Get Mystery Box with random crypto!

#3ት_የጊዜ_ምክሮች ጊዜህ ወደር የማይገኝለት ስጦታህ ነው። በተፈጥሮ ያገኘኸው ውድ የሆነ መዋለ- | Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

#3ት_የጊዜ_ምክሮች

ጊዜህ ወደር የማይገኝለት ስጦታህ ነው። በተፈጥሮ ያገኘኸው ውድ የሆነ መዋለ-ንዋይህ ሆኗል። ሁላችንም ቀናችንን ከምንጀምርበት ስንቆጥር እኩል 24 ሰአታት አሉን። ነገር ግን ጥቂት ሰዎች እንዴት ልዩ እና ስኬታማ ይሆናሉ? ሌሎች ምንም ነገር እንዳልቻሉ በሚሰማቸው በእኩል ሰአት!

ቁልፉ ይሄው ነው- በትክክል ጊዜያቸውን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ያውቁበታል!

እነዚህን ሶስት ነገሮች ተመልከት። ጊዜህን በትክክል እንድትጠቀም ይረዱሃል።

#አንደኛ 'የሁለት ደቂቃ ህግ'

ብዙ ጊዜ ላድርግ አላድርግ የማለት ማመንታቶች ጊዜህን ሳታውቀው ይሰርቁሃል። ምናልባት ለማድረግ ብትወስን ያን ያህል ልትፈጽመው ከባድ አይሆንም። ስለዚህ አእምሮህን በሁለት ደቂቃ ውስጥ የማድረግ ውሳኔን እንዲችል አሰልጥነው። ያ ጊዜህን በማመንታት ስንፍና እንዳታጣው ይረዳሃል!

#ሁለተኛ ለትላልቅ አላማዎች ትናንሽ መነሳሻዎች ይኑሩህ

ትላልቅ አላማዎችህ ያንተ መዳረሻ ምስል የምታስቀምጥባቸው ይሆናሉ። ትናንሽ መነሳሻዎችህ ደግሞ የምትሰራቸው ጥቃቅን ስራዎች ይሆናሉ። እነዚህም የህይወትህን ዋና ግብ እውን የምታደርግባቸው ብልሃትህ ይሆናሉ። ጥቃቅን ነገሮችን መስራት የቀን ተቀን ልማድህ ሊሆን ይገባል። አሊያ ትልቁን ማሳካት አይቻልም። ጊዜህንም ባንዴ የመግዘፍ ፍላጎትህን እያለምክ ከማባከን ታድናለህ።

#ሶስተኛ በይበልጥ አንድ ስራ ላይ አተኩር

ብዙ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ ሃይል ማጥፋት ውጤታማ አያደርግም። ጊዜን በመባከን ማጥፋት ይሆናል። ሳይኮሎጂ መኪና እየነዱ ቴክስት መጻጻፍ አደጋ እንደሚኖረው ያስረዳል። ለምን ይመስልሃል? ሰው ሁለት ወይም ሶስት ነገሮች ላይ እኩል ትኩረት ማድረግ ስለማይችል ነው። አንዱ ላይ ካተኮርክ ግን ውጤታማ እንደሚያደርግህ አያጠራጥርም። ስለዚህ ትኩረትህን አላማህ ላይ አድርግ። ያኔም በጥራት፣ በከፍታ የምትፈልገውን ታሳካለህ።

#በልኬት_ወደ_ስኬት መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- http://shorturl.at/binrX