Get Mystery Box with random crypto!

Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

የቴሌግራም ቻናል አርማ teklu_tilahun — Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን T
የቴሌግራም ቻናል አርማ teklu_tilahun — Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን
የሰርጥ አድራሻ: @teklu_tilahun
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.25K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-06-02 19:56:56
#የራስህን_ሲኦል_አትፍጠር!

ለብዙ ነገሮች ግድ ሲኖርህ፣ ስለ ሁሉም ሰውና ስለ ሁሉም ነገር ስትጨነቅ ሁልጊዜ የሚመችህና ደስተኛ እንደምትሆንና ሁሉም ነገር ልክ አንተ በምትፈልገው መንገድ መሄድ እንዳለበት እንዲሰማህ ያደርግህ ይሆናል፡፡

ይህ ግን በሽታ ነው፡፡

በቁመናህ የሚበላህ ነገር ነው፡፡ እንደዚህ ስታደርግ እያንዳንዱን የሀሳብ ልዩነት እንደ የፍትህ አለመኖር፣

እያንዳንዱን ችግር እንደ ውድቀት፣

እያንዳንዱን አለመመቸት እንደ የግል ጥላቻ፣

እያንዳንዱን አለመግባባት እንደ መከዳት ስለምትቆጥር የራስህን ሲኦል ፈጥረህ የትም በማያደርስ የማያቋርጥ አዙሪት ውስጥ ትዋጣለህ፡፡

የራስህን ሲኦል አትፍጠር፣ ከአዙሪቱ ውጣ! መንገዱን ደግሞ መጽሐፉ ያሳይሀል

#በጥበብ_መኖር መጽሐፍ #5ተኛው ዕትም በገበያ ላይ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
5.8K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 06:53:29
#ምርጥ_10_አባባሎች

#አንድ "እናንተ የእጣ ፈንታችሁ ጌታ ናችሁ። የራሳችሁን አካባቢ የመቀየር፣ የመምራት እና የመቆጣጠር አቅም አላችሁ።"

#ሁለት "ሀሳብህን በአንድ የተወሰነ ግብ ላይ አኑር፤ ያኔ ዓለም አንተን ለማሳለፍ ምን ያህል በፍጥነት ገለል ብሎ እንደሚቆም ትመለከታለህ።"

#ሶስት "ቆራጥነትን ለማዳበር መንገዱ ካለህበት መጀመር ነው።"

#አራት "ጥንካሬ እና እድገት የሚመጣው ቀጣይነት ባለው ጥረት እና ትግል ብቻ ነው። "

#አምስት "የስኬቶቻችሁ ከፍታ ብቸኛው ገደብ የህልሞቻችሁ ትልቅነት እና ለእነሱ ጠንክሮ ለመስራት ፈቃደኛ መሆን ነው።"

#ስድስት "አስታውሱ! በህይወት ከፍ ያለ ነገር ለማለም እና የተትረፈረፈ ህይወትን ለመጠየቅ፤ መከራን እና ድህነትን ከመቀበል የበለጠ ጥረት አያስፈልግም።"

#ሰባት "አብዛኞቹ ሰዎች ሽንፈት የሚያጋጥማቸው ፤ አዳዲስ እቅዶችን ለማቀድ ጽናት ስለማይኖራቸው ነው።"

#ስምንት "ራስህን ካላሸነፍክ በራስህ ትሸነፋለህ።"

#ዘጠኝ "የሁሉም ስኬት መነሻ ነጥብ ግልጽ የሆነ የህይወት ዓላማ መኖር ነው።"

#አስር "ራእዮቻችሁን እና ህልሞቻችሁን የነፍሳችሁ ልጆች፣ የመጨረሻ የስኬቶቻችሁ ንድፍ እንደሆኑ አድርጋችሁ ተንከባከቡ። "

#አስበህ_ሀብታም_ሁን መጽሐፍ #8ተኛው ዕትም በገበያ ላይ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
6.2K views03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 20:11:37
#ግንኙነትን_ሊያበላሹ_የሚችሉ_4_የገንዘብ_ስህተቶች

#1_ዕዳ

ገንዘብን ማስተዳደር አለመቻል ሰዎች ብድር ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋል። ዕዳ ሲከማች ግንኙነትን ብቻ ሳይሆን ሙሉ ህይወትን ምስቅልቅል ውስጥ ይከታል።

#2_ያለ_በጀት_መንቀሳቀስ

ፋይናንስን አለመከታተል በተዘዋዋሪ መልኩም ቢሆን ግንኙነትን ይጎዳል። አጋሮች ገንዘባቸው በምን ላይ እንደሚውል በግልፅ ካልተረዱ የገንዘብ እጥረት ውጥረት ውስጥ ይከታል። ይህም ወደ ግጭት መንስዔዎች ያመራል።

#3_ከመጠን_ያለፈ_ቁጠባ

ተመጣጣኝ ቁጠባን ያካተተ የሂሳብ አያያዝ በእርግጥ ጥሩ ነገር ነው። ነገር ግን መሰረታዊ ፍላጎትን ያላካተተ የገንዘብ ስግብግብነት ጤናማ ኑሮን ያዛባል።

#በአንዱ_የገንዘብ_ምንጭ_ላይ_ብቻ_መደገፍ

ይህ ሁኔታ አንድ ሰው ሌላውን ገንዘብ በሚመዘብርበት ወቅት የሚፈጠር ክስተት ነው። አሁን ባለንበት ዘመን ጥንዶች እንደ ኢኮኖሚ ደረጃቸው ግንኙነታቸውን በገንዘብ መደገፍ አስፈላጊ የሆነበት ዘመን ነው።

#ገንዘብ_ሳይኮሎጂ መጽሐፍ
#The_Psychology_of_Money

#በአማርኛ እና #በእንግሊዘኛ ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል።


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
5.9K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 06:37:48 #ዓለም_እንደምታያት_ናት!

ከተፈጥሮ በስተቀር ከአንተ በላይ የሆነ ምንም ኃይል አጋጥሞህ አያውቅም፡፡

በከፍተኛ ጉልበት የሚነፍሰውን ነፋስ ያስጀመርከው አንተ አይደለህም፡፡ ተፈጥረህ ተገኘህ እንጂ ራስህንም የፈጠርከው አንተ አይደለህም፡፡ ከአንተ በላይ ያለ ኃይል ወይም የሆነ ነገር ባይኖር ኖሮ ምንም ነገር ሊከሰት አይችልም ነበር፡፡

አንተን የፈጠረህ ነገር ምን እንደሆነ ስለማታውቅ፥ ቀጥሎ የምትለው ነገር የሰራኝ ፈጣሪ መሆን አለበት ነው፡፡

ፈጣሪ የመጣው ከየት ነው?

አንተ ሰው ስለሆንክ፥ ፈጣሪ በሰው መልክ የተሰራ ትልቅ አካል እንደሆነ ታስባለህ፡፡ ጎሽ ብትሆን ኖሮ ደግሞ፥ ፈጣሪ በጎሽ መልክ የተሰራ ትልቅ አካል እንደሆነ ታስብ ነበር፡፡ ስለ ፈጣሪ ያለህ አመለካከት በሙሉ የመጣው ስለ ማንነትህ ካለህ ውስን ተሞክሮና ውስን ምናብ ነው፡፡

በሰው መልክ ስለተሰራህ፥ ፈጣሪ የሰው መልክ የያዘ ትልቅ አካል እንደሆነ ታስባለህ፡፡ ስለዚህ ፈጣሪ ወይም ኃይል ብለህ የምትጠራው የትኛውም ነገር አንተ ወይ የምታስበው አለዚያም የምታልመው በአእምሮህ ውስጥ ብቻ ያለ ነገር ነው፡፡ በእውነት መለማመድ የምትችለው ብቸኛው ነገር በውስጥህ ያለውን ነው፡፡ በውስጥህ ያለውን ደግሞ በጥልቀት አይተኸው አታውቅም፡፡

