Get Mystery Box with random crypto!

Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

የቴሌግራም ቻናል አርማ teklu_tilahun — Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን T
የቴሌግራም ቻናል አርማ teklu_tilahun — Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን
የሰርጥ አድራሻ: @teklu_tilahun
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.25K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-29 20:05:40
#ዛሬ_የት_እንዳላችሁ_አትጨነቁ!

"... እያንዳንዱ ሳይንቲስት የሆነ ቀን ላይ የሚያለቅስ ህጻን ልጅ ነበር፤ እያንዳንዱ ታላቅ ኪነ ሕንፃም የሆነ ቀን ላይ ባዶ ካርታ ብቻ ነበር።

ዛሬ የት እንዳላችሁ መጨነቁ አስፈላጊ አይደለም ነገር ግን ነገ የት እንደምትደርሱ ማለምና ማስኬድ ላይ ነው ትልቁ ቁም ነገር ያለው።

ልብ በሉ አልበርት አንስታይን ሲወለድ ከንፅፅር ፅንሰ ሀሳብ ጋር አልተወለደም፤ አይዛክ ኒውተንም የእንቅስቃሴ ህጎቹን በእናቱ ማህፀን ውስጥ ቀምሮ አልወጣም፤

ዱባይ ውስጥ የሚገኘው ስምንት መቶ ሠላሳ ሜትር ገደማ የሚረዝመው “ቡርጅ ካሊፋ” የተሰኘው የዓለማችን ረዥሙ ኪነ ህንፃም ከሆነ ጊዜ በፊት ሕንፃ ሳይሆን ባዶ ካርታ ብቻ ነበር።

ሁሉም ነገር ከባዶ ነው የሚጀምረው።

ስለዚህ እናንተም በሙሉ ተስፋ ከጣራችሁ እና ዓላማችሁን ለማሳካት ቁርጠኛ ከሆናችሁ ከምንም እና ከየትም ተነስታችሁ የስኬትን ጫፍ መቆናጠጥ ትችላላችሁ” በማለት ሰሎሞን ተሰናብቷቸው ከክፍሉ ራመድ ራመድ ብሎ ወጣ።

#ከስሙር_መጽሐፍ_የተቀነጨበ

ከአንድ አብራክ የወጡ ሶስት ምርጥ መጽሐፍት

#ስሙር
#ሉባር
#ሰርድዮን

በገበያ ላይ:: በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ፡፡


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
5.4K views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 06:31:39
አንተ ማግኔት ነህ

የአዕምሮ አይኖችህን ከከፈትክ እና በውስጥህ ያለውን ሀይል መጠቀም ከቻልክ ወሰን የለሽ ሀብቶች በዙሪያህ እንዳሉ ልታይ ትችላለህ። ህይወትህን በደስታ ለመኖር የሚያስፈልግህን ሁሉ የያዘው የወርቅ ማዕድን በአንተ ውስጥ ነው።

ብዙዎች አንቀላፍተዋል ምክንያቱም በውስጣቸው ስላለህ እምቅ ሀይል ስለማያውቁ ነው።

የማግኔትነት ባሕሪ ያለው ብረት የክብደቱ አሥራ ሁለት አጥፍ ያህል ያነሳል። ይህንኑ ብረት ማግኔታማ ባሕሪውን ብታሳጣው ላባ እንኳ አያነሳም።

ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ። በራስ በመተማመን ስሜት የተሞሉ ማግኔቲዝድ ሰዎች እና በፍርሃትና በጥርጣሬ የተሞሉ ምንም የማይስቡ ሰዎች።

እድሎች ይመጣሉ፣ “ላይሳካልኝ ይችላል፣ ገንዘቤን ላጣ እችላለሁ፣ ሰዎች ይሳቁብኛል” የምትል ከሆነ እድሎቹን ትገፋለህ። በህይወት ውስጥ ብዙ ርቀት አትጓዝም፤ ምክንያቱም ወደፊት ለመሄድ የምትፈራ ከሆነ ባለህበት ብቻ ትቆያለህ።

አንተ ማግኔት ነህ... ወደፊት እየተጓዝክ መሳብህን ቀጥል!!

