Get Mystery Box with random crypto!

በእርግጥም 'ሦስት ለሚሆን አምላክ፣ ሦስት ቅዱስ፣ ሦስት ልዑላን፣ ሦስት ጌቶች፣ ሦስት ነገሥታት፣ | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

በእርግጥም "ሦስት ለሚሆን አምላክ፣ ሦስት ቅዱስ፣ ሦስት ልዑላን፣ ሦስት ጌቶች፣ ሦስት ነገሥታት፣ ሦስት ገዢዎች" ብላችሁ ካስተማራችሁ በግልጽ መድብለ አማልክታውያን ናችሁ፦
፨ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 22-23
“ሦስት ልዑላን ገዢዎች፥ ሦስት ጌቶች ናቸው”።
፨ ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 26
“ሦስት ነገሥታት አንድ አገዛዝ ናቸው”።
፨ ሰይፈ ሥላሴ ዘረቡዕ ምዕራፍ 4 ቁጥር 52
“እነዚህ ገዢዎች በገጽ ሦስት በፈቃድ አንድ ናቸው”።

"ገጽ" ማለት "ፊት" ማለት ነው፥ ባለ ሦስት ፊት አምላክ የዐረማውያን እንጂ የአብርሃም አምላክ በፍጹም አይደለም፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 24
"ሦስት ገጽ አንድ አመለካከት ናቸው"።

ሥላሴ አካላቸው የተለያዩ ከሆኑ አካላቸው አንድ ዓይነት ወይስ የተለያየ? አንድ ዓይነት ከሆነ ምን ዓይነት አንድ ዓይነት? ከተለየስ ምን ዓይነት የተለየ አካል ነው? ገጽታቸውን ሦስት አርጎ ያለያየ ምን ዓይነት ገጽታ ይሆን? "መለኮት ሦስትም አንድም ነው" ማለት የጤና አይደለም፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘቀዳሚት ምዕራፍ 7 ቁጥር 68
"ለመለኮት ሦስትነት ምስጋና ይገባል"።
ሰይፈ ሥላሴ ዘቀዳሚት ምዕራፍ 7 ቁጥር 69
"ለመለኮት አንድነት ምስጋና ይገባል"።
ገድለ ተክለ ሃይማኖት 60(61)፥12
"የመለኮት ሦስትነት መቆፈሪያ ልቡን በኮሰተረው እና በቆፈረው ጊዜ"።

በምድር ላይ ያለው እያንዳንዱ ሰው የራሱ ገጽ ያለው ሲሆን በስም፣ በአካል፣ በግብር ስምንት ቢልዮን ነው፥ ግን የሁሉም ምንነት አንድ ምንነት ስለሆነ ስምንት ቢልዮን ሰው አንድ ሰው አይባልም። ስምንት ቢልዮን ሰዎች ያሰኘው በማንነት እከሌ እየተባለ ስለሚለያይ ነው፥ አምላክ በማንነት እከሌ እየተባለ በስም፣ በአካል፣ በግብር ከተለያየ አንድ ሳይሆን ብዙ ነው። በሦስት ፊቶች የተለያየ መለኮት፣ ጌታ፣ ንጉሥ፣ አምላክ እና ፈጣሪ መድብለ አማልክት እንጂ ሌላ አይደለም፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘእሑድ ምዕራፍ 8 ቁጥር 41
"ሥስት የምትሆን ጌታዬ፣ ንጉሤ፣ አምላኬ፣ ፈጣሪዬ ሆይ! ለአዳራሽህ መብራት ለመመላለሻህም ፀሐይ አትፈልግም"።
መልክአ ሥላሴ ቁጥር 39
“ሥሉስ ቅዱስ ሆይ! የአደም እና የሔዋን "ፈጣሪዎቻቸው" እንደመሆናችሁ የምርኮኞች ነጻ አውጪ የሆነ ኃይላችሁ የጣዖታትን ሐሰተኝነት አጋለጠ"።

ሥላሴ "ፈጣሪዎች" ከተባሉ ስንት ፈጣሪ ሊኖር ነው? እነርሱም በድፍረት፦ "ኤሎሂም" ማለት "አማልክት" ማለት ነውና "አማልክት" የተባለው ሥላሴን አምልካች ነው" በማለታቸው ሥላሴ "አማልክት" መሆናቸው በግልጽ ነግረውናል። ሳያቅማሙም "ሦስት በአንድ የሆነ አምላክ"Triune God" ይሉታል፣ በአገራችን "ሥላሴ" ማለት "ሦስትነት" ማለት ነው፣ በዐረብ ክርስቲያኖች ዘንድ "ተሥሊስ" تَسْلِيث‎ ይሉታል። በፕሮቴስታንት ዘንድ ደግሞ፦ "አብ እራሱን የቻለ አእምሮ፣ ፈቃድ እና ስሜት አለው፣ ወልድ እራሱን የቻለ አእምሮ፣ ፈቃድ እና ስሜት አለው፣ መንፈስ ቅዱስ እራሱን የቻለ አእምሮ፣ ፈቃድ እና ስሜት አለው" ይላሉ፥ ይህ በኦርቶዶክስ ሦስት አማልክት ነው፦
መጽሐፈ ሜላድ 6፥38 ሦስት ልብ፣ ሦስት ቃል፣ ሦስት እስትንፋስ የሚል ግን ሦስት አማልክት አመለከ"።

"ለበወ" ማለት "አወቀ" ማለት ከሆነ ሦስቱ ማንንነቶች የየራሳቸው ዕውቀት ካላቸው እና እርስ በእርስ የሚነጋገሩ ከሆነ ሦስት ልብ ይሆናል፥ በፕሮቴስታንት ልክ እንደ አርጌናሳውያን አብ ወልድን እና መንፈስ ቅዱስን የሚገዛቸው አስተዳዳሪያቸው ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥28 አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማብራሪያ፦ "ወልድ ለአብ የሚገዛው በአስተዳደር ረገድ ሲሆን..በሥላሴ አካላት መካከል አብ የበላይ አስተዳዳሪ ነው"

እንግዲህ ሥላሴ ሰው በማመኑ የሚድንበት እና በመካዱ የሚጠፋበት አንቀጸ እምነት ቢሆን ኖሮ ነቢያት እና ሐዋርያት በግልጽ ልክ እንደ ተውሒድ ያስቀምጡልን ነበር። ነገር ግን በግልጠተ መለኮት ውስጥ የሥላሴ አሳቡ ስለሌለ «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛን ጽናቱን ይስጠን! አሚን። 

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም