Get Mystery Box with random crypto!

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

የቴሌግራም ቻናል አርማ wahidcom — ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
የቴሌግራም ቻናል አርማ wahidcom — ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
የሰርጥ አድራሻ: @wahidcom
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.43K
የሰርጥ መግለጫ

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-06-26 14:23:30 የዘላለም ሕይወት መልእክት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥71 የመርየም ልጅ አል-መሢሕ ዒሣ የአላህ መልእክተኛ ብቻ ነው። إِنَّمَا الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ اللَّهِ

"ረሡል" رَسُول የሚለው ቃል "አርሠለ" أَرْسَلَ ማለትም "ላከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መልእክተኛ" ማለት ነው፥ "ሪሣላህ" ማለት "መልእክት" ማለት ሲሆን "ሙርሢል” مُرْسِل ማለት ደግሞ "ላኪ" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ "ሙርሢል" ሲሆን ዒሣ ኢብኑ መርየም ደግሞ "ረሡል" ነው፦
4፥71 የመርየም ልጅ አል-መሢሕ ዒሣ የአላህ መልእክተኛ ብቻ ነው። إِنَّمَا الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ اللَّهِ

አሏህ ለዒሣ እንዲያስተላልፍ የሰጠው "ሪሣላህ" ኢንጂል ነው፥ መልእክተኛ የራሱ ሙሉ ዕውቀት ስለሌለው የላከው ዕውቀት የሚያስለላልፍ ነው።
ወደ ባይብል ስንመጣ ኢየሱስ የአንዱ አምላክ መልእክተኛ ስለሆነ አንዱ አምላክ ለኢየሱስ እንዲያስተላልፍ መልእክት ሰቶታል፦
ዮሐንስ 17፥8 የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና።

"የሰጠኸኝን ቃል" የሚለው ይሰመርበት! ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ቃል አለው፥ ይህን የዘለዓለም ሕይወት ቃል የሚሰጠው አብ እንዲሰጥ ሥልጣን ስለሰጠው እንጂ እርሱ ከራሱ ምንም ማድረግ አይችልም፦
ዮሐንስ 6፥68 አንተ "የዘላለም ሕይወት ቃል" አለህ።
ዮሐንስ 12፥49 እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም "ትእዛዝ ሰጠኝ"።
ዮሐንስ 12፥50 "ትእዛዙም የዘላለም ሕይወት እንደ ሆነች" አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ የምናገረውን አብ እንደ ነገረኝ እንዲሁ እናገራለሁ።

ኢየሱስ የሚለው እና የሚናገረው ከራሱ ካልሆነ እና የሚለው እና የሚናገረው ትእዛዙ የላከው ከሰጠው ያ የተሰጠው ትእዛዝ የዘላለም ሕይወት ነው። የዘላለም ሕይወትን የሆነውን ይህንን ትእዛዝ ለአማኞች እንዲሰጥ ሥልጣን የሰጠው አብ ነው፦
ዮሐንስ 17፥2 በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው።

የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ሥልጣን ከተሰጠው ይህም የዘላለም ሕይወት ዕውቀት እንደሆነ ዐውደ ንባቡ ይናገራል፦
ዮሐንስ 17፥3 እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ አንተን እና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። αὕτη δέ ἐστιν ἡ αἰώνιος ζωή, ἵνα γινώσκωσιν σὲ τὸν μόνον ἀληθινὸν θεὸν καὶ ὃν ἀπέστειλας Ἰησοῦν Χριστόν.
1ኛ ዮሐንስ 5፥20 የአምላክም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ መረዳት እንደ ሰጠን እናውቃለን። οἴδαμεν δὲ ὅτι ὁ Υἱὸς τοῦ Θεοῦ ἥκει, καὶ δέδωκεν ἡμῖν διάνοιαν ἵνα γινώσκομεν τὸν ἀληθινόν·

"ይህቺ" ተብሎ በአምልካች ተውላጠ ስም የተቀመጠው የዘላለም ሕይወት አብን ብቻውን እውነተኛ አምላክ መሆኑን እና ኢየሱስ የእውነተኛው አምላክ መልእክተኛ መሆኑን "ማወቅ" ነው። በዚህም መልእክተኛው ወልድ እውነተኛ አምላክን የሆነውን አብን ለማወቅ መረዳት(ዕውቀት) ሰጥቷል፥ "እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ መረዳት እንደ ሰጠን እናውቃለን" የሚለው ይህንኑ ነው። ኢየሱስ ከአብ የሰማውን ዕውቀት አስታውቋል፦
ዮሐንስ 15፥15 ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።

ኢየሱስ፦ "ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ" በሚል ኃይለ ቃል ውስጥ "ለሰጠኸው" ሲል ከአብ ለወልድ የተሰጡት አማኞች ናቸው፦
ዮሐንስ 10፥29 "የሰጠኝ" አባቴ ከሁሉ ይበልጣል።
ዮሐንስ 17፥6 ከዓለም "ለሰጠኸኝ ሰዎች" ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ ለእኔም "ሰጠሃቸው"።

ኢየሱስ ከአብ የተሰጠውን ቃል፣ ትእዛዝ፣ ዕውቀት ለአማኞችም ስለሚሰጥ "ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ" ማለቱ ይህንን ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው፦
ዮሐንስ 10፥28 እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ።

"ለበሬ ሁሉ ነገር ጭድ ይመስለዋል" ለየት ያለ ጥቅስ ሲገኝ ጎትጉቶ እና ጎትቶ ለኢየሱስ አምላክነት መደረብ ሚሽነሪዎች ዋንጫ የወስዱበት ጉዳይ ነው፥ በድፍ ቅል ጉሳንጉስ የሥነ መለኮት ቅመራ ከመቀመር ይልቅ ማጥናት ይገባል። "የዘላለም ሕይወት" የተባለው ቃል፣ ትእዛዝ፣ ዕውቀት እንደሆነ ከተረዳን ዘንዳ ይህንን የዘላለም ሕይወት እንዲሰጥ ሥልጣን ተሰቶታል እንጂ ኢየሱስ ከራሱ ምንም ነገር ማድረግ አይችልም፦
ዮሐንስ 5፥30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም።

"እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም" "እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና" ካለ እርሱ የዘላለምን ሕይወት የሆነውን መልእክት ከላኪው ከአብ እንዲያስተላልፍ ሥልጣን የተሰጠው መልእክተኛ ብቻ ነው፥ ኢየሱስ "እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ" ብሎ የተናገውን ንግግር ይዞ ለአምላክነት መሞገት ዛብ የሌለው ፈረሰኛ ምሳ የሌለው ኮሰኛ ነውና ሙግቱ ያልፋፋ እና ያልዳበረ ሙግት ነው። ይህንን ሰው የሆነ መልእክተኛ የምታመልኩ አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
4.6K views11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 07:13:37 "በኢየሱስ ስም" ማለት ደግሞ "ኢየሱስ እንዴት መጸለይ እንዳለባቸው ባዘዛቸው መሠረት ወደ አብ መጸለይ በኢየሱስ ስም መጸለይ" ማለት ነው፥ "በ" የሚል መስተዋድድ ባለበት ቃል ላይ "ስም" የሚል ቃላት አንዳንድ ናሙና እንመልከት፦
1ኛ ስሙኤል 25፥9  የዳዊትም ጕልማሶች መጡ፥ ይህንም ቃል ሁሉ "በዳዊት ስም" ለናባል ነግረው ዝም አሉ።

"በዳዊት ስም" የሚለው ይሰመርበት! የዳዊትም ጕልማሶች ለናባል "በዳዊት ስም" ነገሩት ማለት "በዳዊት ትእዛዝ" ነገሩት ከሆነ እንግዲያውስ "በኢየሱስ ስም" አብን መለመን ማለት "በኢየሱስ ትእዛዝ" አብን መለመን ማለት ነው። ሌላ ናሙና እንመልከት፦
ማቴዎስ 10፥42 ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ "በደቀ መዝሙር ስም" የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋበትም።

"በደቀ መዝሙር ስም" የሚለው ይሰመርበት! "በደቀ መዝሙር ስም" ጽዋ ውኃ ለታናናሾች ማጠጣት ዋጋ እንደሚያሰጥ ሁሉ "በኢየሱስ ስም" ጽዋ ውኃ ማጠጣት ዋጋ ያሰጣል፦
ማርቆስ 9፥41 የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ "በስሜ" ጽዋ ውኃ የሚያጠጣችሁ ሁሉ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ።

እንደ እናንተ ስሑት ሙግት "በኢየሱስ ስም" ማለት ልክ "በአሏህ ስም" እንደ ማለት ከሆነ "በዳዊት ስም" "በደቀ መዝሙር ስም" ማለት "በአምላክ ስም" ማለት ነው ብላችሁ ለምን አልተረዳችሁትም? ዳዊት እና ኢየሱስ ነቢያት ሲሆኑ ሐዋርያቱ ደግሞ ጻድቃን ናቸው፥ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል፦
ማቴዎስ 10፥41 ነቢይን "በነቢይ ስም" የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም "በጻድቅ ስም" የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።

"በነቢይ ስም" እና "በጻድቅ ስም" የሚለው ይሰመርበት! ያ ማለት ነቢይን እንደ ነቢይ የሚቀበል ጻድቅን እንደ ጻድቅ የሚቀበል ዋጋ አለው፥ ዐውደ ንባቡ ላይ "እናንተን የሚቀበል" በማለት ሐዋርያትን እንደ ጻድቅ መቀበል እንዲሁ "እኔን የሚቀበል" በማለት መልእክተኛውን ኢየሱስን እንደ ነቢይ መቀበል ምንዳ እና ትሩፋት አለው፦
ማቴዎስ 10፥40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።

ስለዚህ "በኢየሱስ ስም" የተባለው "በዳዊት ስም" "በደቀ መዝሙር ስም" "በነቢይ ስም" "በጻድቅ ስም" በተባለበት ስሌት እና ቀመር ነው። “በ” የሚለውን “ለ” ብሎ ከተረዱት እንግዲያውስ “በ”-ጽዮን” የሚለውን “ለ”-ጽዮን” ብለው መረዳት ይኖርባቸዋል፦
መዝሙር 65፥1 አቤቱ “በ”-ጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል።  לַמְנַצֵּ֥חַ מִזְמֹ֗ור לְדָוִ֥ד שִֽׁיר׃ לְךָ֤ דֻֽמִיָּ֬ה תְהִלָּ֓ה אֱלֹ֘הִ֥ים בְּצִיֹּ֑ון

ስለዚህ “ኢየሱስ ይመለካል” ብሎ ኲታ ገጠም ርእስ አርጎ በደምሳሳው መሞገት ወትሮም ቢሆን ዘንድሮም የሚያዋጣ ሙግት አይደለም፥ የሚለምንን ለማኝ መለመን በራሱ ሺርክ ነው። በኢሥላም ግን የመርየም ልጅ ኢየሱስ ከእርሱ በፊት እንዳሉት መልእክተኞች የሆነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
7.4K viewsedited  04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 07:13:37 በስሜ ብትለምኑ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥75 የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

የተለያዩ ሰዎች በአንድ ጊዜ በተለያየ ሥፍራ ሆነውን የሚለምኑትን ልመና የሚሰማ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ ልመና የአምልኮ ክፍል ስለሆነ ልመናን የሚቀበል እና የሚሰማ ኢየሱስን የላከው አንዱ አምላክ አብ ብቻ ነው፦
ማቴዎስ 7፥11 በሰማያት ያለው አባታችሁ "ለሚለምኑት" እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? πόσῳ μᾶλλον ὁ Πατὴρ ὑμῶν ὁ ἐν τοῖς οὐρανοῖς δώσει ἀγαθὰ τοῖς αἰτοῦσιν αὐτόν.

"በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት" የሚለው ኃይለ ቃል ተለማኝ አብ ለማኝ ፍጡራን እንደሆኑ ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ኢየሱስ እራሱ አንዱን አምላክ ጠይቆ መልስ የሚጠብቅ ለማኝ ነበር፦
ዮሐንስ 11፥22 አሁንም ከአምላክ የምትለምነውን ሁሉ አምላክ እንዲሰጥህ አውቃለሁ አለችው። καὶ νῦν οἶδα ὅτι ὅσα ἂν αἰτήσῃ τὸν Θεὸν δώσει σοι ὁ Θεός.

ኢየሱስ አምላክን ለምኖ የሚሰጠው ከሆነ እርሱ ለማኝ ነቢይ እንጂ ተለማኝ አምላክ በፍጹም አይደለም፥ ኢየሱስ ይህንን አንድ አምላክ ሌሊቱን ሙሉ ሲለምን በአምልኮ አሳልፏል፦
ሉቃስ 6፥12 በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ አምላክ ሲጸልይ አደረ። Ἐγένετο δὲ ἐν ταῖς ἡμέραις ταύταις ἐξελθεῖν αὐτὸν εἰς τὸ ὄρος προσεύξασθαι, καὶ ἦν διανυκτερεύων ἐν τῇ προσευχῇ τοῦ Θεοῦ.

