Get Mystery Box with random crypto!

Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

የቴሌግራም ቻናል አርማ teklu_tilahun — Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን T
የቴሌግራም ቻናል አርማ teklu_tilahun — Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን
የሰርጥ አድራሻ: @teklu_tilahun
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.25K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 75

2022-07-08 12:29:57
#ሉባር እና ሰርድዮን የተሰኙ ሁለት መጽሀፍት በገበያ ላይ ማዋላችንን በመግለጽ ሀገራችንን ከዓለም ልዩ የሚያደርጋትን የገለጸ ይሸለማል በሚል ማወዳደራችን ይታወቃል፡፡ በውድድሩ ሶስተኛ የወጣው ኢትዮጵያን ልዩ የሚያደርጋትን እንደዚህ ገልጿታል፡፡

#እናት_ሀገር_ኢትዮጵያ

፩የራሷ የሆነ ፊደል፣ ቋንቋ ያላት
፪የሰው ዘር መገኛ በመሆኗ
፫የ13 ወር ፀጋ ያለባት ብቸኛ ሀገር በመሆኗ
፬Active የሆነ volcano ያለባት ሀገር በመሆኗ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ትለያለች

ፍቅር ይበልጣል
98 ላይክ ያገኘ

#ሉባር 3ተኛ ዕትም
#ሰርድዮን አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

*
ቤተሰብ ይሁኑ

Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/

Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
4.7K views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 06:51:03
#ይህ_አንቺ_የምታወሪለት_ፍቅር_ሀገሩ_የት_ነው?

ጠዋት ቢሮ ውስጥ እንደተቀመጥን አንዲት የስራ ባልደረባዬ ፊቴን አተኩራ ተመለከተችው፡፡ ከዚያም እየተገረመች፡-

“ምንድን ነው የሆንሽው?” አለችኝ፡፡

“ምነው?” ጠየቅኳት፡፡

“ፊትሽ አንድ አይነት አይደለም፡፡”

“አንድ አይነት አይደለም ማለት ምን ማለት ነው?”

“ከሆነ ከውስጥ ገፅሽ የሚወጣ ብርሀን አለ፡፡ ፍቅር ይዞሻል?”

“ፍቅር?!”

“ፍቅር ምን ማለት እንደሆነ ታውቂያለሽ?”

“አላውቅም” በሀዘኔታ መለሰችልኝ።

“ምስኪን” አልኳት።

“ግራ የገባሽ ምስኪን ሴትማ አንቺ ነሽ፡፡ ለመሆኑ ፍቅር አለ ብለሽ ታምኛለሽ?” አለችኝ።

“ፍቅር እኔን አዲስ ሰው፣ ልዩ ሰው አድርጎ እንደገና ፈጥሮኛል፡፡ ፍቅር አለምን ውብ አድርጎ ይሰራል” አልኳት።

“ይህ አንቺ የምታወሪለት ፍቅር ሀገሩ የት ነው?” አለችኝ።

#ማራ መጽሐፍ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ
በገበያ ላይ ውሏል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ https://www.facebook.com/booklandbook/

https://t.me/teklu_tilahun
4.6K views03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 19:56:48
#መንግስት_ይውረድ!

አንዳንዴ ደግሞ ሁሉም ተማሪ የትምህርት ቤት ቅጥር ግቢውን ለቅቆ በመውጣት መንግስትን በመቃወም በሚደረገው አመፅ ወደ ጎዳና ላይ ሲወጣ አብሬ ስወጣ አስበዋለሁ፤

“መንግስት ይውረድ!”

“መንግስት ይውረድ!”

“መንግስት ይውረድ!”

ከሚሉ የልጃገረዶች ድምፅና ሰልፍ ፊት እራሴን አገኘዋለሁ፡፡ ወደ ትምህርት ቤት ግቢ ስመለስ ድምፄ ተዘግቶ፣ ፀጉሬ ተበታትኖ፣ ልብሴ ብዙ ቦታ ተቀዳድዶ አየዋለሁ፡፡

መንግስት ግን መቼ ነው የሚወርደው?

#ማራ መጽሐፍ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ።

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
facebook
https://www.facebook.com/booklandbook/
Telegram
https://t.me/teklu_tilahun
4.6K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:40:42
#ማራ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

#ሙሉ_በሙሉ_እውነተኛ_ታሪክ

የሞት ፍርድ የተፈረደባት አንዲት እንስት ይቅርታ ጠይቂና የሞት ፍርዱ ይነሳልሽ ብትባል እንቢ አሻፈረኝ ትላለች፡፡

ምሕረትን እንዳትቀበል ያደረጋት፣ ሕይወቷን ያስመረረውና የሞት ጽዋውን ያሰኛት ምክንያት ምን ይሆን?

