2023-06-10 06:40:28
#10_የገንዘብ_ሳይኮሎጂ_ትምህርቶች
ለአነቃቂ መልዕክቶች Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
The Psychology of Money በሚል በሞርገን ሃውስል የተጻፈው መጽሐፍ #በእንግሊዘኛ እንዲሁም #የገንዘብ_ሳይኮሎጂ በሚል ርዕስ ደግሞ #በአማርኛ ተተርጉሞ ሁለቱም መጽሐፍት በገበያ ላይ ውለዋል፡፡
#የገንዘብ_ሳይኮሎጂ መጽሐፍ ስለ ገንዘብ፣ ስለ ሀብት፣ ሰዎች ስለ ገንዘብ እና ስለ ሀብት ስለሚኖሯቸው ባህሪያት፣ ስለ ኢንቨስትመንት እና ገንዘብን በተመለከተ ምን አይነት ውሳኔዎችን መወሰን እንደሚገባን የሚያስተምር መጽሐፍ ነው፡፡ ገንዘብን ስለ ማሳደግ፣ ሀብት ስለ ማፍራት፣ ሀብታም ሆኖ ስለ መኖር፣ ስግብግብነት ስለሚያስከትለው ጉዳት፣ ስለ ኢንቨስትመንት ወዘተ ጥልቅ ጥበቦች ያሉበት መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ታትሞ ሁለቱም መጽሐፍት በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ እንደሚገኙ እየጠቆምን #አስሩን ነጥቦች እነሆ ለቅምሻ ብለናል፡-
#1_ወሳኙ_ለገንዘብ_ያለህ_አስተሳሰብ_ነው፡፡
እጅግ በጣም ወሳኙ ነገር አካላዊ ገንዘቡ ሳይሆን ስለ ገንዘብ ያለህ አስተሳሰብ ነው፡፡ ስለ ገንዘብ ያለህ አእምሯዊ አስተሳሰብ እና አመለካከት ከጥሬ ገንዘቡ ይልቅ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ አእምሯዊ አስተሳሰብህ ምን ያህል ሀብት እንደምትገነባ፣ ምን ያህል ገንዘብ እንደምታገኝ፣ ምን ያህል ገንዘብ መቆጠብ እንደሚገባህ፣ ገንዘብህንና ሀብትህን በምን ያህል እጥፍ ማብዛት እንደምትችል እናም በዋነኝነት እንዴት ደስተኛ እንደምትሆን ይወስናል፡፡ ስለዚህም ስለ ገንዘብ ትክክለኛ አመለካከትን ገንባ፡፡
#2_በቃ_ዕድል_ነው፡፡
በህይወትህ ልዩነት የሚፈጥረው አንዳንዴ ተሰጦኦህ፣ ችሎታህና ክህሎትህ፣ የትምህርት ብቃትህ፣ ያሉህ ግንኙነቶችና ትውውቆች፣ አሊያም ምን ያህል ሀብታም መሆንህ አይደለም፤ በቃ ዕድል ነው፡፡ ይህን መቀበል ነው፡፡ የባንክ ባለሙያ፣ ኢኮኖሚስት፣ ስራ ፈጣሪ እና የበርካታ ድርጅቶች ባለቤት ስለሆነው ስለ ናይጄሪያዊው ቢሊነየር ቶኒ ኢሉሜሉ አስብ፡፡ ትሁት ሁን፡፡ ስኬትን ስታገኝ አትኮፈስ፡፡ ራስህን ዝቅ አድርግ፡፡ በስኬትህ ዕድል እንዳለበት አስብ፡፡
#3_ስግብግብ_አትሁን፡፡
ይበቃኛልን ተማር፡፡ በህይወትህ ደስታን የምታገኘው የይበቃኛል ስሜት ሲኖርህ ነው፡፡ ስግብግብ ከሆንክ ሕግን ትተላለፋለህ፤ ለሌሎች ማሰብን ትተዋለህ፡፡ ይህም ብዙ ነገር ያሳጣሃል፡፡ በዓለም እጅግ ስኬታማ የነበሩ ሰዎች ስግብግብ ስለሆኑና ይበቃኛል ስላሉ ውድቀት እና ክስረት ገጥሟቸዋል፡፡ ይበቃኛል በል፡፡ በምታገኘው ትርፍ፣ በስኬትህ እና በምትደርስበት ደረጃ ተደሰት፡፡ ወደፊት ስለምታደርገው አስተዋጾ እና ለማህበረሰብህ እና ለሌሎች የሰው ልጆች ስለምትሰጠው ጠቀሜታ አስብ፡፡ ደስታ፣ ክብርና ሞገስ የሚገኘው ማህበረሰብን በማገልገል እና ሌሎች ሰዎችን በመጥቀም ነው፡፡ እናም ስግብግብ አትሁን፡፡
#4_ሀብት_መገንባት_ጊዜ_ይፈልጋል፡፡
ከምናስበው እና ከምንጠብቀው በላይ ጊዜ ይጠይቃል፡፡ ስለ ዋረን በፌት አስቡ፡፡ አብዛኛውን ሀብቱን ያገኘው ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው፡፡
#5_ለጉራ_ስትል_ውድ_ነገርን_አትግዛ፡፡
