Get Mystery Box with random crypto!

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

የቴሌግራም ቻናል አርማ wahidcom — ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
የቴሌግራም ቻናል አርማ wahidcom — ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
የሰርጥ አድራሻ: @wahidcom
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.43K
የሰርጥ መግለጫ

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-11-25 11:17:16 እኛ ሙሥሊሞች ክርስቲያኖችን፦ ኢየሱስ "እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ" ያለበት ጥቅስ ስጡን ስንላቸው እነርሱ፦ "ኢየሱስ አልፋ እና ዖሜጋ ነኝ" ብሏል ብለው ይመልሳሉ፥ እውን "አልፋ እና ዖሜጋ ነኝ" የሚለው ማን ነው? ኢየሱስ ወይስ የኢየሱስ አምላክ? ያድምጡና ያስደምጡ፦

12.7K views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-16 11:15:21 የክርስቶስ ተቃዋሚ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥111 ወደ ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ» በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي

"የክርስቶስ ተቃዋሚ" ማለት "ጸረ ክርስቶስ"antichrist" ማለት ሲሆም በግሪክ ኮይኔ "አንቲኽሪስቶስ" ይባላል፥ "አንቲኽሪስቶስ" ἀντίχριστος የሚለው ቃል "አንቲ" ἀντί ማለትም "ተቃራኒ" "ተቃዋሚ" "ሐሳዌ" እና "ኽሪስቶስ" Χριστός ማለትም "መሢሕ" "ቅቡዕ" "ክርስቶስ" ከሚል ሁለት ቃላት የተዋቀረ ሲሆን "የክርስቶስ ተቃራኒ" "የክርስቶስ ተቃዋሚ" "ሐሳዌ መሢሕ" ማለት ነው፦
1ኛ ዮሐንስ 2፥18 ልጆች ሆይ! መጨረሻው ሰዓት ነው፥ "የክርስቶስም ተቃዋሚ" ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ። Παιδία, ἐσχάτη ὥρα ἐστίν, καὶ καθὼς ἠκούσατε ὅτι ἀντίχριστος ἔρχεται,

እዚህ አንቀጽ ላይ በነጠላ "የክርስቶስም ተቃዋሚ" የተባለው ዋናው ሐሳዌ መሢሕ ሲሆን ከእርሱ መምጣት በፊት የመጡት አሳቾች እራሱ "የክርስቶስ ተቃዋሚዎች" ተብለዋል፦
1ኛ ዮሐንስ 2፥18 አሁን እንኳ ብዙዎች "የክርስቶስ ተቃዋሚዎች" ተነሥተዋል፥ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን። καὶ νῦν ἀντίχριστοι πολλοὶ γεγόνασιν· ὅθεν γινώσκομεν ὅτι ἐσχάτη ὥρα ἐστίν.

ግዕዙ "ሐሳውያነ መሢሕ" ይለዋል፥ ሐሳውያነ መሢሕ እነዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፦
2ኛ ዮሐንስ 1፥7 ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹ እና "የክርስቶስ ተቃዋሚው" ነው። ὅτι πολλοὶ πλάνοι ἐξῆλθον εἰς τὸν κόσμον, οἱ μὴ ὁμολογοῦντες Ἰησοῦν Χριστὸν ἐρχόμενον ἐν σαρκί· οὗτός ἐστιν ὁ πλάνος καὶ ὁ ἀντίχριστος.

እኛ ሙሥሊሞች ግን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ፣ ክርስቶስ ከአባቶች በሥጋ እንደመጣ፣ አንዱ አምላክ ኢየሱስን የዳዊት ዘር ከሆነችው ከማርያም ካለመኖር ወደ መኖር እንዳመጣው እናምናለን፦
ሮሜ 9፥5 አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ "ከእነርሱም" ክርስቶስ በሥጋ መጣ። καὶ ἐξ ὁ Χριστὸς τὸ κατὰ σάρκα
የሐዋርያት ሥራ 13፥23 ከዚህም ሰው ዘር አምላክ እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ። τούτου ὁ Θεὸς ἀπὸ τοῦ σπέρματος κατ’ ἐπαγγελίαν ἤγαγεν τῷ Ἰσραὴλ Σωτῆρα Ἰησοῦν,

