Get Mystery Box with random crypto!

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

የቴሌግራም ቻናል አርማ wahidcom — ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
የቴሌግራም ቻናል አርማ wahidcom — ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
የሰርጥ አድራሻ: @wahidcom
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.43K
የሰርጥ መግለጫ

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-03-21 17:41:59 ታላቁ ገደል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

23፥100 ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ "ግርዶ" አለ፡፡ وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

በኢሥላም ስለ በርዘኽ ያለው እሳቤ ከብዙ በጥቂቱ አይተን ነበር። በባይብልም ደግሞ ስለ በርዘኽ እንዲህ ይናገራል፦
ሉቃስ 16፥26 ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ የሚፈልጉ እንዳይችሉ፥ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛ እና በእናንተ መካከል ታላቅ "ገደል" ተደርጎአል" አለ።

የገነት ሰዎች ከሲኦል ሰዎች እንዳይተላለፉ እና እንዳይሻገሩ በመካከላቸው ያለው ገደል ምንድን ነው? ባለ ጠጋው በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ ማየቱ በራሱ ሲኦል እና ገነት ከሞት በኃላ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ጊዜአዊ መቆያ ከሆነ በመካከላቸው ያለው ገደል በርዘኽ ነው፦
ሉቃስ 16፥22 ድሀውም ሞተ፥ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት።
ሉቃስ 16፥23 ባለ ጠጋው ደግሞ ሞተና ተቀበረ፥ በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ።

"መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት" የሚለው በራሱ ልክ እንደ አን ናዚዓት እና አን-ናሺጧት መላእክት መኖራቸውን ጉልኅ ማሳያ ነው፥ አብርሃም ያለበት ስፍራ ደግሞ ገነት ነው፦
1ኛ መቃብያን 3፥38 መላእክትም የጣሉዋቸው ሰዎች ሲያዩ ተቀብለው ነፍሳቸውን ይስሐቅ፣ አብርሃም፣ ያዕቆብ ወዳሉበት ተድላ እና ደስታ ወደሚገኝበት ወደ ገነት ወሰዷቸው ።
1ኛ መቃብያን 6፥2 የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርገዋልና ይስሐቅ፣ አብርሃም፣ ያዕቆብ፣ ሰሎሞን፣ ዳዊት እና ሕዝቅያስ ማደሪያቸው ብርሃን የሆነች እና ያማሩ ነገሥታት ሁሉ ባሉበት በገነት ማደሪያቸውን በማይመረመር ብርሃን ያበራል ።

"በአዳም የተነሳ ሁሉም ነፍሳት ሲኦል ገብተው ኢየሱስ ከሲኦል አወጣቸው" የሚለው ትምህርት ባይብላዊ ማስረጃ የሌለው ከመሆንም ባሻገር ከመቃብያን አሳብ ጋር ይጋጫል። ድሀው ሲሞት የሄደበት የአብርሃም እቅፍ ገነት ከተባለ እና ባለ ጠጋው ሲሞት የሄደበት ሲኦል ከተባለ፣ ባለ ጠጋው በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አልዓዛርንም በእቅፉ ካየ፣ አብርሃም በገነት ባለ ጠጋው በሲኦል ሆነው የንግግር ልውጥውጥ ካደረገ እና ሁለቱ እንዳይገናኙ ገደል ካለ ለምን ይሆን ክርስቲያን ሚሽነሪዎች በኢሥላም ያለውን የበርዘኽ እሳቤ የሚሳለቁበት? ስንል ሚሽነሪዎች የራሳቸውን መጽሐፍ ጠንቅቀው አለማወቃቸውን እያሳበቀባቸው ነው። የሁሉም ሰው መንፈስ ወደ ፈጣሪ ይመለሳል፦
መክብብ 12፥7 አፈርም(ሥጋም) ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ አምላክ ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ። וְיָשֹׁ֧ב הֶעָפָ֛ר עַל־הָאָ֖רֶץ כְּשֶׁהָיָ֑ה וְהָר֣וּחַ תָּשׁ֔וּב אֶל־הָאֱלֹהִ֖ים אֲשֶׁ֥ר נְתָנָֽהּ׃

ከአፈር የመጣው ሥጋ ወደ አፈር ሲመለስ መንፈስ ደግሞ ወደ አምላክ ይመለሳል። "ሩአሕ" רוּחַ ማለት "መንፈስ" ማለት ሲሆን በቁርኣን መንፈስ በእሳት ሲቀጣ "በእኛ ላይ ከውኃ አፍስሱብን" ማለታቸውን ስትሳለቁ በባይብል መንፈስ በእሳት ሲቀጣ "በዚህ ነበልባል እሣቀያለሁና የጣቱን ጫፍ በውኃ ነክሮ መላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ስደድልኝ" ማለቱን ስታውቁ ምን ይውጣችሁ ይሆን? "እሳት፣ ውኃ፣ ጣት፣ ምላስ የሩቅ ነገር ምሥጢር ናቸው" ካላችሁ እንግዲያውስ ውኃ እና እሳት የሩቅ ነገር ምሥጢር ናቸው፦
ሉቃስ 16፥24 እርሱም እየጮኸ፦ "አብርሃም አባት ሆይ! ማረኝ፥ በዚህ ነበልባል እሣቀያለሁና የጣቱን ጫፍ በውኃ ነክሮ መላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ስደድልኝ" አለ።

አምላካችን አሏህ ከእሳት ቅጣት ይጠብቀን! የጀነት ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
1.5K viewsedited  14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 08:54:28 በርዘኽ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

23፥100 ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ "ግርዶ" አለ፡፡ وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

አምላካችን አሏህ ሕያው አርጎ እንደፈጠረን በሞት የሚያሞተን እርሱ ነው፥ ካሞተን በኃላ ሁላችንም ወደ እርሱ እንመለሳለን፦
22፥23 እኛም ሕያው የምናደርግ እና የምናሞት እኛው ብቻ ነን፡፡ وَإِنَّا لَنَحْنُ نُحْيِي وَنُمِيتُ
10፥56 እርሱ ሕያው ያደርጋል ያሞታልም፥ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ هُوَ يُحْيِي وَيُمِيتُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
5፥105 የሁላችሁም መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡ إِلَى اللَّهِ مَرْجِعُكُمْ جَمِيعًا فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

"ቀብር" قَبْر የሚለው ቃል "ቀበረ" قَبَرَ ማለትም "ሸፈነ" "ደበቀ" "ሸሸገ" "ቀበረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሽፍን" "ድብቅ" "ሽሽግ" "ቀብር" ማለት ነው፥ "ቀብር" አጠቃላይ ከሞት በኃላ ከአምስቱ የስሜት ህዋሳት ባሻገር ተሸፍኖ፣ ተደብቆ፣ ተሸሽጎ፣ ተቀብሮ ያለ የአኺራህ የመጀመሪያው ደረጃ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 5
የዑስማን ነጻ ባሪያ ሃኒእ ሰምቶ እንደተረከው፦ "ዑስማን መቃብር ላይ ሲቆሙ ፂሙ በእንባ እስኪርስ ድረስ አለቀሰ፥ ለእርሱም፦ "ጀነት እና እሳት ሲዘከሩ ሳታለቅስ ለዚህ ለምን ታለቅሳለህ? ተባለ፥ እርሱም እንዲህ አለ፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በእርግጥ ቀብር የአኺራህ መጀመሪያ ደረጃ ነው። ስለዚህ አንድ ሰው ከቀብር የዳነ ከሆነ ከዚያ በኋላ የሚመጣው ከቀብር የበለጠ ቀላል ነው፥ አንድ ሰው ከቀብር ካልዳነ ከዚያ በኋላ የሚመጣው ከቀብር የከፋ ነው። أَنَّهُ سَمِعَ هَانِئًا، مَوْلَى عُثْمَانَ قَالَ كَانَ عُثْمَانُ إِذَا وَقَفَ عَلَى قَبْرٍ بَكَى حَتَّى يَبُلَّ لِحْيَتَهُ فَقِيلَ لَهُ تُذْكَرُ الْجَنَّةُ وَالنَّارُ فَلاَ تَبْكِي وَتَبْكِي مِنْ هَذَا فَقَالَ إِنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ إِنَّ الْقَبْرَ أَوَّلُ مَنَازِلِ الآخِرَةِ فَإِنْ نَجَا مِنْهُ فَمَا بَعْدَهُ أَيْسَرُ مِنْهُ وَإِنْ لَمْ يَنْجُ مِنْهُ فَمَا بَعْدَهُ أَشَدُّ مِنْهُ ‏"‏

"አኺራህ" آخِرَة ማለት "ቀጣይ ዓለም" ማለት ሲሆን ከሞት በኃላ ያለው ዓለም ነው። አን ናዚዓት እና አን-ናሺጧት በተባሉ የሞት መላእክት ስንወሰድ በቀብር "አል ሙንከር" الْمُنْكَر እና "አን ነኪር" الْنَّكِير የተባሉ መላእክት ለሰው፦ "ጌታህ ማን ነው? ዲንህ ምንድን ነው? ነቢይህ ማን ነው?” ብለው ይጠይቃሉ። አማኝም ከሆነ፦ "ጌታዬ አሏህ ነው፣ ዲኔ ኢሥላም ነው፣ ነቢዬም የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ነው" ብሎ ሲመልስ ለእርሱ ጀነት እዲገባ ይከፈትለታል፥ ከሓዲ ከሆነ፦ "ዐላውቅም፣ ዐላውቅም፣ ዐላውቅም" ብሎ ሲመልስ ለእርሱ እሳት እዲገባ ይከፈትለታል፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 158
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 107

"በርዘኽ" بَرْزَخ ማለት ሁለት ነገርን እንዳይገናኝ በመካከላቸው ያለ "ጋራጅ"partition" ነው፥ ለምሳሌ፦ ጥቁር ባሕር፣ ባልቲክ ባሕር፣ ቀይ ባሕር፣ ሜድትራኒያን ባሕር፣ ፓስፊክ ውቂያኖስ፣ አትላንቲ ውቂያኖስ እና የሕንድ ውቂያኖስ በውስጣቸው መራራ ውኃ እና ጣፋጭ ውኃ ይዘዋል። እነዚህ ሁለቱ ባሕሮች እንዳይገናኙ በመካከላቸው በርዘኽ አለ፦
55፥19 ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡ مَرَجَ الْبَحْرَيْنِ يَلْتَقِيَانِ
55፥20 እንዳይገናኙ በመካከላቸው "ጋራጅ" አለ፡፡ አንዱ ባንዱ ላይ ወሰን አያልፉም፡፡ بَيْنَهُمَا بَرْزَخٌ لَّا يَبْغِيَانِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጋራጅ" ለሚለው የገባው ቃል "በርዘኽ" بَرْزَخ ሲሆን "ግርዶ" "መለያ" "ክልል" ማለት ነው። በተመሳሳይም ሁሉም ሰው ወደ አሏህ ከተመለሰ በኃላ አማንያን ያሉበት ጀናህ እና ከሓዲያን ያሉበት እሳት በመካከላቸው እንዳይገናኙ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በርዘኽ አለ፦
23፥100 ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ "ግርዶ" አለ፡፡ وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ግርዶ" ለሚለው የገባው ቃል "በርዘኽ" بَرْزَخ ሲሆን ልክ የእናት ማኅፀን ከፅንስ እስከ ልደት ጊዜአዊ መቆያ እንደሆነ ሁሉ በርዘኽም ከሞት እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ያለ መካከለኛ ቀጠና"intermediate zone" ነው። በጊዜአዊ መቆያ የገነት ሰዎች እና የእሳት ሰዎች የንግግር ልውውጥ ያረጋሉ፦
7፥44 የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎች፦ «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፡፡ ጌታችሁ የዛተባችሁንስ እውነት ኾኖ አገኛችሁትን?» ሲሉ ይጣራሉ፡፡ «አዎን አገኘን» ይላሉ፡፡ በመካከላቸውም «የአላህ ርግማን በበደለኞች ላይ ይኹን» ሲል ለፋፊ ይለፍፋል፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ أَصْحَابَ النَّارِ أَن قَدْ وَجَدْنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقًّا فَهَلْ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمْ حَقًّا ۖ قَالُوا نَعَمْ ۚ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنٌ بَيْنَهُمْ أَن لَّعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ
7፥50 የእሳትም ሰዎች የገነትን ሰዎች፦ «በእኛ ላይ ከውኃ አፍስሱብን ወይም አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ጣሉልን» ብለው ጠሩዋቸዋል፡፡ እነርሱም «አላህ በከሓዲዎች ላይ እርም አድርጓቸዋል» ይሏቸዋል፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ النَّارِ أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَنْ أَفِيضُوا عَلَيْنَا مِنَ الْمَاءِ أَوْ مِمَّا رَزَقَكُمُ اللَّهُ ۚ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ حَرَّمَهُمَا عَلَى الْكَافِرِينَ

የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎችን የእሳትም ሰዎች የገነትን ሰዎችን ቢያነጋግሩም በመካከላቸውም እንዳይገናኙ "ግርዶሽ" አለ፦
7፥46 በመካከላቸውም "ግርዶሽ" አለ። وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ

አምላካችን አሏህ ከእሳት ቅጣት ይጠብቀን! የጀነት ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
155 viewsedited  05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 23:59:52 እነዚህ የሞት መላእክት በጥቅሉ "አን ናዚዓት" እና "አን-ናሺጧት" ይባላሉ፥ "አን ናዚዓት" النَّازِعَات ማለት "በኃይል ወሳጆች" "ሩሕን ከአካል በኃይል አውጪዎች" ማለት ሲሆን አን-ናዚዓት በመባል የሚታወቁት የሞት መላእክት የከሓድያንን ሩሕ በኃይል አውጪዎች ናቸው። አን ናዚዓት ከሓድያንን የሚወስዷቸው ኾነው በመጡባቸው ጊዜ "ከአላህ ሌላ ትገዟቸው የነበራችሁት የት አሉ?» ይሏቸዋል፡፡ «ከእኛ ተሰወሩን» ይላሉ፥ እነርሱም ከሓዲያን እንደነበሩ በራሳቸው ላይ ይመሰክራሉ፦
79፥1 በኃይል አውጪዎች በኾኑት"። وَالنَّازِعَاتِ غَرْقًا
7፥37 የሞት መልእክተኞቻችንም "የሚወስዷቸው" ኾነው በመጡባቸው ጊዜ «ከአላህ ሌላ ትገዟቸው የነበራችሁት የት አሉ?» ይሏቸዋል፡፡ «ከእኛ ተሰወሩን» ይላሉ፡፡ እነርሱም ከሓዲያን እንደነበሩ በራሳቸው ላይ ይመሰክራሉ፡፡ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَتْهُمْ رُسُلُنَا يَتَوَفَّوْنَهُمْ قَالُوا أَيْنَ مَا كُنتُمْ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ ۖ قَالُوا ضَلُّوا عَنَّا وَشَهِدُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا كَافِرِينَ
8፥50 መላእክት እነዚያንም የካዱትን ፊቶቻቸውን እና ጀርባዎቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎንም ስቃይ ቅመሱ» እያሉ በሚወስዷቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር፡፡ وَلَوْ تَرَىٰ إِذْ يَتَوَفَّى الَّذِينَ كَفَرُوا ۙ الْمَلَائِكَةُ يَضْرِبُونَ وُجُوهَهُمْ وَأَدْبَارَهُمْ وَذُوقُوا عَذَابَ الْحَرِيقِ

"አን-ናሺጧት" النَّاشِطَات ማለት "በቀስታ ወሳጆች" "ሩሕን ከአካል በቀስታ መዘማዦች" ማለት ሲሆን አን-ናሺጧት በመባል የሚታወቁት የሞት መላእክት የአማንያንን ሩሕ በቀስታ አውጪዎች ናቸው። አን-ናሺጧት አማንያንን፦ "ሰላም በእናንተ ላይ" እያሉ የሚወስዷቸው ናቸው፡፡ "ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ" ይባላሉ፦
79፥2 "በቀስታ መምዘዝንም መዘማዦች በኾኑት"። وَالنَّاشِطَاتِ نَشْطًا
16፥32 እነዚያ በመልካም ኹኔታ ላይ ኾነው መላእክት «ሰላም በእናንተ ላይ» እያሉ የሚወስዷቸው ናቸው፡፡ «ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ» ይባላሉ፡፡ الَّذِينَ تَتَوَفَّاهُمُ الْمَلَائِكَةُ طَيِّبِينَ ۙ يَقُولُونَ سَلَامٌ عَلَيْكُمُ ادْخُلُوا الْجَنَّةَ بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

ከሞት በኃላ ሩሕ ሲወሰድ የሞት መላእክት እና ሩሓችን መነጋገራቸው በራሱ ሩሕ በሞት ጊዜ የሚወሰድ እንጂ ከአካል ጋር በአፈር የሚበሰብስ አለመሆኑን በቂ ማሳያ ነው። አምላካችን አሏህ "ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ" ከሚላት የጀነት ባለቤቶች ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
1.9K views20:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 23:59:27 ከሞት በኃላ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

39፥42 አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፥ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፡፡ ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا

አሏህ ሩሓችንን በእንቅልፏ ጊዜ ሲወስዳት ያለ ውጫዊ ነገር በውሳጣዊ ነገር ታያለች፣ ትሰማለች፣ ትሄዳለች፣ ትናገራለች፥ የሕልም ዓለም ሩሕ ከአካል ከተለየች በኃላ ያለውን ሕይወት ማሳያ ናሙና ነው። አምላካችን አሏህ በሌሊት ይወስደናል፥ ከዚያም በቀን ይቀሰቅሰናል፦
6፥60 "እርሱም ያ በሌሊት "የሚወስዳችሁ" በቀንም የሠራችሁትን ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈፀም ዘንድ በእርሱ በቀን ውስጥ "የሚቀሰቅሳችሁ" ነው"፡፡ وَهُوَ الَّذِي يَتَوَفَّاكُم بِاللَّيْلِ وَيَعْلَمُ مَا جَرَحْتُم بِالنَّهَارِ ثُمَّ يَبْعَثُكُمْ فِيهِ لِيُقْضَىٰ أَجَلٌ مُّسَمًّى

"የሚወስዷችሁ" ለሚለው የገባው ቃል "የተወፋኩም" يَتَوَفَّاكُم ሲሆን "የሚያስተኛችሁ" ማለትም ነው። አምላካችን አሏህ በቀን ደግሞ ይቀሰቅሰናል፥ "በቀን ውስጥ የሚቀሰቅሳችሁ ነው" የሚለው ይሰመርበት! አሏህ ሩሓችንን በእንቅልፍ ጊዜ ወስዶ በንቃት ጊዜ ይመልሳል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 97
አቡ ቀታዳህ እንደተረከው፦ "ከሶላት ሰዎች በተኙ ጊዜ የአሏህ ነቢይም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ በሚሻው ጊዜ ሩሓችሁን ይወስዳል፥ በሚሻው ጊዜ ይመልሳል"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي قَتَادَةَ، عَنْ أَبِيهِ، حِينَ نَامُوا عَنِ الصَّلاَةِ، قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ قَبَضَ أَرْوَاحَكُمْ حِينَ شَاءَ، وَرَدَّهَا حِينَ شَاءَ ‏"‌‏

