Get Mystery Box with random crypto!

Walia bookstore gallery

የቴሌግራም ቻናል አርማ waliabooks — Walia bookstore gallery W
የቴሌግራም ቻናል አርማ waliabooks — Walia bookstore gallery
የሰርጥ አድራሻ: @waliabooks
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.78K
የሰርጥ መግለጫ

Books

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 18:33:45
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

መግቢያ  በነፃ

በህይወት ተሞክሮ ተምሳሌት ከሆኑ እንግዶች ጋር ቆይታ

የእለቱ የክብር እንግዳ:-
ዶክተር መሐመድ  ሽኩር
የአሚን ጀነራል  ሆስፒታል  መስራች  እና  ዋና
ስራ አስኪያጅ

አወያይ:- ዶክተር ቢላል  ሺኩር
የቢልኮር ኢንስቲትዩት ኦፍ ሊደርሺፕ  ኮቺንግ ኤንደ ሪሰርች መስራች  እና  ዋና ስራ አስኪያጅ

የስሜት ብልህነትና ስኬት ላይ የሀሳብ እና የልምድ ልውውጥ መድረክ

ቦታ:- አራት ኪሎ: ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ:  ኢክላስ ህንጻ ዋልያ መጻሕፍት::

ቀን:- ሐሙስ ነሀሴ 26/ 2014 ከሰዓት በኋላ ከ11:00 እስከ 12:30 ድረስ:: (በሰዓቱ ይጀመራል)

የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዋልያ መጻሕፍት እና ቢልኮር ኢንስቲትዩት ኦፍ ሊደርሺፕ  ኮቺንግ ኤንደ ሪሰርች

ከዚህ ቀደም የተደረጉ መሰል ፕሮግራሞችን ለመከታተል በዋልያ ቡክ ስቶር ቻናል ያገኙናል።

( https://m.youtube.com/channel/UCT2s8ZltG5kIS6Q1n7NGGxw
830 views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 06:57:43 Walia bookstore gallery pinned a photo
03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:40:23
#ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል። 
-----
መግቢያ በነፃ

አቅራቢ አርክቴክት ሚካኤል ሽፈራሁ

በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ስራወች ላይ ዳሰሳ እና ወይይት።

የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዋልያ መጻሕፍት

ቦታ:- አራት ኪሎ: ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ:  ኢክላስ ህንጻ ዋልያ መጻሕፍት::

ቀን:- ቅዳሜ: ነሀሴ 28 2014:: ከሰዓት በኋላ ከ10:00 እስከ 12:00 ድረስ:: (በሰዓቱ ይጀመራል)

ማስታወሻ::

በእለቱ ከአርክቴክት ሚካኤል ሽፈራው ጋር የፎቶ እና የመፅሐፍ ፊርማ ስለሚኖር የደራሲውን ቀደምት ስራወችን ይዞ መገኘት አልያም ከቦታው መግዛት  የሚቻል ይሆናል።

ከዚህ ቀደም የተደረጉ መሰል ፕሮግራሞችን ለመከታተል በዋልያ ቡክ ስቶር ቻናል ያገኙናል።

( https://m.youtube.com/channel/UCT2s8ZltG5kIS6Q1n7NGGxw
534 views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:32:10 #ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል። 
-----
የመጻሕፍ ዳሰሳ፦የመጻሕፉ ረዕስ፡የከፍተኛ፡ትምህርት፣ ዘይቤ

የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዋልያ መጻሕፍት እና
የዶ/ር እጓለ:ገብረ ፡ዩሐንስ ቤተሰቦች።

መግቢያ መጻሕፉን መያዝ  አልያም ከቦታው መግዛት።

ተጋባዥ እንግዶች:(አቅራቢዎች)
1. ዶ/ር ኃይሉ ሀብቱ
2. ዶ/ር ዳኛቸው
3. መ/ር  ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል
4. መ/ር ግርማ ባቱ
5. ተመስገን ዋና


ቦታ:- አራት ኪሎ: ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ:  ኢክላስ ህንጻ ዋልያ መጻሕፍት::

ቀን:- ቅዳሜ: ነሀሴ 21 2014:: ከሰዓት በኋላ ከ10:00 እስከ 12:00 ድረስ:: (በሰዓቱ ይጀመራል)

ማስታወሻ::



ከዚህ ቀደም የተደረጉ መሰል ፕሮግራሞችን ለመከታተል በዋልያ ቡክ ስቶር ቻናል ያገኙናል።

( https://m.youtube.com/channel/UCT2s8ZltG5kIS6Q1n7NGGxw
1.3K views05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 13:28:16

1.3K views10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 08:04:40 Walia bookstore gallery pinned a photo
05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 18:44:05
#ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል።
-----
የመጻሕፍ ዳሰሳ፦የመጻሕፉ ረዕስ፡የከፍተኛ፡ትምህርት፣ ዘይቤ

የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዋልያ መጻሕፍት እና
የዶ/ር እጓለ:ገብረ ፡ዩሐንስ ቤተሰቦች።

መግቢያ መጻሕፉን መያዝ አልያም ከቦታው መግዛት።

ተጋባዥ እንግዶች:(አቅራቢዎች)
1. ዶ/ር ኃይሉ ሀብቱ
2. ዶ/ር ዳኛቸው
3. መ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል
4. መ/ር ግርማ ባቱ
5. ተመስገን ዋና


ቦታ:- አራት ኪሎ: ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ: ኢክላስ ህንጻ ዋልያ መጻሕፍት::

ቀን:- ቅዳሜ: ነሀሴ 21 2014:: ከሰዓት በኋላ ከ10:00 እስከ 12:00 ድረስ:: (በሰዓቱ ይጀመራል)

ማስታወሻ::



ከዚህ ቀደም የተደረጉ መሰል ፕሮግራሞችን ለመከታተል በዋልያ ቡክ ስቶር ቻናል ያገኙናል።

( https://m.youtube.com/channel/UCT2s8ZltG5kIS6Q1n7NGGxw
1.9K viewsedited  15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 11:23:02 ምስጋና እና የመረጃ ማቃኛ!
___

ሰሞኑን አሜሪካ ወደሚገኘው IOWA ዩኒቨርስቲ ከማምራቴ ጋር ተያይዞ እዚሁ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሃሳቦች ሲንሸራሸሩ ሶስት ነገሮችን አስተዋልኩ።

የመጀመርያው በደግ ዐይናቸው የሚያዩኝና ስኬቴን የሚናፍቁ ሰዎች መብዛታቸው! የምሥራቹን ለማብሰር መጣደፋቸው! (ክብረት ይስጥልኝ ከማለት ውጪ ምን እላቸው ኖሯል?)

ሁለተኛው ማቃኛ የሚፈልጉ መረጃዎች በፍጥነት መራባታቸው። አንዳንድ ቦታ እንደተባለው ቆይታዬ ለአመታት አይደለም ለጥቂት ወራት እንጂ። IOWA ዩኒቨርስቲ ብቻ ለአስር ሳምንታት ስንቆይ ሶስት አራት ሳምንቱን ደግሞ ይህን በመሰለ በሌሎች ፕሮግራሞች እንጠመዳለን። እርግጥ ለዚህ ፕሮግራም ተመራጭ ሆኖ መገኘት ይህን ለመሰለ ሌላ ዕድል በር የሚያስከፍት መሆኑን የቀደመ ተመክሯቸውን አንስተው ነግረውናል።

ሶስተኛው ደግሞ " አንተ ከሄድክ ዘወትር ቅዳሜ ከአስር እሰከ አስራሁለት ሰአት ከተለያዩ ደራስያን ጋር የምናደርገው (ዛጎል የመጻሕፍት ባንክና ዋልያ መጻሕፍት አንድ ላይ የሚያሰናዱት) ቆይታስ? ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ መጻሕፍት እየሰበሰበ መልሶ በገጠር ከተማው የሚያሰራጨው ነገርስ? በእጥልጥል ሊቀር?" የሚሉ ጥያቄዎች እየተነሱልኝ ነው። ከደራስያን ጋር የሚደረገው ውይይት እኔን ተክቶ ሌላ ሰው እንዲያወያየው ተወጥኖ የነበረ ቢሆንም ይህም በልዩ ልዩ ምክንያቶች ሳይሆንልን ቢቀርም: ፕሮግራሙ ግን በተለመደው ሰአት በልዩ ልዩ ኪናዊ ስራዎች ዝግጅቱን ያቆዩታል። ውይይቶች ዲስኩሮችና የመጻሕፍት ምርቃቶች ይካሄዱበታል። የመጻሕፍት ባንካችን አገልግሎትም አይቋረጥም። (እስካሁን ከሰላሳ አራት ሺህ በላይ መጻሕፍት በገጠር ከተማው እንዲዳረስ ምክንያት በመሆናችን እና ከዋልያ መጻሕፍት ጋር ሆነንም
ከሰባ በላይ የሆኑ መጻሕፍት ላይ ትኩረት ማድረጋችን ደስታ ቢሰማንም ካደረግነው ይልቅ ልናደርግ ያሰብነው እንደሚልቅ ደግሞ ደጋግመን ልንነግራችሁ እንወዳለን)

በመጨረሻም አሸናፊ ስለሆንኩበት ፕሮግራም በአጭሩ! (ወደፊት ዘለግ አድርገን እስክናወጋ)

