Get Mystery Box with random crypto!

. . .. ያልደረሳት ደብዳቤ . . . ልረሳሽ የወሰን | ትዝታዊ🐣

. . .. ያልደረሳት
ደብዳቤ . . .



ልረሳሽ የወሰንኩ ቀን . . . #1

: ::. . . የውሸት ተኝቼ እንደነበር አይነት መባነን ባነንኩ ፣ ስለ ውሸት ህልሜ ተከዝኩ . . . ጠላሁሽ
:
:
ልረሳሽ የወሰንኩ ቀን. . . #2

: ::. . . ለዓይኖቼ ፈተና የነበሩ እንባዎችን ተደብቄ አነባው ሙቅ አልነበሩም እንደ ጥቅምት ንፋስ ቅዝቃዜያቸው ይወጋል . . . ጠላሁሽ
:
:
ልረሳሽ የወሰንኩ ቀን . . . #3

: ::. . . የነበሩንን የቁስ ትዝታዎች ከኔ ሰወርኳቸው ፣ ያለፍንበትን ጎዳናዎች ሸሸዋቸው
፣ እጆችሽ ያረፈባቸውን አካሎቼን ናኳቸው እራሴን በመስታወት ማየት አቆምኩ. . . ጠላሁሽ

.
.
. ያላረኩትን ጠይቂኝ ልረሳሽ ፈልጌ?! . . . የሆነው ግን ይሄ ነው ልረሳሽ ስፈልግ የበለጠ አፈቅርሽ ነበር . . . ጠላሁሽ ባልኩት ልክ እሰቃይ ነበር . . . አየሽ ውዴ ፍቅሬ ድርጊታችን ላይ ፣ ማስታዎሻዎቻችን ውስጥ ፣ ጓዳናዎች ላይ አልነበረም . . . በነዚህ ስላልገባሽ በነዚህ አልወጣም አልሽ . . .

እናም
.
.
.

ላልረሳሽ የወሰንኩ ቀን. . . #

ስለነበረን ጊዜ ፣ ስለሆንሽልኝ መልካም ነገሮች፣ ስለጣፋጭ ፍቅርሽ ፣ ስለደግነትና መልካምነትሽ አሰብኩ እና አከበርኩሽ . . . መውደዴን ቀጠልኩ. . !


. . . ባለፍንባቸው ጎዳናዎች አልፋለው ፣ ትዝታዎቻችንን ለጊዜ ትቼያቸዋለው. . አሁን ነበርን ግን የለንም ሚለውን ተቀብያለው . . !

መሮጥም ባይሆን መራመድ ጀምርያለው. .

/ትዝታ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