እስካሁን የምታውቃቸውን ነገሮች የተለማመድካቸው በአምስቱ የስሜት ህዋሳት የተወሰኑ ናቸው፡፡

አለምንም ይሁን ራስህን በተመለከተ እስካሁን የምታውቃቸው ነገሮች ሁሉ፥ የመጡት በማየት፥ በመስማት፥ በመንካት፥ በመቅመስና በማሽተት ብቻ ነው፡፡

እነዚህ ስሜት ህዋሳት ባይሰሩ፥ አለምንም ሆነ ራስህን አታውቅም ነበር፡፡

የስሜት ህዋሳት ሁሉንም ነገሮች የሚነግሩን ከሌላ ነገር ጋር በማነጻጸር ነው፡፡ ለምሳሌ ብረት ብትነካና ቅዝቃዜ ቢሰማህ የሰውነትህ ሙቀት ከብረቱ ሙቀት መጠን የበለጠ ስለሆነ ነው፡፡ የሰውነትህን ሙቀት ከብረቱ ሙቀት እጅግ ያነሰ ብታደርገው ብረቱ ሞቃት እንደሆነ ይሰማሃል፡፡ ስለዚህ ይህ የምትተማመንበት ልምምድ ሳይሆን በአካላዊ እውነታ ውስጥ ለመኖር ብቻ በቂ የሆነ ልምምድ ነው፡፡

በአምስቱ የስሜት ህዋሳት ግንዛቤዎች ምንም አይነት ተሞክሮ ቢኖርህ፥ ያ ተሞክሮ በዚህ ህልውና ውስጥ ለመኖር ብቻ በቂ የሆነ ልምድ ነው፡፡

#የሕይወት_ኬሚስትሪ መጽሐፍ #2ተኛው ዕትም በገበያ ላይ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
6.1K views03:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 06:37:44
5.1K views03:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 20:04:28
#አቦ_አትጨናነቅ!!

ሰዎችም ሆነ የቲቪ ማስታወቂያዎች የመልካም ሕይወት ቁልፉ አሪፍ ስራ ማግኘት፣ ወይም ዘናጭ መኪና ወይም ቆንጆ ሴት ጓደኛ ያለህ መሆን እንደሆነ እንድታምን ይፈልጋሉ፡፡

አለም ያለማቋረጥ የሚነግርህ ነገር፣ የተሻለ የሕይወት መንገድ የሚባለው ብዙ መግዛት፣ ብዙ ማግኘት፣ ብዙ መስራት፣ ብዙ መሆን እንደሆነ ነው፡፡

ስለዚህ ሁልጊዜ በተደጋጋሚ ስለሁሉም ነገር ግድ እንዲኖርህ በሚነገሩ መልዕክቶች ስለምትጨናነቅ ያለማቋረጥ አዲስ ቲቪ ስለመግዛት፤ የእረፍት ጊዜህን ከስራ ባልደረቦችህ በተሻለ ስለማሳለፍና አዲስ ጌጥ ስለመግዛት የምታስብ ትሆናለህ፡፡

ለምን? የእኔ ግምት ብዙ ነገሮችን ለማግኘት መጨነቅ ለስራ ጥሩ ስለሆነ ነው፡፡ የጥሩ ስራ መኖር ስህተት ባይሆንም ችግሩ ስለ ብዙ ነገሮች መጨነቅ ግን ለአእምሮ ጤንነት መጥፎ መሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በማይገባ አይነት የማይረቡና የውሸት ከሆኑ ነገሮች ጋር የተጣበቅክ እንድትሆንና ሕይወትህን ሙሉ የማይጨበጥ ደስታና እርካታ ስታሳድድ እንድትኖር ያደርግሃል፡፡

የመልካም ሕይወት ቁልፍ ስለ ብዙ ነገሮች መጨነቅ ሳይሆን፣ ስለ ትንሽ ለዚያውም እውነት፣ አስቸኳይና አስፈላጊ ስለሆነው ብቻ መጨነቅ ነው፡፡

#በጥበብ_መኖር መጽሐፍ
#The_subtle_art_of_not_giving_a...

