Get Mystery Box with random crypto!

Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

የቴሌግራም ቻናል አርማ teklu_tilahun — Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን T
የቴሌግራም ቻናል አርማ teklu_tilahun — Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን
የሰርጥ አድራሻ: @teklu_tilahun
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 67.94K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-07 06:35:57
#3_ሚስጥሮች_ስለ_ገንዘብ

ገንዘብህን ማዋል ያለብህ ቦታ ላይ ካዋልክ በእጥፍ ልታሳድገው ትችላለህ። እንዴት መሰለህ ...

#አንደኛ ሀብታሞች መቼም ለገንዘብ አይሰሩም። ገንዘብ እንዲሰራላቸው ብልሃትን ይከተላሉ።

ገንዘብህ የበለጠ ገቢ እንዲያስገኝልህ መንገድ መፍጠር ይኖርብሃል።

አሁን ያለህ ገንዘብ ምን ያህል ተጨማሪ ገንዘብ ሊያስገኝልህ እንደሚችል አቅድ፤ እንጂ ባለበት ላይ ቁጠባ በሚል እሳቤ ብቻ የምትከምረው ከሆነ የማድረግ አቅሙ ይወርድና ይናድብሃል then ሁሌም የምትፈልገውን የማታገኝ ለፊ ብቻ ትሆናለህ። የምትቆጥበው ለተሻለ ምርት ይሁን።

#ሁለተኛ ላደርገው አልችልም የምትለውን እምነት አቁም። ይልቁንም እንዴት ልታሳካው እንደምትችል አስብበት። ይህ ራስንና አቅምን የማስፋት መመሪያ ነው። አሁን ያለህበትን ተጨባጭ ሁኔታ በመገንዘብ ፍላጎትህን ማሳኪያ ድርጊቶችን ማከናወን ይኖርብሃል።

#ሶስተኛ ለልጆችህ መቼም በእነሱ ምክንያት ሀብታም መሆን እንዳልቻልክ እንዳትነግራቸው። ይልቁንም በእነሱ ምክንያት ሀብታም እንደሆንክ አብስራቸው። ለዛም ብልሃቶችን ማወቅ ይኖርብብሃል። ያን አይነት አመስጋኝ ለመሆን ብልሃት ከቅልጥፍና ጋር ያንተ መሆን ይኖርበታል።

ተጨማሪ ብልሀቶችን ትፈልጋለህ? RICH DAD POOR DAD የተሰኘውን መጽሐፍ የጻፈው ሮበርት ኪዮሳኪ አዲሱ መጽሐፍ #ሀብት_የመገንባት_ጥበብ በገበያ ላይ ውሎልሀል፡፡ ብeብ ብልሀቶችን ያስተምርሀል፡፡

#ሀብት_የመገንባት_ጥበብ መጽሐፍ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
1.9K views03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 20:01:57
#10_መረዳት_ያለብህ_እውነቶች

#አንድ- ደሞዝ ማለት ህልምህን እንዳትኖረው ቀጣሪዎችህ የሚሰጡህ አደንዛዥ እጽ ማለት ነው።

#ሁለት- ነገሮችን ለመጀመር ጥሩ ጊዜ የምትጠብቅ ከሆነ፣ ሙሉ ህይወትህን ታባክናለህ እንጂ ምንም የሚፈጠር አዲስ ነገር አይኖርም። ምክንያቱም ትክክለኛው ጊዜ አሁን ስለሆነ።

#ሶስት- ምንም ያህል ቅርብ የምትላቸው ጓደኞችህን እና ቤተሰቦችህን ብታምናቸው እንኳ፣ ስላንተ ሁሉን ነገር እንዲያውቁ አታድርግ።

#አራት- ሙሉ ለሙሉ የቅርብ ጓደኞችህን የምታጣው ያኔ ነው... ራስህን መለወጥ ስትጀምር!

#አምስት- አስር እጥፍ ደስተኛ መሆን ከፈለግክ ይቅር ባይ ሁን እና ለችግርህ ማንንም ተወቃሽ ማድረግ አቁም።

#ስድስት- በሳል ሰው የምትሆነው ራስህን መምራት ስትጀምር ነው።

#ሰባት- ራስህን እንዴት እንደምትቀይር የሚያስተምሩ መቶ መጽሐፎች አያስፈልጉህም። የሚያስፈልግህ ተግባራዊ መሆን እና በራስህ የምትከተለው ስነ-ስርአት ነው።

#ስምንት- በአለም ላይ ያለህ ከባዱ ተልእኮ ቢኖር ትኩረትህን አላማህ ላይ ማድረግ ነው። ቀላሉ ደግሞ እያማረሩ መኖር ነው። የቱን ትመርጣለህ?