ኢየሱስ በጸሎት የሚለምን ለማኝ ከሆነ ጸሎቱን ሰምቶ የሚመልስለት አምላኩ ተለማኝ ነው። ሰዎችም የእርሱ ፈለግ ተከትለው አምላኩን ቢለምኑ ልመናቸውን ይሰማል፦
ዮሐንስ 15፥16 አብም በስሜ "የምትለምኑትን" ሁሉ ይሰጣችኃል። ἵνα ὅ τι ἂν αἰτήσητε τὸν Πατέρα ἐν τῷ ὀνόματί μου δῷ ὑμῖν.

"በስሜ" የሚለው ይሰመርበት! በኢየሱስ ስም አብ ሲለመን ልመናውን ሰምቶ አብ ይሰጣል። አብን በኢየሱስ ስም ሲለመን ኢየሱስ ደግሞ አብን አማላጅ ሆኖ ይለምናል፦
ዮሐንስ 14፥14 ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ። ἐάν τι αἰτήσητε ἐν τῷ ὀνόματί μου, ἐγὼ ποιήσω.

"አደርጋው"I will do" የሚለው መጻኢ ግሥ "ፓኤሶ" ποιήσω ሲሆን ምን እንደሚያደርግ ዐውዱ ላይ ተገልጿል፦
ዮሐንስ 14፥15 እኔም አብን "እለምናለሁ"፥ κἀγὼ ἐρωτήσω τὸν Πατέρα

"እለምናለሁ"I will pray" በማለት "አደርጋለው" የሚለው ድርጊት ጸሎት እንደሆነ እንቅጩን ፍርጥ አርጎ ተናግሯል። ኢየሱስ ለማኝ እንዲሁ አምላክ ደግሞ ተለማኝ ከሆነ ኢየሱስ በአምላክ ቀኝ አብን ስለ አማኞች ይለምናል፦
ሮሜ 8፥34 በአምላክ ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ "የሚማልደው" ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ὅς ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ Θεοῦ, ὃς καὶ ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

"ኢንቱካኖ" ἐντυγχάνω ማለት "ጠራ" "ማለደ" "አማለደ" ማለት ሲሆን ኢየሱስ ለማኝ መሆኑን አምላክ ተለማኝ መሆኑን ፍንትው አርጎ ያሳያል፥ በቋንቋ ደረጀ "ማለደ" ማለት "ለመነ" "ደጅ ጠና" ማለት ነው። ኢየሱስ አማላጅ ስለመሆኑ ከዚህ ቀደም የጻፍኩትን ያንብቡ፦ https://t.me/Wahidcom/3374

ኢየሱስ ለሐዋርያቱ፦"አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኃል" ባለው መሠረት ሐዋርያት አብን በተግባር ለምነውታል፦
የሐዋርያት ሥራ 4፥29 አሁንም ጌታ ሆይ! ወደ ዛቻቸው ተመልከት! ባሪያዎችህ በፍጹም ግልጥነት ቃልህን እንዲናገሩ ስጣቸው።
የሐዋርያት ሥራ 4፥30 ለመፈወስም እጅህን ስትዘረጋ በቅዱስ ባሪያ በኢየሱስ ስም ምልክት እና ድንቅ ይደረግ። ἐν τῷ τὴν χεῖρά ἐκτείνειν σε εἰς ἴασιν καὶ σημεῖα καὶ τέρατα γίνεσθαι διὰ τοῦ ὀνόματος τοῦ ἁγίου Παιδός σου Ἰησοῦ.

"ፓይዶስ" Παιδός ማለት "ባሪያ" "አገልጋይ" ማለት ነው፥ በዚህ ባሪያ ስም የሚለመነው ጌታ አብ እንደሆነ በቂ ማሳያ ነው። ኢየሱስ ሰማይ ላይ እንደ አምላክ ተገልጋይ ሳይሆን አገልጋይ ነው፦
ዕብራውያን 8፥2 እርሱም የመቅደስ እና የእውነተኛይቱ ድንኳን "አገልጋይ" ነው፥ እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት።
6.0K viewsedited  04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 00:11:11 የሁሉ ጌታ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

6፥164 በላቸው «እርሱ አላህ የሁሉ ነገር ጌታ ሲሆን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

አምላካችን አሏህ ስለ ራሱ በሦስተኛ መደብ "የሁሉ ነገር ጌታ" እንደሆነ ይናገራል፦
6፥164 በላቸው «እርሱ አላህ የሁሉ ነገር ጌታ ሲሆን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ሚሽነሪዎች ይህንን አንቀጽ ይዘው "በባይብል ኢየሱስ "የሁሉ ጌታ" ተብሏልና የእርሱ ጌትነት የባሕርይ ነው" በማለት ይህንን ጥቅስ ይጠቅሳሉ፦
የሐዋርያት ሥራ 10፥36: "የሁሉ ጌታ በሚሆን" በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እየሰበከ ይህን ቃል ወደ እስራኤል ልጆች ላከ። Tὸν λόγον ὃν ἀπέστειλεν τοῖς υἱοῖς Ἰσραήλ, εὐαγγελιζόμενος εἰρήνην διὰ Ἰησοῦ χριστοῦ― οὗτός ἐστιν πάντων κύριος―

ሲጀመር "የሁሉ ጌታ በሚሆን"he is Lord of all" የሚለው ኃይለ-ቃል በ 400 ድኅረ ልደት በተዘጋጀው ኮድ በፊደል D በቁጥር 05 በሆነው ኮዴክስ ቤዛይ ላይ በቅንፍ የተቀመጠ ነው፦
― οὗτός ἐστιν πάντων κύριος―

ለማመሳከሪያ ኦርጅናሉ ስለሌለ የተለያዩ ቨርዥኖች "he is Lord of all" የሚለውን በቅንፍ አስቀምጠውታል፥ ለምሳሌ፦
1. English Standard Version
2. King James Bible
3. New American Standard Bible
4. American Standard Version
5. Literal Standard Version
6. Young's Literal Translation
ተጠቃሾ ናቸው።

ልክ ሉቃስ 3፥23 "እንደመሰላቸው"as was supposed" የሚለው ኮዴክስ ቤዛይ ላይ በቅንፍ እንደተቀመጠው ማለት ነው፦
ሉቃስ 3፥23 ― ὡς ἐνομίζετο―

ሲቀጥል ጥቅሱ ላይ "የሁሉ" የሚለው ገላጭ ቅጽል "ፓንቶን" πάντων አይሁድ እና አሕዛብ ለማሳየት የገባ አንጻራዊ እንጂ ፍጹማዊ አይደለም። ለምሳሌ፦ "ፓንቶን" የሚለው ቃል በአንጻራዊ ደረጃ ይመጣል፦
1 ቆሮንቶስ 4፥13 እስከ አሁን ድረስ የዓለም ጥራጊ "የሁሉም" ጉድፍ ሆነናል። δυσφημούμενοι παρακαλοῦμεν· ὡς περικαθάρματα τοῦ κόσμου ἐγενήθημεν, πάντων περίψημα ἕως ἄρτι.

