Get Mystery Box with random crypto!

Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

የቴሌግራም ቻናል አርማ teklu_tilahun — Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን T
የቴሌግራም ቻናል አርማ teklu_tilahun — Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን
የሰርጥ አድራሻ: @teklu_tilahun
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.25K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-05-20 06:43:19
3.9K views03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 20:09:26
#የሰው_ልጅ_የፈጣሪ_ቅንጣት_አካል_ነው

በመለኮታዊ አባባል በውስጥህ ያለው የመለኮት ብልጭታ አንተ የራስህ ሳይሆን የእግዚአብሔር መሆንህን የሚያስረዳ ነው፡፡

በዘፍጥረት መሰረት የሰው ልጅ የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳያ ነው፡፡ ንቃተ ህሊናም አብሮ ተሰጥቶናል፡፡ በሌላ አባባል የሰው ልጅ የፈጣሪ ቅንጣት አካል ነው፡፡

እኛ ትክክለኛውን የእግዚአብሔር ባህሪይ የያዝን ባለመሆናችን ከትርምስ ውስጥ ስርዓትን ማውጣት እንደምንችል ሁሉ፣ በተመሳሳይ ከሥርዓት ውስጥም ትርምስን ማፍለቅ እንችላለን፡፡

#የሕይወት_ቀመሮች መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- http://shorturl.at/binrX
4.7K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 06:32:32
#ተአምር_ከትንሽ_ይነሳል!

የትኛውም ሰው እንደተወለደ እምነትም ሆነ አመለካከት አይኖረውም። ሁላችንም ከተለያየ ቦታ፣ ኃይማኖት፣ ባህል እንዲሁም ልማድ እንወርሳለን። ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች የምናገኘውን እኛነት እንዴት በራሳችን ድጋሚ ልንቀርጸው እንችላለን? ታሪካችን የሆነው በድግግሞሽ ነው።

ስለዚህ ልምድ ቀጣይነት ያለው ድግግሞሽ ነው። ምናልባት ሂሳብ ላይ ጎበዝ አለመሆን፣ የሰዎችን ስም መዘንጋት፣ አቅጣጫ ለመጠቆም መቸገር ባለፈ ታሪክ ውስጥ ድክመቶቻችን ናቸው።

የትክክለኛው አድራጎት ባለቤት፣ የትክክለኛው ንግግር አዋቂ...ለመሆን ደጋግሞ መሞከር ያስፈልጋል።

የሚፈለገውን ሰው ለመሆን ትናንሽ የሚባሉ ልምዶችን ማዳበር ወሳኝ ይሆናሉ። ምናልባት በአንድ ምሽት ቅጽበት ህይወትን ላይቀይሩ ይችላሉ። ትናንሽ ልምዶች ሲባል አንድ ፑሻፕ መስራት ሰውነትን አይቀይርም፤ ለአንድ ደቂቃ ተመስጦ ማካሄድ ምንም ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ትናንሽ ልምዶችን እያዳበርናቸው ስንሄድ፣ እየደጋገምናቸው ስንመጣ፣ እያሳደግናቸው ስንከሰት የምንፈልገውን ሰው ለመሆን አንቸገርም።

በራስ መተማመን ሲባል እኔ ጸሐፊ እሆናለሁ፣ እኔ እሯጭ እሆናለሁ ብሎ የማውራት አይደለም። ይልቁንም ጸሐፊ ለመሆን ንባብን መደጋገም፣ አሸናፊ ሯጭ ለመሆን ዘወትር ልምምድ ማድረግ ለዛ ግብ ትናንሽ ልምዶችን ማዳበር ይጠይቃል።

#Atomic_Habits_የልማድ_ኃይሎች መጽሐፍ #7ተኛው ዕትም በገበያ ላይ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- http://shorturl.at/binrX
5.4K views03:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 20:16:31
#የጊዜ_ስኮርት_የለውም

ገንዘብህን ለጠየቀህ ሰው ሁሉ አፍሰህ ትሰጣለህ?

ገንዘብ ለጠየቀ ሰው ሁሉ ታፍሶ ካልተሰጠ፣ እና ታዲያ ውዱን ጊዜህን እንዴት ለማንም ትሰጣለህ?

ገንዘብ ከተረፈህ ባንክ ልታስቀምጠው ትችላለህ።

ልታበድረው ወለድም ልታገኝበት ትችላለህ። ገንዘብ ከሌለህ ልትበደር አልያም ሰርተህ ልታገኘው ትችላለህ።

የጊዜ ትርፍ ግን የለውም። ሲተርፍህ ለሰው ልታበድረው ወይም ሲያንስህ ከሰው ልትዋሰው አትችልም።

የጊዜ ስኮርት የለውም!!

