Get Mystery Box with random crypto!

ጭራሽ አዳም ላይ ያሉ የአካል ክፍሎች ሁሉ ሥላሴ ላይ እንዳሉ እና በተጠቃሽነት ራስ፣ ፊት፣ ጆሮዎች | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ጭራሽ አዳም ላይ ያሉ የአካል ክፍሎች ሁሉ ሥላሴ ላይ እንዳሉ እና በተጠቃሽነት ራስ፣ ፊት፣ ጆሮዎች፣ ዓይኖች፣ አፍንጫ፣ ከንፈር፣ እጆች፣ እግሮች እና ብብቶች እንዳሉት መጽሐፈ ሜላድ በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ አስቀምጦታል፦
መጽሐፈ ሜላድ ዘወርኃ ግንቦት ቁጥር 7
በአዳም ላይ ያለው መልክ ሁሉ በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ላይ አለ፥ ራስም ቢሆን፣ ገጽ(ፊት) ቢሆን፣ ጆሮዎች እና ዓይኖች ቢሆኑም፣ አፍንጫ እና ከንፈር ቢሆን፣ እጆች እና እግሮች፣ ብብቶች ቢሆኑ ከአብ፣ ለወልድ እና ለመንፈስ ቅዱስ ሙሉ አካል አላቸው። ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ሊቃውንት አባቶቻችን እንደተናገሩት ለእግዚአብሔር ዓይኖች፣ ጆሮዎች፣ እጆች እና እግሮች ሌሎች የቀሩት አካላት እንዳሉት እናምናለን።

መልአክ ሥላሴ የተባለው የኦርቶዶክስ መጽሐፍ ሥላሴ "ደም" "ወርች" "ጎን" "ከርስ" "ኩላሊት" "ወገብ" "አብራክ" "ተረከዝ" "ጫማ" "ጥፍር" "ጣት" እንዳላቸው ይናገራል፦
"ደም"
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ! "ስርየተ ደማችሁ" ስርየተ ኃጢኣት ነውና የነፍሴን ቤት መቃን በስርየት "ደማችሁ" እርጩት።

"ወርች"
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የአዳምን ወርች ላጸና መለኮታዊ "ወርቾቻችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ጎን"
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የወርቅ አስፈላጊያቸው ላይደለ መለኮታዊ "ጎኖቻችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ከርስ"
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የፍጡራንን ሆድ ለፈጠረ ለማይመረመር "ከርሳችሁ" ሰላምታ ይገባል።”

"ኩላሊት"
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! በህላዌ አካል ትክክል ለሚሆኑ "ኩላሊታችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ወገብ"
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! መታጠቂያው የቸርነት ሰቅ ለሆነው "ወገባችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"አብራክ"
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የፍጥረት ሁሉ አብራክ ለሚያሰግድ "አብራካችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ተረከዝ"
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ብርሃናት ለተጎናፀፈው "ተረከዛችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ጫማ"
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ለሚራመድ "ጫማችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ጥፍር"
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! "ከጥፍሮቻችሁ" ጋር ያለመነጣጠል ተባብረው ተመሳስለው ላሉ "ጣቶቻችሁ" ሰላምታ ይገባል።

"ወርች" ማለት ለከብት "የፊት እግር" ሲሆን ለሰው "ባት" ነው፣ "ከርስ" ማለት "ማኅፀን" ወይም "ሆድ" ማለት ነው፣ "አብራክ" ማለት ተራክቦ የሚደረግበት "የዘር ከረጢት ነው። "ደም" እና "ኩላሊት" ሥጋ ነው፥ ሌሎቹ ይሁኑ እሺ! "ከርስ" ምን ያረግላቸዋል? ምግብ ይበላሉ ወይስ ያረግዛሉ? "አብራክ" ምን ያረግላቸዋል? ተራክቦ ያረጋሉ? የእኛን ዓሣ ስትጎረጉሩ የእናንተን ዘንዶ አወጣንባችሁ።
አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም