Get Mystery Box with random crypto!

ትዝታዊ🐣

የቴሌግራም ቻናል አርማ tiztawe — ትዝታዊ🐣
የቴሌግራም ቻናል አርማ tiztawe — ትዝታዊ🐣
የሰርጥ አድራሻ: @tiztawe
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.26K
የሰርጥ መግለጫ

ስላላቹ አመሰግናለው !!
ለሃሳብና አስተያየታቹ . . . . @tiztawe1_bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-27 20:06:24 #*
*#1 ያለፉ ፈገግታዎች . . . /እኔን ብሎ ርዕስ ሰጪ /


የማር ጠብታ ምታክል ሩቢ ወደኔ ድክ ድክ ትላለች. , አቀፍኳት . . . እሩቅ አልመስልህ አለችኝ
ማውቀው አይን. . . በዘመኔ እርቀት የማይጨልምብኝ ፍክት ያለ ገፅ . . .

ትንንጥ ጣቶቿን በየተራ ሳምኳቸው . . .

"ማነው ሽምሽ. . ."

አይኗቿ ተንከራተቱ . . . ስሟ በዝቶባት ነው ብዬ ገመትኩ . . .. የቱን እንደምትነግረኝ ግራ ገብቷት መሰለኝ . . .ወይ አታውቀውም . .. . . ፈተናዋ የሷን አለማወቋ ብቻ አይደለም የአባቷንም ነው ብዬ አሁንም ገመትኩ . . .

"እናትሽ የታለች . . ."

ፈለገቻት . .. አልታየቻትም


አሰብኩ. . . የቱ ነው ከባዱ የህይወት ምዕራፏ.. . አሁኗ ወይስ በኋላዋ ?


ትናንሽ ነፍሶች ምርጫ የላቸውም. . . ከዝናቡ መርከፍከፍ በሱም መራስ ወይስ ሙቅ ፍራሽ ተብለው አልመረጡም ወላጅ ሳይፈጥራቸው በፊት የመረጠውን ለመኖር ይገደዳሉ . . .

እምቡጥ የወይን ፍሬ የመሰለ እግሯ ጫማ የለውም ከመሬቱ እርጥበት ጋር ተስማምተዋል ፣ ለመክዳት ጥቂት ሰበበ የሚፈልጉ ጨርቆች እዛም እዚህ አካላቷ ላይ ተበታትነዋል ፣ ከእግዜር ካፍያ በስተቀር በሰው እጆች ያልታጠበ ፀጉሯ በግንቦት ፀሃይ እንደተኮማተሩ ቅጠሎች ደክሞዋል. . .፣ ከሚያውቁት ደረቅ ጡት ጋር የታገሉ ከንፈሮቿ ብሶተኛ የጨለማ አበቦች ይመስላሉ፤
ሆዷ በእንቁልልጭ መመገብ ለምዷልና ላለማልቀስ እንደሚቀምስ ያስታውቃል. . .

ብዙ

ብዙ

ብዙ

የማታውቃቸው ስቃዬች አሏት ምን አልባት ለነገ ያሴሩባት. . . .

ከዝች ትንጥዬ ነፍስ ውስጥ የሚነፍሰው ብቸኛ ነገር ፍልቅልቅ ልጅነት ብቻ ነው . . ያልገባትን የምትኖር የበርሃ አደይ . . . የበርሃ ምንጭ . ..

'
'
"ኑኑ . . . "

ወደጠራት ድምፅ ከመሄዷ በፊት እጇን ዘረጋችልኝ . . .

"ባቦ. . " አለችኝ ጆሮን ሰርስሮ ልብን በሚያቃጥል ጥንጥዬ አንደበት

የጠራትን ማንነት ለማየት ዙርያዬን ቃኘው ለሷ ብር መስጠት ጨዋነት አልመስልክ ብሎኝ. . ርሃብ ግዴታው በሆነ የሰው ዘር ፊት ጨዋነት ሚለውን እቃቃ ለመጫወት ያፈረ አእምሮ አልነበረኝም /ምን አልባትም ጭራሱኑ የለኝም /

ኪሴ ውስጥ የነበሩትን ገንዘቦች ጥቅልል አረኩና

"ይኼን ለማማ ብቻ ስጭያት እሺ"

"እሲ ናልያም ትስት" ብላኝ ከእቅፌ ብን ብላ በረረች. . ..

