2023-06-11 06:46:04
የድብቁና ተአምረኛው አእምሮህ 10 ምስጢራት
ለአነቃቂ መልዕክቶች Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
ድብቁ አእምሮህ ድብቁ ኃይልህ እና
ተአምረኛው አእምሮህ ከተሰኙ ሁለት ድንቅ መጽሐፎች የተወሰዱ 10 ምክሮች
#1 የሕይወት ፕላሲቦህ ምንድነው?
ሀኪሞች ለታካሚዎቻቸው የሚሰጡት የውሸት መድኃኒት ፕላሲቦ ይባላል፡፡ ሰዎች ከካንሰር ተፈውሰዋል፤ ከሞት ወደ ሕይወት መጥተዋል፤ ምንም ማድረግ የማይችለውንና የውሸት የሆነውን መድኃኒት እውነተኛና ገዳይ ነው ብለው ራሳቸውን ለማጥፊያነት ተጠቅመውበት ሞተዋል!!!
የዳኑትም፣ የሞቱትም ስላመኑ እንጂ መድኃኒቱ የውሸት ነው፤ የውሸት!!
ለመሆኑ ያንተ የሕይወት ፕላሲቦ ምንድነው?
#2 ፈልገህም ይሁን ሳትፈልገው የእምነቶችህ ተጠቂ ነህ!
“ደህና ጫማ እንኳ መግዛት የማልችል ሰው እንዴት ነው ትልቅ ሬስቶራንት ለመክፈት የማስበው?” ትላለህ። ሆኖም የማይመስል ቢሆን እንኳ የምታምንበትን የመምረጥ መብት አለህ።
አንተ የዕምነቶችህ ተጠቂ ነህና እምነትህን መፈተሽ አለብህ፡፡ ለመሆኑ ምንድነው እያመንክ ያለኸው?
#3 አወንታዊ ስሜቶችን መፍጠር
ምንም አይነት አወንታዊ ሃሳቦችን መርጠህ ብታስብም፣ ውስጣቸው ስሜት ከሌለ ትርጉም አይኖራቸውም። ሃሳቦችህን በ ‘ቢሆን ኖሮ’ ስር ከቀበርካቸው፣ ጊዜህን በከንቱ እያባከንክ ነው። አንድ ነገርን ስላሰብከው ብቻ ታምነዋለህ ማለት አይደለም
መልካም ሃሳቦችህ መልካም የሆኑ ስሜቶችን ሊፈጥሩልህ ይገባል... ለመሆኑ ስሜቶቹ የሚሰሙህ ከልብ ነው?
#4 ወደ ድብቁ አእምሮ የመግቢያ ቁልፍ
አእምሯችን ልክ እንደ ወንዝ ነው - የሃሳብ እንቅስቃሴዎች በበዙበት ቁጥር በደንብ ይደፈርሳል - ቻቻታም ይበዛበታል። በማስተዋልም ውስጥ ሁነን ማሰብ ያቅተናል። የሃሳቦች ፍሰት እና መጠናቸው እየቀነሰ ሲመጣ - የደፈረሰው ይጠራል - ማስተዋላችንም ይጨምራል።
የሃሳቦችን ፍሰት በመቀነስ ወደ ስክነት ሂደት በመግባት እንዴት የአእምሮህን ተአምር መጠቀም ትችላለህ?
#5 ስለወደፊትህ ስታስብ መልካምና አዲስ የሆኑ እድሎችን አስብ
ራስህን መጠየቅ ጀምር - ‘ምንም አይነት ተግዳሮቶች ባይኖሩብኝ የት እደርሳለሁ?’ ወዲያውም አእምሮህ ትኩረቱን ከጭንቀት እና ከፍርሃት ያላቅቅና ስለ ነገ በነጻነት ማሰብ ይጀምራል።
ባትወድቅ ምን ታደርጋለህ? እንደሚሳካልህ እርግጠኛ ብትሆን ምን ትሞክራለህ?
#6 ስለ ገንዘብ ምንድነው የምታስበው?
አንድ ሰው በገንዘብ ጉዳይ ለምን ስኬታማ እንደሚሆን እና ሌላው ለምን ተስፋ እንደሚቆርጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?