እኛ ሙሥሊሞች ኢየሱስ መሢሕ እንደሆነ ስለምናምን "አል መሢሑ ዒሣ" الْمَسِيحُ عِيسَى በሚል ማዕረጋዊ ስም ብዙ ቦታ በቁርኣን ተጠቅሷል። 3፥45 4፥171 ተመልከት!
በተቃራኒው ግን "ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለም" ብሎ የሚክድ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፦
1ኛ ዮሐንስ 2፥22 "ክርስቶስ አይደለም" ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብን እና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።

"አብ" ማለት በፍካሬአዊ ቃል "አስገኚ" "ምንጭ" "ፈጣሪ" ማለት ሲሆን "ወልድ" ማለት በፍካሬአዊ ቃል "ተገኝ" "ተመንጭ" "ፍጡር" ማለት ነው። ኢየሱስ "በአምላክ እመኑ" ሲል እና "በእኔም ደግሞ እመኑ" ሲል አንዱ አምላክ ላኪ ኢየሱስ ተላኪ መሢሕ መሆኑን የሚያሳይ ነው፦
ዮሐንስ 14፥1 በአምላክ እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። πιστεύετε εἰς τὸν Θεόν, καὶ εἰς ἐμὲ πιστεύετε.

"በእኔ" በሚለው ቃል ላይ “ም” የሚለው ጥገኛ ምዕላድ በዐማርኛ ተጨማሪ ነገርን ለማሳየት የገባው በግሪኩ "ካይ" καὶ ማለትም "እና" የሚለውን መስተጻምር ለማሳየት የገባ ነው፥ ይህም አምላክ እና መልእክተኛው ሁለት የተለያዩ ሃልዎት እና ኑባሬ እንደሆኑ ቁልጭ አርጎ ያሳያል። በእርግጥም በመልእክተኛው ማመን በላከው ማመን የሚሆንበት ምክንያት መልእክቱ የላኪው እንጂ የተላኪው ስላልሆነ ነው፦
ዮሐንስ 12፥44 ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም አለ፦ በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም።
ዮሐንስ 14፥24 የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።

እውነት ነው! ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክን አብ እና መሢሑን ኢየሱስ የሚክዱ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ናቸው፦
ይሁዳ 1፥4 ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። καὶ τὸν μόνον δεσπότην θεὸν καὶ κύριον ἡμῶν Ἰησοῦν χριστὸν ἀρνούμενοι.

"ዴስፖቴን ቴዎን" δεσπότην θεὸν የሚለው ኮዴክስ ቤዛይ ላይ ሲሆን 1611 ድኅረ ልደት በታተመው ቅጂ The King James Version (KJV) ላይ ልክ እንደ ኮዴክስ ቤዛይ፦ "ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ"and denying the only Lord God, and our Lord Jesus Christ" ብለው አስቀምጠውታል።
አምላካችን አሏህ ለዒሣ በሰጠው ወሕይ በኢንጂል ለሐዋርያት፦ "በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ" ብሎ አዟቸው ነበር፦
5፥111 ወደ ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ» በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي

እዚህ አንቀጽ "ባዘዝኩ" ለሚለው የገባው ቃል "አውሐይት" أَوْحَيْتُ የግሥ መደብ ሲሆን የስም መደቡ "ወሕይ" وَحْي ማለትም "ግልጠተ መለኮት"revelation" ነው፥ በአሏህ አምላክነት በመልእክተኛው በኢየሱስ መሢሕነት ማመን የአርካኑል ኢማን ክፍል ነው። እንደተግባባን ተስፋ አደርጋለው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
12.9K views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-11 19:49:39
ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን፦ "ወደ መንፈስ ቅዱስ አንጸልይም፥ ወደ ኢየሱስ አንጸልይም። የምንጸልየው በኢየሱስ ስም ወደ አብ ነው" ብሏል። It's so wonderful that.
ይህ ትልቅ ለውጥ ነው። እኛም የምንለው ይህንን ነው። መመለክ የሚገባው ኢየሱስ ሳይሆን ኢየሱስ የላከ የኢየሱስ አምላክ ብቻ እና ብቻ ነው።
12.6K viewsedited  16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-21 21:47:12 "ኢየሱስ ነቢይ ነው" ካልን ጥያቄአችን "የማን ነቢይ ነው? መልሱ "የአምላክ ነቢይ ነው" አምላክ ስንት ነው? "አንድ አምላክ" ስለዚህ ኢየሱስ የአንዱ አምላክ ነቢይ ከሆነ ፊሽካው ተነፋ፥ ከዚያ በኃላ "አምላክ ነው" "የአምላክ ሁለተኛው አካል እና አባል ነው" የሚለው አስተምህሮት ፉርሽ ነው። በኢየሱስ ነቢይነት ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰተናልና ያድምጡ ያስደምጡ፦



ሙሥሊም ወንድሞቼ እና እኅቶቼ መልእክቱ ተደራሽነት እንዲኖረው ላይክ፣ ኮሜንት፣ ሼር እና ሰብስክራይብ በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን። ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
13.0K views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-18 22:20:12 የምርኮ ገንዘብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

8፥1 ከአንፋል ይጠይቁሃል፡፡ በል፦ «አንፋል የአሏህ እና የመልእክተኛው ናቸው፡፡» يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَنفَالِ ۖ قُلِ الْأَنفَالُ لِلَّهِ وَالرَّسُولِ

የግጭት አዙሪት እና የጭቅጭቅ ቀለበት አባዜ የተጠናወታቸው ሚሽነሪዎች "ቁርኣን ዝረፉ ይላል" በማለት መጥኔ የሌለው ሥርዋጽ ሲለቁ እያየን ነው፥ የመካከለኛው ምሥራቅ ትኩሳት ተስታኮ ለማሳጣት ሾርኔ መሆኑ ነው። "ጅብ በቀደደው ውሻ ይገባል" ነውና ነገሩ መስመር የሳተ አስተሳሰብ ቢሆንም ጥሩ የውይይት ማሳለጫ ነው፥ ከከርሞ ዘንድሮ ለያዥ ለገናዥ በማያመች መልኩ ቅሌቱ ቢያገረሽባቸውም እኛ ደግሞ "ከፋህም ከረፋህም" ሳንል መልስ እንሰጣለን።
"ነፈል" نَفَل የሚለው ቃል"ነፈለ" نَفَلَ ማለትም "ማረከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ምርኮ" ማለት ነው፥ የነፈል ብዙ ቁጥር ደግሞ "አንፋል" أَنفَال ሲሆን "ምርኮዎች" ማለት ነው፦
8፥1 ከአንፋል ይጠይቁሃል፡፡ በል፦ «አንፋል የአሏህ እና የመልእክተኛው ናቸው፡፡» يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَنفَالِ ۖ قُلِ الْأَنفَالُ لِلَّهِ وَالرَّسُولِ

እዚህ አንቀጽ ላይ በዐማርኛ ትርጉም ላይ "የጦር ዘረፋ" "የዘረፋ ገንዘብ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "አል አንፋል" الْأَنفَال ሲሆን በቀላሉ ከጦነት በኃላ የሚገኙ "ምርኮዎች" ናቸው፥ 8ኛ ሡራህ እራሱ ስሙ "ሡረቱል አንፋል" سُورَة الْأَنفَال ነው። ይህም ምርኮ አንድ አምስተኛው ለአሏህ፣ ለመልእክተኛው፣ ለዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለምስኪኖች፣ ለመንገደኛ የተገባ ነው፦
8፥41 ከማንኛውም የምርኮ ገንዘብ የዘረፋችሁትም አንድ አምስተኛው ለአሏህ እና ለመልክተኛው፣ የዝምድና ባለቤቶችም፣ ለየቲሞችም፣ ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኛም የተገባ መኾኑን ዕውቁ። وَاعْلَمُوا أَنَّمَا غَنِمْتُم مِّن شَيْءٍ فَأَنَّ لِلَّهِ خُمُسَهُ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَابْنِ السَّبِيلِ

