2023-06-04 07:02:42
#ድንቅ_ምክሮች
1. ጉራ አያዋጣም ዝቅ ብላችሁ ኑሩ። ስለሪኮርዶቼ ሌሎች ሰዎች እንዲያወሩ እንጂ እኔ ብዙም ላወራ አልፈልግም።
2. ሪከርድ ከሰበርኩ በኋላ አስሬ አሱን አላስብም። ከአንድ ቀን በኋላ ሌላ ሪከርድ ስለመስበር ነው ማስበው።
3. ትችላላችሁ! ለራሳችሁ የምትነግሩት ነገር ቢኖር ከኃይሌ የተሻለ እድል አለኝ የሚል ነገር ነው።
4. ነገ አንድ ነገር አደርጋለሁ ካላችሁ አድርጉ።
5. በአትሌቲክስ ሌላውን ለማሸነፍ ከመሮጣችሁ በፊት እራሳችሁን አሸንፉ ይባላል። አንድ ሯጭ የፈረስ ጉልበት ያለው እንኳን ቢሆን እራሱን ማሸነፍ ካልቻለ ሌላውን ማሸነፍ አይችልም። Win yourself first. ስለዚህ እንቅልፍ፣ ምግብ፣ መዝናናት፣ ማህበራዊ ህይወት፣ ኬኩ፣ መጠጡ ሌላ ሌላውም ነገር ላይ ልትቆጠቡ ይገባል።
6. እራስህን እመነው። የግድ በሌሎች መወደድ አይጠበቅብህም። ለራስህም ታመን። እራስን መሸወድ አይቻልም።
7. ለሙያህ የሚያስፈልገውን ስነስርአት (Discipline) አክብር። እንደ ሯጭ ስልጠና መጨረስ፣ ዝናብ እና ዶፍ መታገስ፣ በቂ እረፍት ማድረግ እና በአግባቡ መመገብ ልታከብራቸው የሚገቡ ስነ ስርአቶች ናቸው። No Discipline No Result። በሁሉም፡ዘርፍ ይሄው ነው።
8. ጠንክሮ መስራት ግድ ነው። ለምንድነው ከ 8 ሰአት በላይ የማትሰሩት። ህይወት የሰጠሃትን ያህል ነው መልሳ የምትሰጥህ። 24 ሰአት ለመኖር ለምን 8 ሰአት ብቻ ትሰራላችሁ? ኢትይጵያዊያን ሌላ ሃገር ሲሄዱ 16 ሰአት ይሰራሉ። ለምን ሃገራችን ላይ አንሰራም?
9. ቁጥር አንድ ጥሬ ሃብት ቤንዚን፣ ጋዝ፣ ወይም ሌላ ሳይሆን ጊዜ ነው። ጊዜን በአግባቡ እንጠቀም። ወደ ኋላ ያለው ህጻንነት ፊታችሁ ያለው እርጅና ነው። ዛሬ ያለውን ዛሬ ተጠቀሙበት።
10. ፊንላንድ ላፕላንድ (ሰሜን ዋልታ) ውጪ ብታድር የሚገኘው ሬሳህ ነው። እኛ ሃገር አየሩ ተስማሚ ነው ግን ይሄ ሊያዘናጋን አይገባም።
11. መጽሐፍ ስራን የማይወድ አይብላ ይላል። ስራን የማይሰራ ሳይሆን የማይወድ ነው የሚለው። ስራን ውደዱ።
12. በፍጹም ሌሎች ላይ አታሳብቡ። ሁሉም ነገር እኛ ከተፈጠርን በኋላ የተሰጠን ነው። ዳቦ እላይ ወጥቶ ቀረ። ቢራ እላይ ወጥቶ ቀረ። ግን እራሳችሁን ማሸነፍ ትችላላችሁ።
13. ብዙ ቢሊየኖርች ጋር የመገናኘት እድል ነበረኝ። ከአዲዳስ ባለቤት ከሌሎችም ጋር። ብዙ ፎቶ አብሬያቸው አልተነሳሁም ግን ሁሉንም አጠናቸው ነበር። የተረዳሁት ሁሉም እንደኛ በቱታ እና በስኒከር የምታገኟቸው ቀላል ሰዎች መሆናቸውን ነው።
14. እኔ የድርጅት ሰራተኞቼን ባለቤት ነው ማድረጋቸው። አሰሪዎች ሰራተኞቻችሁን ባለቤት አድርጉ። የእኔነት እንዲሰማቸው አድርጉ።
15. ድርጅት የአንተ አይደለም። የእኔ የሚባል ድርጅት የለም። ሁላችንም ጥለነው እንሄዳለን። ድርጅቱ ባለቤት ካለው ምናልባት ሃገሪቱ ነች።
16. ስራን ለደሞዝ፤ ቢዝነስንም ለገንዘቡ የምንሰራ ከሆነ ሃብታም አንሆንም። እኔ ለገንዘብ የሮጥኩባቸውን ሩጫዎች ተሸንፌያለሁ። ገንዘብ ዋናው ነገሬ ሲሆን እሸነፋለሁ። ስራውን ስታስቀድሙ ገንዘቡ ይመጣል። ስራን አፍቅሩ።
17. የመጀመሪያ ሆቴሌን ስገነበ እቃ ላይ እንጂ ሰው ላይ ወጪ ስላላወጣሁ ብዙ ብር ከስሬያለሁ። ሰው ላይ Invest አድርጉ።
18. ምክር ሲነገራችሁ መካሪውን አክብራችሁ በደንብ ስሙ። ነገር ግን ምክሩን ከራሳችሁ ህልም አንጻር ገምግማችሁ የማትቀበሉትን አትቀበሉ። የአባቴን ምክር ሙሉ በሙሉ ብቀበል ኖሮ ዛሬ የደረስኩበት አልደርስም።
19. ቋጣሪ ስባል ደስ ይለኛል። ትክክለኛ ነገር እየሰራሁ እንደሆነ አረጋግጣለሁ። ከእኔ ገንዘብ ለማውጣት ምክንያታዊ መሆን አለበት።
20. በልጅነቴ የሰፈር ድልድይ እጠግን ነበር። ያንን ድልድይ የመስራት ህልም ነበረኝ። የመጀመሪያ ሩጫ እንዳሸንፍኩም እንደምንም ድልድይ ሰርቼ ነበር። ከ 30 አመት በኋላም ሰዎች ዛሬ ደውለው ያመሰግኑኛል። ለመርዳት ከድሮም ፍላጎት ነበርኝ።
21. ብዙ ድሎቼ ቢወሩም እጅግ ብዙ ሽንፈቶች አስተናግጃለሁ። ሩጫ፣ ማናጀሬ ሁሉ ያስጠሉኝ ጊዜያት ነበር። ግን ቀጥዬ ብዙ ድሎችን ተጎናጽፌያለሁ። ድል ከሽንፈት በኋላ ነው ያለው።
(Solomon WG እንደከተበው)
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)
Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
5.7K views04:02