Get Mystery Box with random crypto!

♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

የቴሌግራም ቻናል አርማ desupome — ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹
የቴሌግራም ቻናል አርማ desupome — ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹
የሰርጥ አድራሻ: @desupome
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.82K
የሰርጥ መግለጫ

☞ የስብህና ልቀት ለማምጣት ከመፃህፍት ጋር እናዉጋ
☞ በዚህ ቻናል ተወዳጅ የሆኑ ግጥሞችንና አስተማሪ ታሪኮችን ይቀርቡበታል
ለሃሳብ አስተያዬታች
@Almnu6
@Almnu6
መነጋገር ይቻላል
ገጣሚ ማለት በአጭረር አነጋገር እረጅም ሃሳብን መግለፅ ነዉ፡፡

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 11:24:26
184 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:20:35 ይህንን ፅሁፍ ካላነበብክ ፌስቡክ መጠቀምህን አቁም

ባልና ሚስት በትዳርና በፍቅር አብረው ይኖሩ ነበር ። እኚህ ባልና ሚስት ሁለት ልጆች ነበራቸውና ለልጆቹ ማሳደጊያ ባልየው ተጨማሪ ስራ ሊሰራ ተሰማምተው ራቅ ወዳለ አገር ሄዶ መስራት ጀመረ ። ለብዙ ዓመታት ከቆየ በኋላ ወደናፈቁት ቤተሰቦቹ ለመሄድ ሲነሳ ያልገመተው ነገር ከቀጣሪዎቹ ሰማ ። ደሞዙ በተለያየ ምክንያት ተቆራርጦ ከሚጠብቀው ከግማሽ በታች የሆነው 30 ብር ተሰጠው ።

የተሰጠውን ተቀብሎ እግረ መንገዱ ስራ ካገኘ እየሰራ ጠርቀም ያለ ብር ይዞ ቤተሰቦቹ ጋር ለመሄድ ተነሳ ። በመንገዱ አንድ ሸምገል ያሉ አባት አገኘ "ወዴት ትሄዳለህ ልጄ ከየት ነውስ ምትመጣው ?" አሉት ። እሱም ከመጀመርያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው ። እሳቸውም እንዲህ አሉት "እንግዲያውስ የምትፈልገውን ነገር ማግኘት ቀላል ነው ፤ እሱም እንዴት አባቴ ?" ሲል ጠየቃቸው እሳቸውም "በል አንድ አስር ብሩን አምጣና እነግርሃለሁ" አሉት የቸገረው ነውና አንስቶ ይሰጣቸዋል ።

እኒህ አባትም "አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ" ይህ ምክር አንድ ነው ይሉታል ። ሁለተኛውን አምጣና ሁለተኛውን መንገድ ልንገርህ ይሉታል ። እሱም በየዋህነት ይሰጣል "በማያገባህ አትግባ ፤ ይሄ ደግሞ ሁለተኛው ምክሬ ነው" ይሉታል ። "በቃ ይሄ ነው ?" ቢላቸው "አዎን ልጄ ሶስተኛውን አምጣና በጣም አሰፈላጊውና የመጨረሻውን ስጦታዬን ልስጥህ" አሉት ሰጠ ። እሳቸውም "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" ብለውት በባዶ ኪሱ ከሶስቱ ምክሮች ጋር አሰናበቱት ። እሱም ጉዞውን ወደ ቤቱ አደረገ ።

በመንገድ ነጋዴዎች አግኝቶ እያወጋ ሲጓዝ መሸ ። ነጋዴዎቹም ለምን ባቋራጭ አንሄድም በማለት ጉዞ ጀመሩ ። እሱም አብሯቸው ጉዞ እንደጀመረ የሽማግሌው አባት ምክር አንድ ትዝ አለው ። "አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ" የሚለው ። ስለዚህ ተመልሶ በሚያውቀው መንገድ ተጉዞ ብቻውን ከጨለመ በኋላ ከተማ ገባ ። "የመሸበት እንግዳ ነኝ አሳድሩኝ" በማለት ሰው ጠየቀ ። አንድ የዛ ከተማ ሰውም "ይኸውልህ ወንድሜ እዛ ቤት ሂድ ያሳድርሃል ፤ ነግር ግን እዛ ሰው ቤት የገባ አይወጣም ለማንኛውም እድልህን ሞክር ።" እሱም የተባለበት ቤት አንኳኩቶ ቤት የእንግዳ ነው ተብሎ ገባ ።