ለሽርፍራፊ የደቂቃ ግማሾች ከቦታው ላይ ተከዝኩ. . መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ወደፊት ሳዘው ወደኋላ የቀረ እኔ ነበረ. . . ተመለስ ሚለኝ
"ኑኑ" የሚል ሙቅ ድምፅ . . በተስፋ መቁረጥ የምትጣራ ለስላሳ እናት . . . . . የት ይሁን ይኼን ድምፅ ማውቀው . . . ? የት ቦታ ? መኪናዬ ወደፊት እኔ ወደኃላ . . ...

/ትዝታ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
1.4K viewsedited  17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 11:49:29
/ዘካሪያስ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
1.2K views08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 11:27:00
. . .. ያልደረሳት
ደብዳቤ . . .



ልረሳሽ የወሰንኩ ቀን . . . #1

: ::. . . የውሸት ተኝቼ እንደነበር አይነት መባነን ባነንኩ ፣ ስለ ውሸት ህልሜ ተከዝኩ . . . ጠላሁሽ
:
:
ልረሳሽ የወሰንኩ ቀን. . . #2

: ::. . . ለዓይኖቼ ፈተና የነበሩ እንባዎችን ተደብቄ አነባው ሙቅ አልነበሩም እንደ ጥቅምት ንፋስ ቅዝቃዜያቸው ይወጋል . . . ጠላሁሽ
:
:
ልረሳሽ የወሰንኩ ቀን . . . #3

: ::. . . የነበሩንን የቁስ ትዝታዎች ከኔ ሰወርኳቸው ፣ ያለፍንበትን ጎዳናዎች ሸሸዋቸው
፣ እጆችሽ ያረፈባቸውን አካሎቼን ናኳቸው እራሴን በመስታወት ማየት አቆምኩ. . . ጠላሁሽ

.
.
. ያላረኩትን ጠይቂኝ ልረሳሽ ፈልጌ?! . . . የሆነው ግን ይሄ ነው ልረሳሽ ስፈልግ የበለጠ አፈቅርሽ ነበር . . . ጠላሁሽ ባልኩት ልክ እሰቃይ ነበር . . . አየሽ ውዴ ፍቅሬ ድርጊታችን ላይ ፣ ማስታዎሻዎቻችን ውስጥ ፣ ጓዳናዎች ላይ አልነበረም . . . በነዚህ ስላልገባሽ በነዚህ አልወጣም አልሽ . . .

እናም
.
.
.

ላልረሳሽ የወሰንኩ ቀን. . . #

ስለነበረን ጊዜ ፣ ስለሆንሽልኝ መልካም ነገሮች፣ ስለጣፋጭ ፍቅርሽ ፣ ስለደግነትና መልካምነትሽ አሰብኩ እና አከበርኩሽ . . . መውደዴን ቀጠልኩ. . !


. . . ባለፍንባቸው ጎዳናዎች አልፋለው ፣ ትዝታዎቻችንን ለጊዜ ትቼያቸዋለው. . አሁን ነበርን ግን የለንም ሚለውን ተቀብያለው . . !

መሮጥም ባይሆን መራመድ ጀምርያለው. .

/ትዝታ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
1.3K viewsedited  08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 00:14:03
"...አንዳንዶቻችን ምናልባት ላልጠየቅነው
ጥያቄ መልስ እየፈለግን ነው..."

/ዘካሪያስ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
1.5K views21:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:08:41 . . . .