IOWA ዩኒቨርስቲ በየአመቱ ከየአለማቱ ደራስያንን መርጦ ፕሮግራም የማሰናዳት ልማድ አለው። ጉምቱ ጉምቱ የብዕር ሰዎችም የኖቤል ሽልማት ወሳጆችም የዕድሉ ተቋዳሽ ሆነዋል። እንዲህ ያለው አጋጣሚ ኢትዮጵያ ሊያልፋት አይገባም በማለት ሲብሰከሰክ የምናውቀው ጌዲዮን ማሞ እንዳጫወተኝ ኤምባሲው በየአመቱ ያለመታከት አወዳድሩልኝ ብሎ ምርጦቹን ቢልክም እንደዘንድሮ ግን በለስ ቀንቶት አያውቅም።

የሆነው ሆኖ ዘንድሮ ውድድሩ የተከናወነው በሚከተለው መንገድ ነው። መጀመርያ እያንዳንዱ አገር ለዚህ ዕድል ብቁ ናቸው የሚላቸውን ደራስያን ስም ዝርዝር ላከ። ለምሳሌ ኢትዮጵያ የሚገኘው ኤምባሲ ሶስት ደራስያንን መርጦ ስለሚጽፉበት ርዕሰጉዳይ ገልጾ "አርአያ ናቸው: ኢትዮጵያን ይወክሉልኛል: ቢያሸንፉ እነሱም እናንተም ደስታና ኩራት ውስጥ ትገባላችሁ!" ብሎ ዝርዝር መረጃ ላከላቸው። እነሱ ደግሞ ስለደራስያኑ የተባለውን በራሳቸው መንገድ አጠኑ። ከዚያም ከሶስቱ አንዱን ብቻ ለይተው ዕጩ አደረጉ። እንደገና እሱንና የሌሎች አገራት ዕጩዎቹን ደግሞ አወዳደሩ። መቶ አስራአምስት ገደማ(?) ደረሱ። የሚፈልጉትና እርስ በርስ ልምድ እንዲለዋወጡ የሚፈልጓቸው የደራስያን ቁጥር ደግሞ ከሰላሳ እስከ ሰላሳአምስት ባለው ቁጥር ቢወሰኑ እንጂ እንዲበዙባቸው አይፈልጉም።
ስለዚህ የአሸናፊዎች አሸናፊን ለይቶ ለማውጣት ቃለመጠይቅ አደረጓቸው። መረጃዎቻቸውን አሰባሰቡ። ስለሚያተኩሩባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መረመሩ።

በመጨረሻም አሸናፊ ሆኖ ሲገኝ ለኤምባሲውም ለደራሲውም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ። ሙሉ ወጪውም በአሜሪካ ኤምባሲና በዩኒቨርስቲው እንደሚሸፈን አበሰሩ።

(እኛም ተደሰትነ!)

በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ በዚህ ዩኔስኮ የሥነጽሑፍ ከተማ ብሎ በሰየማትና በየዓመቱ ታላላቅ የሥነጽሑፍና የቴአትር መሰናዶዎች በሚኮመኮምባት IOWA CiTY ስሟ ሲነሳ ይህ መጀመርያዋ አይደለም። እኤአ በ1967 ስመጥሩው ደራሲ ዳኛቸው ወርቁም (የ"አደፍርስ" ደራሲ) አሸናፊ ሆኗል::

ወደፊት ደግሞ እንበዛለን ብዬ አምናለሁ።

ሰላም!!!!!
2.0K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 10:41:00 ስለ ዶክተር እንዳለ ጌታ ከበደ ጉዞ መረጃ ለጠየቃችሁን።

https://www.facebook.com/photo.php?fbid=382398010717701&set=a.167504332207071&type=3&flite=scwspnss&mibextid=OF0ZnoewP5EtbOZi
1.3K viewsedited  07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 18:06:53
#ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል። (በነጻ)
-----
ልዩ መርሐግብር:- መጽሐፍ የማስፈረም: ከደራስያን ጋር የመተዋወቅና የመጨዋወት ልዩ ሥነስርዓት::

የዕለቱ የክብር እንግዳ:- በድሉ ዋቅጅራ(ዶ/ር)

የተመረጠው መጽሐፍ:- የ፭ ግጥም እድሜ

የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ እና ዋልያ መጻሕፍት::

ቦታ:- አራት ኪሎ: ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ: ኢክላስ ህንጻ ዋልያ መጻሕፍት::

ቀን:- ቅዳሜ: ነሀሴ 14 2014:: ከሰዓት በኋላ ከ10:00 እስከ 12:00 ድረስ:: (በሰዓቱ ይጀመራል)

ማስታወሻ::

1) እንዲህ ዓይነቱ ፕሮግራም ቀጣይነት ያለው ነው::

2) ከዚህ ቀደም የተደረጉ መሰል ፕሮግራሞችን ለመከታተል በዋልያ ቡክ ስቶር ቻናል ያገኙናል።

( https://m.youtube.com/channel/UCT2s8ZltG5kIS6Q1n7NGGxw
2.3K views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