2023-05-08 06:35:02
#10_በጥበብ_የመኖር_ጥበቦች
#THE_SUBTLE_ART_OF_NOT_GIVNG_A_F*CK ከተሰኘውና #በጥበብ_መኖር በሚል ከተተረጎመው መጽሐፍ የተወሰዱ አስር በጥበብ የመኖር ጥበቦች፡-
#1_ጦርነቶችህን_በጥበብ_ምረጥ
ጉልበትህን አስፈላጊ በሆነበት ቦታ እንዲውል አድርግ፡፡ "ብስለት የሚከሰተው አንድ ሰው በእውነት ሊጨነቅበት ዋጋ ላለው ነገር ብቻ መጨነቅ እንዳለበት ሲማር ነው።"
#2_ውድቀት_የህይወት_አካል_ነው
ውድቀት የምትማርና የምታድግበት ነው። "አንድ ህፃን ልጅ በእግሮቹ ለመራመድ በሚሞክርበት ጊዜ፥ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ጊዜያት እየወደቀ ራሱን ይጎዳል። ነገር ግን ያ ልጅ በምንም አይነት ሁኔታ ቆም ብሎ ‘በቃ መራመድ ለእኔ የሚሆን ነገር አይደለም፤ እዚህ ነገር ላይ ጥሩ አይደለሁም ማለት ነው በማለት አያስብም''
#3_ሕይወት_አንተ_እንደምታስበው_ላይሆን_ይችላል
ሕይወት ሁልጊዜ አንተ በምትፈልገው መንገድ እንዲሄድ የታሰበ አይደለም፤ ያም ቢሆን ግን ምንም አይደል።
"ብዙ ስትጨነቅ፣ እንዲሁም ስለ ሁሉም ነገር መጨነቅ በምትመርጥበት ጊዜ፣ በማንኛውም ጊዜ ምቾት እና ደስታ እንዲሰማህ መብት እንዳለህ ይሰማሀል፤ ህይወት አንተን የሚያስጨንቅህም ያን ጊዜ ነው፡፡"
#4_ከመጠን_በላይ_መስራት_ምንም_ነገር_ካለመስራት_ጋር_ተመሳሳይ_ነው
"አንተ የምትገለጸው መተው በምትመርጠው ነገር ነው። ምንም ነገር የማትተው ከሆነ ማንነት የለህም ማለት ነው።"
#5_ትልቁ_ጠላትህ_የመውደቅ_ፍርሃትህ_ነው
"በእውነት ስኬታማ መሆን የምትችለው ልትወድቅበት ፈቃደኛ በሆንከው ነገር ላይ ነው። ለመውደቅ ፈቃደኛ ካልሆንክ ስኬታማ ለመሆንም ፈቃደኛ አይደለህም ማለት ነው"
#6_ማንነትህን_አትወቅ
ማንነትህ በየጊዜው ስለሚለዋወጥ በፍጹም "ራስህን ማግኘት" አትችልም፤ ያ ደግሞ ጥሩ ነገር ነው።
"ራስህን እንዳታገኝ፥ በፍጹም ማንነትህን አትወቅ እልሀለሁ። ምክንያቱም አንተን እንድትጥርና እንድታውቅ የሚያደርግህ እንዲሁም በፍርድህ ትሁት እንድትሆን እና በሌሎች ውስጥ ያለውን ልዩነት እንድትቀበል የሚያስገደድህ ያ ነው።
#7_ሁሉም_ችግር_የግድ_አሉታዊ_ነገር_መሆን_የለበትም
"በጥሩ ችግሮች የተሞላ ሕይወት እንጂ ችግር የሌለበትን ህይወት ተስፋ አታድርግ። ምክንያቱም እንደዚያ አይነት ነገር የለም።"
#8_በአንድ_ነገር_ጥሩ_ከሆንክ_ቀጥሎ_በሌላው_ላይ_ታላቅ_ለመሆን_ግብ_አድርግ
"በአንድ ነገር ጥሩ የሆኑ ሰዎች፥ ገና የሚቀራቸው መሆኑን ስለሚረዱ እንዲሁም መካከለኛ፥ አማካይ መሆናቸውን ስለሚገነዘቡ በጣም ጥሩ ይሆናሉ። በጣምም የተሻሉ ሊሆኑ ይችላሉ።
#9_ቆም_ብሎ_አንድ_ጊዜ_ባለህ_ነገር_መርካት_አስፈላጊ_ነው
"ሁልጊዜ የተሻለ ስሜት እንዲሰማህ በተከታተልክ ቁጥር እርካታህ እየቀነሰ ይሄዳል፣ ምክንያቱም የሆነን ነገር መከታተል በመጀመሪያ ደረጃ ያ ነገር የጎደለህ የመሆኑን እውነታ የሚያጠናክር ነው።"
#10_አስቸጋሪ_ጊዜያት_የህይወት_አስፈላጊ_አካል_ናቸው
" 'ራስን ማሻሻል' የሚለው ነገር በአጭሩ ለተሻሉ እሴቶች ቅድሚያ መስጠት፣ ለመጨነቅ የተሻሉ ነገሮችን መምረጥ ነው። ምክንያቱም የተሻሉ የምትጨነቅባቸው ነገሮች ስትመርጥ የተሻሉ ችግሮች ታገኛለህ። ‘’
"ማንነትህ የሚገለፀው ለመታገል ፈቃደኛ በሆንከው ነገር ነው።"
ይህ ድንቅ መጽሐፍ #በጥበብ_መኖር በሚል ርእስ ለ #5ተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል፡፡
#በጥበብ_መኖር መጽሐፍ
#THE_SUBTLE_ART_OF_NOT_GIVNG_A_F*CK
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)
Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- http://shorturl.at/binrX
3.6K views03:35