ከሰዎች አድናቆት እና ክብር ለማግኘት ስትል ነገሮችን ከመግዛት ተቆጠብ፡፡ ማንም በምትገዛቸው ውድ ነገሮች አይደነቅም፡፡ ውድ የሆኑ ነገሮችን መግዛት ከሰዎች አድናቆትንና ክብርን አያስገኝልህም፡፡ ውሳኔዎችህ መሆን ያለባቸው በውስጥ ፍላጎትህ እና በሚያስፈልጉህ ነገሮች ነው፡፡ ጎረቤቶችህን ወይም ጓደኞችህን ለማስደነቅ ስትል በገንዘብህ ምንም ነገር አታድርግ፡፡ ውድ መኪና፣ ቅንጡ ቤት፣ ውድ ቁሳቁሶች፣ ውድ አልባሳት መግዛትህ አያስደንቃቸውም፡፡ እንዲያደንቁህ እና እንዲያከብሩህ አያደርጋቸውም፡፡ ይልቁንም ማንነትህ እና ደግነትህ ያለህ ባህሪ በእነርሱ ዘንድ የሚኖርህን ስፍራ ይወስናል፡፡
#6_ዋጋ_ያለውን_ነገር_ለይ፡፡
ስምህና ክብርህ፣ ቤተሰብህ፣ ዘመዶችህ፣ ሰራተኞችህ፣ ጓደኞችህ እና የስራ አጋሮችህ ከምንም በላይ ዋጋ አላቸው፡፡ ገንዘብ ለማግኘት ብቻ ስትል እነዚህን አደጋ ውስጥ መጣል አይኖርብህም፡፡
#7_ሁሌም_ተስፈኛ_ሁን፡፡
ጨለምተኛ መሆን አንዳች ነገር አያስገኝም፡፡ ተስፈኛ ሰው ብቻ በአላማው ላይ ሆኖ በረጅም ጊዜ ሂደት ስኬትን ይጎናጸፋል፡፡ የአሁን ሁናቴዎችህ ምንም ይሁኑ የወደፊት ጊዜህ የተሻለ እንደሚሆን ማመን ይኖርብሃል፡፡ ይህ ወደፊት እንድትቀጥል ጥረትህን እንዳታቋርጥ እና የተሻለ ነገር እንድታደርግ ያስችልሃል፡፡
#8_የጊዜ_ነጻነት_እጅግ_ስኬታማ_እንድትሆን_ያስችልሃል፡፡
የጊዜ ነጻነትን የሚሰጥህን ስራ ምረጥ፡፡ ሙሉ ጊዜህን የሚቆጣጠር ስራ የራስህን አላማ እንዳትኖር፣ የራስህን ዕቅድ እንዳትተገብር ያደርግሃል፡፡ ስለዚህም የምትመኘውንና የምትፈልገውን ስኬት ለማግኘት የጊዜ ነጻነትን የሚሰጥህን ስራ በጉዞህ የሚያግዝህን ስራ በጥንቃቄ ምረጥ፡፡
የምትሰማራበትን ስራ በተግባር አይተኸው ወደፊት ሃያ እና ሰላሳ ዓመት ብቆይበት እደሰትበታለሁ ወይ ፍላጎቶቼን አሳካበታለሁ ወይ ብለህ ምረጠው፡፡ የጊዜ ነጻነት እና በራስህ ላይ የበላይነትን የሚሰጥህ ስራ ለስኬትህ እጅግ በጣም ጠቃሚ እና ተፈላጊ ነው፡፡
#9_የምታገኘውን_መረጃ_ሁሉ_አትጠቀም፡፡
የምታገኘውን መረጃ ሁሉ በህይወትህ አትተግብር፡፡ ለሌላው ሰው የሰራው ለአንተ ላይሰራ ይችላል፡፡ ለሌሎች የሰራው ለአንተ ጎጂ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህም ለግል አላማህ የሚያግዝህ የትኛው መረጃ እና እውቀት እንደሆነ በጥንቃቄ ለይተህ እወቅ፡፡
#10_ማንኛውም_ነገር_ዋጋ_አለው፡፡
ምንም ነገር ያለ ዋጋ አይገኝም፡፡ ሀብት ማግኘት ዋጋ ይጠይቃል፡፡ የሚጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ፍቃደኛ መሆን ይኖርብሃል፡፡ መቆጠብ፣ ጥሩ ኢንቨስትመንት ማካሄድ፣ እውቀት ማግኘት፣ ክህሎት ማግኘት ይኖርብሃል፡፡ ሀብት ማግኘት ከፈለግክ ዋጋውን ለመክፈል ፍቃደኛ መሆን ይኖርብሃል፡፡ በሀብት እና በገንዘብ የተደላደለ እና የተሟላ ህይወት ለመኖር ዋጋ ክፈል፡፡ ምንም ነገር ነጻ አይደለም፡፡ አንዳች ነገር ያለ ምንም ነገር አይገኝም፡፡
#የገንዘብ_ሳይኮሎጂ መጽሐፍን፣ #አስበህ_ሀብታም-ሁን የተሰኘውን መጽሐፍ የተረጎመው ውድሰው ደግዋለ ተርጉሞታል፡፡
#የገንዘብ_ሳይኮሎጂ መጽሐፍ
#The_Psychology_of_Money
#በአማርኛ እና #በእንግሊዘኛ ታትመው ሁለቱም መጽሐፍት በገበያ ላይ ውለዋል፡፡
ሁለቱንም መጽሐፍት በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኟቸዋል፡፡
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)
Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
4.8K views03:40