Get Mystery Box with random crypto!

Bemnet Library

የቴሌግራም ቻናል አርማ bemnet_library — Bemnet Library B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bemnet_library — Bemnet Library
የሰርጥ አድራሻ: @bemnet_library
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 46.21K
የሰርጥ መግለጫ

ሁሉም ዓይነት መፅሀፍ ለእርስዎ ቀርቧል
#ማጋራት መተሳሰብ ነው
! ከ 2014 ጀምሮ! እንደ እርስዎ ላሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ቁጥር 1 ምርጫዎች ነበርን
💬 @Bemni_Alex

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-11-11 10:33:17 እንዲው በደፈና "ወደድኳት! አበድኩላት።" የሚያሰኝ ድፍን ፍቅር አልነበረም የያዘው።በርህራሄ እና በመተሳሰብ ላይ መሰረቱን የጣለ እውን የሚዳሰስ እና የሚጨበጥ፤ንፋስ የማይገፋውና ውርጭ የማያበርደው ፍቅር.....

ወገግታ
                      የሺጥላ ኮኮብ

@Bemnet_Library
12.9K viewsBEMNET, 07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-10 10:02:06 ሀኒቾን የምወዳት በጠይም ቆንጆ ፊቷ አልነበረም፤የተማረኩት በጥቁር ዞማ ፀጉሯም አልነበረም፤ያሸነፈችኝ በየዋህነቷ ነው።ለመድመቅ አለመፍጨርጨሯ ነው።ተፈላጊነትን ለማሳየት አትዳክርም፤ያላትን ለማጉላት አትታከክም።ምንም የሌለውም ሰው እንደሚወደድ ያሳየችኝ ሀኒቾ ነበረች።

  አዎ እሱጋ ያመኛል
             አድሀኖም ምትኩ

@Bemnet_Library
13.2K viewsBEMNET, 07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-04 19:17:16 ተናግረን ማለት ባልፈለግነውና ማለት ፈልገን ባልተናገርነው መሀል እጅግ ብዙ ፍቅር ባክኗል።...

ካህሊል ጂብራን

@Bemnet_Library
13.2K viewsBEMNET, edited  16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-03 09:49:23 ርዕስ= የነፍስ መንገድ

ደራሲ=ኦሾ(Osho)

@Bemnet_Library
14.1K viewsBEMNET, 06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-03 09:43:29 ርዕስ=ሾተላዩ ሰላይ
ደራሲ=ኬን ፎሌት

@Bemnet_Library.
13.0K viewsBEMNET, edited  06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-08 20:36:25 ርዕስ (መከረኞች)

ደራሲ ( ቪክቶር ሁጎ)

ተርጓሚ (ሳህለስላሴ ብርሀነማርያም)

ዘውግ (ልብ ወለድ)

የገፅ ብዛት (578)

instagram
13.1K viewsBEMNET, edited  17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-06 20:53:39 ርዕስ - የገንዘብ ፍሰት ኳድራንት
ደራሲ - ሮበርት ኪዮሳኪይ
ትርጉም- ዮሐንስ አባተ
ዘውግ - ራስ አገዝ
የህትመት ዘመን - 1999
የገፅ ብዛት - 255

የ Cashflow Quadrant" በሮበርት ኪዮሳኪ የተጻፈ መጽሐፍ ሲሆን ግለሰቦች ገቢን ለማግኘት ሊከተሏቸው ስለሚችሉት የተለያዩ መንገዶች ላይ በጥልቀት የዳሰሰ መጽሐፍ ነው። ኪዮሳኪ አራቱን ሩቢዎች(Quadrant) ይዘረዝራል፡
                   |
                   |
       ተ         |       ባ
----------------|---------------
                  |
     ራ.ቀ.      |        ኢ
                  |

ተ= ተቀጥሮ የሚሰራ፣
ራ.ቀ.= ራሱን ቀጥሮ የሚሰራና የሚያሰራ፣
ባ= ለቢዝነስ ባለቤት እና
ኢ= ኢንቨስተር

ከእያንዳንዱ ኳድራንት ጋር የተያያዙትን አስተሳሰቦች፣ ጥቅሞች እና ተግዳሮቶች ይመረምራል፣ ከግራ በኩል (ተ እና ራ.ቀ.) ወደ ቀኝ ጎን (ባ እና ኢ) መንቀሳቀስ የገንዘብ ነፃነት ያስገኛል እና ነፃነትን ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ይሰጣል።  ተዛማጅ ታሪኮች እና ተግባራዊ ምክሮች ኪዮሳኪ ስለ ንብረቶች ግንባታ እና አተገባበር፤ የገቢ ዥረቶችን ስለመፍጠር ለአንባቢዎች ግንዛቤ ይሰጣል።"የገንዘብ ፍሰት ኳድራንት" በፋይናንስ አለምን ለመምራት እና በመጨረሻም ፋይናንስ የወደፊት ህይወታቸውን ለመለወጥ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ጠቃሚ ግብአት እንደሆነ ይጠቅሳል።

