2023-07-01 20:15:12
#10_ራስን_የመምራት_ትምህርቶች
ከ #ራስን_መምራት መጽሐፍ
የዴል ካርኒጌ #ራስን_መምራት መጽሐፍ #2ተኛው ዕትም በገበያ ላይ
#1_ደህና_ነኝ_ደህና_ነህ
ሁሉም ሰው የቻለውን ሁሉ እያደረገ ካለበት ቦታ ጀምር፤ ከዚያ እነሱን ለመደገፍ እና ለማበረታታት መንገዶችን ፈልግ፤ ይህ በሰዎች ላይ ስህተት ከመፈለግ የበለጠ ጠቃሚ ነው።
#2_ትክክለኛ_ሁን
ስለምታምንበት ነገር ትክክለኛ፣ ጥልቅ ስሜት ያለህ፣ ስሜታዊም ሁን። ራዕይህን አካፍል፥ እሴቶችህን ኑር። ግላዊ ሀሳብህ ከሂደቱ የበለጠ አሳታፊ፣ እንዲያውም አነሳሽ ነው።
#3_ፈጥነህ_ወደ_መፍትሄዎች_አትግባ
አስቀድመህ የምታውቃቸውን ነገሮች መሥራትህን ከቀጠልክ እና ሌሎች ሰዎች እንዲሞክሩ የማትፈቅድ ከሆነ፣ ማንም አዲስ ነገር አይማርም። ሌሎች ሰዎች የተለየ ወይም የተሻለ መንገድ ሊያገኙ እንደሚችሉ አስብ፤ ያ ካልሆነ ደግሞ … ስህተቶችም ዋጋ አላቸው።
#4_ብዙ_አድምጥ_ትንሽ_ተናገር
ሰዎች በያዝከው ቦታ ምክንያት አንተ ለምትናገራቸው ነገሮች ትኩረት ይሰጣሉ። የመሪ ተግባር ግን ሌሎች በተለይም አመለካከታቸው ተቀባይነት እንደሌለው አድርገው የሚያስቡ ሰዎች ለሚናገሩት ነገር ትኩረት መስጠት ነው። ሰዎች የሚነግሩህን ነገሮች በተግባር በማዋል ሀሳባቸውን እያዳመጥክ መሆንህን አሳይ፤ ለእነሱ ምስጋናውን በመስጠትም አመኔታቸውን አግኝ።
#5_ወደኋላ_አትመለስ።
የመሪነት ስራህ ሌሎችን እንዲያምኑ እና በጋራ ግብ ላይ እንዲሰሩ ማድረግ እንጂ ሃሳብን ወይም ታማኝነትን መከፋፈል ስላልሆነ፥ አንድ ጊዜ በቦርዱ ወይም በአመራር ቡድን ውሳኔ ከተሰጠ፣ በውይይት ወቅት ውሳኔውን ብትቃወምም ራስህን ችለህ መሆን አለበት።
#6_በክፍሉ_ውስጥ_ያለኸው_በጣም_ብልሁ_ሰው_አትሁን
መሪ መሆን ማለት ከማንም በላይ ማወቅ ማለት አይደለም። ስለዚህ ሌሎችንም እንደ ባለሙያ እውቅና መስጠት፣ ማበረታታትና ማስተዋወቅ ይገባል። በራሳቸው አገባብ ፈጣሪ እንዲሆኑ እና ጥሩ ስራ እንዲሰሩ አመኔታ እና የራስ ገዝነት ስጣቸው። ይህ በጣም ጥሩ የሆነ ስራ ለጋራ ዓላማ አስተዋፅዖ ማድረግ እንዲችል በቀላሉ መመሪያውን ትሰጣለህ።
#7_የዓላማ_ስሜት
ቡድንህ ምን እንደሚሰራ እና እንዴት እንደሚሰራ ያውቃል፤ ነገር ግን ለምን እንደሚያደርገው እና ወዴት እያመራ እንደሆነ ጠንከር ያለ ስሜት በማጋራት ትልቅ ለውጥ ማምጣት ትችላለህ። ለቡድኑ አባላትም የቡድኑን ዓላማ በተመለከተ ሰፋ ያለ ግንዛቤ እንዲያዳብሩ እርዳቸው፤ የእነሱ ሚና ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ለመሆኑ እምነት ይኑርህ።
#8_ትክክል_መሆን_ብቻውን_በቂ_አይደለም
ሌሎች እንዲቀበሉት ማሳመን እና ከዚያ ደግሞ ሀሳብህን እውን ለማድረግ እንዲከተሉህ ማድረግ ካልቻልክ ታላቅ ሀሳብ ያለህ መሆኑ ውጤት የለውም። ይህንን ለማድረግ ከሁሉ የተሻለው መንገድ ደግሞ ሃሳቡን የእነርሱ እንዲሆን ማድረግ ነው።
#9_በጥቂት_ነገሮች_ላይ_አተኩር
ትኩረትህን በጣም አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ እና ለውጥ ማምጣት በምትችልበት ቦታ ላይ አድርግ። ምናልባት በርካታ የተለያዩ ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮችና ጥያቄዎች እንዲሁም አንተ ምላሽ ልትሰጥ የምትችልባቸው እጅግ ብዙ መንገዶች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ውጤት የሚሰጡት ግን በጥንቃቄ የተመረጡት ጥቂቶቹ ናቸው።
#10_ውጣ_እና_ስራዎች_ስራ
ዝም ብለህ በመቀመጥ ስራው በትክክል ስለ ምን እንደሆነ ያለውን ስሜት ማቆየት ከባድ ነው። ስለዚህ ወጣ ብለህ ስራዎች ስራ።
#ራስን_መምራት_መጽሐፍ በጠብታ ማር ደራሲ ዴል ካርኒጌ
#2ተኛው_ዕትም በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)
Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
5.0K views17:15