#ዘጠኝ- ሰዎች አስፈላጊ ያልሆነ ጓደኝነት ላይ የሚቆዩት ብቸኝነትን ስለሚፈሩ ብቻ ነው። አንተስ?

#አስር- ከላይ ያነበብካቸው አንተን እንደሚጠቅሙህ ካሰብክ #የሕይወት_መመሪያን መጽሐፍ እንድታነብ እንዲሁም ይሄን #ሼር በማድረግ ወዳጆችህን እንድትጋብዛቸው በትህትና እጠይቅሀለሁ፡፡

መልካም ጊዜ

#የሕይወት_መመሪያ_መጽሐፍ 9ኛው ዕትም በገበያ ላይ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
3.4K views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 08:26:51 #ይገርማል!

በአንድ ወቅት፤ አንድ እጅግ ሀብታም የሆነ ሰአሊ በአንዲት ትንሽዬ መንደር ውስጥ ይኖር ነበር። እጅግ ማራኪ ስእሎችን በውድ ዋጋ በመሸጥም ነበር የሚተዳደረው።

ታዲያ በመንደሯ የሚኖሩ ድሀ ሰዎች እጅግ ይጠሉት እና ስግብግብ እንደሆነ ያሙታል።

ወደ ቤቱም በመሄድ ''አንተ ብዙ ገንዘብ ያለህ ሰው ነህ። ነገር ግን በመንደሯ ያሉትን ድሆች አትደግፍም። ስጋ የሚሸጠውን ሰው ብትመለከት ያንተን ያህል ሃብታም አይደለም። ነገር ግን ከሚሸጠው ስጋ ላይ ለድሆች ያካፍላል። የመንደሩ ሰዎችም ይወዱታል። እንዲሁም ዳቦ ሻጩን ተመልከት እሱም ድሀ ሲሆን ብዙ ቤተሰቦች አሉት። ነገር ግን ለድሆች በነጻ ዳቦ ይሰጣል። አንተ ለምን በዚህ ልክ ስግብግብ ትሆናለህ?'' አሉት።
ሰአሊውም ለወቀሳቸው መልስ ሳይሰጥ ሁሌም በፈገግታ ይመልሳቸው ነበር።

የመንደሯ ነዋሪዎችም የሰአሊው ፈገግታ ግራ ያጋባቸው ነበር። በዚህም ራስ ወዳድ እና ሀብት በመሰብሰብ ብቻ የተጠመደ ስግብግብ አድርገው ይቆጥሩት ነበር።

አንድ ቀንም ሀብታሙ ሰአሊ በጠና ታመመ ነገር ግን አንድም የመንደሯ ኗሪ ሊጠይቀው ወይም ሊረዳው አልመጣም። ስለዚህ ብቻውን የሚኖረው ሰአሊ ህይወቱ ያልፋል።

ከዚያም በኋላ ስጋ-ሻጩ እና ዳቦ-ጋጋሪው ለመንደሩ ይሰጡት የነበረውን ስጋ እና ዳቦ መስጠት ያቆማሉ።
ስለዚህ የመንደሩ ድሆች ለምን እርዳታቸውን እንዳቆሙ በሀዘን ተሞልተው ይጠይቃሉ።

ሁለቱም ከዚህ በፊት ወር እስከ ወር ለሚሰጧቸው ስጋ እና ዳቦ ህይወቱ ያለፈው ሰአሊ ሰው ይከፍላቸው እንደነበር እንዲሁም አሁን ያ ሰው ስለሞተ ለስጋም ሆነ ለዳቦ ዋጋ የሚከፍላቸው እንደሌለ ይነግሯቸዋል።

በዚህም የመንደሩ ኗሪዎች ይጠሉት እና ስግብግብ እያሉ ያሙት የነበረው ሰአሊ ይረዳቸው እንደነበር ይገነዘባሉ።

ቁምነገሩ~ ሰዎችን በውጫዊ ገጽታቸው እና ስለ እነሱ በሚወራው አሉባልታ ልንገምታቸው አይገባም። እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች የሚያደርጉትን መልካም ነገር በግልጽ ማሳየት አይፈልጉም ማለት ክፉ ናቸው ማለት አይደለም።

መልካምነት ራስ ጋር የሚቆይ ሰላም ነውና።

#በልኬት_ወደ_ስኬት_መጽሐፍ በገበያ ላ#ድሀ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
4.3K views05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 06:31:38
4.1K views03:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 20:03:34
#ደስታ_ባንተ_ይደሰት!

