Get Mystery Box with random crypto!

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

የቴሌግራም ቻናል አርማ wahidcom — ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
የቴሌግራም ቻናል አርማ wahidcom — ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
የሰርጥ አድራሻ: @wahidcom
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.28K
የሰርጥ መግለጫ

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-05 20:26:51 "ኢየሱስ በቀጣይ እሑድ ይመጣል"

ልደታ ቤተክርስቲያን መምህርት አስካለ በልጅነታችን ኢየሱስ፦
፨በዕለተ እሑድ
፨በእሑደ ደብረ ዘይት
፨በቀኑ 29 ቀን
፨በወሩ መጋቢት ወር
፨በዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ከገጠመ ይመጣል" ብላ አስተምራናለች።
ባሕረ አሳብን ቀምረው የአገራችን ሊቃውንት "በዘመነ ዮሐንስ፣ እሑድ በደብረ ዘይት፣ በመጋቢት 29 ቀን ይመጣል" ባሉት መሠረት እየጠበቅን ነው። ይህን ካልሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሐሰተኛ ነቢያት ተለይታ አትታይም።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
12.8K viewsedited  17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 12:14:34 ዘካህ ለሠለምቴዎች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥219 ”ምንን እንደሚመጸውቱም መጠኑን ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን መጽውቱ» በላቸው”፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ الْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ

“ዘካህ” زَكَاة ጥቅላዊ የግዴታ ምፅዋት ማለት ሲሆን የዘካህ ብዙ ቁጥር “ዘካት” زَكَوَات ሲሆን በተናጥል ዘካት በሁለት ይከፈላል፥ እነርሱም “ዘካቱል ማል” زَكَاة المَال እና “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ናቸው።
“ማል” مَال ማለት “ሀብት” ማለት ሲሆን የማል ብዙ ቁጥር ደግሞ “አምዋል” أَمْوَال ነው፥ ከተቀማጭ ሀብት ላይ ወይም ከትርፍ ላይ የሚሰጠው ዘካህ “ዘካቱል ማል” زَكَاة المَال ይባላል። በነቢያችን”ﷺ” ሸሪዓህ ግን ዘካቱል ማል ከካፒታል ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ከሁለት መቶ ዲርሀም 5% ዘካህ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ያ ማለት የዘካህ ሒሳብ በመቶ ዲርሀም 5፥2=2.5 ይሆናል፦
2፥219 ”ምንን እንደሚመጸውቱም መጠኑን ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን መጽውቱ» በላቸው”፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ الْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 18 ዐሊይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ሁለት መቶ ዲርሀም ለአንተ በሆነች ጊዜና ዓመት ከሞላች አምስት ደራሂም ይወጣል፥ በአንተ ምንም ነገር አይሆንም ሃያ ዲናር እስኪሆን ድረስ”። عَنْ عَلِيٍّ، – رضى الله عنه – عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِبَعْضِ أَوَّلِ هَذَا الْحَدِيثِ قَالَ ‏”‏ فَإِذَا كَانَتْ لَكَ مِائَتَا دِرْهَمٍ وَحَالَ عَلَيْهَا الْحَوْلُ فَفِيهَا خَمْسَةُ دَرَاهِمَ وَلَيْسَ عَلَيْكَ شَىْءٌ – يَعْنِي فِي الذَّهَبِ – حَتَّى يَكُونَ لَكَ عِشْرُونَ دِينَارًا