በቁርኣን ስለ አንፋል እዚህ ድረስ አጥለን እና አጠንፍፈን ከተረዳን ዘንዳ መጅ እና ወፍጮ ይዘን ስለ ምርኮ በባይብል የተነገሩት በቅጡ አድቅቀን እናያለን። ነቢዩ አብርሃም ነገሥታትን ገድሎ ሲመለስ ከነገሥታቱ የዘረፈውን ለሳሌም ንጉሥ ለመልከ ጼዴቅ ሰጥቶታል፦
ዕብራውያን 7፥4 የአባቶች አለቃ አብርሃም "ከዘረፋው" የሚሻለውን አስራት የሰጠው ይህ ሰው እንዴት ትልቅ እንደ ነበረ እስኪ ተመልከቱ።

"ከዘረፋው" የሚለው ይሰመርበት! አብርሃም በጦርነት ምርኮን ስለዘረፈ ሌባ ነውን? መዝረፉስ ሌብነት ነውን? ጉድ ፈላ፥ ይህ ከድጡ ወደ ማጡ ነው። የያዕቆብ ልጆች እኅታቸው ዲና ስለተደፈረች ደፋሪዎችን ገድለው በከተማይቱ ያሉትን በጎቻቸውን፣ ላሞቻቸውን፣ አህዮቻቸውን፣ በውጭም ያለው፣ ሀብታቸውን ሁሉ፣ ሕፃናቶቻቸውን፣ ሴቶቻቸውንም እና በቤት ያለውንም ሁሉ ዘረፉ፦
ዘፍጥረት 34፥27-29 የያዕቆብም ልጆች እኅታቸውን ዲናን ሰለ አረከሱአት ወደ ሞቱት ገብተው ከተማይቱን "ዘረፉ"፤ በጎቻቸውንም ላሞቻቸውንም አህዮቻቸውንም በውጭም በከተማም ያለውን ወሰዱ። ሀብታቸውን ሁሉ ሕፃናቶቻቸውንና ሴቶቻቸውንም ሁሉ ማረኩ፥ በቤት ያለውንም ሁሉ "ዘረፉ"።

"ዘረፉ" የሚለው ይሰመርበት! ይህንን ስታነቡ ሰኔ እና ሰኞ ይሆንባቸዋል። በዚህ ቢቆም ጥሩ ነበር፥ እስራኤላውያንም ከግብፅ ሲወጡ የግብፅ ንብረት በዝብዘው ነበር። ይህንን ያደረጉት ከተማይቱን በማቃጠል ነው፥ ይህንን ያዘዛቸው የእስራኤል አምላክ እንደሆነ ባይብሉ ይናገራል፦
ዘጸአት 3፥22 ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤትዋ በቤትዋም ካለችው ሴት የብር ዕቃ የወርቅ እቃ ልብስም ትለምናለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም "ትበዘብዛላች"።
ዘጸአት 12:36 እግዚአብሔርም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት የፈለጉትን እንዲሰጡአቸው ሞገስን ሰጠ። እነርሱም ግብፃውያንን "በዘበዙ"።

"ትበዘብዛላች" የሚለው መጻኢ ግሥ እና "በዘበዙ" የሚለው አላፊ ግሥ ይሰመርበት! በትእዛዙ መሠረት በመንገድ ላይም ያደረጉት ይህንን ተግባር ነው ፦
ዘኍልቍ 31፥9-11 የእስራኤልም ልጆች የምድያምን ሴቶችና ልጆቻቸውን "ማረኩ"፤ እንስሶቻቸውንና መንጎቻቸውንም ዕቃቸውንም ሁሉ "በዘበዙ"። የተቀመጡባቸውን ከተሞቻቸውን ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። "የሰውን እና የእንስሳን ምርኮና ብዝበዛ ሁሉ ወሰዱ"።
ዘኍልቍ 31፥53 ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ሁሉ "ከምርኮአቸው ለራሳቸው ወሰዱ"።
ኢያሱ 8፥27 ነገር ግን ያህዌህ ኢያሱን እንዳዘዘው ቃል የዚያችን ከተማ ከብት እና ምርኮ እስራኤል ለራሳቸው "ዘረፉ"።
ኢያሱ 11:14 የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ ከብቶቹንም ለራሳቸው "ዘረፉ"።