ታድያ ከቤቱ ባለቤት ጋር ሲያወጉ ከየት እንደመጣ ቢነግረው ባለቤቱ ተገርሞ "እንዴት ሆነክ ተረፍክ ባልከው መስመር ይመጡ የነበሩ ነጋዴች ተዘርፈው ነጋዴዎቹም ተገለው ከተማው ለቅሶ ብቻ እኮ ነው የሆነው" አለው ። ያቺ አስር ብር የገዛት ምክር በብር የማትገዛ ህይወቱን አተረፈችለት ማለት ነው ። ስለመሸ የቤቱ እመቤት ምግብ ለእንግዳው ልታቀርብ ከጓዳ ብቅ አለች" እንግዳው አይኑን ማመን አልቻለም ። የተወሰነ አካሏ ብቻ ነው ሰው የሚመስለው በዛ ላይ ማስፈራቷ ወደ ጓዳ እስክትገባ ናፈቀ ።

"ከዚህች ጋር እንዴት ትኖራለህ?" ብሎ ሊጠይቅ ሲል አንድ ነገር ትዝ አለው "በማያገባህ አትግባ" የሚለው ። ሆዱ መጠየቅ እየፈለገ ፍላጎቱን ተቋቁሞ አደረ ። ደግሞ ሌላ ፈተና የቤቱ ባለቤት ከመሄድህ በፊት የማሳይህ ነገር አለኝ ብሎ ወደ ጓሮ ወሰደውና የሰው አጽም የሞላበት ሜዳ አሳየው እንግዳውም "ይሄ ምንድ ነው ?" ማለት ፈልጎ ነበር ግን በማያገባህ አትግባ ብሎ ራሱን እየነቀነቀ ዝም አለ ። የቤቱ ባለቤትም ተገርሞ "በእውነት አንተ የምትገርም ሰው ነህ ፤ ይህ የምታየው ሰው ሁሉ ስለሚስቴ የማያገባቸውን አስተያየት ስለሰጡ የተገደሉ ናቸው ፤ እንዳንተ እዚህ ቤት በእንግድንት የመጡ ነበሩ ።

አንተ ግን ታላቅ ሰው ስለሆንክ የሀብቴን 1/4 ኛ ሰጥቼሃለሁና ይዘህ ትሄዳለህ" ተብሎ ባለ ብዙ ሀብት ሆኖ ወደ ቤቱ ሄደ ። እዛች ደሳሳ ጎጆ የደረሰው ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ነበር ። ሁሉም ነገር ቢለወጥም ቤቱን ግን አላጣውም ። በትልቅ እንጨት የምትዘጋ በሩን ገፋ ሲያደርጋት ተከፈተች ። አይኑ ግን ከማያምነው ነገር ላይ አረፈ ። ሚስቱ ሁለት ጎረምሶች መሀል ተኝታለች ። በንዴት ጦፎ ትልቅ ድንጋይ አንስቶ ወደ ውስጥ ሊገባ ሲል 3ተኛው ምክር ትዝ አለው ። "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" የሚለው ። ከቤቱ ውጭ በተጋደመው ዛፍ ላይ ቁጭ ብሎ አደረ ። ሚስት በጠዋት ተነስታ ደፋ ቀና ስትል ድንገት ባሏን ስታየው እልልታዋን አቀለጠችው ዘላ ተጠመጠመችበት ።

ከእንቅልፉ የነቃው ባል በመደናገጥ ሳለ እጆቹን ይዛ ወደ ቤት ገብታ ሁለቱን ጎሮምሶች አሰተዋወቀችው "ይህ የመጀመርያ ልጅህ ይህ ደግሞ ሁለተኛው" ብላ እንግዲህ የመጨረሻው ምክር የልጆቹን ነፍስ ከማጥፋት እረዳው ማለት ነው ። ሰውዬው ሶስቱ የሽማግሌው አባት ምክሮች በደስታ ከቤተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል አደረጉት ።

ስለዚህ ወዳጄ ሆይ አንተም በህይወት ስትኖር ፦
1. አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ
2. በማያገባህ አትግባ
3. ክፉ ለማድረግ አትቸኩል