“ፊጥር” فِطْر ማለት “ፆም መግደፊያ” ማለት ሲሆን የፊጥር ብዙ ቁጥር ደግሞ “ፉጡር” فُطُور ነው፥ የረመዷን ፆም ማብቂያ በዓል እራሱ “ዒዱል ፊጥር” عِيدُ ٱلْفِطْر ይባላል። “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ደግሞ ለመሣኪን በዒዱል ፊጥር ቀን ለማስፈጠሪያነት የሚውል ገንዘብ ነው፥ “መሣኪን” مَسَاكِين ማለት የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ የሌላቸው “ነዳያን” ማለት ነው። “ለግው” لَّغْو ማለት “ውድቅ ንግግር” ማለት ሲሆን “ረፈስ” رَّفَث ማለት ደግሞ “ስሜት ቀስቃሽ ንግግር” ማለት ነው፥ ዘካቱል ፊጥር ለፆመኛ ውድቅ ንግግር እና ስሜት ቀስቃሽ ንግግር ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 45
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ዘካቱል ፊጥርን ለፆመኛ ለግው እና ረፈስ ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል እንዲሆን ግዴታ አድርገዋል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ فَرَضَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ زَكَاةَ الْفِطْرِ طُهْرَةً لِلصَّائِمِ مِنَ اللَّغْوِ وَالرَّفَثِ وَطُعْمَةً لِلْمَسَاكِينِ .‏

“ግዴታ አድርገዋል” ለሚለው የገባው የግስ መደብ “ፈረዶ” فَرَضَ መሆኑ በራሱ ዘካቱል ፊጥር ፈርድ መሆኑ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፥ “ፈርድ” فَرْض የሚለው ቃል እራሱ “ፈረዶ” فَرَضَ ማለትም “ግዴታ አደረገ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግዴታ” ማለት ነው።

ዘካቱል ማል ከቤት ለተባረሩ ሠለምቴዎች መቋቋሚያ መስጠት ከፈለጋችሁ እና ዘካቱል ፊጥር ለመሣኪን ሠለምቴዎች ማስፈጠሪያ መስጠት ከፈለጋችሁ ከዚህ በታች ያሉትን አድሚናት አናግሩ፦
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa

ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
13.4K viewsedited  09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-28 12:00:57 በስልጥኛ ደርሥ ተለቋል። አንብቡ፦ https://t.me/wahidcomselitiy/26
12.8K viewsedited  09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-26 12:51:21 የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ

በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 11ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ!

"ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በእሥልምና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ-መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው።

፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
በሥላሴ"trinity" እሳቤ፣
በነገረ-ክርስቶስ ጥናት"Christology"፣
በነገረ-ማርያም ጥናት"Mariology"፣
በነገረ-መላእክት ጥናት"angelology"፣
በነገረ-ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው።

፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
በአህሉል ኪታብ"People of the Book"፣
በመጽሐፍት"scriptures"፣
በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation"፣
በመጽሐፍት ልኬት"Standardization"፣
በባይብል ግጭት"Contradiction"፣
በኦሪት"Torah"፣
በወንጌል"Gospel" ላይ ነው።

አባሪ ኮርሶች፦
1. ዐቂዳህ"creed"
2. ሥነ ምግባር"ethics"
3. ሥነ አመክንዮ"logic"
4. ሥነ ልቦና"psychology"
5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው።

ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ!
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦ http://t.me/selemtewa

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
12.8K views09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-12 20:09:40 አትግደሉ ገቢር አንድ
አትግደሉ ገቢር ሁለት
አትግደሉ ገቢር ሶስት
አትግደሉ ገቢር አራት
አትግደሉ ገቢር አምስት
13.0K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-10 12:04:04 "እንፍጠር" በሚል ትምህርት ተለቋል። ፈጣሪ “እንፍጠር” ሲል ምን ማለት ነው? "እንፍጠር" ያለው ማን ነው? "እንፍጠር" ያለው ለእነማን ነው? በዚህ ዙሪያ ዳሰሳ አድርገናልና ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦



ሌሎቻችሁ ሼር አርጉት!
12.7K views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-08 12:18:33 ሰማይ እና ምድር

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

41፥11 ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ وَهِيَ دُخَانٌ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ائْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًا قَالَتَا أَتَيْنَا طَائِعِينَ

አምላካችን አሏህ ሰማይን ጭስ"gas" አርጎ ከፈጠራት በኃላ በጭስ ደረጃ እያለች ለእርሷ እና ለምድር፦ "ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ" አላቸው፥ እነርሱም፦ "ታዛዦች ኾነን መጣን" አሉ፦
41፥11 ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ وَهِيَ دُخَانٌ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ائْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًا قَالَتَا أَتَيْنَا طَائِعِينَ