ጳውሎስ "የሁሉም" ሰው ጉድፍ ሆነናል" ሲል በአንጻራዊ እንጂ ጳውሎስ የማያውቁት ሁሉንም ያጠቃልላል ማለት አይደለም። በተመሳሳይም ኢየሱስ "የሁሉ ጌታ" የተባለው በአንጻራዊ ደረጃ ነው፥ ምክንያቱም አንደኛ ጌትነቱ መነሻ አለው፣ ሁለተኛ ከእርሱ በላይ ያለውን ጌታውን "ጌታዬ" እያለ ተናግሯል፣ ሦስተኛ የእርሱ ጌታ አብ እርሱን "ባሪያዬ" ብሎታል፣ አራተኛ ከበላዩ ራስ አለው።
ሢሠልስ አማኞች "የሁሉ ጌታ" ተብለዋል፦
ገላትያ 4፥1 ነገር ግን እላለሁ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ ምንም "የሁሉ ጌታ" ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም። Λέγω δέ, ἐφ’ ὅσον χρόνον ὁ κληρονόμος νήπιός ἐστιν, οὐδὲν διαφέρει δούλου κύριος πάντων ὤν,

"ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ ምንም "የሁሉ ጌታ" ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም" የተባለው ሕፃን አማንያንን እንደሆነ ዐውደ ንባቡ"contextual passage" ይናገራል፦
ገላትያ 4፥2-3 ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው። እንዲሁ እኛ ደግሞ ሕፃናት ሆነን ሳለን ከዓለም መጀመሪያ ትምህርት በታች ተገዝተን ባሪያዎች ነበርን።
ገላትያ 4፥7 ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።

ዮሴፍ በአንጻራዊ ደረጃ በግሪክ ሰፕቱአጀንት "የሁሉ ጌታ" ተብሏል፦
ዘፍጥረት 45፥9 "አምላክ" በግብፅ ምድር ላይ "የሁሉ ጌታ" አደረገኝ። τάδε λέγει ὁ υἱός σου ᾿Ιωσήφ· ἐποίησέ με ὁ Θεὸς κύριον πάσης γῆς Αἰγύπτου·

ዮሴፍ በመደረግ "የሁሉ ጌታ" ከተባለ ኢየሱስም በመደረግ "የሁሉ ጌታ" ቢባል ያንስበታልን? ወይስ ይበዛበታል? ፈጣሪ አምላክ ዮሴፍን ጌታ ስላረገው ዮሴፍ፦ "አምላክ" በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ "ጌታ" አደረገኝ" ብሎአል፦
ዘፍጥረት 45፥9 "አምላክ" በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ "ጌታ" አደረገኝ። שָׂמַ֧נִי אֱלֹהִ֛ים לְאָדֹ֖ון לְכָל־מִצְרָ֑יִם

"ጌታ አደረገኝ" ሲል የዓለማቱ ጌታ ሆነ ማለት ሳይሆን በጸጋ እና በስጦታ ያገኘው እንጂ የባሕርይ ጌትነት በፍጹም አይደለም። በተመሳሳይም የኢየሱስ ጌትነት በመደረግ ላይ የተመሠረተ መነሾ ያለው ስለሆነ የባሕርይ ጌትነት በፍጹም አይደለም፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥36 ኢየሱስን አምላክ ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ። ἀσφαλῶς οὖν γινωσκέτω πᾶς οἶκος Ἰσραὴλ ὅτι καὶ Κύριον αὐτὸν καὶ Χριστὸν ἐποίησεν ὁ Θεός, τοῦτον τὸν Ἰησοῦν.

እዚህ አንቀጽ ላይ "አምላክ" ባለቤት ሲሆን "ኢየሱስ" ተሳቢ ነው፥ በባለቤት እና በተሳቢ መካከል "እንዳደረገው" የሚል ተሻጋሪ ግሥ አለ። ጌታ አድራጊ አንዱ አምላክ ሲሆን ጌታ ተደራጊ ኢየሱስ ነው፥ አምላክ ኢየሱስን ጌታ ካረደገው የኢየሱስ ጌትነት መነሾ ያለው ስለሆነ ጌታ ከመደረጉ በፊት በባዶነት ስለሚቀደም ጌትነቱ ሥልጣን እና ሹመት ወይም እልቅና እና ማዕረግን ብቻ ያሳያል እንጂ የባሕርይ ገንዘቡ መሆኑን በፍጹም አያሳይም።
ስለዚህ ኢየሱስ "የሁሉ ጌታ" የተባለው ልክ አማኞች እና ዮሴፍ በተባሉበት ሒሣብ አንጻራዊ ነው፥ የኢየሱስ ጌታ አሏህ ግን በጌትነቱ ባርነት የሌለበት የሁሉም አንድ ጌታ አምላክ ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
10.2K views21:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-15 17:30:08 አዳም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

32፥7 ያ የፈጠረውን ነገር ሁሉ ያሳመረው የሰውንም ፍጥረት ከጭቃ የጀመረው ነው፡፡ الَّذِي أَحْسَنَ كُلَّ شَيْءٍ خَلَقَهُ ۖ وَبَدَأَ خَلْقَ الْإِنسَانِ مِن طِينٍ

"አዳም" אָדָם ማለት በዕብራይስጥ "ሰው" ማለት ሲሆን የመጀመሪያው ሰው ማንነት እና ምንነት ነው፦
ዘፍጥረት 2፥7 ያህዌህ አምላክ "ሰውን" ከምድር አፈር አበጀው። וַיִּיצֶר֩ יְהוָ֨ה אֱלֹהִ֜ים אֶת־הָֽאָדָ֗ם עָפָר֙ מִן־הָ֣אֲדָמָ֔ה

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰው" ለሚለው የገባው ቃል "ሃ አዳም" הָֽאָדָ֗ם ነው፥ "ሃ" הָֽ አመልካች ውስን መስተአምር ሲሆን በኢ-አመልካች አመልካች "አዳም" אָדָם የመጀመሪያው ሰው የተጸውዖ ስም ነው፦
ዘፍጥረት 5፥5 "አዳም" የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፤ ሞተም። וַיִּֽהְי֞וּ כָּל־יְמֵ֤י אָדָם֙ אֲשֶׁר־חַ֔י תְּשַׁ֤ע מֵאֹות֙ שָׁנָ֔ה וּשְׁלֹשִׁ֖ים שָׁנָ֑ה וַיָּמֹֽת׃ ס