ስለ ዘረፋ በባይብል ልቀጥል ብል ቦታ አይበቃኝም፥ አንባቢንም ማሰልቸት ነው። መቼም ሚሽነሪዎች የኢሥላም ትምህርት ጥንብ እኩሱን ቢወጣ እና ዶግ አመድ ቢሆንላቸው ደስታቸው እጥፍ ድርብ ነው፥ ይህ ጡዘቱ ጣራ የነካና ዙሪያ ገባ ምኞች ስለማይሳካ በቁጭ ይሙቱ! ከእነርሱ ቅንነት የተሞላው ትምህርት መጠበቅ ማለት ከጅብ አፍ ላይ ሥጋ እንደመጠበቅ ነው። እነርሱ የሚሰጡት ትችት እኛ ሙሥሊሞችን የሚያፍረከርክ ሳይሆን ከእለት ወደ እለት የሚያጀግን ነው፥ ለማንኛውም የተነሳውን ትችት አብጠርጥረን እና አንጠርጥረን መልስ ሰተናል። አሏህ ለእነርሱ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
12.9K viewsedited  19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-15 11:26:11 ክርስቲያኖች "ኢየሱስ ይመለካል" ብለው አዘውትረው የሚጠቅሷቸውን ተወዳጆች ጥቅሳት "ለኢየሱስ መመለክ ድምዳሜ በፍጹም አያደርስም" ብለን በመሞገት ድባቅ አስገብተናል። ኢንሻላህ ሙግቱን ያድምጡ ያስደምጡ፦




ሙሥሊም ወንድሞቼ እና እኅቶቼ መልእክቱ ተደራሽነት እንዲኖረው ላይክ፣ ኮሜንት፣ ሼር እና ሰብስክራይብ በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን። ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
12.8K views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 22:47:28 ፍልስጥኤም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥251 "በአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፥ ዳውድም ጃሉትን ገደለ"፡፡ فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ

"ፊልሥጢን" فِلَسْطِين ማለት "ፍልስጥኤም" ማለት ሲሆን በአንድ ወቅት የፍሊሥጢን ንጉሥ "ጃሉት" جَالُوت ማለትም "ጎልያድ" እና ሠራዊቱ ከጧሉት ማለትም ከሳኦል ሠራዊት ተዋግተዋል፦
2፥249 ጧሉትም በሠራዊቱ ታጅቦ በወጣ ጊዜ፡- «አላህ በወንዝ ፈታኛችሁ ነው፥ ከርሱም የጠጣ ሰው ከእኔ አይደለም፡፡ ያልቀመሰውም ሰው በእጁ መዝገንን የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር እርሱ ከእኔ ነው» አለ፡፡ ከእነርሱም ጥቂቶች ሲቀሩ ከርሱ ጠጡ፡፡ እርሱ እና እነዚያም ከእርሱ ጋር ያመኑት ወንዙን ባለፉት ጊዜ፡- «ጃሎትን እና ሠራዊቱን በመዋጋት ለኛ ዛሬ ችሎታ የለንም» አሉት፡፡ እነዚያ እነርሱ አላህን ተገናኝዎች መኾናቸው የሚያረጋግጡት፡- «ከጥቂት ጭፍራ በአላህ ፈቃድ ብዙን ጭፍራ ያሸነፈች ብዙ ናት፤ አላህም ከታጋሾች ጋር ነው» አሉ፡፡ فَلَمَّا فَصَلَ طَالُوتُ بِالْجُنُودِ قَالَ إِنَّ اللَّهَ مُبْتَلِيكُم بِنَهَرٍ فَمَن شَرِبَ مِنْهُ فَلَيْسَ مِنِّي وَمَن لَّمْ يَطْعَمْهُ فَإِنَّهُ مِنِّي إِلَّا مَنِ اغْتَرَفَ غُرْفَةً بِيَدِهِ ۚ فَشَرِبُوا مِنْهُ إِلَّا قَلِيلًا مِّنْهُمْ ۚ فَلَمَّا جَاوَزَهُ هُوَ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ قَالُوا لَا طَاقَةَ لَنَا الْيَوْمَ بِجَالُوتَ وَجُنُودِهِ ۚ قَالَ الَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَاقُو اللَّهِ كَم مِّن فِئَةٍ قَلِيلَةٍ غَلَبَتْ فِئَةً كَثِيرَةً بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ مَعَ الصَّابِرِينَ

