Get Mystery Box with random crypto!

ትዝታዊ🐣

የቴሌግራም ቻናል አርማ tiztawe — ትዝታዊ🐣
የቴሌግራም ቻናል አርማ tiztawe — ትዝታዊ🐣
የሰርጥ አድራሻ: @tiztawe
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.26K
የሰርጥ መግለጫ

ስላላቹ አመሰግናለው !!
ለሃሳብና አስተያየታቹ . . . . @tiztawe1_bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-15 18:34:23
ስናፍቀው ምፅፍለት . .

አንዳንዴ ህይወቴ ውስጥ መክሰም ያልነበረባቸው አደዬች እደከሰሙ ይሰማኛል . . ውስጤ እደብሶተኛ ለሊት ይኮማተራል . . ፍርሃት ይበርደኛል. . . ቀርፋፋ ናፍቆት ሲነዳኝ ይሰማኛል. . አዎ ጥልቅ ሀዘን ነው እሹሩሩ ማይባል . . . የሄዱ ማይመጡ በኔ ብቻ ሚዘከሩ ትዝታዎች አሉ . . . የደነስናቸው ዳንሶች ፣ ደረጃ ላይ የተካፈልናቸው ከንፈሮች . . . ባለመድከም ያወራናባቸው ለሊቶች ሁሉም እኔ ጋር ብቻ ይታወሳሉ . . እደተረሳው ማሰብም ፣ በሌላ ምዕራፍ እደተቀየርኩ ማሰብ . . .ሁሉም እደትኩስ ህመም ያማል ... ማያብብ ፍቅርን መናፈቅ ምን የሚሉት እብደት ነው? ይሉኛል. . . ምን አልባት ፈሪ ነኝ ምን አልባትም እብድ ነኝ ምን አልባትም ያኔ አላመንኩክም . . . አየህ በሌላ እቅፍ ውስጥ እያንቀላፋው በቅጡ ላልዘለቀው ፍቅርህ የተሰዋ ልቤን ወዳንተ እዲያልም እማፀነዋለው . . .

ታስታውሰኝ ይሁን . . ?

* * * *


. . ቢፅፍልኝ ብዬ ምመኘው

እኔ ውስጥ አሁንም አልሞትሽም . . . ! . .

* * *
/ትዝታ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
2.2K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 22:29:01
...ያባቴ ረጃጅም እርምጃዎች ያስቀኑኛል... በራፋችንን አቆልቁላ ምትገላመጠውን ጉብታ... እንደ ውሃ መንገድ ፉት ሲላት አይና እኮራበታለው... በራፌ ላይ ሆኜ ... አባቴ እኮ ነው ማለት ይቃጣኛል...እርምጃዎቼ ያባቴን እስኪያኽሉ... ብዙ ዳዴዎች አልፌያለው...
እርሱም ያኔ...እኔም ዛሬ...ለሌላ ፈተና ዳዴ እያልን ነው...


/ዘካሪያስ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
2.1K views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 18:53:30
". . ዝናብ ከመሬት ጋር በሚያካሂደው
ተፈጥሮኣዊ ዳንስ . . . ተመልካች
መሆን አልወድም ፣ አካሌ አያርፍልኝም
ምን አልባት በሁለቱ ፍቅር መሃል
መጠመቅ የፈለገ ጥላቻ ስላለኝ
ይሆናል . . . "

/ትዝታ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
2.4K views15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 20:21:18 . . .. እኔ እንደ ፃፍኩላት


እናትዬ... እንደምን ቆየሽልኝ... ዘመቻ ላይ ሁኜ ስለነበር ባለፈው የላክሽልኝ ደብዳቤ አሁን ወደካምፕ ስመለስ ነው የደረሰኝ። እድልዬ ስምንተኛ ክፍል በጥሩ ውጤት እንዳለፈች ሰማው። ደስ ብሎኛል የላክሽልኝ መፅሃፍም ደርሶኛል ብለሽ ሳሚልኝ።

እናትዬ አንቺ ለጤናሽ እንዴት ነሽ። ብቻሽን ጥዬሽ ... ልጆቹን እንዴት አረግሻቸው... አስቸገሩሽ ይሆን ... ናፍቀሺኛል እናቴ።