ድብቁ አእምሮህ ድብቁ ኃይልህ መጽሐፍ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
6.1K viewsedited  03:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 20:23:59
የማይሸጡ ነገሮች አሉ

በገንዘብ ቤት ልትገዛ ትችላለህ መኖሪያህን ግን አትገዛም።

በገንዘብ ሰአት ልትገዛ ትችላለህ ጊዜህን ግን አትገዛም።

በገንዘብ አልጋ ልትገዛ ትችላለህ እን ቅልፍህን ግን አትገዛም

በገንዘብ ምግብ ልትገዛ ትችላለህ የመብላት ፍላጎትህን ግን አትገዛም።

በገንዘብ ዶክተር ልትቀጥር ትችላለህ ጤናህን ግን ልትገዛ አትችል።

በገንዘብ ''ኢንሹራንስ'' ልትገዛ ትችላለህ ደህንነትህን ግን ልትገዛ አትችልም።

ቁምነገሩ~ ይሄ ሁሉም ነገር ቢኖረን ራሱ ያለብን ትልቅ ችግር ነው። ሁሉንም ነገር መግዛት ሰው እንደመሆናችን የማንችለው ነገር ነው። ሁሌም በገንዘብ ቁሳዊ ነገሮችን ብቻ መሸመት እንችል ይሆናል፤ ነገር ግን የማይሸጡ ነገሮች እንዳሉ መገንዘብ ይኖርብናል። ያም መንፈሳዊ እና አዋቂ ሰው መሆናችን የማንገዛውን ነገር እንደሚሰጠን መረዳት አለብን፡፡

የገንዘብ ሳይኮሎጂ መጽሐፍ በገበያ ላይ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
5.7K viewsedited  17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 20:09:11 #The_One_Thing book
በገበያ ላይ

ON SALE

አለም አቀፍ ሽያጭን የተቀዳጀውና ከ 5.4 ሚሊየን ኮፒ በላይ የተሸጠው #The_One_Thing የተሰኘው የእንግሊዘኛ መጽሐፍ በገበያ ላይ፡፡

በመላው ኢትዮጵያ በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

እነሆ 10 የመጽሐፉን ትምህርቶች ለቅምሻ፡-

#The_One_Thing book

An international bestseller which has sold more than 5.4 million copies, is now on the market.

Here are ten lessons from Gary Keller's book #The_One_Thing

#1_Not_everything_matters_equally. Not all tasks are created equal. Some tasks are more important than others. The key is to focus on the most important tasks and ignore the rest.

#2_Multitasking_is_a_lie. You can't do two things at once and do them both well. When you multitask, you're actually switching back and forth between tasks, which takes time and effort.

#3_Discipline_is_a_result_of_habit. The more you do something, the easier it becomes. The key to developing discipline is to start small and gradually build up your habits.

#4_Willpower_is_a_finite_resource. Willpower is like a muscle. The more you use it, the weaker it becomes. The key to conserving willpower is to focus on one thing at a time and avoid distractions.

#5_Big_is_bad. Trying to do too much at once will only lead to overwhelm and stress. The key to success is to focus on one thing at a time and do it well.

#6_The_Domino_Effect. When you focus on the most important task, it can have a cascading effect on other areas of your life. For example, if you focus on your health, it can lead to more energy, which can lead to more productivity, which can lead to more success.

#7_The_80_20_Principle. The 80/20 Principle states that 80% of your results come from 20% of your efforts. The key is to identify the 20% of your efforts that are most important and focus on those.

#8_The_Power_of_Focus. When you focus on one thing at a time, you're able to give it your full attention. This leads to better results and less stress.

#9_The_Importance_of_Rest. Rest is essential for productivity. When you're well-rested, you're able to focus better and make better decisions.

#10_The_Power_of_Persistence. Persistence is key to success. Don't give up on your goals, even when things get tough. Keep going and you will eventually achieve your goals.

#The_One_Thing book

It is available in bookstores and peddlers throughout Ethiopia.