"አዳም" אָדָם ለመጀመሪያው ሰው የምንነቱ እና የማንነቱ የተጸውዖ ስሙ ነው። ነገር ግን ይህ አዳም ብቻውን በነበረበት ጊዜ ከጎኑ እረዳት ሌላ ሰው ተፈጠረለት፦
ዘፍጥረት 2፥18 ያህዌህ አምላክ አለ፦ "ሰው" ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፥ የሚመቸውን ረዳት ልፍጠርለት"። וַיֹּ֙אמֶר֙ יְהוָ֣ה אֱלֹהִ֔ים לֹא־טֹ֛וב הֱיֹ֥ות הָֽאָדָ֖ם לְבַדֹּ֑ו אֶֽעֱשֶׂהּ־לֹּ֥ו עֵ֖זֶר כְּנֶגְדֹּֽו׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰው" ለሚለው የገባው ቃል "ሃ አዳም" הָֽאָדָ֗ם ሲሆን ይህ አንዱ አዳም አንድ ነጠላ ማንነት ነበረ፥ ከጎኑ አንዲት አጥንት ወስዶ ሔዋን የምትባል ሴት ፈጠረ። በዚያን ቀን ወንዱ አዳም እና ሴቷ ሔዋን በጋራ "አዳም" אָדָ֔ם ተብለዋል፦
ዘፍጥረት 5፥2 ወንድ እና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን "አዳም" ብሎ ጠራቸው። זָכָ֥ר וּנְקֵבָ֖ה בְּרָאָ֑ם וַיְבָ֣רֶךְ אֹתָ֗ם וַיִּקְרָ֤א אֶת־שְׁמָם֙ אָדָ֔ם בְּיֹ֖ום הִבָּֽרְאָֽם׃ ס

ግን ሔዋን "አዳም" אָדָ֔ם ናት ወይ? ስንል የመጀመሪያው አዳም ባትሆንም ሌላዋ አዳም ናት። ሁለቱ ሰዎች ተራክቦ አርገው ሲዋለዱ ብዙ ሰዎች በዙ፦
ዘፍጥረት 6፥1 እንዲህም ሆነ "ሰዎች" በምድር ላይ መብዛት በጀመሩ ጊዜ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው። וַֽיְהִי֙ כִּֽי־הֵחֵ֣ל הָֽאָדָ֔ם לָרֹ֖ב עַל־פְּנֵ֣י הָֽאֲדָמָ֑ה וּבָנֹ֖ות יֻלְּד֥וּ לָהֶֽם׃

እዚህም አንቀጽ ላይ "ሰዎች" ለሚለው የገባው ቃል "ሃ አዳም" הָֽאָדָ֗ם እንደሆነ ልብ አድርግ! በዓለም ላይ ዛሬ በጥናት 7.8 ቢልዮን ሰዎች አሉ፥ ሰውን ብዙ ያረገው ማንነቱ እንደሆነ እሙን እና ቅቡል ነው።
ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ ግን በማንነት ሆነ በምንነት አንድ ስለሆነ የምንነቱ ስም እና የማንነቱ ስም "አሏህ" ይባላል። ሰዎች ይህንን ምንነት እና ማንነት በዕውቀት እየመረመሩ ፈልገው ያገኙት ዘንድ ሰዎችን ሁሉ ከአዳም ፈጠራቸው፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥26 ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደ ሆነ አምላክን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ "ከ-"አንድ" ፈጠረ። ἐποίησέν τε ἐξ ἑνὸς πᾶν ἔθνος ἀνθρώπων κατοικεῖν ἐπὶ παντὸς προσώπου τῆς γῆς,

"አምላክን ይፈልጉ ዘንድ" የሚለው ይሰመርበት! እዚህ አንቀጽ ላይ "አንድ" የተባለው የመጀመሪያው ሰው አዳም ሲሆን እርሱ አንድ ምንነት እና ማንነት እንደነበረ ካወቅን ዘንዳ ሁላችንን የፈጠረ አንድ አምላክ አንድ ማንነት እንደሆነ መርምረን መረዳት ችለናል፦
ሚልክያስ 2፥10 አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? הֲלֹ֛וא אֵ֥ל אֶֽחָ֖ד בְּרָאָ֑נוּ

አዳም ከጎኑ ሴት የምትባል ሰው ባትገኝ እና በመዋለድ ባይባዛ ኖሮ በማንነት እና በምንነት አንድ የሆነ ሰው እና ስሙም አንድ የሆነ ሰው ብቻ ይኖር ነበር፥ ነገር ግን ሰው በዓለም ላይ ብዙ ስለሆነ እከሌ ወይም እከሊት የሚል የተጻውዖ ስም ለእያንዳንዱ ሰው ወቶለታል።

ፈጣሪ ግን አንድ አምላክ ስለሆነ የምንነቱ ስም እና የማንነቱ ስም "አሏህ" ሲሆን ከእርሱ ውጪ ሌላ አምላክ ስለሌለ ብዙ አሏህ የለም፥ ምንነቱን የሚያሳዩ የባሕርያት ስሞች ቢኖሩትም የእርሱ ኢሥሙል ዐለም እና ኢሥሙዝ ዛት “አሏህ” ٱللَّه ነው። “ኢሥሙል ዐለም” اِسْم العَلَم ማለት “የተጸውዖ ስም”proper name” ማለት ሲሆን "ኢሥሙዝ ዛት" اِسْم الذَات ማለት "የምንነት ስም" ማለት ነው፥ “አሏህ” ٱللَّه ማለት ትርጉሙ “አምልኮ የሚገባው” ማለት ሲሆን ከጥንትም ቁርኣን ከመውረዱ በፊት በሴማዊ ዳራ ደግሞ ከሁሉ በላይ የሆነው አንዱ አምላክ ሲጠራበት የነበረ ስም እንደነበር የተለያየ መድብለ ዕውቀቶች"encycolopedias" ያትታሉ፦
1. የሃይማኖት መድብለ-ዕውቀት 1987: “አሏህ የሚለው ስም ሥረ መሠረት የጋራ በሆኑ በተለያዩ ጥንታዊ የሴም ቋንቋዎች ይገኛል” ገጽ 27.
Encycolopedia of religion 1987: “the orgin of Allah is found in a root common to various ancient semetic languages” p27.

2. የክርስትና መድብለ-ዕውቀት 2001: “ቅድመ-ቁርኣን ዐረብ ተናጋሪ ክርስቲያን እና አይሁድ እንዲሁ አሏህ ለታላቁ አምላክ ይጠቀሙበት ነበር” ገጽ 101.
Encyclopedia of Christianity 2001: “before Quran Arabic-speaking Christians and Jews also refer to supreme God as Allāh” page 101.

3. የኢሥላም መድብለ-ዕውቀት 1913: “ዐረቦች ቅድመ-ነቢዩ ሙሐመድ በነበሩት ዘመናት አሏህ የሚባል ታላቅ አምላክ ያመልኩ ነበር” ገጽ 302.
Encyclopedia of Islam 1913: “Before prophet Muhammad Arabian was worshiping supreme God who is Allah” page 302.