ወደቤት መመለሻዬን ቀን ስጠብቅ አለሁ።

ናፍቆትስ ነው መሰል አሁን እባባለሁ... በሞት ላንቃ ተላውሼ ስመለስ ... መች ያበቃል እላለው... ድካም አይገልም ... ጥሩ ነው ... ትስፋ ሲኖር...ድካም አይገድም... ምናልባት ጥሩ አይደለም... መቻልን ተስፋ አድርገን ከቆየን... ድካም ቢገድለን አይሻልም... ስለኔ አይደለም ማወራው እናቴ ... አይናቸውን ጨፍነው የገቡ ብዙ ጓዶች አይቻለው... ምናልባት በድፍረት... በጀግንነት ይሆናል... አላውቅም ...ወይም ፈሪ ነኝ ወይም ጀግንነት አልገባኝም...

እናቴ እዚህ ይደክማል ... ካንቺ ጋር ስሆን ሰላም ይዞ የሚነፍሰው ንፋስ... እዚህ ጫጫታ ይዞ ይመጣል...

የቀን አቆጣጠሬ ጠፍቶኛል... በፀህይ ፋንታ የመጀመሪያውን የተኩስ ድምፅ መጠበቀ ጀምሪያለው... ከቀልሃው እኩል እንደቅጠል የሚረግፉ ነፍሶች ላይ አይኔን እጨፍናለው... "ወንድሜ ነህ ይቅር በለኝ" አልልም... እስትንፋሳቸው አካላቸውን ለቆ በወጣበት ፍጥነት ከንቅ ሃሳቤ ይጠፋሉ... በመሃከላችን ያለው ልዩነት የቦታ ብቻ እንደሆነ አስባለው... ባልገዛነው ሃሳብ ታስረን ተፋጠን እንዋደቃለን... በእጃችን ከምንዳሣቸው ፍላጎቶቻችን ርቀን በአማላይ ሃሳቦች ቅዠት እንድንዋልል ላደረጉን ሰዎች እንሞታለን ... ይደክማል... ቢሆንም ድካም አይገልም...እሱም ጥሩ ነው ...ተስፋ ካለን...

በዚህ ድርጊቴን እጠይቃለው በዚህ አንቺን አስባለው... ነፍስ ለመብላት ስጋሽን መበደሌን... ብቸኝነትን ማስታቀፌን አስባለው... ዛሬ ላይሆን ልጅ ነፍስሽን ሳስረጅብሽ እየታወቀኝ ... ቀዝቃዛ ሃዘን እታመማለሁ... መቼ ልምጣ አልልሽ ነገር... መችህ ትመጣለህ መልስ የለው ነገር...ልቤ ይርዳል ልቀር መቻሌን ሳስብ። ሰግቼ ተስፋሽን ልገምሰው አልሻም ።

እነዚህ ሃሳቦች አንደበቴ ደጃፍ ያልሞቱት ... ካለሁበት አለም ውጪ... አንቺ ስላለሽ ነው... በለሆሳስ ያንሾካሸኩት... ኩልል ብሎ እንደሚሰማሽ ስለማውቅ ነው ... አንዳንድ ገፆች አሸናፊና ተሸናፊ የግድ ይፈልጋሉ... እዚህ ገፅ ላይ... ያሸናፊው ስም የኔ ይሆናል... ላንቺ ስል አሸንፋለው... ጀግንነትና ጀብዱ ፍለጋ አይደለም... ፈሪ ልቤን አንቺ ብቻ ንነሽና ምታውቂው... ያኔ እንዳጀገንሽ አሁንም ገስጪልኝ እናትዬ

ስትይልኝ እድልዬን አባትሽ ኮርቶብሻል በይልኝ። ግንባሯን ሳም አርጊልኝ። ሁላችሁንም እዎዳችኋለው።

ደህና ቆዪኝ እማ



. . . . እኔ እንደ ፃፍኩለት

ናፍቀከኛል

"መች ትመጣለህ . . . ?" አትልም የወታደር ሚስት! ጦርነት ማለቅያውን ቀን አይቆርጥም . .