". . እኔም በጣም የምወደው ጊዜ ነበር። የሆነ በህይወት ውስጥ የሚከሰት ክስተት ነበር። መመለስ ቢቻል ጊዜን ብቻ አይደለም በጊዜው የነበረንን አስተሳሰብ ሁላ ቢሆን ሆኜ የምቀርበት ወቅት ነው። #ወርቃማው የህይወቴ ዓመት ነው. . "

". . . . ሕልመኞች ነበርን. . . እሩቅ ድረስ አልመናል. . . የኖርነው እስኪመስለን "


". . የሚደሳሰስ የሚጨበጥ እንደውም ምስል ሰርቶ የሚታይ ነገር ነበር. . "


". . . ቢያንስ በህልማችን ውስጥ ውብ ጎጆ አለ. . ታድለናል. ."


". .ሳስበው አሁን ራሱ ፈገግ እላለሁ የምርም እደሰትበታለሁ።"


"እውነት ስለነበር ነው. ."


"የምንወደድ ሰዎች ነበርን ነገር....በቃ ሁሉ ነገራቹ ይመርላቹ የተባልን..."


". . . . ህይወት ውስጥ ደስ የሚል ህመም አለ ኣ . . እምም

ብቻ ጥሩ ነው . . እስከምንችለው ደምቀናል. ."


". . ይበልጥ ደሞ አንቺ በቃ የማይደገም የሚመስል በህይወትሽ ውስጥ የሚገርም ከለር ለዛ ነበረሽ። የምታሳሺ አውርቼሽ አይደለም አስታውሼሽ የምረካብሽ ንፁህ እጅግ ንፁህ ማንንም የማትመስይ ራስሽን የሆንሽ ልጅ ልብ ያላት ግን ደሞ የምትገርም ...."

* * *

በምኞት ጀምረነው በትዝታ ላበቃነው የጋራ ታሪካችን የስልኮቻችን መፃፍያ ላይ ያሉት ቃላት ተክዘው ነበር . . . .

/ትዝታ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
1.8K viewsedited  19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 21:42:04 "አባ...አንድ ነገር ልነግርህ ነበር"

"ምን" ከሚቀጠቅጡት ጫማ አይናቸውን ሳያነሱ...

አቤኔዘር ዝምታው ውስጥ ጨለመ

ደጀኔ የአቤኔዘር አባት ዝምታው እንደ ጥልቅ ጉርጓድ አስደንግጧቸው ወደ ልጃቸው ሲዞሩ የአቤኔዘር በድን ሲባጎ ላይ ተንጠልጥሉ "አባ" አላቸው...

ይህን አይተው ከቅዠታቸው ባነኑ... ትንፋሻቸው ይቆራረጣል... አንገታቸው ስር ላብ አጥሞቋቸዋል... አይናቸው እንባ ሞላ... በዝግታ ከደኑት ... ትኩስ የእንባ እንክብሎች በዝምታ ረገፉ... ሲረጋጉ የባለቤታቸው ሲቃ ተሰማቸው...

"ተዋቡ?” አሉ ድምፃቸውን ገታ አድርገው።
ተዋቡ የታፈነ ለቅሶዋቸውን ለቀቁት... ሰውነታቸው እየተርገፈገፈ አለቀሱ ... ባለቤታቸው ደጀኔ ልባቸው ራደ... ክንዳቸውን ዘርግተው ተዋቡን ከለሏቸው ... የተዋቡ የንባ ጎርፍ ከደጀኔ ደረት ሸለቆ ውስጥ ሰጠሙ... ተዋቡ የባለቤታቸውንም ጨምረው አነቡ።


/ዘካሪያስ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
1.5K views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 18:14:43
"የሆነ ወቅት ላይ የማይበላ ሚታከክ
ቁስል አለ. . በግድ ምንፎክተው
በመፈለግና ባለመፈለግ
መሃል ምንታመመው. . . "

/ትዝታ /


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
2.0K views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 18:59:29 #ችግሮችን ለማለፍ ሁለት መንገድ አለህ. . . !?