ከዚያም በጦርነቱ ተፋልመው ተስፋ በቆረጡ ጊዜ ዳውድ ጃሉትን ገሎታል፦
2፥250 ለጃሉት እና ለሠራዊቱ በተሰለፉም ጊዜ፡- «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አንቧቧ፤ ጫማዎቻችንንም አደላድል፤ በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ እርዳን» አሉ፡፡ وَلَمَّا بَرَزُوا لِجَالُوتَ وَجُنُودِهِ قَالُوا رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَانصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ
2፥251 "በአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፥ ዳውድም ጃሉትን ገደለ"፡፡ فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ

ቁርኣን ላይ ስለ ፍልስጥኤማውያን የሚናገረው እነዚህ አናቅጽ ላይ ነው። ሚሽነሪዎች፦ "ፍልስጥኤማውያን ፍልስጥኤም የምትባል አገር የላቸውም" እያሉ ባላነበቡት ነገር ይዘባርቃሉ። ፈጣሪ እስራኤልን ከግብጽ ምድር እንዳወጣ ሁሉ በጥንት ጊዜ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር አውጥቶ የራሳቸው ግዛት ሰቷቸዋል፦
አሞጽ 9፥7 እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?
ኢዮኤል 3፥4 ጢሮስና ሲዶና የፍልስጥኤምም ግዛት ሁሉ ሆይ! ከእናንተ ጋር ለእኔ ምን አለኝ? በውኑ ብድራትን ትመልሱልኛላችሁን?

"የፍልስጥኤምም ግዛት" የሚለው ይሰመርበት ፍልስጥኤም ግዛት ከነበረች ለምን መብቷ አይከበረም? እስራኤላውያን ቦታቸው መጥተው ሰፈሩባቸው እንጂ ጥንትም ቢሆን የእስራኤል ቅም አያት አብርሃም ከከላዳውያን ኡር በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀምጧል፦
ዘፍጥረት 21፥34 "አብርሃምም በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀመጠ"።

ፍልስጥኤም መጤ ሳትሆን የራሷ ምድር ስለሆነ "በፍልስጥኤም ምድር" የሚል ኃይለ-ቃል ተጽፏል። ባይብል ላይ ብዙ ቦታ "የፍልስጥኤም ምድር" እያለ ይናገራል፦
ኤርምያስ 25፥20 የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ "የፍልስጥኤም ምድር" ነገሥታትንም ሁሉ አስቀሎናንም ጋዛንም አቃሮንንም የአዞጦንንም ቅሬታ"።
ዘጸአት 13፥17 እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር "በፍልስጥኤማውያን ምድር" መንገድ አልመራቸውም።

ፍልስጥኤማውያን የራሳቸው አገር አላቸው፥ እስራኤላውያን የሰፈሩበት ከነዓን ሁሉ ሳይቀር የፍልስጥኤማውያን ምድር ነው፦
2ኛ ነገሥት 8፥2 ሴቲቱም ተነሥታ እንደ እግዚአብሔር ሰው ቃል አደረገች፤ ከቤተ ሰብዋም ጋር ሄዳ "በፍልስጥኤም አገር" ሰባት ዓመት ተቀመጠች"*።
ሶፎንያስ 2፥5 "የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ"፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው።