መልሱ ቀላል ነው - ያላቸው የገንዘብ አስተሳሰብ መለያየት ነው።
ከገንዘብ ጋር ያለህ ግንኙነት አሉታዊ ነው ወይንስ አወንታዊ? ገንዘብህን በምክንያት ወይስ በስሜት ታወጣለህ? ብዙ ገንዘብ እንዳለህ ወይስ ገንዘብ እንዳጠረህ ሆኖ ይሰማሃል?
#7 እራስህን ፈውስ!
ከሞት ሕይወትን ብትፈልግ- ተአምሩ አእምሮህ ዘንድ ይገኛል፡፡
ከውድቀት ስኬትን ብትመርጥ- ተአምረኛው አእምሮህ ይችላል፤
ከአርባ ቀን እድልህ ይልቅ በረከትን ብትሻ- አአምሮህ ተአምር ይሰራል!
የድብቁ አእምሮህን ኃይል በመጠቀም ሰውነትህን እንደ አዲስ መገንባት እና መፈወስ ትችላለህ፡፡ ሰውነትህን የፈጠረ አምላክ መዳኛህንም በውስጥህ ቀብሮታል፡፡
#8 ከምቾት ጉሬ ማምለጥ
የመለወጥን መንገድ እንደ ጀመርክ ... ፍርሃት ይወርሃል፣ ወደ ኋላ ታፈገፍጋለህ። ወደ ምቾት ጎሬህም ትመለሳለህ፤ ለራስህም ‘ይሄ ጥሩ ነው፤ ይሄ ልክ ነው፣ ይሄን ቦታ አውቀዋለሁ፤ እዚህ ምንም አልሆንም” ትለዋለህ። ከፍርሃቶችህ በላይ ሆነህ እንዴት የመለወጥ መንገድህን መቀጠል ትችላለህ?
ከምቾት ጎሬህ አሁኑኑ መውጣት ያለብህ አይመስልህም?
#9 በእምነት ተራራም ይናዳል
“በቅድሚያ ካንተ የሚጠበቀውን ሁሉ አድርግ፤ እናም በራስህ ላይ እምነት ይኑርህ፤ እችላለሁ በል፡፡ ነገ የእኔ ቀን ነው፤ ይህ ከፊት ለፊቴ ያለው ሰው ልክ እንደ እኔ ያለ ሰው ነው፤ ሁለት እግሮች አሉት፤ ሁለት እግሮች አሉኝ፡፡ ለማሸነፍ ይህ ይበቃል፤ አለቀ፡፡ እንደዚህ ነው ከፊትህ ላለው ፍልሚያ መዘጋጀት ያለብህ፡፡” አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ
ለመሆኑ እምነትህ ምን ያህል ነው? ተራራ ይንዳል?
#10 ድብቁ አእምሮህ ተአምራቶችህ ሁሉ የተደበቁበት ቦታ ነው
ብዙ ሰዎች ድብቁ አእምሮህ በውስጥህ እንዳለ ኑክሊየር ቦንብ ነው ሲሉ ይገልጹታል፡፡ ቦንቡን እንዴት እንደምትጠቀምበት መወሰን ያንተ ፈንታ ነው፤ ተራራህን ልታፈልስበት ወይም ሕይወትህን ልታበላሽበት ምርጫው ያንተ ነው፡፡
የሁሉ ፈጠራ ምንጭ፣ የሁሉ በረከት ምንጭ፣ የፈጣሪ አምሳያ የሆነው ድብቁ አእምሮህ ሕይወትህን ሊቀይር አንድ ጥያቄ እየጠየቀህ ነው፡-
ለመሆኑ እንዴት እንደምትጠቀምብኝ ታውቃለህ?
እነዚህ ድንቅ በአእምሮ ላይ የተጻፉ መጽሐፍት አትጠራጠር ሕይወትህን በትክክል ይቀይሩታል
ድብቁ አእምሮህ ድብቁ ኃይልህ እና
ተአምረኛው አእምሮህ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ፡፡
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)
Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
4.1K viewsedited 03:46