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
6.1K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 06:33:45
#አንተ_እኮ_ውድ_ነህ!

ሰዎች ቢያገሉህ ወይም ቦታ ባይሰጡህ አትዘን። ብዙ ሰዎች ውድ ነገሮችን ባለማወቅ ይንቃሉ፤ ርካሽ ነገሮች ላይም ይሻማሉ።
ሁሉም ነገር በጊዜ ሂደት ያልፋል። ሁሉም ሰው በተለያዬ ሁኔታ፣ ለተወሰነ ጊዜ በህይወትህ ይከሰታል። ስለዚህ በህይወት እውነታ ተደሰት። መንገድህን ቀጥል።

የተወለድከው ከድሃ ቤተሰብ ከሆነ 'እንኳን ደስ ያለህ!' ምክንያቱም ይሄ ቤተሰብህን በጉብዝናህ ሃብታም እንድታደርግ ፈጣሪ የሰጠህ እድል ነው። ቀጣይነት ያለው ሰው ሁን። ነገሮችን በጅምር አታቋርጥ። ለራስህም ይሁን ለቤተሰብህ ለውጥን የምትጽፍ ልዩ ትሆናለህ።

ዋጋ ሳትከፍል ያለመሰዋትነት የምታሳካው ምንም ነገር አይኖርም። መሰዋትነት፣ ችግሮችን መጋፈጥ የህይወት አካል ስለሆነ- እመንበት። ትክክለኛውን ነገር ለማግኘት ተገቢውን ዋጋ እስከ-ከፈልክ ጸጸት ህመም ሆኖ ሰላምህን አይነሳህም።

የሰዎች መሄድ መምጣት ሳይሆን፣ ያ'ንተ መስራት አለመስራት ጥያቄ ሊሆንብህ ግድ ነው።

ልብ በል… አንተ ርካሽ ነገር አይደለህም- አንተ ውድ ነህ!

ምን ያህል ውድና ድንቅ አእምሮ የያዝክ መሆንህን ደግሞ

#ድብቁ_አእምሮህ_ድብቁ_ኃይልህ መጽሐፍ ያሳይሀል፡፡

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
6.4K views03:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 07:03:31
#መልካም_ጠዋት_መልካም_ዕሁድ!!!

የዛሬው ቀን . . . 

•  የራቀው ሰላማችሁ የሚመለስበት ቀን . . .

•  ከወደቃችሁበት የምትነሱበት ቀን . . .

•  ጀምራችሁ ያቆማችሁትን መልካም ነገር እንደገና የምትጀምሩበት ቀን . . . 

•  ግራ የገባችሁ ነገር መልክ የሚይዝበት ቀን . . . 

•  ተስፋ በቆረጣችሁበት ነገር ላይ የተስፋ ጭላንጭል የምታዩበት ቀን . . .

•  ፍርሃታችሁን አሸንፋችሁ የምትሄዱበት ቀን . . . 

#ይሁንላችሁ!!!

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
3.3K views04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 20:03:38
#4_ነገሮችን_ምንጊዜም_ቢሆን_አትርሳ!

#አንድ

መጥፎ ቀን ማሳለፍ ማለት ሙሉ ህይወትህ አብቅቶለታል ወይም ቀሪ ህይወትህ መጥፎ ይሆናል ማለት አይደለም።

#ሁለት

ፍጹም መሆንን ከራስህ አትጠብቅ፤ ነገር ግን በምትችለው ሁሉ የተሻለና ምርጥ ለመሆን ሁሌም የነቃ ሁን!