#. 1. . 95% ሃላፊነቱን ለሰው መስጠት

#. .2. .95% ሃላፊነት እራስ መውሰድ

#. . እነዚህ ችግሮችን ለማፍ የተጠቀምከው መንገድ እድታረግ የሚያደርግህ ተግባሮች

#. . 1. 95% ሃላፊነቱን ለሰው ሰተካል.
- እከሌ ነው ይኼ ነገር ሂወቴ ላይ እዲፈፀም ያደረገው ፤ እነርሱ ናቸው . . . እያልክ ስለምትቀስር የችግሩ መውጫ መስሎ ሚታይክ
አመፅ ፣ ግድያ ፣ ብጥብጥ ፣ ስድብ . . .ና የጠቆምከው አካል ላይ ብቻ ማተኮር ይሆናል!

#2.. . . ለችግርህ 95% ሃላፊነቱን እራስህ ወስደህ ከሆነ ግን የሚታይህ መውጫ እራስህን ማየትና መመርመር ነው. . . ("እኔ ምን እያረኩ ነው ? ፣ ጊዜዬን ምን ላይ እያሳለፍኩ ነው ፣ የተናገርኩት ንግግር ፣ የሄድኩት መንገድ ፣ ያየሁት ነገር ፣ ያደረኩት ተግባር ፣ የተማርኩት ትምህርት፣ የመጣሁበት አመጣጥ . . ትክክል ነውን ?" ትላለህ ) ፣ ቀጥለህ ሃሳብን ታስበዋለህ. . ሃሳብን ማሰብ ስጀምር ደሞ እራስህንም ሃገርህንም መስራት ትችላለህ !!


# ከትላንቶቹ ተሽለን እንገኝ!

#ታሪክ መደጋገም ይብቃን!

# አንድ አይነት ቋንቋ ላንናገር እንችላለን ፣ አንድ አይነት ባህል ላይኖረን ይችላል ፣ እምነታችን ላይመሳሰል ይችላል. . . ብዙ . . ብዙ
ግን ሁላችንም ሰው ነን!!

/ትዝታ /


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
2.2K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 22:07:20
ፍልስፍና ከዘረያቆብ እስከ ሶቅራጥስ የሚለውን መፅሐፍ እየገዛሁት

" የዓለማየሁ ገላጋይን መፅሐፍ እንዴት አየሽው? " አለኝ

"አሌክስዬ ከተለመደው ውጪ ከፍ ብሎ መጥቶዋል" አልኩት

"እረ ብዙ ሰው ግን በዚህ መፅሐፉ ተናዶበታል ፣ የመለሰውም አለ " ብሎኝ እርፍ አለ . .

ይባስ ብሎ እዳለ ጌታ ከበደ በሚያዘጋጀው ዝግጅት ላይ ያለፈው ሳምንት እንግዳ "አሌክስዬ " ነበር (ምፅ ባልገኝም ፣ ዝግጅቱን በዩቲዩብ ገፃቸው ላይ ማየት ችያለው )

ከታዳሚ ውስጥ አንዷ "ሸልፌ ላይ እዳይኖር ማልፈልገው መፅሐፍ ነው" ብላ ክው አርጋኛለች(ያው መብቷ ነው ፣ በልኩ ነው ሰው ሚያስበው !)


. . . . ለምኑም ሰው ክፍቱ ሲነገረው ይደነግጣል እስቲ እራሳቹን ታዘቡ . . ስበከቶችን ወይም ሃዲሶችን የሚስማሙን የማይነኩንን ነገር ሲነግሩን ነው. . . . ስለ ጉድፋችን ሲነገረን እንደ ደነበረ ጥጃ እንፈረጥጣለን. . . .

ለምኑም እኔ መፅሐፉ እልል አርጎኛል. . .
ያለንበትን እውነት ቁልጭ አርጎ የነገረን ይመስለኛል. . . .

ከፈለጋቹት አንብቡት . . .