ሰው የመንፈስ እና የአካል ሁለትዮች"bi-partite" ቀዋሚ ማንነት ሲሆን አካሉ በሌሊት እንቅልፍ እንደሚያርፍ እና በቀን እንደሚቀሰቀስ ሁሉ በሞትን ጊዜ አካሉ በትልቁ እንቅልፍ ያርፍ እና በትንሳኤ ቀን ይቀሰቀሳል፦
36፥51 በቀንዱም ይነፋል፥ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ الْأَجْدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يَنسِلُونَ
36፥52 «ወይ ጥፋታችን! ከእንቅልፋችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን እና መልእክተኞቹ እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ፡፡ قَالُوا يَا وَيْلَنَا مَن بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا ۜ ۗ هَـٰذَا مَا وَعَدَ الرَّحْمَـٰنُ وَصَدَقَ الْمُرْسَلُونَ

እንቅልፍ ሩሕ እና አካል የሚለያዩበት ስለሆነ የሞት ወንድም ተብሏል፥ እንቅልፍ ትንሹ ሞት ስለሆነ ለዛ ነው የምሽት ዚክር ላይ "አሏህ ሆይ! በስምህ እሞታለው ሕያው እሆናለው" የንጋት ዚክር ላይ ደግሞ፦ "ለአሏህ ምስጋና ይሁን! ለዚያ ከአሞተን በኃላ ሕያው ላደረገን፥ መቀስቀስም ወደ እርሱ ነው" የምንለው፦
አል-ሙጀመል አውሠጥ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 938
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "የአሏህ ነቢይም"ﷺ" እንዲህ ተጠየቁ፦ "የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! የጀናህ ባለቤቶች ይተኛሉን? የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ "እንቅልፍ የሞት ወንድም ነውና የጀናህ ባለቤቶች አይተኙም"። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ سُئِلَ نَبِيُّ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ أَيَنَامُ أَهْلُ الْجَنَّةِ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ النَّوْمُ أَخُو الْمَوْتِ وَأَهْلُ الْجَنَّةِ لا يَنَامُونَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 23
ሑዘይፋህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ወደ አልጋቸው በሄዱ ጊዜ፦ "አሏህ ሆይ! በስምህ እሞታለው ሕያው እሆናለው" ይሉ ነበር፥ በነቁ ጊዜ፦ "ለአሏህ ምስጋና ይሁን! ለዚያ ከአሞተን በኃላ ሕያው ላደረገን፥ መቀስቀስም ወደ እርሱ ነው"። عَنْ حُذَيْفَةَ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِذَا أَوَى إِلَى فِرَاشِهِ قَالَ ‏"‏ اللَّهُمَّ بِاسْمِكَ أَحْيَا وَأَمُوتُ ‏"‌‏.‏ وَإِذَا أَصْبَحَ قَالَ ‏"‏ الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَحْيَانَا بَعْدَ مَا أَمَاتَنَا وَإِلَيْهِ النُّشُورُ ‏"‌‏

"ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል" ማለት ሩሕ በእንቅልፍ ጊዜ መወሰዷን ሲያመለክት "አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል" ማለት ደግሞ በሞት ጊዜ አካል ወደ አፈር ሲመለስ ሩሕ ወደ አሏህ ይወሰዳል፦
39፥42 አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፥ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፡፡ ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይወስዳል" ለሚለው የገባው ቃል "የተወፈ" يَتَوَفَّى ሲሆን አሏህ መለኩል መውትን በመላክ ነፍስን ይወስዳል፦
32፥11 «በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት ይወስዳችኋል፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡ قُلْ يَتَوَفَّاكُم مَّلَكُ الْمَوْتِ الَّذِي وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ

"የተወፋኩም" يَتَوَفَّاكُم ማለት "ይወስዳችኋል" ማለት ሲሆን "መለኩል መውት" مَلَكُ المَوت ማለት "መልአከ ሞት" ወይም "የሞት መልአክ" ማለት ነው። "ሞት" የሚለው ቃል ተዛራፊ እንጂ ባለቤትን አያመለትም፥ መልአከ ሞት የሚባሉት መላእክት ብዙ ናቸው፦
6፥61 አንዳችሁንም ሞት በመጣበት ጊዜ የሞት መልእክተኞቻችን እነርሱ ትእዛዛትን የማያጓድሉ ሲኾኑ ይወስዱታል፡፡ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ تَوَفَّتْهُ رُسُلُنَا وَهُمْ لَا يُفَرِّطُونَ
1.9K views20:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 01:52:56 ነፍስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

75፥2 ራሷን ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ وَلَا أُقْسِمُ بِالنَّفْسِ اللَّوَّامَةِ

"ነፍሥ" نَّفْس የሚለው ቃል "እራስ"own self" ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ "ቀተለ ነፍሠ-ሁ" ‏قَتَلَ نَفْسَهُ ስንል "እራሱን አጠፋ" ማለት ነው፣ "ረአይቱ ነፍሢ ፊል መርኣህ" ‏رَأَيْتُ نَفْسِي فِي ٱلْمِرْآةِ ስንል "እራሴን በመስታዎት አየሁኝ" ማለት ነው። "ዶሚሩ አን-ነፍሢያህ" ضَمِير الْنَفْسِيَّة‎ ማለት እራሱ "ድርብ ተውላጠ-ስም”reflexive pronoun” ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ ተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" አምላካችን አሏህ ያዘዛቸው ላይ "እራሴ" ሲሉ "ነፍሢ” نَفْسِي በማለት እንዲሉ ተናግሯል፦
7፥188 በላቸው፦ "አላህ የሻውን በስተቀር "ለ-"እራሴ" ጥቅምንም ጉዳትንም ማምጣት አልችልም፡፡ قُل لَّا أَمْلِكُ لِنَفْسِي نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ

በዚህ አንቀጽ ላይ "እራሴ"my-self" ለሚለው የገባው ቃል "ነፍሢ" نَفْسِي መሆኑ ልብ አድርግ! ይህ ያቀረብነው ናሙና በመጀመርያ መደብ ሲሆን አሏህ በሁለተኛ መደብ "እራስህ" ለማለት "ነፍሢከ" نَفْسِكَ በማለት ይናገራል፦
4፥79 ከደግም የሚያገኝህ ከአላህ ነው፤ ከፉዉም የሚደርስብህ "ከ-"እራስህ" ነው።  مَّا أَصَابَكَ مِنْ حَسَنَةٍ فَمِنَ اللَّهِ ۖ وَمَا أَصَابَكَ مِن سَيِّئَةٍ فَمِن نَّفْسِكَ ۚ وَأَرْسَلْنَاكَ لِلنَّاسِ رَسُولًا ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا

በዚህ አንቀጽ ላይ "ራስህ"your-self" ለሚለው የገባው ቃል "ነፍሢከ" نَفْسِكَ ነው። አሏህ በሦስተኛ መደብ "እራሱ"him-self" ለማለት "ነፍሢሂ" نَفْسِهِ በማለት ይናገራል፦
2፥207 ከሰዎችም ውስጥ የአላህን ውዴታ ለመፈለግ "እራሱን" የሚሸጥ ሰው አለ፡፡ አላህም ለባሮቹ በጣም ርኅሩህ ነው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْرِي نَفْسَهُ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ

ስለዚህ በጥቅሉ "ነፍሥ" نَّفْس ማለት "ሁለንተናዊ ማንነት"wholly identity" ማለት ነው፥ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ሲገድል "ነፍሰ ገዳይ" ይባላል፦
17፥33 ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ላ ተቅተሉ አን-ነፍሥ" لَا تَقْتُلُوا النَّفْس ማለት "ነፍስን አትግደሉ" ማለት ነው፥ በዚህ ዐውድ "ነፍሥ" نَّفْس የሚለው "አካል" የሚለውን ለማመልከት የገባ ነው፦
39፥6 ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ፡፡ ከዚያም ከእርሷ መቀናጆዋን አደረገ፡፡ خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ ثُمَّ جَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا

እዚህ አንቀጽ ላይ "አንዲት ነፍሥ" የተባለው አደም ሲሆን "መቀናጆዋን" የተባለችው ከአደም የተፈጠረችው ሐዋን ነው፥ እኛ ሆንን እናታችን ሐዋ ከአደም የተፈጠረው አካላችን ነው። ሩሓችን ግን ከአፈር ሳይሆን ከአሏህ ነው፦
17፥85 ስለ ሩሕ ይጠይቁሃል፥ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፥ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ ۖ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا
39፥62 አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

"ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው" የሚለው ኃይለ-ቃል በራሱ ሩሕ "ነገር" ውስጥ ስለሚካተት እና አሏህ የሁሉ “ነገር” ፈጣሪ ስለሆነ የማንም ሰው ሩሕ ፍጡር ነው። "ነፍሥ" نَّفْس የሚለው "ሩሕ" رُّوح በሚል ዐውድ ለማመልከት መጥቷል፦
39፥42 አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፥ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፡፡ ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا

"አንፉሥ" أَنفُس የነፍሥ ብዙ ቁጥር ሲሆን በሞት ጊዜ የሚሄደውን መንፈሳችንን ለማልከት የገባ ነው፥ "ሩሕ" رُّوح ማለት “መንፈስ” ማለት ሲሆን "ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል" ማለት አሏህ ሩሓችንን በእንቅልፍ ጊዜ ወስዶ በንቃት ጊዜ ይመልሳል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 97
አቡ ቀታዳህ እንደተረከው፦ "ከሶላት ሰዎች በተኙ ጊዜ የአሏህ ነቢይም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ በሚሻው ጊዜ ሩሓችሁን ይወስዳል፥ በሚሻው ጊዜ ይመልሳል"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي قَتَادَةَ، عَنْ أَبِيهِ، حِينَ نَامُوا عَنِ الصَّلاَةِ، قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ قَبَضَ أَرْوَاحَكُمْ حِينَ شَاءَ، وَرَدَّهَا حِينَ شَاءَ ‏"‌‏

"አርዋሕ" أَرْوَاح ማለት "መንፈሶች" ማለት ሲሆን "ሩሕ" رُّوح ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ አሏህ ነፍሥን በእንቅልፏ ጊዜ ሲወስዳት ያለ ዓይን ታያለች፣ ያለ ጆሮ ትሰማለች፣ ያለ እግር ትሄዳለች፣ ያለ አፍ ትናገራለች።
ስለዚህ በኢሥላም አስተምህሮት ከወላጆች የሚወሰደው አካል እንጂ መንፈስ ስላልሆነ "ከወላጆች ነፍስ ይወሰዳል" ከተባለ አካልን ታሳቢ ባደረገ እንጂ መንፈስን ዋቢ ባደረገ መልኩ ከወላጆች ነፍስ አይወሰድም፥ "አካልን ከወላጆቻችን አካል እንደተገኘ ሁሉ መንፈሳችን ከወላጆቻችን መንፈስ የተገኘ"traduction" ነው" የሚል ተስተምህሮት ዲኑል ኢሥላም ውስጥ የለም። በጥቅሉ ነፍሥ "እራስነት"own self-hood" ነው፦
75፥2 ራሷን ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ وَلَا أُقْسِمُ بِالنَّفْسِ اللَّوَّامَةِ
89፥27 ለአመነች ነፍስም፦ «አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ! يَا أَيَّتُهَا النَّفْسُ الْمُطْمَئِنَّةُ
89፥28 ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡ ارْجِعِي إِلَىٰ رَبِّكِ رَاضِيَةً مَّرْضِيَّةً
89፥29 በባሮቼም ውስጥ ግቢ፡፡ فَادْخُلِي فِي عِبَادِي
89፥30 ገነቴንም ግቢ» ትባላለች፡፡ وَادْخُلِي جَنَّتِي

አምላካችን አሏህ ያመነችን ነፍስ "ገነቴንም ግቢ" ሲላት አጠቃላይ አካላዊ እና መንፈሳዊ ማንነት ያላትን ነው። አሏህ "ገነቴንም ግቢ" ከሚላት ነፍስ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
274 views22:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 00:36:42 ፨ "ፊጥራህ" فِطْرَة ማለት "ተፈጥሮ ማለት ሲሆን አሏህ ስለመኖሩ ማረጋገጫ የሥነ ኑባሬ ሙግት"ontological argument" ነው፦
30፥30 ወደ እውነት ተዘንባይ ኾነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት፡፡ فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا ۚ فِطْرَتَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 38
አቢ ሙዓዊያህ እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ "ማንም የሚወለድ ሰው በአንደበቱ እስከሚል ድረስ በአል-ፊጥራህ ላይ ሆኖ እንጂ አይወለድም። عَنْ أَبِي مُعَاوِيَةَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِلاَّ عَلَى هَذِهِ الْمِلَّةِ حَتَّى يُبَيِّنَ عَنْهُ لِسَانُهُ ‏"‏ ‏.