4. የብሪታኒካ መድብለ-ዕውቀት 1996: “ቅድመ-ቁርኣን በነበሩት ዐረቢያን መጻሕፍት ውስጥ አላህ የሚለው ቃል ይገኛል” ገጽ 106.
Encyclopedia of britannica 1996: “Before Quran The word Allah was in the Arabic books” page 106.

የአዳምን አፈጣጠር አይታችሁ የአሏህ ስም የምትረዱ ያርጋችሁ! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
10.4K viewsedited  14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 08:21:23 የሰንበት ጌታ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥124 ሰንበት የተደረገው በእነዚያ በእርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا جُعِلَ السَّبْتُ عَلَى الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ

"ሠብት" سَّبْت የሚለው ቃል "ዕረፍት" ሲሆን "ሰንበት" የሚለው የግዕዙ ቃል በራሱ "እረፍት" ማለት ነው፥ "ሠብዓህ" سَبْعَة ማለት እራሱ "ሰባት" ማለት ነው። በዚህ በሰባተኛው ቀን እረፍት የተደረገው በእስራኤል ልጆች ብቻ ነው፦
16፥124 ሰንበት የተደረገው በእነዚያ በእርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا جُعِلَ السَّبْتُ عَلَى الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ

ወደ ባይብንም ስንገባ "ሰንበት" ማለት "እረፍት" ማለት ሲሆን ሰው ስድስት ቀን ሠርቶ በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ቀኑ ነው፦
ዘሌዋውያን 23፥3 ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፥ በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት ነው።

ሰው የተፈጠረው አምላኩን እንዲያመልክ ሲሆን አምላኩ ለሰው ሰንበትን የፈጠረለት እንዲያርፍበት ነው፥ ሰንበት ለሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም፦
ማርቆስ 2፥27-28 ደግሞ አላቸው፦ ሰንበት ለሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም። እንዲሁም የሰው ልጅ ለሰንበት እንኳ ጌታዋ ነው።

በባይብል ዐውድ "ሰው" እና "የሰው ልጅ" ተብሎ ተያይዞ ከመጣ አጠቃላይ የሰው ልጆችን ያመላክታል፦
ኢዮብ 25፥6 ይልቁንስ ብስብስ የሆነ "ሰው"፥ ትልም የሆነ "የሰው ልጅ" ምንኛ ያንስ!
መዝሙር 144፥3 አቤቱ እርሱን ታውቀው ዘንድ "ሰው" ምንድር ነው? ታስብለት ዘንድ "የሰው ልጅ" ምንድር ነው?
ኢሳይያስ 51፥12 የሚሞተውን "ሰው" እንደ ሣርም የሚጠወልገውን "የሰው ልጅ" ትፈራ ዘንድ አንተ ማን ነህ?
ዘኍልቍ 23፥19 ሐሰትን ይናገር ዘንድ አምላክ "ሰው" አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ "የሰው ልጅ" አይደለም።

አምላክ ሰው እና የሰው ልጅ አይደለም፥ እንግዲህ ሰው" እና "የሰው ልጅ" አጠቃላይ የሰው ልጆችን ካመለከተ ሰንበት የተፈጠረው ለሰው ማረፊያ ስለሆነ የሰው ልጅ ለሰንበት እንኳ ጌታዋ ነው። ሴት “ለ”-ወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ “ለ”-ሴት አልተፈጠረምና፥ ወንድ የሴት ጌታዋ ነው፦
1 ቆሮንቶስ 11፥9 ሴት “ለ”-ወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ “ለ”-ሴት አልተፈጠረምና።
ዘፍጥረት 3፥16 ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም "ገዥሽ" ይሆናል።
1ኛ ጴጥሮስ 3፥5 ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ ለባሎቻቸው ሲገዙ ተሸልመው ነበርና፥ እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ ጌታ" ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት።
ዘፍጥረት18፥12 ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች። ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? "ጌታዬም" ፈጽሞ ሸምግሎአል።

ሴት ለወንድ ስለተፈጠረች እና ወንድ የሴት ጌታዋ ስለሆነ "ወንድ የባሕርይ ጌታ ነው" እንደማንል ሁሉ ሰንበት ለሰው ስለተፈጠረች እና የሰው ልጅ የሰንበት ጌታዋ ስለሆነ "የሰው ልጅ የባሕርይ ጌታ ነው" አንልም።
ሲቀጥል ኢየሱስ "የሰንበት ጌታ ነው" ቢባል እንኳን ከዐውዱ አንጻር ሰንበትን የሰጠ ነው ተብሎ በፍጹም አይተረጎምም፥ ከዚያ ይልቅ በሰንበት ቀን መልካም በማድረጉ በሰንበት ላይ የበላይ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
ሢሠልስ "የጌታችን አምላክ" የሚለው ቃል የሰንበት ጌታ የተባለው ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ያሳብቃል፦
ኤፌሶን 1፥17 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ἵνα ὁ Θεὸς τοῦ Κυρίου ἡμῶν Ἰησοῦ Χριστοῦ,

ዐማርኛ ግልጽ ባይሆንም ግሪኩ "ሆ ቴዎስ ቶዩ ኩርዮዩ ሄሞን" ὁ Θεὸς τοῦ Κυρίου ἡμῶν ማለትም "የጌታችን አምላክ"the God of our Lord" ይላልና። "ጌታችን" ብዙ ቦታ ለፍጡራን ሰዎች ማዕረግ ሆኖ ጥቅም ላይ ውሏል፥ ለምሳሌ፦ ዮሴፍ፣ ሙሴ፣ ዳዊት "ጌታችን" ተብለዋል፦
ዘፍጥረት 44፥9 እኛም ደግሞ "ለ-"ጌታችን ባሪያዎች እንሁን።
ዘኁልቅ 36፥2 እግዚአብሔር አንተን "ጌታችንን" አዘዘህ።
1ኛ ነገሥት 1፥43 በእውነት "ጌታችን" ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን አነገሠው።

አንድ ሰው ተነስቶ፦ "የእኛ ጌታ አምላክ አለው" ቢልህ ጌታቸው ማእረግ እንጂ እውን ለጌታ የፈጠረው አምላክ አለውን? አሏህ ይቅር ይበለን! ኢየሱስን የባሕርይ ጌታ ለማድረግ የምትፍጨረጨሩት መፍጨርጭ እንዲህ ድባቅ ይገባል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
7.3K viewsedited  05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 09:22:24 የውሻ ልጋግ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

7፥176 ብጤውም ብታባርረው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ ወይም ብትተወው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ እንደ ኾነ ውሻ ነው፡፡ فَمَثَلُهُ كَمَثَلِ الْكَلْبِ إِن تَحْمِلْ عَلَيْهِ يَلْهَثْ أَوْ تَتْرُكْهُ يَلْهَث