#የተማሩ መሃይም የሆኑት የብሄር ፖለቲካ አስጨፋሪዎቻቹን አስተሳሰብ እምቢ ማለት እስካለመዳቹ ድረስ በተማረ መሃይም ትመራላቹ . . . !!! (መልዕክቱ አለን አለን ምትሉ በሁሉም አቅጣጫ ያላቹን ብሔርተኞችን ይመለከታል)

ይኼን አለች ብላቹ እኮ ቻናሉን በንዴት ምለቁም አጠፉም ባትለቁ ግን ጥሩ ነው

/ትዝታ/



❀:✧๑♡๑✧
@tiztawe
@tiztaw
❀:✧๑♡๑✧
2.1K viewsedited  19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:13:47 እደመልእክት (ምለቃቸውን ስታነቡ ለሃሳቡ ብዬ ብቻ እደምፅፍ ተረዱልኝ፣ ምንም አይነት የፅሁፍ እውቀትም የለኝም፣ፀሐፊም አደለሁም ለመሆንም አደለም)

*
"ደናግል ሆይ የሰማያዊ ሕይወት አርአያና አምሳል የሆነችው የድንግል ማርያም ሕይወት ይኑራችሁ። እርስዋ ለክርስቶስ እናት ለመሆን በምንም የምታንስ አልነበረችም " የሚለውን ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ስለ ድንግሊቱ ሕይወት እንዲህ ይላላል ፦ ". . ልቀጥል አልቀጥል ንባቤን በሚል ጥርጣሬ ፌቷን አጠናሁት . . እዳጨለመችው ዓይኖቿ ይሰልሉኛል . . .

"የማን መፅሐፍ ነው . .?"

"የዲያቆን ሄኖክ. . "

"እምም. . "

"ይብቃሽ. . "

"እስቲ ልስማው . . "

. . . "እግዚአብሔር ዳኛዋ እንዲሆንላት ትፀልይ ነበር እንጂ በወንዶች መታየትን አችሻም ነበር። ከቤት ለመውጣት አትቸኩልም ነበር። በሕዝባዊ ስፍራዎች የሚያውቃት ሰው አልነበረም።

ማር እንደምትሰራ ንብ በቤትዎ ውስጥ ብቻ መቆየትን ትመርጥ ነበር።በቤትዋ የቀረውን ሁሉ ለድሆች በቸርነት ትሰጥ ነበር። ቃላትዋ ጥንቃቄን የተሞላ ነበር . . ድምፅዋም የተመጠነ ነበር ። ጮኻ አትናገርም ነበር። ማንም ላይ ክፋ አልተናገረችም. . ."

"ኤጭ . . በቃሽ"

ምራቄ ትን አለኝ . . . ስቅታዬ አንቆኝ ለማውራት ሲያኮላትፈኝ የዶርማችንን በር በርግዳው ወጣች. .

#
. . ባገኙት አጋጣሚ ስለ ሃጥያቴ ይዘምራሉ. . . ቢራቢሮ ለመሆን የምዳክር ትንሽዬ አባጨጓሬ ነኝ . .. እጭነቴን ይጠሉታል. . . ለአስርት ዓመታት አልጋ ወዳጁ ያረጋት እናቴ እግርና እጆቿ እኛን ለፍተው ለማብላት እንቢ ሲሉ ሞፈሩን የተቀበልኩ የበኩር ልጅ ነኝ. . ሂወት ያልገባቸው በእኩል የተሰፉ እህቶች አሉኝ . . በአባት ተንቀን የተተፋን እንቁላሎች ነን. . . እንዳይሰበሩ ነው አስኳሉን ለማቀፍ የቅርፊቱን ድርሻ ያለመቻሌን ያህል የተሸከምኩት

አዎ አመንዝራ ነኝ . . የርሃብ ሰልፍን ለመበተን ቀሚሴን አይኔን ጨፍኜ ገልጫለው። ያልተቀጣው አውታታ ልጅ ነኝ ፣ ያልተገራው ገርጋሪ

ስትሰበር ለማይቆም ጊዜ ታድያ እኔ ምን ላርግ ?
በብር ስክተት ላይ እደቆሙ የወርቅ ምስሎች የተመሰለችዋን ሴት ሆኜ እዳልፀና ለእህቶቼ ዳቦ አይገዛልኝም ፣ ለእናቴ ለህመሟ መድሃኒት አይሸምትልኝም . . ውልቅ ውልቅ እደሚለው የበሬ ቀንበር መሆን የመረጥኩት በኔ መገዛት በርሃብ የማያለቅስ ቀጫጫ ነፍስ ለማቆየት ነው. . የሚለበልበኝን የምድር ሲኦል እያለፍኩ ነው ታድያ ስለማላውቀው የሰማይ ሲኦል ለምን ፈራለው ?