ያለህ ጊዜ ተመጥኖና ተሰፍሮ ነው የተሰጠህ።

ስለዚህ ጊዜና ትኩረትህን ለጠየቀህ ሁሉ አትስጥ። ሶሻል ሚዲያ ላይ፣ በፌስቡክ እና በቲክቶክ፣ በቲቪ ሰዎች የሰሩትን በማየት እንዲሁ ጊዜህን በከንቱ አታባክን።

ጊዜህን እራስህን ለመስራት ተጠቀምበት።

ሕይወት እና ጊዜ ዋጋ ለሌለው ነገር ሊሰጡ አይገባምና።

#የሕይወት_ኬሚስትሪ መጽሐፍ #2ተኛ ዕትም በገበያ ላይ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
5.6K views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 06:40:41
#ተስፋ_ቁረጥ_እግዚአብሔር_አይሰማህም!

ምንም ነገር ይሁን ካልተቆጣጠርከው ያንተ ሆኖ ሊቀጥል አይችልም። ታጣዋለህ! እግዚአብሔር መቼም የምትጸልየውን ነገር አይሰጥህም።

እግዚአብሔር ሁሌም የሚሰጥህ ነገር ልትቆጣጠረው የምትችለውን ብቻ ነው። ምናልባት አዲስ ቤት እንዲሰጥህ ጸልየሃል፤ እናም እግዚብሔር ላንተ አንድ አፓርትመንት ያያል፤ ቤቱ የተመሰቃቀለ አይነት። ቤቱን ማስተካከል ያንተ ሃላፊነት ስለሆነ ይሰጥሃል።

ስለዚህ እግዚአብሔር ሁሌም የሚሰጥህ ልትቆጣጠረው የምትችለውን ነው። አቅምህን፣ ችሎታህን አለማወቅ ያንተው ችግር ይሆናል።

አካልህን መቆጣጠር ካልቻልክ በበሽታ፣ በጉዳት በተለያዩ ነገሮች ታጣዋለህ፡፡

የትዳር ህይወትህን የማትቆጣጠር ከሆነ (ቸል የምትል ከሆነ) ከባለቤትህ ጋር በመጣላት፣ በመሰለቻቸት ታጣዋለህ።

ልጆችህን የማትቆጣጠር ከሆነ ልጆችህን በሱስ፣ በስራት አልበኝነት ... ታጣቸዋለህ።

ገንዘብህን የማትቆጣጠር ከሆነ በአላስፈላጊ ወጪ፣ እቅድን ባላማከለ አባካኝነት ... ገንዘብህ ከፊትህ ተኖ ይጠፋል።

በሃላፊነት ያሉህን ነገሮች መቆጣጠር ካልቻልክ፣ ሁሉንም ነገር በቶሎ ለማጣት ፍቃደኛ እንደሆንክ ቁጠረው።

በዚህ የተነሳ ነው የህይወት ቀውስ የሚከሰተው፤ ስለዚህ በዙሪያህ ያሉትንና ያሉህን ነገሮች ሁሉ በብልሃት ልትቆጣጠራቸው ይገባል።

የማይልስ ሙንሮ ሁለት መጽሐፍት

#አስቸጋሪ_ሁኔታዎችን_ማሸነፍ እና #የመሪነት_ሳይንስ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- http://shorturl.at/
2.8K views03:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 19:55:37
#ልብህን_ተከተል

የሆነ ቀን... ደስታ
⁃ ስለ ስራህ፣
⁃ ስለ ዲግሪህ ወይም
⁃ ስለ ፍቅር ግንኙነትህ እንዳልሆነ ትረዳለህ።

ደስታ ከፊትህ ያሉትን ሰዎች ዱካ ስለመከተል እንዳልሆነ፣

በጭራሽ ሌሎችን ለመሆን ስለመሞከርም እንዳይደለ ትረዳለህ።

አንድ ቀን ደስታ
-0በመንገድህ ላይ ስላለው ግኝት፣
⁃ ስለ ተስፋው፣
⁃ ልብህን ስለ መከተል እንደሆነ ትረዳለህ።

ደስታ ለራስህ ስላለህ ርህራሄ፣ እየሆንክ ያለኸውን አዲሱን ሰው ስለ መግለጠጥ ነው።

አንድ ቀን ይህን ትረዳለህ -

ደስታ ከራስህ ጋር በመስማማት መኖርን መልመድ ነው።

ደስታህ በሰዎች እጅ ላይ አይደለችም፤

በእጅህ ላይ ናት፤ በእጅህም ላይ ሁሌም ትሆናለች።

አትከፍልበት እስቲ ደስ ይበልህ ... እኛም እንወቅ ደስታህን ግለጽልን

#የሕይወት_ቀመሮች መጽሐፍ
#12_RULES_FOR_LIFE

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል።


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- http://shorturl.at/#
3.5K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 13:16:33
#ሕይወት_እንደዚህ_ናት!

ምንም አደረግክ ምን፣ ሰዎች ስላንተ የሚያወሩት መጥፎ ነገር አያጡም፤

ሕይወት እንደዚህ ናት!


