሆኑ "ሸህሩ ሙባረክ" شَهْرُ مُّبَارَك ማለትም "የተባረከ ወር" ተብሏል፦
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 17
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የተባረከው ወር ረመዷን መጣላችሁ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَتَاكُمْ رَمَضَانُ شَهْرٌ مُبَارَكٌ

ከዚህ አንጻር "ረመዷን ሙባረክ" رَمَضَان مُّبَارَك የሚለውን በቋንቋዬ ተርጉሜ "የተባረከ ረመዷን" ብል የቃላት ልዩነት እንጂ የአሳብ ልዩነት ከሌለው "ረመዷን ከሪም" رَمَضَان كَرِيم ሲባል "መልካም ረመዷን" "የተከበረ ረመዷን" ብል የቃላት እንጂ የአሳብ ልዩነት የለውም። "ኢማን" إِيمَان የሚለውን ቃል ቁርኣን እና ሐዲስ ውስጥ በቁናህ ታገኘዋለህ፥ ቅሉ ግን የኢማን ተለዋዋጭ ቃል "ዐቂዳህ" عَقِيدَة የሚለውን በስም መደብ ቁርኣን እና ሐዲስ ውስጥ አታገኘውም። ነገር ግን ዐቂዳህ እያልን እንማራለን እናስተምራለን፥ "ሙባረክ" እና "ከሪም" የሚለውን በዚህ ስሌት እና ሒሣብ መረዳት ይቻላል። ስለዚህ "ረመዷን ሙባረክ" رَمَضَان مُّبَارَك እና "ረመዷን ከሪም" رَمَضَان كَرِيم ተለዋዋጭ ቃላት እስከሆኑ ድረስ መርጠን መጠቀም እንችላለን።

"አሏሁ አዕለም! ይህ ሙግት የቋንቋን ሙግት ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ሙግት ነው።

"ረመዷን ከሪም" رَمَضَان كَرِيم

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
2.4K viewsedited  07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 20:31:38 የረመዷን ስጦታ

ረመዷን ሙባረክ ያ ሙሥሊሙን ወሙሥሊማት!

በ 13 አርስት የተሰደረ መጣጥፍ በረመዷን ወር እንካችሁ ብለናል። ሊንኩን በማስፈንጠር ያግኙት!

1. ሶውም
https://t.me/Wahidcom/3136

2. የጦም ትሩፋት
https://t.me/Wahidcom/3470

3. ረመዷን
https://t.me/Wahidcom/2727

4.. የረመዷን ወር
https://t.me/Wahidcom/3107

5. የክርስትና ጦም
https://t.me/Wahidcom/3176

6. የጨረቃ አቆጣጠር
https://t.me/Wahidcom/2717

7. ጨረቃ እና ኮከብ
https://t.me/Wahidcom/2360

8. የሚታሰሩ ሰይጣናት
https://t.me/Wahidcom/2724

9. ሡሑር
https://t.me/Wahidcom/2726

10. ተራዊህ
https://t.me/Wahidcom/833

11. ኢዕቲካፍ
https://t.me/Wahidcom/2286

12. ለይለቱል ቀድር
https://t.me/Wahidcom/2289

13. መሓላ እና ማካካሻው
https://t.me/Wahidcom/2336

ሁሉም ቦታ ለሁሉም ሰው እንዲዳረስ አሰራጩ!

ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ!
380 views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 09:49:09 የጦም ትሩፋት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥184 የምታውቁ ብትኾኑ መጾማችሁም ለእናንተ የበለጠ ነው። وَأَن تَصُومُوا خَيْرٌ لَّكُمْ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

"ዒባደቱል ዐመልያ" عِبَادَة العَمَلِيَّة ማለት "የገቢር አምልኮ" ማለት ነው፥ "ዐመል"عَمَل የሚለው ቃል "ዐሚለ" عَمِلَ ማለትም "ገበረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ገቢር" "ድርጊት" ማለት ነው። በድርጊት ከሚፈጸሙ አምልኮ መካከል አንዱ ጦም ነው፥ "ሶውም" صَوْم ማለት ከፈጅር እስከ መግሪብ ከምግብ እና ከመጠጥ ተከልክሎ ተቅዋእ መቀበያ ነው፦
2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጦም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፥ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

ጦም የምንጦምበትን ምክንያት ደግሞ ለማመልከት "ለዐለኩም ተተቁን" لَعَلَّكُمْ تَتَّقُون ማለትም "ተቅዋእ ታገኙ ዘንድ" ይለናል፥ የጦም ትሩፋቱ ተቅዋእ ለማግኘት ነው። አሏህን እንድናከብረውና እንድናመሰግነው ጦምን ደነገገልን፥ ጦም የምጦመው አሏህን በመጠነ ሰፊ አምልኮ ልናከብረው እና ልናመሰግነው ነው፦
2፥185 ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩት እና ታመሰግኑት ዘንድ ይህን ደነገግንላችሁ፡፡ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