በመላው ኢትዮጵያ በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡


(Join our Facebook and Telegram pages for daily motivational messages, PDFs of our published books, cash and book prizes.)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
5.5K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 20:09:05
4.8K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 12:44:08
#የእኔ_ሀብት_የመገንባት_ፍልስፍና

ከ 32 ሚሊዮን ኮፒ በላይ ከተሸጠው ከ RICH DAD POOR DAD መጽሐፍ ጸሐፊ ሮበርት ኪዮሳኪ አዲሱ #ሀብት_የመገንባት_ጥበብ መጽሐፍ በገበያ ላይ መዋሉን ምክንያት በማድረግ
#የእኔ_ሀብት_የመገንባት_ጥበብ የምትሉትን በማቅረብ እንድትሳተፉ መጋበዛችን ይታወቃል፡፡

በውድድሩ አንደኛ የወጣው የእኔ ሀብት የመገንባት ፍልስፍና ይለናል፡-

መጀመሪያ ለገንዘብ ያለንንን አመለካከት መቀየር ነው፤ ገንዘብ ሊያኖረን እንደሚችለው ያህል ሊያጠፋን ይችላል::

ገንዘብ ካገኘን በኋላ ደሞ የብር አያያዝን ማወቅ ነው። ያ ማለት ገንዘብን ያለምክንያት አለማጥፋት አልባሌ እና ቅንጡ ነገሮችን አለመግዛት ነው::

ገንዘብ መቆጠብ:: ቁጠባ ትልቁ የሀብት የመገንባት ምንጭ ነው፤ ገንዘብ አግኝተን መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ካሟላን በኋላ የቀረውን መቆጠብ አስፈላጊ ነው።

የቆጠብነውን ብር ላመንበት ቢዝነስ ማዋል ነው ከዛ እዛ ቢዝነስ ላይ በሙሉ አቅም በመስራት ማሳደግ ነው::

ሀብት ካካበትን በኋላ ለሰዎች ያለን አመለካከት መቀየር የለበትም፤ ያ ማለት ጉራ ጢባር አስፈላጊ አይደለም ያካበትነውን ሀብት ሊያጠፋው ይችላል::

ሀሳቤ ከተመቻቹ እና ከወደዳች ላይክ አርጉልኝ አመሰግናለው

Germa Germa
ያገኘው የላይክ ብዛት 44
30 ላይክ ከቡክላንድ

#ሀብት_የመገንባት_ጥበብ መጽሐፍ በገበያ ላይ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
5.8K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 07:00:20
#የእናት_ፍቅር

"ምድር ላይ እንደ እናት ፍቅር ኃያል ነገር አላውቅም።

የእናት ፍቅር ፀሐይ ሲጠልቅ አይጠልቅም፤ ሌሊቱን ሙሉ በጨለማም እንደ ሻማ ያበራል::

ወጣትነት በዘመን ብዛት ይጠፋል፤ የተቃራኒ ፆታ ፍቅርም የሆነ ጊዜ ላይ ይደበዝዛል፤ የእናት ምስጢራዊ ጥልቅ ፍቅር ግን ከሁሉም በልጦ ነግሶ ይኖራል።"

#ከስሙር_መጽሐፍ_የተቀነጨበ

#ስሙር
#ሉባር
#ሰርድዮን

በገበያ ላይ:: በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ፡፡


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
5.7K viewsedited  04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 20:39:58
#አልፈልግም!

ነገ ላይ ወደ ኋላ ተመልሼ

‹‹ምናለ አድርጌው በነበር›› ማለት አልፈልግም!

#የመሪነት_ሳይንስ መጽሐፍ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
6.0K views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 12:44:50 #7ቱ_የሳሳ_ቦርሳ_የማደለቢያ_ዘዴዎች

ከ 32 ሚሊዮን ኮፒ በላይ ከተሸጠው ከ RICH DAD POOR DAD መጽሐፍ ጸሐፊ ሮበርት ኪዮሳኪ አዲሱ #ሀብት_የመገንባት_ጥበብ መጽሐፍ በገበያ ላይ መዋሉን ምክንያት በማድረግ
#የእኔ ሀብት_የመገንባት_ጥበብ የምትሉትን በማቅረብ እንድትሳተፉ መጋበዛችን ይታወቃል፡፡

በውድድሩ ሁለተኛ የወጣው ካነበብኩት ብሎ #7_የሳሳ_ቦርሳ_የደለቢያ_ዘዴዎች ይለናል፡-

#የመጀመሪያ_ፈውስ- ቦርሳህን ማደለብ ጀምር፤ ማለትም ከምታገኘው ወርሃዊ ገቢህ 10% መቆጠብ ጀምር።

#ሁለተኛ_ፈውስ- ወጪዎችህን ተቆጣጠር፤ ፍላጎቶችህነ ከአስፈላጊ ወጪዎች ጋር አታምታታ። ከዚያም የአስፈላጊ ወጪህን በጀት አዘጋጅ። ከገቢህ ከዘጠኝ አስረኛ በላይ ሳታወጣ የበጀትህ ዓላማ ቦርሳህን እንዲወፍር ማገዝ ነው።