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- http://shorturl.at/binrX
4.2K views10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 06:54:58
#ሕይወት_ስጦታ_ናት

ዓይነ ስውር ስለነበረች ብቻ እራሷን የምትጠላ ሴት ነበረች። ከፍቅረኛዋ በስተቀር የምትወደው አልነበረም። እሱ ሁልጊዜ ከጎኗ አይጠፋም። ሁሌም '' አለምን ማየት ብችል ፍቅረኛዬን አገባለዋለሁ '' ትላለች ።

አንድ ቀን አንድ ሰው ጥንድ አይን ሰጣትና ፍቅረኛዋን ጨምሮ ሁሉንም ነገር ማየት ቻለች። ፍቅረኛዋም " አሁን አለምን ማየት ችለሻል ታገቢኛለሽ ? " ሲል በፍቅር ጠየቃት።

ልጅቷም ፍቅረኛዋ ዓይነ ስውር መሆኑን ባየች ጊዜ ደነገጠች። እና ልታገባው እንደማትፈልግ ነገረችው። ፍቅረኛዋም ከተለያዩ ከብዙ ጊዜ በሁዋላ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ላከላት።

" ውዴ አይኖቼን ብቻ አደራ ተንከባከቢልኝ። "

ከለውጥ በኋላ አብዛኛው ሰው እንዲህ ይሆናል። ጥቂቶች ብቻ ናቸው ህይወታቸው ምን እንደነበረ እና ማን በችግራቸው ጊዜ እንደደረሰላቸው የማይዘነጉ።

ሕይወት ስጦታ ናት ኑሩት፣ ተዝናኑበት፣ አክብሩት፣ እና - አሟሉት።

#በልኬት_ወደ_ስኬት መጽሐፍ በገበያ ላይ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል።


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- http://shorturl.at/binrX
4.5K views03:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 19:54:04
#የሕይወት_ሚስጥር

... መምህሩ እንዲህ አላቸው ''ተማሪዎች የዛሬው ፈተና በጣም ከባድ ነው። እዚህ ትምህርት ቤት ውስጥ አንጋፋ የተባሉ መምህራን ራሱ ሊሰሩት አልቻሉም።''

ተማሪዎቹ ደነገጡ -ፈሩ። እውነትም ፈተናው እጅግ ከበዳቸው። ጎበዝ የተባሉ ተማሪዎች ሳይቀር አንድ ጥያቄ መስራት አቅቷቸው ግማሽ ሰአት አለፈ።

ይሄኔ አንድ ተማሪ አርፍዶ ደረሰ። ፈተናውን በተቀበለ በአስር ደቂቃ ውስጥ ፈተናውን ጨርሶ ሰጠ።

በመጨረሻም ፈተናው ሲመለስ አርፍዶ የመጣው ተማሪ ብቻ ከፍተኛ ውጤት አምጥቷል።

ይህ የህይወት ሚስጥር ነው። አየህ መምህሩ ስለ ፈተናው ክብደት በሚናገርበት ጊዜ ያ ተማሪ ስላልነበረ ፍርሃት አላጠቃውም።

ፍርሃት የሰው ልጅ ትልቁ ጠላት ነው። ሰዎች ስለያዝከው አላማ ብዙ የሚያስፈሩ ነገሮችን ሊነግሩህ ይችላሉ መስማት ያለብህ ግን #የልብህን_እምነት ነው!

#ድብቁ_አእምሮህ_ድብቁ_ኃይልህ መጽሐፍ በገበያ ላይ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- http://shorturl.at/binrX
4.7K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 06:57:11
#ትግልህን_ምረጥ!

“ከሕይወት የምትፈልገው ምንድነው?” ብዬ ብጠይቅህና “ደስተኛ መሆን፣ ታላቅ ቤተሰብ መመስረትና የምወደው ስራ እንዲኖረኝ፡፡” ብለህ ብትመልስልኝ፣ መልስህ የተለመደና የሚጠበቅ ከመሆኑ የተነሳ ምንም ትርጉም የሌለው ይሆናል፡፡

ሁሉም ሰው ጥሩ በሆነው ይደሰታል፡፡ ሁሉም ሰው ጭንቀት የሌለበት፣ ደስተኛና ቀላል ሕይወት መኖር፤ በፍቅር መውደቅ፣ በጣም ደስ የሚል ወሲባዊ ግንኙነትና ጓደኝነት፣ ዘናጭ መሆንና ገንዘብ መስራት፣ ታዋቂና የተከበረ መሆን፣ በጣም የተደነቀ ከመሆን የተነሳ ወደ አንድ ቦታ ሲራመድ ሰዎች እንደ ቀይ ባህር የሚከፈሉለት ቢሆን ይፈልጋል፡፡

ሁሉም ሰው ያንን ይፈልጋል፤ ያንን መፈለግ ቀላል ነው፡፡

በጣም ደስ የሚለውና ብዙ ሰዎች በጭራሽ የማያስተውሉት መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ግን “በሕይወትህ ውስጥ ምን አይነት ስቃይ ትፈልጋለህ? ልትታገል የምትፈልገው ምንድነው?” የሚል ነው፡፡ ምክንያቱም ህይወታችን እንዴት እንደሚሆን የሚወስነው ትልቁ ነገር ያ ነውና፡፡

#በጥበብ_መኖር መጽሐፍ #5ተኛው ዕትም በገበያ ላይ
#THE_SUBTLE_ART_OF_NOT_GIVING_A...


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- http://shorturl.at/binrX
5.0K views03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