በዚህች ምድር ያለ -የሰው ልጅ ሁሉ ለማግኘት የሚጥረው #ደስታ ነው።

ደስታንም ለማግኘት ከፈለግክ፣ እርግጠኛ የምትሆንበት አንድ መንገድ አለ።

እሱም ሀሳብህን መቆጣጠር ነው።

ደስታ ከውጭ ሁኔታ የሚታይ አይደለም።

የሚያምር ልብስ ብትለብስ፣ ያማረ ቤት ቢኖርህ፣ አዲስ መኪና ብትገዛ፣ ቆንጆ ፍቅረኛ ብትኖርህ፣ አቋምህ የተስተካከለ ቢሆን... ውስጥህ ሰላም ያለው ሀሳብ ከሌለ ደስተኛ ልትሆን አትችልም።

ስለዚህ ደስታ የውስጥ ስሜት እንጂ ከላይ የሚታይ አይደለም።

ደስታህን የምታገኘው ሀሳብህን መቆጣጠር ስትችል ነው።

ለሁሉም ነገር ጊዜ እንዳለው ሲገባህ

ትግስት መራራ፣ ፍሬዋ ግን ጣፋጭ እንደሆነ ስታውቅ

ለምትሰራው ስራ ለቤተሰብህ፣ ለጓደኞችህ፣ በዙሪያህ ላሉ ሰዎች ሁሉ ፍቅር ሲኖርህ

አዎንታዊ እና አርቆ አሳቢ ስትሆን

ከውጪህ ይልቅ ውስጥህን በአእምሮ እውቀት፣ በልብ ፍቅር ለማሳመር ስትሻ…

አንተ ብቻ ሳትሆን ደስታም ባንተ ይደሰታል!

#ራስን_መምራት_መጽሐፍ በጠብታ ማር ደራሲ ዴል ካርኒጌ

#2ተኛው ዕትም በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል::


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
4.8K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 15:08:15
የሕይወት ህግ!

የሕይወት ህግ ቀላል ነው፤

አዳኝ ወይም ታዳኝ መሆን

ምርጫው ያንተ ነው!

ሕይወት ቀመሮች መጽሐፍ በገበያ ላይ፡፡ በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
5.1K viewsedited  12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 06:30:32
ቃላት እውን ይሆናሉ

በሰንበት ትምህርት ቤት ስማር ያገኘሁት ጠቃሚ ትምህርት፡-

“ቃል ስጋ ሆነ በመካከላችንም አደረ፡፡” ዮሐ 1÷14

በእውናዊ ህይወት፣ ቃላት አካላዊ እውን ይሆናሉ፡፡

እያንዳንዱ የኢኮኖሚ መደብ ማንነቱን የሚያሳይበት እና ራሱን የሚገልጥበት ቃላት አሉት፡፡

ሀብታም ሰዎች ሀብታም ቃላትን ይጠቀማሉ፤

የመካከለኛ መደብ ሰዎች የመካከለኛ መደብ ቃላትን ይጠቀማሉ፤

ድሀ ሰዎች ድሀ ቃላትን ይጠቀማሉ፡፡

“የምታስበውን ነገር ታመጣለህ” ይባላል፡፡ በተመሳሳይም የምንናገራቸው እና የምንጠቀማቸው ቃላት እውን እንደሚሆኑ አምናለሁ፡፡

የድሀ ሰዎች የተለመዱ ቃላት “አልችልም፤ መግዛት አልችልም፤ አቅም የለኝም፤ አይሆንልኝም” የሚሉ ናቸው፡፡

ሀብታም ሰዎች እንዲህ ይላሉ፣ “ልገዛው የምችለው እንዴት ነው? አቅም ሊኖረኝ የሚችለው እንዴት ነው?” በአጭሩ፣ ሕይወትህን መቀየር ከፈለግክ፣ አስተሳሰብህን እና የምትናገራቸውን ቃላት ቀይር፡፡

ሀብት የመገንባት ጥበብ መጽሐፍ በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል::


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
5.3K viewsedited  03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 19:58:05 #ሰዎች_እንዲወዱህ_4ቱን_ተጠቀም!