የሴተኛ አዳሪዎች ንግስት፣ የልኡላን ቅምጥ የሆነችው እንስት በሴቶች የሚደረጉ አስገራሚ አብዮቶች ምልክት ተብላ ተሞግሳለች፡፡ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ የሆነው #ማራ መጽሐፍ እነሆ በገበያ ላይ ውሏል፡፡


“ከእስር ቤት የምትወጪበት አንድ ተስፋ ተገኝቷል፡፡ ለፕሬዚዳንቱ የይቅርታ መልዕክት ፅፈሽ ይቅርታ እንዲደረግልሽና ሁለተኛ ወንጀል ላለመስራት ቃል የምትገቢ ከሆነ ከእስር ቤት እንደምትወጪ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡”

“ይቅርታ እኔ ነፃ መሆን አልፈልግም፡፡ ለሰራሁት ወንጀል ደግሞ ይቅርታ መጠየቅ አልፈልግም፡፡ በዚያ ላይ እናንተ ወንጀል ብላችሁ የምትጠሩት ወንጀል አይደለም” አልኩት፡፡ “ከዚህ ወጥቼ አንተ እንደምትለው እንደገና መኖር ብጀምር መግደሌን አላቆምም፡፡ ስለዚህ የይቅርታ ደብዳቤ ለፕሬዚዳንቱ መላክ አያስፈልግም፡፡ እኔ በመኖርም፣ በመሞት… በሁለቱም አሸናፊ ነኝ፡፡”

“አንቺ ወንጀለኛ ነሽ!”

“አይደለሁም! እናንተ ሁላችሁም ወንጀለኞች ናችሁ፡፡ አባቶች፣ አጎቶች፣ ባሎች፣ የሴተኛ አዳሪ ደንበኞች፣ ሁላችሁም ወንዶች! አባቴ፣ አጎቴ፣ ባሌ… ሁላችሁም ሴተኛ አዳሪ ሆኜ እንዳድግ አስተምራችሁኝ አልፋችኋልና ወንጀለኞች ናችሁ!!!”
#ከመጽሐፉ_የተወሰደ

#ማራ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡
*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
4.7K views09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 06:41:19
#የህይወት_ወርቃማ_ህጎች_2

#ያለ_ፍርሃት_በአዎንታዊነት_ተንቀሳቀስ
የሆነ ነገር ውስጥ እንደገባህ በተሰማህ ጊዜ ሁሉ… ተረጋጋ፣ አስብ፣ እቅድ አውጣና ያለ ፍርሃት በአዎንታዊነት ተንቀሳቀስ። የፍርሃት ወጥመድ ውስጥ መቆየትና አሉታዊ ነገሮችን ማሰብ ብቻ መፍትሄ አይሆንም፨ ስለዚህ, በእያንዳንዱ አሉታዊ ሁኔታ ውስጥ አዎንታዊ ጎን መፈለግ ተማር፨

#በረከቶችህን_ቁጠር_መልካም_አድርግ
በውጤቱ ላይ ሳታተኩር መልካም መስራትህን ቀጥል፤ ሁልጊዜም የዘራነውን የምናጭድ በመሆኑ በተቻለ መጠን መልካም ነገሮችን ስራ፨ በተጨማሪም ያለፈው ጊዜ ታሪክ ነው፣ መጪው ጊዜ ምስጢር ነው፣ ዛሬ ደግሞ ስጦታ ነው። ስለዚህ ዛሬ ላይ ትኩረት አድርግ፨

#ፈገግ_ማለትህን_ቀጥል
አንድ ቀላል ፈገግታ የአንድን ሰው መጥፎ ቀን ወደ ጥሩ ቀን ሊለውጠው ይችላል። ስለዚህ፣ ፈገግ ማለትህን ቀጥል ይህም የአንተን ግንዛቤ ይለውጣል፨

#ሲያስፈልግ_ብቻ_ይቅርታ_ጠይቅ
አሁን አሁን <ይቅርታ> እና <አዝናለሁ> የሚሉት ቃላት በሚጠቀሙባቸው በአብዛኛው ሰዎች ከቃላት ባለፈ ብዙም ትርጉም የላቸውም፨ ይቅርታ መጠየቅ መልካም ቢሆንም፥ ከመጠን በላይ ይቅርታ መጠየቅ ግን ሰዎች የሚፈለገውን አክብሮት እንዳይሰጡህ ያደርጋል፨ ስለዚህ ይቅርታ ስትጠይቅ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ብቻ ይሁን።

#ወርቃማ_ሕጎች መጽሐፍ

*
ቤተሰብ ይሁኑ https://www.facebook.com/booklandbook/

https://t.me/teklu_tilahun
4.5K views03:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