ፌስቡክን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም ፡፡ ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ፡፡ በምድር ላይ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና ፡፡

ስለዚህ አንተም ይህ አሁን ያነበብከው መጣጥፍ ትምህርት ሰጪ ሆኖ ካገኘሀው የእርስዎ ዘመዶችህ እንዲያነቡትና ትምህርት እንዲወስዱ ዘንድ ሼር ያድርጉላቸው ።

አዳዲስና ትምህርት ሰጪ የሆኑ ፅሁፎች በየቀኑ እንዲደርሳችሁ ሼር፣፣ላይክ
ከfb የተወሰደችችችችችችች
190 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:42:26 .የታፈነ እውነት...
ከቃል አፋ ተፋትቶ፣በዝምታ ምርኳዝ፣
ለነግህ ተቋጥሮ፣በስሌት የሚጓዝ፣
በአንደበት ተቀብሮ፣ደጃዝማች የራቀው፣
በደሳሳ ጎጆ፣
በነተበ ገላ፣
ህያው ሁኖ ሊኖር፣ከታይታ መንፍቆ፣
ክብር ላለማጉደፍ፣ከጢሻ ያልወጣ እራሱን ደብቆ፣
አለ ድንቅ እውነት፣
በበሳል አይምሮ፣ተንጋሎ ያደረ፣
ከሽንገላ ጩኸት፣
በአርምሞ ፀበል፣አለሙን ያሰረ፣
ለእርግማን ሲጠሩት፣ጎልቶ ያልከበረ፣
ከነ ቡትት ጓዙ፣ከውሸት ተጣልቶ ጮራን የሚናፍቅ፣
አለም ስትጨልም፦
ይወጣል በክብር፣
ከነ አስፈሪ ግርማው፣
አድማሱን በሞላ ከውሸት ሊያስለቅቅ።
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764
248 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:17:42 እስኪ ግጥሜ የናፈቀው
ዝምታዬ የናፈቀው
ከሁለቱም ያልሆነ
231 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:29:36 እንቆቅልሽ፦
ምናውቅልህ እንዳትይኝ ስለ ፍቅር መንገብገቤን፣
በማጀትሽ ፀ'ላይ መንፈስ እኔነቴን መነጠቄን፣
እንቆቅልሽ፦
ምናውቅልህ እንዳትይኝ በጎ ሀሳብ ተቀብሮ፣
ስብናን መናፈቅ ትርፉ ድካም እንጂ ም'ን ሊገኝ ዘንድሮ፣
እንቆቅልሽ፦
ምናውቅልህ እንዳትይኝ ጊዜ በዘመኑ አ'ግጦ ሲወረዎር፣
ሰው በሰው ሲበላ ሲቃን ስናነባ ፍትሃችን ስትቀበር፣
እንቆቅልሽ፦
ምናውቅልህ እንዳትይኝ ፍቅር በዲናር ስትረገጥ፣
በአለም ፍኖት ተመዝና ገነታዊ መለኮቷን ስትለውጥ፣
እንቆቅልሽ ያልኩሽን፣
ምናውቅልህ እንዳትይኝ፣
እውነትስ ከየት አውቀሽ፣
እኔስ ብሆን ምን አውቄ፣
መጥፍ እድል እንዳይደል ሰበብ የሚያመጣ፣
ወንጀል እንዳይደለ በህግ የሚያስገጣ፣
ሀ'ጢያታችን ተሽሞንሙኖ በእርቃን ጀንበር ሳይሞሸር፣
ሀገርን ታህል ባ'ዕት ሳትከፈል በየጢሻው በክልል ዘር፣
የእኔስ እንቆቅልሽ መልሱ ምንአውቅልህም አልነበር፣
ሀገሬ አንቺ ነበርሽ በፍቅርሽ ሰዳፍ የጨለጥሽኝ፣
በኤዶም ገነት ያለ ከልካይ ጥሩ ሽቶ የረጨሽኝ፣
ከጉያሽ ስር ሰፊ ገዳም ማንነቴን የጋረድሽኝ፣
ግና እጣፈንታችን፦
አንችም እንደ ሀገሬ ፍቅርን ገድለሽ ቀብረሽው፣
የአፅሜን ጉዝጓዝ ተንተርሰሽ ለንቦጭሽን አሳመርሽው፣
እወቂና የጭንቀቴን ሸማ ከነክብሩ ደርቢልኝ፣
እውነት መርጠሽ በትንሳኤሽ ጥያቄየን መልሽልኝ፣
በእንቆቅልሽ እንዳልከስም ምን አውቅልህ አትበይኝ።
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764
186 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 06:17:51 እንዲያው እንደምን ነሽ

