የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 7ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ! "ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በእሥልምና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ-መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው። ፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ-አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦ በሥላሴ"trinity" እሳቤ፣ በነገረ-ክርስቶስ ጥናት"Christology"፣ በነገረ-ማርያም ጥናት"Mariology"፣ በነገረ-መላእክት ጥናት"angelology"፣ በነገረ-ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው። ፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦ በአህሉል ኪታብ"People of the Book"፣ በመጽሐፍት"scriptures"፣ በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation"፣ በመጽሐፍት ልኬት"Standardization"፣ በባይብል ግጭት"Contradiction"፣ በኦሪት"Torah"፣ በወንጌል"Gospel" ላይ ነው። አባሪ ኮርሶች፦ 1. ሥነ-አመክንዮ"logic" 2. ሥነ-ልቦና"psychology" 3. ሥነ-ቋንቋ"linguistics" ናቸው። ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት የቦርዱ አካላት በውስጥ ያናግሩ! እኅት ረምላን፦https://t.me/REMLANEG እኅት ሰላምን፦ http://t.me/SeuweSe አኅት ዘሃራን፦ https://t.me/Zhara_mustefa እኅት አበባ፦http://t.me/temariwalji እኅት ነስርያን፦ https://t.me/Nesriyaaa ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ! ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ! 4.3K viewsedited 01:34