#ሶስት

ሰዎች ስላንተ ላላቸው አሉታዊ አስተሳሰብ አንተ ሃላፊነቱን መውሰድ የለብህም። ያ ችግርህ ሊሆን በፍጹም አይገባም።

#አራት

ሁሌም እያንዳንዷን በህይወት የምታጋጥምህ ፈተና አንድ እርምጃ ወደ ፊት የምታራምድህ፣ ለስኬትህ የምታቀርብህ መንደርደሪያ በመሆኗ፣ በፍጹም ተስፋ ለመቁረጥ ምክንያት አድርገህ እንዳታያት።

ፈገግታ ከፊትህ የማይለይ ለሌሎች ሰላምን የምታንጸባርቅ ሁን!!!

#የስኬት_አቡጊዳ መጽሐፍ በገበያ ላይ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
3.7K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 06:43:21 #3ት_የጊዜ_ምክሮች

ጊዜህ ወደር የማይገኝለት ስጦታህ ነው። በተፈጥሮ ያገኘኸው ውድ የሆነ መዋለ-ንዋይህ ሆኗል። ሁላችንም ቀናችንን ከምንጀምርበት ስንቆጥር እኩል 24 ሰአታት አሉን። ነገር ግን ጥቂት ሰዎች እንዴት ልዩ እና ስኬታማ ይሆናሉ? ሌሎች ምንም ነገር እንዳልቻሉ በሚሰማቸው በእኩል ሰአት!

ቁልፉ ይሄው ነው- በትክክል ጊዜያቸውን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ያውቁበታል!

እነዚህን ሶስት ነገሮች ተመልከት። ጊዜህን በትክክል እንድትጠቀም ይረዱሃል።

#አንደኛ 'የሁለት ደቂቃ ህግ'

ብዙ ጊዜ ላድርግ አላድርግ የማለት ማመንታቶች ጊዜህን ሳታውቀው ይሰርቁሃል። ምናልባት ለማድረግ ብትወስን ያን ያህል ልትፈጽመው ከባድ አይሆንም። ስለዚህ አእምሮህን በሁለት ደቂቃ ውስጥ የማድረግ ውሳኔን እንዲችል አሰልጥነው። ያ ጊዜህን በማመንታት ስንፍና እንዳታጣው ይረዳሃል!

#ሁለተኛ ለትላልቅ አላማዎች ትናንሽ መነሳሻዎች ይኑሩህ

ትላልቅ አላማዎችህ ያንተ መዳረሻ ምስል የምታስቀምጥባቸው ይሆናሉ። ትናንሽ መነሳሻዎችህ ደግሞ የምትሰራቸው ጥቃቅን ስራዎች ይሆናሉ። እነዚህም የህይወትህን ዋና ግብ እውን የምታደርግባቸው ብልሃትህ ይሆናሉ። ጥቃቅን ነገሮችን መስራት የቀን ተቀን ልማድህ ሊሆን ይገባል። አሊያ ትልቁን ማሳካት አይቻልም። ጊዜህንም ባንዴ የመግዘፍ ፍላጎትህን እያለምክ ከማባከን ታድናለህ።

#ሶስተኛ በይበልጥ አንድ ስራ ላይ አተኩር

ብዙ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ ሃይል ማጥፋት ውጤታማ አያደርግም። ጊዜን በመባከን ማጥፋት ይሆናል። ሳይኮሎጂ መኪና እየነዱ ቴክስት መጻጻፍ አደጋ እንደሚኖረው ያስረዳል። ለምን ይመስልሃል? ሰው ሁለት ወይም ሶስት ነገሮች ላይ እኩል ትኩረት ማድረግ ስለማይችል ነው። አንዱ ላይ ካተኮርክ ግን ውጤታማ እንደሚያደርግህ አያጠራጥርም። ስለዚህ ትኩረትህን አላማህ ላይ አድርግ። ያኔም በጥራት፣ በከፍታ የምትፈልገውን ታሳካለህ።

#በልኬት_ወደ_ስኬት መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- http://shorturl.at/binrX
4.6K views03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