#
ላስቆጣት አስቤ አደለም ያነበብኩላት "ስለቅድስት ድንግል ማርያም ስሰማ ጨለማ ነፍሴ ትረካለች ስለምትለኝ " ላስደስታት ማሰቤ ነበር

እናቴን እሷ ውስጥ አያለው. . ቀኑ መጥለቅ ሲጀምር እራሷን መስታወት ፊት አቁማ ታሰናዳዋለች . . ከድና ያዘጋጀችልኝን እራት እድበላ እያስጠነቀቀችኝ በሩን ከውጭ ቆልፋብኝ ትፈተለካለች. . የጫማዋ ቋቋታ ከጆሮዬ እስኪደበቅ በመረበሽ ሸኛታለው . . . እነዛ የሰቀቀን ምሽቶች አሁን ድረስ በቁሜ ያቃዡኛል. . . ቆርቆሮውን ንፋስ ሲያንጫጫው ትንሽዬ ነፍሴ ትርዳለች . . የፍርሃት ቁር ያንተከትከኛል. . . ጥርሶቼ እያፏጩም ቢሆን የሆዴን የርሃብ ጥሪ ለመመለስ ማኘካቸውን አይተዉም . . .

ቅድስትም እንደ እናቴ በምሽት መብረር የለመደች የለሊቱ ወፍ ነች. . . የመረቀዘውን ሴትነታቸው እራሳቸው ብቻ ይታመሙታል. .

. . ዶርም ውስጥ ካለነው አምስት ሴቶች ውስጥ በእፍታ ያህል ነው ምትቀርበኝ. . ላውቃት አልጥርም. . . ብቻ እዲሁ ነፍሷ ያሳሳኛል
ልፈልጋት ልውጣ እንዴ ?

#
". . . ያን ምሽት በመቅለስለስ የጀመረው ዝናብ ፍጥነቱን ጨምሮ ዘንቦ ለመገላገል በሚመስል ሁኔታ የቤታችንን የቆርቆሮ ጣርያ ያናጋዋል. . . የታሰረልኝ የቀዘቀዘ ሽሮ በእንጀራ ላንቃዬ ላይ ተለጥፎ ፍርሃቴ ያማስለዋል. . . የእናቴን ጫማ ማይመስል ኮቴ ዝናቡ ከቆርቆሮ ጋር ከሚያደርገው ጩኽት ጋር እየታገለ ለጆሮዬ በትንሹ አንሾኳሾከ. . . እግሮቼ በእርጥበት ሲሞቁ ነበር እራሴ ላይ እደሸናው ያስተዋልኩት . . መሽናቴ አናዶኝ ይሁን ኮቴው አስፈርቶኝ እሪ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ . . እምባዬ ኮቴው ቆርቆሮ በሩን ገንጥሉ ለመግባት ውለታው ይሁን ? አላውቅም. .

በማላውቀው ቀን ስነቃ እጄ ላይ መርፌ ተሰክቶ ከወገቤ በታች በህመም እየተሰቃየው ነበር. . . እናቴን ፈለኩ የለችም. . እስካሁን እፈልጋታለው የለችም. . ምን አልባትም ለወደፊትም አትኖርም

ደግ ኡስታዝ ናቸው ከዛ አልጋ ከወረድኩ ጀምሮ ያሳደጉኝ . . "ጁዲ" አሉኝ . . መልካምነት ፣እዝነት ፣ ርህራሄ፣ ማለት ነው. . . ምን አልባት ያ ሁሉ የድንጋይ ቁስል ለዚህ ለመታጨት ይሆናል. . ምን አልባት ይሄ የኔ መንገድ ይሆናል . . .እደምታዬኝ ትላንቴን የረሳው ብፅእት አደለውም በማንነት ጥያቄ ምሰቃይ ቁስለኛ ነበርኩ. . . " የሆነ ቀን እኚ ደግ አባቴ የዝሁር ሰላት ከመስጅድ ሰግደው ሲመለሱ በፀሃይዋ እየተበላው ስተክዝ አገኙኝ . .

"የአላህ በርሃብ ገደልኩሽ " አሉኝ እየተንሰፈሰፉ

"ማነኝ ጋሼ ? ማነኝ ? "አልኳቸው የተበታተኑ ላባዎቿን እንደምትለቅም እርግብ እየቃጣኝ

በእጃቸው ከያዙት ቅዱስ ቁርዓን ውስጥ አንዲት ምዕራፍ ከፍተው አነበቡልኝ

" በረፋዱ እምላለሁ ፣ በሌሊቱም ÷ ፀጥ ባለ ጊዜ፤ ጌታህ አላሰናበተህም ፤ አልጠላህምም። በመጨረሻይቱ( ዓለም ) ከመጀመርያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት። ጌታህም ወደ ፊት ( ብዙ ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል ፤ ትደሰታለህም። የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን ?(አስጠግቶሃል) የሳትክም ኾነህ አገኘህ ፣ መራህም". .

ላባዎቼን በሌላ ላባ ተክቼ ሙብረሬ ግድ ነበር ያረኩትም ይሄን ነው. .

#
አጠገቤ መታ ከደረጃው ድንጋይ ስትቀመጥ እዳላየ ተውኳት ፣ ሳልጠይቃት ስለራሷ ታወራኝ ነበር. . . ምድር ላይ ብቻዋን ያልተገፋች ሴት እደሆንኩ እዳስብ ፈልጋ ይሆናል. .

"ይቅር እባል ይሁን ?" እደመጣልኝ ጠየኳት

"በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ተኝተን ሳለ ባሉን የሰውነት ቀዳዳዎች ውስጥ ነፍሳት ማይገቡብን ፃድቅ ስለሆንን ይመስልሻል ?"

"እኔጃ "

"ሁላችንም የተጎናፀፍነው ነውር አለ . . በጉልበታችን ተንበርክከን በግንባራችን በመደፋት "ማረን" ምንለው. . . ስለማደፋችን የማይፀየፈን ፣ ስለደጋገምነው ጥፋት ይቅር ማለት ማይደከመው አምላክ ከሰማይ አለ. . . መፅሐፈ መቃብያን ሣልስ ላይ. . 'የወደደኝን እወደዋለሁ ፤ ያከበረኝንም አከብረዋለሁ ፣ ወደ እኔ የተመለሰውንም እጠብቀዋለሁ 'ብሎ የለ ታድያ ለምን ትፈርያለሽ ? "

"እኔጃ. . . ማይቆም ሃጥያት በምኑ ማረኝ ይላል ? እንደ ወፊቷ እምነት የለኝም ይመግበናል ብዬ ባዶ ሆዴን አልበርም፤ እንደ ዩሁዳ ሰነፍ ነኝ ዲናሩ ያስፈልገኛል ቃሉን እረግጬ ገላዬን ሸጣለው. . . "

"እስቲ ተመልከችኝ ?"

እየተረበሽኩ ተመለከትኳት. . . ሚያቅፉ አይኗች አሏት

"ዲናሩን በትኝው እጄን ያዢው አብረን እንለፈው ይሄን እሳት ? "

ለመጀመርያ ጊዜ ከአካሌ ላይ በሚፈሰው
ሰላማዊ ጠረን አፍንጫዬ እየሰከረ ነበር. .

*
እጇን ከእጄ ላይ ስታሳርፍ አንድ የአምላክን ተዓምር ውስጤ ያሰላስል ነበር

'ሁሉም ሰው አንድ መዳኛ ሰዋዊ መልኣክ አለው ! ጥሪውን ማዳመጥ ብቻ ነው !

/ትዝታ/

❀:✧๑♡๑✧
@tiztawe
@tiztaw
❀:✧๑♡๑✧
2.1K viewsedited  17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