አሏህ ሰማይ እና ምድርን «ኑ» ሲላቸው እነርሱም፦ «ታዛዦች ኾነን መጣን» ማለታቸው የሚያስቅ እና የሚያሳልቅ ከሆነ እንግዲያውስ ያህዌህ በባይብል ምድርን እና ሰማያትን ሲጠራቸው በአንድነት እንደሚቆሙ ይናገራል፦
ኢሳይያስ 48፥13 እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች፥ በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ። אַף־יָדִי֙ יָ֣סְדָה אֶ֔רֶץ וִֽימִינִ֖י טִפְּחָ֣ה שָׁמָ֑יִם קֹרֵ֥א אֲנִ֛י אֲלֵיהֶ֖ם יַעַמְד֥וּ יַחְדָּֽו׃

"በአንድነት" ለሚለው የገባው ቃል "የሕዳው" יַחְדָּֽו ሲሆን "አንድ ላይ"together" ማለት ነው፥ የሚጠራቸው መቼ ነው? በአንድ ላይ ሲቆሙ የሚቆሙት አየር ላይ ነው ወይስ ሥፍራ አላቸው? እንኳን ሰማይ እና ምድር ከዋክብትም ሲጠራቸው፦ "ፈጣሪያችን ወደ አንተ መጣን" ይላሉ፦
መጽሐፈ ባሮክ 3፥29(1980 ዕትም) "ይጠራቸዋል እርሱን የሚመስል ሌላ የለምና "ፈጣሪያችን ወደ አንተ መጣን" ይላሉ።
Book of Baruch 3፥35 when he calls them, they answer፦ "Here we are" they shine to delight their Creator"

"ወሒድ ይህ እኮ ፈሊጣዊ አገላለጽ"idiomatic expression" ነው" ካላችሁ እንግዲያውስ "ኢስጢላሕ" اِصْطِلَاح ማለት "ፈሊጣዊ አገላለጽ" ማለት ነውና አሏህ ሰማይ እና ምድርን «ኑ» ሲላቸው እነርሱም፦ «ታዛዦች ኾነን መጣን» ማለታቸው የሚያስቅ እና የሚያሳልቅ ነገር ሳይሆን ኢስጢላሕ ነው። ቢያንስ ቢያንስ የራሳችሁ መጽሐፍ አታነቡምን? አለዚያ እንደዚህ በሰፈራችሁት ቁና መሰፈራችሁ አይቀርም። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
14.4K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-17 11:55:57 ኡማህ ነውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥120 ኢብራሂም ለአሏህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ ሕዝብ ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِّلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

አልምጥ እና አልግጥ የሆኑ ሚሽነሪዎች፦ "ኡማህ" أُمَّة የሚለው ቃል ቁርኣን ላይ ያለ አግባብ ሁለት ቦታ ገብቷል፥ አንደኛው እንስሳትን ሕዝብ ሲል ሁለተኛው ደግሞ ኢብራሂምን ሕዝብ ይላል" እያሉ ያለ ዕውቀት ሲቦተረፉ ግርም ይላል። ሐቅን አጥልቆ እና ታጥቆ ለተነሳ ሙሥሊም ይህ አንኮላ እና እንኩቶ ትችት ከመጤፉ ነው፥ ለዚህ ቅሪላ እና አለሌ ትችት መልስ እንስጥ!
"ኡማህ" أُمَّة የሚለው ቃል "አመመ" أَمَّمَ ማለትም "ሐዘበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሕዝብ" ማለት ነው፥ የኡማህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ኡመም" أُمَم ሲሆን "ሕዝቦች" ማለት ነው፦
6፥38 ከተንቀሳቃሽም በምድር የሚኼድ በሁለት ክንፎቹ የሚበርም በራሪ መሰሎቻችሁ ሕዝቦች እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡ وَمَا مِن دَابَّةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا طَائِرٍ يَطِيرُ بِجَنَاحَيْهِ إِلَّا أُمَمٌ أَمْثَالُكُم