ዛሬ አገር እና ግዛት እንደሌላቸው እና መጤ እንደሆኑ ታይቶ እየተፈናቀሉ ነው፥ አሏህ ነስሩን ያቅርብላቸው! አሚን። ይህንን የምንለው ስለ ሐቅ እና ስለ ፍትሕ ነው፥ "ኢሥላም ሰም እና ወርቅ የያዘ ቅኔ ነው፥ ሰሙ ሐቅ ሲሆን ወርቁ ፍትሕ ነው" ስንል ዕውር ድንብ ጸለምተኛ ሙግት ይዘን ሳይሆን ጠቅሰንና አጣቅሰን በመሞገትና በመሟገት ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
13.5K views19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-17 08:02:00 ክርስቲያኖች፦ "ኢየሱስ ፍጥረትን ፈጥሯል" ብለው ከጳውሎስ ደብዳቤዎች ይጠቅሳሉ። እኛ ደግሞ "ኢየሱስ ምንም አልፈጠረም" ብለን ከጳውሎስ ደብዳቤዎች እንሞግታለን። ኢንሻላህ ከታች ያለውን ሊንክ በማስፈንጠር አድምጡ እና አስደምጡ!


12.9K viewsedited  05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-15 20:59:40 በዐፋርኛ ደርሥ ተለቋል። ዐፋርኛ የምትችሉ ግቡ፦ https://t.me/wahidcomafarega/11
12.7K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-15 16:30:22 ሥላሴአዊ ቅጥፈት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

ከ 260 እስከ 339 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው የቂሳሪያው ኤጲስ ቆጶስ አውሳብዮስ የቤተክርስቲያን ታሪክ"Church History" በሚል መጽሐፉ ሐዋርያው ማቴዎስ ለዕብራውያን በዕብራይስጥ ቋንቋ ደብዳቤ እንደጻፈላቸው ተናግሯል፦
፨፦ "ስለዚህ ማቴዎስ በዕብራይስጥ ቋንቋ ደብዳቤ ጽፏል"።
(አውሳቢዮስ የቤተክርስቲያን ታሪክ መጽሐፍ 3 ምዕራፍ 39 ቁጥር 16)

፨፦ "እርሱ ማቴዎስ በመጀመሪያ ለዕብራውያን የሰበከው ነው"።
(አውሳቢዮስ የቤተክርስቲያን ታሪክ መጽሐፍ 3 ምዕራፍ 39 ቁጥር 16)

ማቴዎስ ይህንን ደብዳቤአዊ ወንጌል ከ 45 እስከ 55 ድኅረ ልደት እንደጻፈ ይገመታል፥ የመጀመሪያ መቶ ክፍለ ዘመን ይኖሩ የነበሩት ኢቦናይት የሚባሉ አይሁዳውያን የኢየሱስ ተከታዮች ማቴዎስ ለዕብራውያን የጻፈውን ይህንን ወንጌል ብቻ ይቀበሉ እንደነበር አውሳብዮስ ይናገራል፦
"እና ለዕብራውያን ተደረሰ የተባለውን ወንጌል ብቻ ይጠቀሙ ነበር"።
(አውሳቢዮስ የቤተክርስቲያን ታሪክ መጽሐፍ 3 ምዕራፍ 25 ቁጥር 4)

የቂሳሪያው አውሳብዮስ "የወንጌል ማረጋገጫ"Proof of the Gospel" በሚል መጽሐፉ ላይ ማቴዎስ በዕብራይስጥ በጻፈው ወንጌል ላይ ኢየሱስ ለሐዋርያት ያላቸው፦ "እንግዲህ ሂዱ እና አሕዛብን ሁሉ በስሜ ደቀ መዛሙርት አድርጉ! ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተማሯቸው" በማለት እንዳዘዛቸው ተናግሯል፦
፨፦ "ከአንድ ቃል እና ድምፅ ጋር እርሱም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፦ "እንግዲህ ሂዱ እና አሕዛብን ሁሉ በስሜ ደቀ መዛሙርት አድርጉ! ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተማሯቸው"።
(አውሳቢዮስ የወንጌል ማረጋገጫ ቅጽ 1 መጽሐፍ 3 ምዕራፍ 6 ቁጥር 132 ገጽ 152)