“ታከብሩት እና “ታመሰግኑት” ዘንድ የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! "ተክቢር" تَكْبِير በአምልኮ "አሏሁ አክበር" اَللّٰهُ أَكْبَرْ ማለት ሲሆን “ሊቱከብሩ” َلِتُكَبِّرُوا ማለት ይህንኑ ያሳያል። "ተሽኩር" تَشْكُر በአምልኮ አሏህን የምናመሰግንበት ነው፥ አላህ “ሻኪር” شَاكِر ማለትም “ተመስጋኝ” ሲሆን ባሮቹ ደግሞ “ሸኩር” شَكُور ማለት እርሱን “አመስጋኝ” ናቸው፥ "ተሽኩሩን" تَشْكُرُون ማለቱ ይህንን ያሳያል። ጦም በኢማን እና በኢሕቲሣብ ከተጦመ ያለፈውን ኃጢአት ይቅር ያስብላል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 32, ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ረመዷንን በኢማን እና በኢሕቲሣብ የጦመ ያለፈውን ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ صَامَ رَمَضَانَ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ

"ኢሕቲሣብ" احْتِسَاب ማለት "ከአሏህ ዘንድ ትሩፋት አገኛለው" ብሎ መነየት ነው፥ ጦም ከምግብ እና ከመጠጥ መከልከል ብቻ ሳይሆን ውድቅ ንግግር እና ከመጥፎ ድርጊትም መቆጠብ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 7, ሐዲስ 52
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም መጥፎ እና ዐላዋቂ ንግግርን ያልተወ እና በዚህ የሚሠራ ምግቡን እና መጠጡን መተው አሏህ አይፈልገውም"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ مَنْ لَمْ يَدَعْ قَوْلَ الزُّورِ، وَالْجَهْلَ، وَالْعَمَلَ بِهِ، فَلاَ حَاجَةَ لِلَّهِ فِي أَنْ يَدَعَ طَعَامَهُ وَشَرَابَهُ ‏"‏ ‏.‏

ጦም በትንሳኤ ቀን ለአሏህ ባሪያ ከጀሃነም እሳት መጠለያ እና ሸፋዓህ ነው፦
ሡነን አን-ነሣኢ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 145
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ጦም ከጀሃነም እሳት መጠለያ ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الصِّيَامُ جُنَّةٌ مِنَ النَّارِ
ሚሽካቱል መሷቢሕ መጽሐፍ 7, ሐዲስ 7
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ጦም እና ቁርኣን በትንሳኤ ቀን ለአሏህ ባሪያ ያማልዳሉ። ጦምም፦ “ጌታ ሆይ! በመዓልት ምግብ እና ፍላጎትን ለከለከልኩት ላማልደው” ይላል፥ ቁርኣንም፦ “ጌታ ሆይ! በሌሊት እንቅልፍ ለከለከልኩት ላማልደው” ይላል፥ እናም ያማልዳሉ”። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ الصِّيَامُ وَالْقُرْآنُ يَشْفَعَانِ لِلْعَبْدِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ يَقُولُ الصِّيَامُ أَيْ رَبِّ مَنَعْتُهُ الطَّعَامَ وَالشَّهَوَاتِ بِالنَّهَارِ فَشَفِّعْنِي فِيهِ وَيَقُولُ الْقُرْآنُ مَنَعْتُهُ النَّوْمَ بِاللَّيْلِ فَشَفِّعْنِي فِيهِ قَالَ فَيُشَفَّعَانِ


በእርግጥ የጦም ትሩፋቱ ብዙ ነው። የጦም ምንዳ ያለ ግምት ነው፥ የጦምን አጅር አሏህ የትንሳኤ ቀን ይከፍለናል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 77, ሐዲስ 142
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" አሏህ እንዲህ አለ አሉ፦ "የአደም ልጅ ሥራው ለራሱ ነው፥ ጦም ሲቀር። ጦም ለእኔ ነው፥ ምንዳውንም እኔ እከፍለዋለው። ከጦመኛ አፍ የሚወጣ ጠረን አሏህ ዘንድ ከሚስክ ጠረን የተሻለ ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ كُلُّ عَمَلِ ابْنِ آدَمَ لَهُ، إِلاَّ الصَّوْمَ فَإِنَّهُ لِي، وَأَنَا أَجْزِي بِهِ، وَلَخَلُوفُ فَمِ الصَّائِمِ أَطْيَبُ عِنْدَ اللَّهِ مِنْ رِيحِ الْمِسْكِ ‏"‌‏.‏

"ሚሥክ" مِسْك ማለት መዓዛው የሚያውድ መልካም ጠረን ያለው ሽታ ነው፥ ከጦመኛ አፍ የሚወጣ ክርፋት ሰው ዘንድ ደስ የማይል ቢሆንም ለአሏህ ተብሎ የተደረገ አምልኮ እስከሆነ ድረስ እርሱ ዘንድ ያለው ደረጃ ከሚሥክ መዓዛ ይበልጣል። አምላካችን አሏህ በጦማቸው ከሚጠቀሙ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
1.8K viewsedited  06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