ዝም ብለን ዝም ያልነው
ለካስ ለነገር ነው
የሚል ፍልስፍና ባሰጠማት ሀገር
ድምፅ አይቆጠርም ካልጮኹ በስተቀር
እውነት ስልሽ ውዴ...
የጠመንጃ አረር የሚለፈልፍን አንደበት ካልዘጋ
በካድሬወች መንደር ጨለማም አይነጋ
እና ደግሞ ሌላው...
ብዙ ጭንጋፍ ካድሬ
አጀብ አስከትለው በገደሏት ሀገር
ሀገሬ አልሞተችም በሚል አንድ ዜማ ይዋላል ሲጨፈር
.......................................

ግን አንቺ እንዴት ነሽ...
እንዴት ነሽ በብዙ እንዴት ነሽ በአያሌው
በዘመናት ክፍተት አይኖችሽን ሳላይ ብዙ ስለቆየው
እንዴት ነሽ? እላለሁ

(አማኑኤል ደርበው/አማን ዘ:ታቦር)
194 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 03:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 13:55:49 አውነትን ልጨብጥ
ከውሸት ልቀርን
ወጣሁ ከራማየ፣ወደ እልፍኝ ገዳሜ፣
አዘቅቱን ጨልፌ፣ውቅያኖስ ፈልሜ፣
ደግሞ ወጣሁ
ከእልፍኝ ገዳሜ
ወጣሁ ወደ አድማሱ፣ካገር ጫፍ ጠረፉ፣
ዳመናን ዘርግቼ፣ውሸታም ኮከቦች ፍፁም እንዲጠፉ፣
አሁንም ወጣሁ
ካገር ጫፍ ጠረፉ
ህዋውን መንፍቄ ሸሸው፣
እውነትን ፍለጋ ፈጋው፣
ግን የት ነው እውነት?፣
ሳሰላስል ለዘመናት፣ልዳኝ ስለውሸት፣
ጉራንጉር ሸለቆውን፣ስመረምር ስመፀውት፣
መልስ አገኜው ከኔው ማህፀን ከኔው አንደበት፣
የት እንዳለ የናፈኩት፣ሙሉው እውነት፣
በአንደበቴ ተፀንሶ፣በእስትንፋሴ የሚወገር፣
በንግሬ የሚረገጥ፣በቃላቴ የሚታሰር፣
ያ'ነው እውነት፦
በኔው ልብ ውስጥ፣ለውሸት ክብር የሚቀበር።
ተፃፈ ደሱ
267 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:02:14 የሰው ልጅን በኦሾ እይታ
ስለ ሰው ልጅ ብዙ ብዙ
ያለው ኦሾ በዚች ምድር አምሳያውን የሚገድል ፍጡር ቢኖር
የሰው ልጅ ብቻ ነው በማለት ያስቀምጥና የትኛውም እንሰሳ
መርዝ አወጋጅቶ ስለት ስሎ ሰዋራ ቦታ ጠብቆ ወይ በገመድ
አንቆ አልያም ጥይት ተኩሶ አምሳያውን የገደለበት አጋጣሚ
በአለም አልታየም ይለናል
ሌላው በትምህርታዊ ነገር ስለ ሰው ልጅ የገለፀልን ነገር
እንዲህ ይላል በአንድ ሆስፒታል ውስጥ የመጀመሪያው ታማሚ
ክፍል የተዘጋ በር ላይ ' በእባብ የተነደፈ ሰው በህክምና ላይ
የሚገኝ ሲሆን ከ30 ደቂቃ ቦኃላ ድኖ ይወጣል ' ይላል
ሁለተኛው በር ላይ " በአንበሳ የተነከሰ ሰው በህክምና ላይ
ይገኛል ከአንድ ሰአት ቦኃላ ድኖ ይወጣል " ይላል ሶስተኛው በር
ላይ ደግሞ በሰው የተነከሰ ሰው በህክምና ላይ ይገኛል ህይወቱ
ስለ መትረፉ እንኳን እርግጠኞች አይደለንም " በማለት የሰው
ልጅን እርኩሳዊ ባህሪ ሊያስረዳን ሞክሯል ቅዱስ ሆናችሁ
ተወልዳችሁ ሰይጣን ሆናችሁ ትሞታላችሁ የሚለን እሾ
እርኩስም ቅዱስም የመሆን ምርጫው እኛው ጋር እንዳለ
አስረግጦ ያሳስበናል
የትኛውም እንሰሳ የተራክቦ ስሜቱን የሚወጣው የሴቷን ሽንት
አሽትቶና እርጉዝ አለመሆኗን አረጋግጦ ሲሆን ይህንንም
ለማድረግ ወቅትና የሴቷን ፈቃደኝነት ተከትሎ ነው የሰው ልጅ
ግን ስግብግብ በመሆኑ ያለ ሴቷ ፍቃድና አስገድዶ ደፋሪ ሆኖ
ከእንሰሳ በታች የዘቀጠ የስብዕና ኖሮት አለማፈሩ አስገራሚ
ፍጡር ያደርገዋል ።ኦሽ/Osho
ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764
362 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 21:01:23 ደግሞ እሙኝ አሏችሁ በፖለቲካ
ዝም ከምል በሚል፦
ስለ ዘመኑ እውነት ስለ ሰው እውነታ፣
ግጥም ልፅፍ ወሰንኩ በቀለም ጠብታ፣
ጀመረኩ ተዘጋጀሁ
አግድሙን ለሚረግጥ ወከባው ለነዳው፣
ማስመሰልን አምኖ እሱነቱን ላጣው፣
ከህሊናው መንፍቆ ለሰፊ ሆዱ ለሚኖረው፣
ለዘመኑ ትውለድ
ሰውነት ለመግጠም
ሆ'ሂያት መፈለግን ቆም ብየ ሳስበው፣
ለካስ ጅላንፎ ነኝ፣
ለካስ ትልቅ ጅል ነኝ፣
ለካስ ጅላጅል ነኝ፣
በእስራቴ ገመድ ጅራፌን የሰራው፣
ሰው ነህ በምለው ፍጡር እኔነቴን ያጣው፣
በዘር ተቀልሜ ብኩርናየን ክጄ ምስሬን የበላው፣
አዎይ የኔ ነገር፦
ሰው ፍለጋ ኳተንኩ ሰው በሌለው ዘመን፣
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764
357 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, edited  18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 19:04:17 የዕለቱ ምርጥ..!