አሏህ በፊጥራህ ጊዜ ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን በማውጣት፦ "ጌታችሁ አይደለሁምን" ብሎ አስመስክሯል፦
7፥172 "ጌታህም ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን ባወጣና፦ «ጌታችሁ አይደለሁምን?» ሲል በራሳቸው ላይ ባስመሰከራቸው ጊዜ የኾነውን አስታውስ፡፡ «ጌታችን ነህ መሰከርን» አሉ፡፡ «በትንሣኤ ቀን ከዚህ ኪዳን ዘንጊዎች ነበርን እንዳትሉ፡፡» وَإِذْ أَخَذَ رَبُّكَ مِن بَنِي آدَمَ مِن ظُهُورِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَأَشْهَدَهُمْ عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَلَسْتُ بِرَبِّكُمْ ۖ قَالُوا بَلَىٰ ۛ شَهِدْنَا ۛ أَن تَقُولُوا يَوْمَ الْقِيَامَةِ إِنَّا كُنَّا عَنْ هَـٰذَا غَافِلِينَ

ሰው በተፈጥሮው የአምልኮ ፍላጎት እና ዝንባሌ ያለው ፍጡር የሆነው በዚህ ምክንያት ነው፥ ሰው በፊጥራህ ጊዜ "ጌታችን ነህ መሰከርን" ማለታቸው በታኅታይ ሕሊና"subconscious" የተቀመጠ ሲሆን በትንሳኤ ቀን ይህ ውስጣችን ያለው ምሥጢር ይገለጻል፦
100፥10 "በልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ እንዴት እንደሚኾን፡፡ وَحُصِّلَ مَا فِي الصُّدُورِ
86፥9 "ምሥጢሮች በሚገለጡበት ቀን"፡፡ يَوْمَ تُبْلَى السَّرَائِرُ

፨ "ዐቅል" عَقْل ማለት "አእምሮ" ማለት ሲሆን አሏህ ስለመኖሩ ማረጋገጫ የሥነ አመክንዮ ሙግት"logical argument" ነው፦
51፥21 በነፍሶቻችሁም ውስጥ ምልክቶች አሉ፤ ታዲያ አትመለከቱምን? وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ

የሰው ውሳጣዊ ተፈጥሮ በሥነ አመክንዮ ፈጣሪ እንዳለ ምስክርነት ነው፥ በነፍሶቻችን ውስጥ ያሉት የአስተሳሰብ ቅኝት"mindset" ተአምራት ሲሆኑ ከተመለከትን የአሏህን መኖር ፍትንው አርገው ያረጋግጣሉ፦
91፥8 አመጽዋን እና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት፡፡ فَأَلْهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقْوَاهَا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ባሳወቀ" ለሚለው የገባው ቃል "አልሀመ" أَلْهَمَ መሆኑን ልብ በል! "ኢልሃም" إِلْهَام የሚለው ቃል እራሱ "አልሀመ" أَلْهَمَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ውሳጣዊ ግንዛቤ ወይም ዕውቀ-ልቦና”intuition” ማለት ነው፥ ለነፍስ በመልካም መታዘዝ እና በክፉን ማመጽ በውስጧ ያሳወቃት መኖሩ በራሱ የአሏህ መኖር የሕሊና ምስክርነት ነው።

፨ "ነቅል" نَقْل ማለት "ግልጠተ መለኮት" ማለት ሲሆን በነቢያቱ በኩል የመጣ ማረጋገጫ ነው፥ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه የሚለው መርሕ የሁሉም ነቢያት መርሕ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ፦ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ
20፥14 እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي

በነቢያቱ በኩል ወሕይ በማውረድ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" እያለ የሚናገር ነባቢ መለኮት መኖሩ፣ ሰዎች የሚመሩበትን ሙሐከማት መስጠቱ እና "ሰማያትን እና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን" ማለቱ በራሱ የሥነ መለኮት ሙግት"theological argument" ነው።
50፥38 ሰማያትን እና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ

፨ "አደብ" اَدَب‎ ማለት "ግብረገብ" ማለት ሲሆን ሰው ግን ነጻ ፈቃድ ስላለው በሚሠራው መልካም ሥራ ስለሚነዳ እና በሚሠራው ክፉ ሥራ ስለሚቀጣ ልቅ ሆኖ አልተተወም፦
75፥36 ሰው ልቅ ኾኖ መተውን ያስባልን? أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَن يُتْرَكَ سُدًى

ይህ ግብረገባዊ ሙግት"moral argument" ነው፥ "መሥኡሉል አደብ” مَسْؤُول الاَدَب‎ ማለት “ግብረገባዊ ተጠያቂነት”moral accountability” ማለት ሲሆን ሰው በተሰጠው ጸጋ ለሚሠራው ሥራ ተጠያቂ መሆኑ በራሱ ጠያቂ ፈጣሪ መኖሩ ማረጋገጫ ነው፦
21፥23 ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ ግን ይጠየቃሉ፡፡ لَا يُسْأَلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْأَلُونَ
16፥93 ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ፡፡ وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنتُمْ تَعْمَلُون
102፥8 ከዚያም ከጸጋችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ። ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ

አምላካችን አሏህ ከሙልሒድ ኢልሓድ ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
985 viewsedited  21:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 00:35:37 የአሏህ ህልውና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

22፥6 ይህ አላህ እርሱ መኖሩ የተረጋገጠ፣ እርሱም ሙታንን ሕያው የሚያደርግ፣ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ በመሆኑ ነው፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّهُ يُحْيِي الْمَوْتَىٰ وَأَنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

በአንድ ወቅት የነገረ ልቦና ምሁር ሲይግመን ፍሮይድ፦ "ሁሉን የሚቆጣጠር እና የሚመግብ አምላክ ፍቅር፣ እንክብካቤ እና ጥበቃ በሚያስፈልገው በሰው ሥነ ልቡና የተፈጠረ ነው"The God who controls and provides everything, is created by the human psyche in response to its need for love, saftey and security" በማለት ኢ-አማኝነቱን ገልጿል። ይህ የኢልሓድ እሳቤ ነው፥ በፈጣሪ እሳቦት ውስጥ ኢማን፣ ኩፍር እና ኢልሓድ ተጠቃሽ ናቸው።
"ኢልሓድ" إِلْحَاد የሚለው ቃል "አልሐደ" أَلْحَدَ‎ ማለትም "ኢ-አመነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን በአምላክ መኖር "ኢ-አማኒነት"atheism" ማለት ነው፥ በነጠላ "ሙልሒድ" مُلْحِد ማለት "ኢ-አማኝ"atheist" ማለት ሲሆን "ሙልሒዱን" مُلْحِدُون‎ ደግሞ የሙልሒድ ብዙ ቁጥር ነው። ሙልሒድ የኢልሓድ እሳቤ የሚያራምዱ ናቸው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 87 ሐዲስ 21
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም፦ “ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “አሏህ ዘንድ የተጠሉ ሦስት ሰዎች አሉ፦ “በሐረም ውስጥ ያለ ሙልሒድ፣ የጃሂሊያህን ሡናህ ኢሥላም ውስጥ ለማስቀረት የሚፈልግ እና ያለ ሕግ የአንድ ሰው ደም ማፍሰስ የሚፈልግ ናቸው"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ أَبْغَضُ النَّاسِ إِلَى اللَّهِ ثَلاَثَةٌ مُلْحِدٌ فِي الْحَرَمِ، وَمُبْتَغٍ فِي الإِسْلاَمِ سُنَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ، وَمُطَّلِبُ دَمِ امْرِئٍ بِغَيْرِ حَقٍّ لِيُهَرِيقَ دَمَهُ. ‏