"ዳባህ" دَابَّة ማለት "እንስሳ" ማለት ነው፥ እንስሳት የየራሳቸው ስብስብ ስላላቸው "ሕዝቦች" ናቸው። ይህ ትችት መልስ በባይብል መሳ ለመሳ ስናየው "ሕዝብ" የሚለው የግዕዝ ቃል "ሐዘበ" ማለትም "ሰበሰበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስብስብ" ማለት ነው፥ እንስሳት እኮ "ስብስብ" አላቸው፦
ምሳሌ 30፥25 ገብረ ጕንዳን ኃይል የሌላቸው "ሕዝቦች" ናቸው። הַ֭נְּמָלִים עַ֣ם לֹא־עָ֑ז וַיָּכִ֖ינוּ בַקַּ֣יִץ לַחְמָֽם׃
ምሳሌ 30፥25 ሽኮኮዎች ያልበረቱ "ሕዝቦች ናቸው። פַנִּים עַ֣ם לֹא־עָצ֑וּם וַיָּשִׂ֖ימוּ בַסֶּ֣לַע בֵּיתָֽם׃

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "አም" עַ֣ם ማለት "ሕዝብ" ማለት ሲሆን ገብረ ጕንዳን እና ሽኮኮዎች "ሕዝብ" መባላቸው ስታነቡ ምን ይውጣችሁ ይሆን? ሁለተኛውን ትችት እስቲ እንመልከት፦
16፥120 ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ "ሕዝብ" ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِّلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ ኢብራሂም "ሕዝብ" የተባለው በመውለድ እና በመክበድ አባት፣ አያት፣ ቅድመ አያት፣ ቅም አያት፣ ቅማንት፣ ሽማት፣ ምንዥላት፣ እንጅላት፣ ፍናጅ እና ቅናጅ በመሆን መባዛቱን የሚያሳይ ነው። ይህ ትችት መልስ በባይብል መሳ ለመሳ ስናየው አብርሃም "ሕዝብ" እንደሚሆን ይናገራል፦
ዘፍጥረት 17፥6 እጅግም አበዛሃለሁ፥ "ሕዝብ" አደርግሃለሁ፥ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ። וְהִפְרֵתִ֤י אֹֽתְךָ֙ בִּמְאֹ֣ד מְאֹ֔ד וּנְתַתִּ֖יךָ לְגֹויִ֑ם וּמְלָכִ֖ים מִמְּךָ֥ יֵצֵֽאוּ׃

አብርሃም ሲወልድ እና ሲዋለድ በመብዛት ሕዝብ መሆኑን ካየን ዘንዳ ሕዝብ ከሆነ በኃላ አምላካችን አሏህ ቁርኣን ላይ "ኢብራሂም "ሕዝብ" ነበር" ቢለን እንዴት ያለ ዕውቀት ለትችት ትሮጣላችሁ? አሏህ የህዲኩም ወዩሠቢትና! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
12.7K views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-16 11:44:15 እውነተኛ እና ታላቁ አምላክ ማን ነው? በሚል ትምህርት ተለቋል። ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖች "ለኢየሱስ አምላክነት ድምዳሜ አደረሰን" ብለው ከሚጠቅሷቸው ተወዳጆች ጥቅሶች 1ኛ ዮሐንስ 5፥20 ቲቶ 2፥13 እና 2ኛ ጴጥሮስ 1፥1 ሲሆኑ ዳሰሳ በማድረግ ሞግተናል። ያድምጡና ያስደምጡ፦



ሌሎቻችሁ ሼር አርጉት!
13.1K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-25 11:17:16 እኛ ሙሥሊሞች ክርስቲያኖችን፦ ኢየሱስ "እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ" ያለበት ጥቅስ ስጡን ስንላቸው እነርሱ፦ "ኢየሱስ አልፋ እና ዖሜጋ ነኝ" ብሏል ብለው ይመልሳሉ፥ እውን "አልፋ እና ዖሜጋ ነኝ" የሚለው ማን ነው? ኢየሱስ ወይስ የኢየሱስ አምላክ? ያድምጡና ያስደምጡ፦

12.7K views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