ስለ ገንዘብ - በድሃ ፊት አትናገር!
ስለ ጤንነትህ - ህመምተኛ ፊት አታውራ!
ስለ ጥንካሬህ - ደካሞች ፊት አትናገር!
ስለ ደስታህ - በተከፋ ሰው ፊር አታውራ!
ስለ ነጻነትህ - እስረኞች ፊት አትናገር!
ስለ ልጆችህ -መሃን ፊት አታውራ!
ስለ እናት እና አባትህ -ወላጅ አልባ ሰዎች ፊት አትናገር!

..ምክንያቱም ቁስሎቻቸውን ከበፊቱ በበለጠ እንዲቆስል እና እንዲደማ ምክንያት ትሆናለህና። ለምትሰጠው ነገር ሁሉ ትንሽ ፈገግ በል፣ ከልብህም ደስታን ጨምርበት፣ ለማንኛውም ሰው ጆሮ ስጥ፣ ግን ድምጽህን ቀንስ ሁሉንም ውደድ ጥቂቶቹን እመን፣ ማንንም ግን አትበድል። የውሸት ጓደኛ እና ጥላ አንድ ናቸው። ሁለቱም የሚቆዩት ጸሃይ እስክትጠልቅ ድረስ ብቻ ነው። መልካም ሰው ከሰው ልጅ የመንፈስ ምግብ ነው የማንም ሰው ህይወት ስህተት ወይም ትክክል መሆኑ የሚታወቀው ተፈትኖ ካለፈ ወይም ከወደቀ ብቻ ነው።ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764
384 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