"ዉጁድ" وُجُود የሚለው ቃል "ወጀደ" وَجَدَ ማለትም "አለወ" "ኖረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መኖር" ሃልዎት" "ህልውና" ማለት ነው፥ "ዉጁዱል ሏህ" وُجُود الله ማለት "የአሏህ ህልውና"the existence of Allah" ማለት ነው። የአሏህ መኖር የተረጋገጠ ነው፦
22፥6 ይህ አላህ እርሱ "መኖሩ የተረጋገጠ"፣ እርሱም ሙታንን ሕያው የሚያደርግ፣ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ በመሆኑ ነው፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّهُ يُحْيِي الْمَوْتَىٰ وَأَنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
24፥25 በዚያ ቀን አላህ እውነተኛ ዋጋቸውን ይሞላላቸዋል፡፡ አላህም እርሱ "መኖሩ የተረጋገጠ" ሁሉን ነገር ገላጭ መኾኑን ያውቃሉ፡፡ يَوْمَئِذٍ يُوَفِّيهِمُ اللَّهُ دِينَهُمُ الْحَقَّ وَيَعْلَمُونَ أَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ الْمُبِينُ

"አል ሐቅ" الْحَقّ ማለት "መኖሩ ተረጋገጠ" ማለትም ሲሆን አንድ ሰው የአሏህን መኖር የሚረጋገጠው እንደ ሲይግመን ፍሮይድ ማየት፣ መስማት፣ ማሽተት፣ መቅመስ እና መዳደስ በሚባሉት አምስት የስሜት ሕዋሳት ሳይሆን በመኽሉቅ፣ በፊጥራህ፣ በዐቅል፣ በነቅል፣ በአደብ ነው። እነዚህ ማረጋገጫዎች እንመልከት፦

፨ "መኽሉቅ" مَخْلُق ማለት "ፍጥረት" ማለት ሲሆን ፍጥረት ውጤት ከሆነ ፈጣሪ መንስኤ ነው፥ አሏህ ስለመኖሩ ጉልኅ ማረጋገጫ የፍጥረት ሙግት"cosmological argument" ነው፦
56፥58 በማኅፀኖች የምታፈሱትን አያችሁን? أَفَرَأَيْتُم مَّا تُمْنُونَ
56፥59 እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹን ነን? أَأَنتُمْ تَخْلُقُونَهُ أَمْ نَحْنُ الْخَالِقُونَ

በተራክቦ ጊዜ በሴት ብልት ውስጥ የሚፈሰውን የወንድ ሕዋስ"sperm cell" ሰው አርገን መፍጠር አለመቻላችን በራሱ የተፈረጠውን የሚፈጥር ፈጣሪ እንዳለ አመላካች ነው፥ በመንስኤ እና በውጤት ሕግ ያለ ሠሪ ተሠሪ እንደሌለ ሁሉ ያለ ፈጣሪ ተፈጣሪ የለም። የፍጥረት ሙግት በመቀጠል ሰው እራሱን እራሱ አለመፍጠሩ የፈጠረውን ፈጣሪ እንዳለ በቂ ማሳያ ነው፦
52፥35 ወይስ ያለ አንዳች "ነገር" ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን? أَمْ خُلِقُوا مِنْ غَيْرِ شَيْءٍ أَمْ هُمُ الْخَالِقُونَ
52፥36 ወይስ ሰማያትን እና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም አያረጋግጡም፡፡ أَمْ خَلَقُوا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ ۚ بَل لَّا يُوقِنُونَ

ፍጥረት ያለምንም ፈጣሪ እንዳልተፈጠረ እሙን እና ቅቡል ነው፥ ፍጥረትን ፍጡር አልፈጠረም። ሰማያትን እና ምድርን ሰው አለመፍጠሩ በራሱ ፈጣሪ መኖሩን ማረጋገጫ ነው። ይህንን ሙግት በምንጨታዊ፣ በስሙር፣ በርቱዕ ሙግት ስናዋቅረው፦
1. ማንኛውም ነገር መነሾ አለው፣
2. መነሾ ያለው ነገር መንስኤ"cause" አለው፣
3. ስለዚህ ፍጥረትን ያስገኘው መንስኤ ፈጣሪ ነው፦
46፥3 በሰማያት እና በምድር ውስጥ ለምእምናን ሁሉ እርግጠኛ ምልክቶች አሉ፡፡ إِنَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ لَآيَاتٍ لِّلْمُؤْمِنِينَ
7፥54 ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ
1.0K viewsedited  21:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 18:57:11
ተውሒድ የሚለው ይህ መጽሐፍ በኡሥታዝ መሐመድ አሕመድ ሙነወር የተከተበ ነውና አንብቡት! መጽሐፉን ለማግኘት ወንድም አወል ብላችሁ በዚህ ደውሉ፦ +251913604751
1.1K viewsedited  15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 11:16:14 ይህ የአሏህ ፍትሓዊነት ምን ያህል ጥልቅ እና ምጥቅ መሆኑን የሚያሳይ ነው፥ የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው። የጠመመም ሰው የሚሚጠመው ጉዳቱ በእርሷ ላይ ነው፥ ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም፡፡ እንደውም አንድ የአሏህ መልእክተኛ ይዞት የመጣውን መልእክት ያልሰማ አይቀጣም፦
17፥15 የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፥ የጠመመም ሰው የሚሚጠመው ጉዳቱ በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም፡፡ መልእክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም፡፡ مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ۗ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًا

"መልእክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም" የሚለው ይሰመርበት! "ፈህም" فَهْم የሚለው ቃል "ፈሂመ" فَهِمَ ማለትም "ተረዳ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መረዳት"understanding" ማለት ነው፥ "መዕና" مَعْنًى የሚለው ቃል "ዐነ" عَنَى ማለትም "ተረጎመ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ትርጉም"meaning" ማለት ነው። አንድ ሰው መልእክተኛ ይዞት የመጣውን መልእክት አመመስማት ብቻ ሳይሆን የመልእክቱን ፈህም እና መዕና ካላወቀ አይቀጣም፥ ይህ "ዑዝር ቢል-ጀህል" عُذْر بِالجَهْل ነውና።
"ኒያህ" نِيَّة የሚለው ቃል "ነዋ" نَوَى ማለትም "ወጠነ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ውጥን"intention" ማለት ነው። ሥራ የሚለካው በኒያህ ነው፥ ማንኛውምንም ሰው የነየተውን ያገኛል። የፍርዱ ቀን ሰዎች ተቀስቅሰው ምንዳ እና ፍዳ የሚበየንባቸው በነየቱት ኒያህ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 47
ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ ብለዋል፦ "ሥራ የሚለካው በኒያህ ነው፥ ማንኛውምንም ሰው የነየተውን ያገኛል።  عَنْ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الأَعْمَالُ بِالنِّيَّةِ، وَلِكُلِّ امْرِئٍ مَا نَوَى
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4370
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሰዎች ተቀስቅሰው የሚበየንባቸው በነየቱት ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏:‏ ‏ “‏ إِنَّمَا يُبْعَثُ النَّاسُ عَلَى نِيَّاتِهِمْ

ሰዎች የምንፈርደው በምላስ በተነገረን እና በውጫዊ አካል በሚደረገው ድርጊት እንጂ በልብ ላይ በተቀመጠው ኒያህ አይደለም፥ በፍርዱ ቀን በሁሉም ላይ በእውነት እና በትክክሉ ፈራጁ አሏህ ነው፦
34፥26 «ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፡፡ እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው» በላቸው፡፡ قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَهُوَ الْفَتَّاحُ الْعَلِيمُ

አምላካችን አሏህ የእርሱን ፍትሕ ከሚያስተነትኑት ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
1.8K views08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 11:15:40 የአሏህ ፍትሓዊነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥49 ጌታህም አንድንም አይበድልም፡፡ وَلَا يَظْلِمُ رَبُّكَ أَحَدًا

አምላካችን አሏህ ፍትሓዊ አምላክ ሰለሆነ ማንንም አይበድልም፥ “ዘራህ” ذَرَّة ማለት “ቅንጣት”atom” ማለት ሲሆን አሏህ ቅንጣት ታክል ማንንም አይበድልም። ነገር ግን ሰው እራሱን የሚበድነው ማመን እና መታዘዝ ሲችል በመካድ እና በማመጽ ነው፦
18፥49 ጌታህም አንድንም አይበድልም፡፡ وَلَا يَظْلِمُ رَبُّكَ أَحَدًا
4፥40 አላህ የብናኝን ክብደት ያህል አይበድልም፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ
10፥44 አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም፡፡ ግን ሰዎች እራሳቸውን ይበድላሉ፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ النَّاسَ شَيْئًا وَلَـٰكِنَّ النَّاسَ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ

ባለማወቅ የሚሠራ መጥፎ ሥራ “ስህተት” ሲባል በመርሳት የማይሠራ መልካም ሥራ “ግድፈት” ይባላል፥ አሏህ ሰዎች ባለማወቅ በሠሩት ስህተት ሆነ በመርሳት በማይሠሩት ግድፈት አይቀጣም፦
2፥286 “ጌታችን ሆይ! ”ብንረሳ ወይም ብንስት አትቅጣን” በሉ፡፡ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِن نَّسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَ
33፥5 በእርሱ በተሳሳታችሁበትም ነገርም በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም፥ ግን ልቦቻችሁ ዐዉቀው በሠሩት ኃጢአት አለባችሁ”። አላህም መሃሪ አዛኝ ነው። وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌۭ فِيمَآ أَخْطَأْتُم بِهِۦ وَلَٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًۭا رَّحِيمًا

“ብንረሳ” ማለት መሥራቱ ግዴታ የሆነ መልካም ሥራ በመርሳት መግደፍ ሲሆን “ብንስት” ማለት መሥራቱ ክልክል የሆነ መጥፎ ሥራ ባለማወቅ መሳሳት ነው። በተሳሳትንበት ነገር በእኛ ላይ ኃጢአት የለብንም፥ ቅሉ ግን ልባችን እያወቀው በሠራነው መጥፎ ሥራ ኃጢአት አለበት። ሰው ድርሻው በሌለበት እና ጣልቃ ገብ ባልሆነበት ጉዳይ ተገዶ ነውና የተገደዱበት ነገር አያስጠይቅም አያስቀጣም፦
2፥173 ሽፍታ እና ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት "የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም"፥ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2123
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”አላህ በኡማዬ ላይ ስህተት፣ መርሳት እና የገተደዱበትን ነገር አንስቷል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ وَضَعَ عَنْ أُمَّتِي الْخَطَأَ وَالنِّسْيَانَ وَمَا اسْتُكْرِهُوا عَلَيْهِ

“ውሥዕ” وُسْع ማለት “ችሎታ” ማለት ሲሆን ሰው አሏህ “አድርግ” ብሎ ያዘዘውን የማድረግ እና “አታድርግ” ብሎ የከለከውን ያለማድረግ ችሎታ እና ዐቅም ያሳያል፥ ጌታችን አሏህ ፍትሓዊ ስለሆነ ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አያስገድድም፦
23፥62 ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አናስገድዳትም፡፡ وَلَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا

“ኪራመን ካቲቢን” كِرَامًا كَاتِبِين ማለት “የተከበሩ ጸሐፊዎች” ማለት ሲሆን እነዚህ ጸሐፊዎች በእያንዳንዱ ሰው ቀኝ እና ግራ ያሉ ሁለት መላእክት ናቸው፥ በቀኝ ያለው መልአክ ሠናይ ተግባራትን በብዕር ሲመዘግብ በግራ ያለው መልአክ ደግሞ እኩይ ተግባራትን በብዕር ይመዘግባል። እነዚህ መላእክት በእንቅልፍ ልብ፣ በዕብደት እና በእንጭጭነት የሚደረግ ሥራ አይመዘግቡትም፦
68፥1 “ኑን”፤ በብርዕ እምላለሁ፥ በዚያም በሚጽፉት”። نٓ ۚ وَٱلْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 48
ዓኢሻህ "ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ብዕር ከሦስት ሰዎች ተነስቷል። እነርሱም፦ የተኛ ሰው እስኪነሳ ድረስ፣ ዕብደ ወደ ዐቅሉ እስኪመለስ ድረስ፣ ልጅ እስኪጎሎብት ድረስ"።  عَنْ عَائِشَةَ، رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ رُفِعَ الْقَلَمُ عَنْ ثَلاَثَةٍ عَنِ النَّائِمِ حَتَّى يَسْتَيْقِظَ وَعَنِ الْمُبْتَلَى حَتَّى يَبْرَأَ وَعَنِ الصَّبِيِّ حَتَّى يَكْبَرَ ‏
1.7K views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