"ልጋግ" ማለት "ላጭ" ማለት ሲሆን ከውሻ አፍ የሚወጣው ልጋግ ሰውን የሚጎዱ ጀርሞችን ስለያዘ ነጃሣህ ነው፥ "ነጃሣህ" نَجَاسَة‎ የሚለው ቃል "ነጀሠ" نَجُسَ‎ ማለትም "አረከሰ" "አቆሸሸ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ርኩስ" "ቆሻሻ" ማለት ነው። የውሻ ልጋግ ስለሚነጅሥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" በቅዱስ ንግግራቸው፦ "ከእናንተ አንዳችሁ ከዕቃው ውስጥ ውሻ ከጠጣ ዕቃውን ሰባት ጊዜ ይጠበው" ያሉን፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1 ሐዲስ 98
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከእናንተ አንዳችሁ ከዕቃው ውስጥ ውሻ ከጠጣ ዕቃውን ሰባት ጊዜ ይጠበው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ "‏ إِذَا شَرِبَ الْكَلْبُ فِي إِنَاءِ أَحَدِكُمْ فَلْيَغْسِلْهُ سَبْعَ مَرَّاتٍ ‏"‏ ‏.‏

ከታች የለቀኩላችሁ ሁለት ቪድዮ የውሻ ልጋግ እና ከጸጉሩ የሚወጣው ነገር ምን ያህል እንደሚነጅሥ የምርምር ጥናቱ ያሳያል።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
9.3K views06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 13:29:00 ንጽጽር በስልጢኛ ለምትፈልጉ ይህንን ሊንክ ያስፈንጥሩ፦ https://t.me/wahidcomselitiy
2.2K viewsedited  10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 03:59:24 ቀጥተኛው መንገድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

36፥4 "በቀጥታም መንገድ ላይ ነህ"፡፡ عَلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ

"ሲሯጥ" صِرَٰط ማለት በመነሻ እና በመዳረሻ መካከል ያለ "መንገድ" ማለት ሲሆን እዚህ ዐውድ ላይ "መንገድ" እያልን የምንጦምረው እማሬአዊ የሆነውን የአስፋት መንገድ ሳይሆን ወደ ጀነት የሚያደርሰውን ፍካሬአዊ የሆነውን መንገድ ነው። አምላካችን አሏህን በብቸኝነት ማምለክ ወደ ጀነት የሚያደርስ "ቀጥተኛው መንገድ" ነው፦
36፥61 "አምልኩኝ! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው" በማለትም አላዘዝኩምን? وَأَنِ ٱعْبُدُونِى ۚ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ

"ይህ" የሚለው አመልካች ተውላጠ ስም "አምልኩኝ" የሚለውን ቃል አመላካች ነው። ዒሣም በተልኮው አሏህን በብቸኝነት ማምለክ "ቀጥተኛ መንገድ" እንደሆነ አበክሮ እና አዘክሮ ነግሮናል፦
3፥51 አላህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነዉ፥ ስለዚህ "አምልኩት! ይህ "ቀጥተኛ መንገድ" ነዉ" አላቸዉ። إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ

እዚህም አንቀጽ ላይ "ይህ" የሚለው አመልካች ተውላጠ ስም "አምልኩት" የሚለውን ቃል አመላካች ነው። ይህ አንዱን አምላክ በብቸንነት ማምለክ ለኢብራሂም የተገለጠ የኢብራሂም መንገድ ነው፥ አምላካችን አሏህ የኢብራሂምን መንገድ መርቶናል፦
6፥161 «እኔ ጌታዬ ወደ "ቀጥተኛው መንገድ" ትክክለኛን ሃይማኖት ወደ እውነት አዘንባይ ሲኾን የአብርሃምን መንገድ መራኝ፡፡ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል፡፡ قُلْ إِنَّنِى هَدَىٰنِى رَبِّىٓ إِلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ دِينًۭا قِيَمًۭا مِّلَّةَ إِبْرَٰهِيمَ حَنِيفًۭا ۚ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

አሁንም "ቀጥተኛው መንገድ" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! አንድ ሙሥሊም በቀጥተኛው መንገድ ላይ ስለሆነ አምላካችን አሏህ፦ "በቀጥታም መንገድ ላይ ነህ" ብሏል፦
36፥4 "በቀጥታም መንገድ ላይ ነህ"፡፡ عَلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ
43፥43 ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ! አንተ "በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና"።فَاسْتَمْسِكْ بِالَّذِي أُوحِيَ إِلَيْكَ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

አንድ ሙሥሊም ቁርኣንን አጥብቆ ከያዘ በቀጥተኛው መንገድ ነው። ከላይ በቁና ጥቅስ እንደተጠቀሰው ሙሥሊም በቀጥተኛ መንገድ ስለሆነ እና ይህም ቀጥተኛ መንገድ አሏህን በብቸኝነት ማምለክ እንደሆነ ተረድቶ አንድ ዳዒ ሰዎችን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይጣራል፦
23፥73 አንተም ወደ "ቀጥተኛው መንገድ" በእርግጥ ትጠራቸዋለህ። وَإِنَّكَ لَتَدْعُوهُمْ إِلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ
16፥125 "ወደ ጌታህ መንገድ" በጥበብ እና በመልካም ግሳጼ ጥራ፡፡ ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ

አንድ ሙሥሊም በቀጥተኛ መንገድ ላይ ባይሆን ኖሮ ወደ ቀጥተኛ መንገድ መጥራቱ ትርጉም አልባ ይሆን ነበር። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሙሥሊም በቀጥተኛ መንገድ ነው።
ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ታዲያ ለምንድን ነው "ቀጥተኛውን መንገድ ምራን" የምንለው? ይህንን ለመረዳት ይህንን ምሳሌ አጢኑት! ለምሳሌ፦ እኔ ፒያሳ መሄድ ፈልጌ የፒያሳን መንገድ መነሻውን ከጦ ሃይሎች ሰፈር አንድ ሰው ከመራኝ በኃላ መንገዱ በጉዞ ልደታ ጋር ስደርስ ወይም ብሔራዊ ጋር ስደርስ መንገድ እንዳልስት እስከመጨረሻው ምሪት ያስፈልገኛል፥ በተመሳሳይ ይህ ቀጥተኛ መንገድ መነሻውን አሏህ ከመራን በኃላ በጉዞ ላይ እያለን ከመንገዱ እንዳንወጣ ምሪት እስከመጨረሻው ለማግኘት አሏህን በቀን 17 ጊዜ ሶላት ላይ ስንቆም በሱረቱል ፋቲሓህ ላይ "ቀጥተኛውን መንገድ ምራን" እንድንል ነግሮናል፦
1፥6 "ቀጥተኛውን መንገድ ምራን። ٱهْدِنَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلْمُسْتَقِيمَ

ምክንያቱም ከአይሁዳውያን ብዙኃኑ ከቀጥተኛው መንገድ ወጥተው አሏህ ተቆጥቷቸዋል፥ ከክርስቲያኖች ብዙኃኑ ከቀጥተኛው መንገድ ወጥተው ተሳስተዋል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚይ መጽሐፍ 47 ሐዲስ 3212
ዐዲይ ኢብኑ ሓቲም እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ "አይሁዳውያን የተቆጣባቸው ናቸው፥ ክርስቲያኖች የተሳቱተት ናቸው"። عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْيَهُودُ مَغْضُوبٌ عَلَيْهِمْ وَالنَّصَارَى ضُلاَّلٌ ‏”‏ ‏.‏

ነገር ግን በጽናት ከአይሁዳውያን ጥቂት ያልተቆጣቸው እንዲሁ ከክርስቲያኖች ጥቂት ያልተሳሳቱ ሙዋሒዲን ነበሩ፥ እኛም ሳንጸና ከመንገዱ እንዳንስት የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋለላቸውን መንገድ ምራን ብለን እንቀራለን፦
1፥7 የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን፣ በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን"በሉ። صِرَٰطَ ٱلَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ ٱلْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا ٱلضَّآلِّينَ

አምላካችን አሏህ ሰዎችን ወደ ቀጥተኛው መንገድ የምንጠራ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
4.0K viewsedited  00:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 18:32:32 የወርሽ ቂርኣህ በሥመላህን መግቢያ አርጎ ተሕሚድን የመጀመሪያው አንቀጽ አርጎ በዚህ መልኩ ያስቀምጧል፦
"በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ
1፥1 ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው። الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ
1፥2 እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ። الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ
1፥3 የፍርዱ ቀን ንጉሥ ለኾነው፡፡ مَلِكِ يَوْمِ الدِّينِ
1፥4 አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡ إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
1፥5 ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ
1፥6 የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን። صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ
1፥7 በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን" በሉ፡፡  غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ

በሥመላህ የቁርኣን ክፍል ነው፥ በአንዱ ቂርኣህ በአንቀጽ መልኩ መቀመጡ እና በሌላው ቂርኣህ በአንቀጽ መልኩ አለመቀመጡ ከተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" የመጣ የአነባነብ ስልት"mode of recitation" ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 13
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ጂብሪል ለእኔ በአንድ ሐርፍ አቀራር ይቀራልኝ ነበር፥ ከዚያም እኔ በሌላ ሐርፍ እንዲያስቀራኝ ጠየኩት። በተደጋጋሚ ስጠይቀው በሰባት አሕሩፍ በመቅራት ጨመረልኝ። أَنَّ ابْنَ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ حَدَّثَهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ أَقْرَأَنِي جِبْرِيلُ عَلَى حَرْفٍ فَرَاجَعْتُهُ، فَلَمْ أَزَلْ أَسْتَزِيدُهُ وَيَزِيدُنِي حَتَّى انْتَهَى إِلَى سَبْعَةِ أَحْرُفٍ ‏”‌‏.‏

የሐፍሥ ሪዋያህ፣ የወርሽ ሪዋያህ፣ የቃሉን ሪዋያህ፣ የዱሪ ሪዋያህ ወዘተ ሲባል ከአሏህ በጂብሪል ለተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" የተወረደ ግልጠተ መለኮት እንጂ ሰዎች የፈጠሩት ልዩነት አይደለም። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ በስመላህ የቁርኣን ክፍል ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 4 ሐዲስ 56
አነሥ እንደተረከው፦ "በመካከላችን የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ሆነው ነበርና ተኙ፥ ከዚያም በፈገግታ እራሳችፕውን አነሱ። እኛም፦ "የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! ለምን ፈገግ አሉ? አልን፥ እርሳቸውም፦ "ሡራህ ወደ እኔ ተወርዶልኛል" አሉ። እርሳቸው፦ "በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
እኛ በጣም ብዙ በጎ ነገሮችን ሰጠንህ፣
ስለዚህ ለጌታህ ስገድ፤ በስሙ ሰዋም፣
ጠይህ እርሱ በእርግጥ የተቆረጠው ነው" የሚለውን ቀሩ"። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ بَيْنَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ذَاتَ يَوْمٍ بَيْنَ أَظْهُرِنَا إِذْ أَغْفَى إِغْفَاءَةً ثُمَّ رَفَعَ رَأْسَهُ مُتَبَسِّمًا فَقُلْنَا مَا أَضْحَكَكَ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ ‏"‏ أُنْزِلَتْ عَلَىَّ آنِفًا سُورَةٌ ‏"‏ ‏.‏ فَقَرَأَ ‏"‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏{‏ إِنَّا أَعْطَيْنَاكَ الْكَوْثَرَ فَصَلِّ لِرَبِّكَ وَانْحَرْ إِنَّ شَانِئَكَ هُوَ الأَبْتَرُ‏}‏ ‏"‏

አያችሁ በሥመላህ የቁርኣን ክፍል ነው። በስመላህ ያለ አንቀጽ መቀመጥ እንደሚችል ደግሞ ይህ ሐዲስ ያሳያል፦
ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 131
አቢ ሁረይራህ”ረ. ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “እስከሚያስምር ድረስ ለሚቀራው ወዳጁ የሚያማልድ ሠላሳ አናቅጽ የያዘ ሡራህ በቁርኣን ውስጥ አለ፥ እርሱም፦ “ያ ንግሥና በእጁ የኾነው አምላክ የተባረከ(ተመሰገነ) ይሁን” የሚለው ሡራህ ነው”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏”‏ إِنَّ سُورَةً فِي الْقُرْآنِ ثَلاَثُونَ آيَةً شَفَعَتْ لِصَاحِبِهَا حَتَّى غُفِرَ لَهُ ‏{تَبَارَكَ الَّذِي بِيَدِهِ الْمُلْكُ}‏ ‏”‏

ሠላሳ አናቅጽ የያዘ ሡራህ ሡረቱል ሙልክ ሠላሳ የተባለው በስመላህን ሳያካትት ነው። ስለዚህ ሡረቱል ፋቲሓህ ላይ በሥመላህ በአንቀጽ መምጣት እና አለመምጣት ኢሥቲሥናዕ ሆኖ በተለያየ ሪዋያህ መምጣቱ ምንም የትርጉም ልዩነት አያመጣምና እዛ ሰፈር አቧራ ከማስነሳት ይልቅ በመታቀብ "ተሰተሩ" እንላለን። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
4.8K viewsedited  15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