#ሶስተኛ_ፈውስ- ወርቅህን እንዲበዛ አድርግ፤ በምታገኘው ገቢህ የብልጽግናህን መሰረት ትጥላለህ። እንዴት ስራ ላይ (ኢንቨስትመንት ላይ) ታውለዋለህ? እዚህ ላይ ካለህበት ቦታ እና ጊዜ አንጻር በደምብ ማሰብ ያስፈልጋል።

#አራተኛው_ፈውስ- ገንዘብህን ከኪሳራ ጠብቅ፤ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት መርህ ዋናው መጠበቅ ነው። ዋናው ካፒታል ሊቀልጥ በማይችልበት ሁኔታ ለወፍራም ትርፍ መጓጓት ብልህነት አይደለም። ገንዘብህን በየትኛውም መስክ ላይ ከማዋልህ በፈት ሊከተል የሚችለውን አደጋ እወቅ። ለማንም ከማበደርህ በፊት ሊከፍልህ መሆኑን አረጋግጥ። ገንዘብህን ተገቢ ትርፍ ማግኘት በሚያስችልህ ነገር ላይ ኢንቨስት በማድረግ ራስህን ከኪሳራ ጠብቅ።

#አምስተኛው_ፈውስ- መኖሪያ ቤትህ አትራፊ ኢንቨስትመንት እንዲሆን አድርግ። አምስተኛ የሳሳ ቦርሳ ፈውስ የራስ መኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን ነው። ከልብ ላሰበበትም ሰው የራስ ቤት ባለቤት መሆን ከአቅም በላይ አይደለም። በብድር ከተሰራ ለአካራይህ ትከፍለው የነበረ ለአበዳሪህ ይሆናል።

#ስድሰተኛው_ፈውስ- ለወደፊት የሚሆን ገቢ እንደሚኖርህ አረጋግጥ። ለእርጅና ዕድሜ ዘመንህና ለቤተሰብህ የሚሆን መጠባበቂያ ገንዘብና ንብረት አስቀድመህ አኑር። ለዚህ አላማ ሲባል ቤቶች ወይም መሬት መግዛት ይቻላል። ወይም የደረስክበት የስልጣኔ ደረጃ የሚጠልበው ዘዴ ተጠቅመህ ገንዘብህን ለወደፊቱ ሊወልድልህ በሚችለው መንገድ ማስቀመጥ።

#ሰባተኛው_ፈውስ- ገንዘብ የማግኘት አቅምህን አሳድግ። ፍላጎት ስኬትን ቀድሞ ሊገኝ ይገባል። ከሁሉም በፊት መምጣት ያለበት ፍላጎት ነው። ፍላጎቶችህ ጠንካራና የነጠሩ መሆን አለባቸው። ጥቅል (ድፍን) ፍላጎቶች ደካማ ምኛቶች ናቸው። ፍላጎቶች ቀላልና ግልጽ መሆን አለባቸው። እጅግ በጣም ከበዙ፣ ግራ የሚያጋቡ ከሆኑ ወይም ብቃትህ (ከአቅምህ) በላይ ከሆኑ ልትቀዳጀው የተነሳህን አላማ ማሳካት አይቻልህም። እውቀትህን ባሳደግክ ቁጥር የበለጠ ገቢ የማግኘት እድል ይኖርሃል። ሰባተኛው የመጨረሻ ፈውስ የራስህን አቅም ማሳደግ፣ መማርና ይበልጥ ብልህ መሆን እንዲሁም የተሻለ ከህሎትን በማካበት ራስህን ማክበር መቻል ነው። በዚህ መልኩ በራስ መተማመንን በመፍጠር በጥንቃቄ የተመዘኑ ፍላጎቶችን ከግቡ መድረስ ይቻላል።

Daniel Kidane
ያገኘው የላይክ ብዛት 8
30 ላይክ ከቡክላንድ

#ሀብት_የመገንባት_ጥበብ መጽሐፍ በገበያ ላይ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)

Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?
6.6K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 12:44:46
5.5K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