፨፦ "እርሱም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፦ "እንግዲህ ሂዱ እና አሕዛብን ሁሉ በስሜ ደቀ መዛሙርት አድርጉ"።
(አውሳቢዮስ የወንጌል ማረጋገጫ ቅጽ 1 መጽሐፍ 3 ምዕራፍ 7 ቁጥር 136 ገጽ 157)

፨፦ "እርሱም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፦ "አሕዛብን ሁሉ በስሜ ደቀ መዛሙርት አድርጉ"።
(አውሳቢዮስ የወንጌል ማረጋገጫ ቅጽ 1 መጽሐፍ 3 ምዕራፍ 7 ቁጥር 138 ገጽ 159)

"አሕዛብ" የሚለው የግዕዝ ቃል "ሕዝብ" ለሚለው ብዜት ሲሆን በጸያፍ ርቢ "ሕዝቦች" ማለት ነው፥ በዕብራይስጥ ለዕብራውያን በተጻፈው የመጀመሪያው የማቴዎስ ወንጌል ላይ ኢየሱስ፦ "አሕዛብን ሁሉ በስሜ ደቀ መዛሙርት አድርጉ" የሚል ሆኖ ሳለ ስሙ እና ማንነቱ በውል የማይታወቅ ሰው የማርቆስን ወንጌል መሠረት አድርጎ በግሪክ ኮይኔ በማቴዎስ ዳቦ ስም የማቴዎስ ወንጌል አዘጋጀ። በዚህ ወንጌል ውስጥ፦ "እንግዲህ ሂዱ እና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው" የሚል ሥላሴአዊ ቅጥፈት ተቀጠፈ፥ ዓይን ያስፈጠጠ እና ጥርስ ያገጠጠ ይህንን ሐቅ መድብለ-ዕውቀት"encyclopedia" እንዲህ ያትታሉ፦
፨፦ "ማቴዎስ 28፥19 በኃላ በቤተክርስቲያን ሁኔታ በተለየ ብቻ ቀኖናዊ የሆነ ነው፥ ለዛ ነው ዓለም አቀፋዊነቷ ከቀደምት የክርስቲያን ታሪክ እውነታዎች ጋር የሚቃረን የሆነው። የሥላሴአውያን ቀመር ለኢየሱስ ንግግር ባዕድ ነው"።
(ዓለም ዓቀር መደበኛ የባይብል መድብለ ዕውቀት ቅጽ 4, ገጽ 2637)

፨፦ "የጥምቀት ቀመር "በኢየሱስ ስም" ከሚል ወደ "በአብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ስም" ወደሚል በዓለም ዐቀፍ ቤተክርስቲያን በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ተለውጧል"።
(የካቶሊክ መድብለ ዕውቀት ቅጽ 2, ገጽ 263)

በተጨማሪም "እንግዲህ ሂዱ እና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው" የሚለውን ሥላሴአዊ ቅጥፈት እና ቅሰጣ የባይብል ማብራሪያ"Commentary" እና እትም"Version" ወሮበላ መሆኑን እንጩን ፍርጥ አርገው ነግረውናል፦
፨፦ "በአብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ስም" የኢየሱስ ቃል ሳይሆን በኃላ የተጨመረ ቃል ነው"።
(ቴንደል የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ ቅጽ 1, ገጽ 275

፨፦ "ዘመናዊ ኂስ ይህንን የሥላሴአውያን ቀመር ኢየሱስን ማስዋሸት ነው፥ ያ በኃላ ላይ የቤተክርስቲያን ትውፊት የሚወክል ነው"።
(1989 አዲሱ የተሻሻለ የመደበኛ ባይብል እትም)

የሥላሴ አማንያን"trinitarian" ሆይ! ፈጣሪን "አንድ ነው" ባላችሁበት አፍ «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም በተውሒድ ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
12.8K viewsedited  13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