#አንደኛ ስማቸውን አትርሳ። በየትኛውም ቋንቋ ስምህን እንደመስማት የሚስደስትህ ወይም ትኩረት እንድትሰጥ የሚያደርግህ ነገር የለም። ለምሳሌ ብዙ ህዝብ ባለበት መሃል ስምህ ሲጠራ ብትሰማ፤ ቆም-ዘወር አትልም? ያንን ነው ልነግርህ የፈለኩት... ሰዎች እንዲወዱህ አሊያም ትኩረታቸውን እንዲሰጡህ ከፈለግክ፣ ስማቸውን አትሳሳት! እናት እና አባትህን 'አባዬ' እማዬ' እያልክ ተጣርተህ ትኩረት ካልሰጡህ.... ለስለስ ባለ ድምጽ ስማቸውን ጥራ፤ በትክክል ትኩረታቸውን ታገኛለህ ይህ የተፈጥሮ እውነታ ነውና።

#ሁለተኛ ለሰዎች እውነተኛ የሆነ ፍላጎት እንዲሰማህ ከእነሱ ምንም ሳትጠብቅ ውደዳቸው። ያኔ እነሱ ባንተ ላይ ፍላጎት ኖራቸው -አልኖራቸው፣ ወደዱህ አልወደዱህ ያ ያንተ ጭንቀት አይሆንም። ደስታህ አንተ ለእነሱ ካለህ ስሜት የሚመነጭ ይሆናል።

#ሶስተኛ አንተ ከምትወደው ነገር ይልቅ እነሱ ስለሚወዱት ነገር የማውራት ልምድ ይኑርህ። ሁሉም ሰው ፊቱን በፈገግታ የሚሞላው አንዳች የጨዋታ ርእስ አይጠፋውም። ምናልባት ፊልም ማየት፣ ማነቃቂያ መድረኮችን መሳተፍ፣ ጋለሪ መሄድ 'ጀማ' ሆኖ መጨዋወት ሌላም ሌላም በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ፍላጎት ሊሆን ይችላል። ግድ የለህም የእነሱን ሙድ ለማራመድ ሞክር፤ እነሱም ያንኑ ያደርጉልሃል።

#አራተኛ አቦ ፈገግ በላ ብዙ ጊዜ ፈገግታ ቁምነገር መስሎ አይታይህም። ወዳጄ ፈገግታ የሚጋባ አስማት ነው። ሰዎች ፈገግ ስትል በድብቁ አእምሯቸው አንተ ለእነሱ ጥሩ ስሜት እንዳለህ ይሰማቸዋል። በዚህም ሊወዱህ ግድ ይሆንባቸዋል ማለት ነው። ለመወደድ ብለህ ብቻ ሳይሆን ውስጥህ እርጋታ እና ሰላም እንዲሰማህ ከፈለግክ፤ ደስታ የሚታይበት ፊት ያንተ ይሁን።

ሃዬ እኒህ ሃሳቦች የዴል ካርኒጌ ናቸው። ከተመቹህ ተጠቀምባቸውና ህይወትህን ቀለል አድርገው።

እኔም ወደዚህ ቻናል #ሼር በማድረግ ወዳጆችህን እንድትጋብዝ በትህትና እጠይቅሃለሁ!

አሃ ፈገግ በላ ደ'ሞ

#ራስን_መምራት_መጽሐፍ በጠብታ ማር ደራሲ ዴል ካርኒጌ

#2ተኛው ዕትም በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል::


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
5.4K views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 19:58:02
4.8K views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 11:45:06
#ጁሊያና

(በስሙር ድርሰት ተወዳጅ ብራዚላዊት ገፀባህርይ)

ጁሊያና ሳቋ ብቻ ሳይሆን ቁጣዋ ሁሉ ልዩ ውበት አለው።

ማርቆስ ከእርሷ ለመራቅ ቢሞክርም አልሆነለትም። ገና ሲያያት ልቡ ቀለጠ።

ከዚች ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ከሚዘምሩላት የላቲን ኮከብ፣ የብራዚል ጨረቃ፣ የሳኦ ፓውሎ ፀሐይ መራቅ ኩነኔ መስሎ ታየው። ህሊናው ወደ ፈትለ ልቡ ወደ ጁሊያና ጎን ወግነው ጦርነት ገጥመዋል።

ነፍሱ አብዝታ ተጨነቀች።

የትኛውን ማዳመጥ እንዳለበት ግራ ገብቶታል። ጁሊያናን መሸሽ በአየርላንድ ውስጥ የሕይወት ኬሚስትሪውን ሙሉ በሙሉ እንደሚያዛባው ጠንቅቆ ተረድቷል። ድንገት ወዷታል። ልቡ ፈትለን ሽሮ ጁሊያናን አንግሷል።

ጁሊያናን ሲቀርብ በዓለም ላይ ያለን ሁሉንም ነገር የጨበጠ ይመስለዋል።

#ከስሙር_መጽሐፍ_የተቀነጨበ

#ስሙር
#ሉባር
#ሰርድዮን

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ፡፡


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)

Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
5.7K views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