አዘጋጅ @Bemnet_Library
13.6K viewsDAGLAS PETROS, edited  17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-02 07:58:52
"የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ "

ኢትዮጵያ ካሏት የልብ ቀዶ ጥገና ሀኪሞች አንዱ የሆነው ዶ/ር ፈቀደ አግዋር ባለፉት 4 ዓመታት ብቻ ከ300 በላይ ልቦችን ቀዶ ጠግኗል። ከእነዚያ መሀል አብዛኞቹ በሀገራችን የልብ ቀዶ ጥገና ታሪክ የመጀመሪያ የሆኑ የ17 አስገራሚ ቀዶ ጥገናዎችን ልብ መሳጭ በሆነ ቋንቋ ከሽኖ አቅርቦላችኋል። ከ90 ዓመቱ የሮይተርስ ጋዜጠኛ የወራት እድሜ እስካላቸው ጨቅላ ህጻናት ልባቸውን ከፍቶ አክሟል።

ይሄ መጽሐፍ በ2 ወር ውስጥ ብቻ 3 ጊዜ የታተመ ሲሆን 4ኛውም እትም በቅርቡ ታትሞ ለንባብ በቅቷል።

Photo & Text፦ Bemnet Library& jafer books

@Bemnet_Library
12.7K viewsBEMNET, 04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 07:01:18
መስከረም 1

የበእምነት ቤተመፅሐፍት የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆንዎ እናመሰግናለን፤ መልካም በአል!

@Bemnet_Library
2.2K viewsBEMNET, 04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 23:38:31 2014 ለእኔ ልዩ አመት ነበር።አንድ ቀን በትንሽዬ ማስታወሻ ላይ 10 ምርጥ የኢትዮጵያ ደራሲዎችን ለማግኘት ዕቅድ ያስኩኝ።

ከነዚህ ምርጥዬ ደራሲዎች ውስጥ፦ ምህረት ደበበ፤ዳዊት ወንድማገኝ፤አሌክስ አብርሃም፤ዓለማየሁ ገላጋይ፤ኤልያስ ገብሩ፤አለማየሁ ዋሴ፤መለሰ ወጉና ደሞዝ አበበ ይገኙበት ነበር።

በጊዜው እንዴት ላገኛቸው እንደምችል ባላውቅም እንደማገኛቸው ግን 100% እርግጠኛ ነበርኩ።ከዛ እንዳቀድኩት ለመጀመሪያ ጊዜ ምህረት ደበበን አገኘሁት፤ከእሱ በኃላ ከ8ቱ ደራሲዎች ጋር ተወዳጀው።ባጠቃላይ ከ10ሩ ምርጥዬ ደራሲዎች ውስጥ 9ቱን የማግኘት ዕድል አጋጠመኝ።ከዛ ጮቤ ረገጥኩኝ፤በጣም ደስ አለኝ።

ነገር ግን እስካሁን ያላገኘሁትና ያልተወዳጀሁት ደራሲ ቢኖር አሌክስ አብርሃምን ነው።እሱን ለማግኘት በየትኛው መንገድ መራመድ እንዳለብኝ አላውቅም።ሁሌ በህልሜ ይመጣብኛል።የምነቃው አሌክስ አብርሃም ብዬ ጮሄ ነው።ከዕለታት ግማሽ ቀን የሚለው መጽሐፉ ይመቸኛል።ለነገሩ ሁሉም መጽሐፉቹ ተነበው ተነበው የማይጠገቡ ናቸው።ለማንኛውም አሌክስዬ አንድ ቀን እንደምንገናኝና ሻይ ቡና እንደምል ይታወቀኛል።

#በነገራችን ላይ ከትላልቅ ደራሲዎች ጋር ተገናኝቶ ማውራት እንዴት እንደሚያስፈራ ልነግራችሁ አልችልም።እኔ ከምህረት ጋር ስገናኝ በጣም ፈርቼ ነበር።እንደውም ምን ማለት እንዳለብኝ ግራ ከመጋባቴ የተነሳ በራሴ ዛቢያ ውስጥ ለደቂቃዎች በሃሳብ ተሸከርክሬያለሁ፤ከዛ ቀስ በቀስ ብዬ እየተጨዋወትን አመሸን።አሁን ምንም አይነት ፍርሃት የለብኝም፤ምክንያቱም ሁሉም ጓዶቼ ሆነዋል።

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
2.7K viewsBEMNET, edited  20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