ጥማተኛ መሬት ዝናብን ሚናፍቀው ለምን ይመስልካል ? አንዳንዴ ጥማትህን ለመቁረጥ ብቻ ውሃ አፈልግም . ... ውሃው ኖሮ ሊላው ሲጠጣው በማየትህ ብቻ ትረካለህ. . .

ከትራሴ ለመንተራስ አንተን ከፈለገው በላይ ነፍሴ ልጆቼ በእቅፎችክ አኩኩሉ ሲጫወቱ ማየት ጠምቶታል. . .

የወታደር ሚስት መሆን ያስፈራል . . . እንደ ሚሉት ጀግንነት አልተሰማኝም . . አብሶ ወንድሜን ለመማረክ ወይም ለመግደል እንደ ሄድክ ማወቅ ያማል . . . ኢላማውን ያላወቀ ፣ አላማ ያለውን ተንኮል ማገልገል ያስፈራል. . .

ሆኖም ቀረ በአንዱ ቤት ውስጥ ጀግና ትባላለክ ፣ ባለኽ ጎረቤት የነበሩት ከፈራሽ የተረፉት ነፍሶች ውስጥ ደሞ የጭካኔ ሃውልት ይቆምልካል . . .

የአፍቃሪ ነፍስ ግን እዴትም ይሁን ይሄን ትላለች
. . . ባሌ ሆይ በሰላም ናልኝ !

እኔና ልጆችህ ያለ በር ነን. .

በር ያላጣች ሃገርን ፣ በር ደብቀው ለላኩክ ባለወቅቶች . . . በስንት ደም ሁለቱን በር ገጥመው እንደ ምትመለስ ባላውቅም . . በፍቅራችን ለተበረከቱት ልጆቻችን ዓለም ከሚሰጣቸው እውቀት በላይ ከፈጣሪ በተሰጣቸው ጥበብ አሳድጋቸዋለው. . . ምን አልባት ለሃጥያታችን መዳኛ ይሆኑን ይሆናል . . ?

የምልካቸውን መፅሐፎች ከእሳት ግብግብ መሃል ታነባለክ ብዬ እርግጠኛ ሆኜ ሳይሆን ምን አልባት በአንዱ ቀን የገለጥካት ገፅ መሳርያህን ካስጣለችክ በሚል ተስፋ ነው . . . አዎ ታማኝ ወታደር ነህ ፣ አውቃለው ለዝና ሳይሆን ለክብር ምትሰዋ ፅኑ ነህ . . . ይሄ ለኔም ክብር ነው!

ግን ይሄ ከማን ጋር ነው ? ሙሴ ህዝቦቹ እያመፁበት ወደከንአን ምድር ሊያሻግራቸው ቻለ እንጂ እዲጠፉ አልፀለየም ወይም እዲጠፉም አላሸረበም . . .

መንፈሳዊ ወታደር ስትሆን ፍርኦንን ሚወጋልህ እውነት ትገነባለህ ፣ ወንድምህንም በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ጀርባህን አሰጠውም!

እንደ ሙሴ ያርገን የኔ ፍቅር. . .

ናፍቀከኛል . . .

"መቼ ትመጣለህ ?" ግን አልልህም. . . የወታደር ሚስት ይሄን አጠይቅም ተስፋ ታረጋለች እንጂ . .

በድል ተመለስም አልልህም . . . ድል የለውምና
ብቻ በሰላም ናልኝ !

እወድሃለው !

/ ዘካርያስ . . . . .ትዝታ /


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
2.3K views17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 19:49:19
". . አንድ አንዴ መፅሐፍት ውስጥ ማርጀት
ያምረኛል ፣ በወደድኩት ገፀባህሪ
ነፍስ ውስጥ መብቀል . . በብዕረኛው
መቀለም . . . አንድ አንዴ በሰዓሊያን
ጣት ውስጥ መነደፍ ፈልጋለው . .
አንድ አንዴ ደሞ ፀጥ ያለውን . .
ባህር ናፍቃለው ፣ በተፈጥሮ ውስጥ
መጥፋት መብረር . . . ሰው ሆኜ ሰው
አለመሆን ማየት ያምረኛል . . . ጩኽታም
ነፍስ ነው ያለኝ . . "

/ትዝታ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
2.2K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 20:14:21
"በወይኑ ስፍራ በጥበብ ላይ ባይኽ
ከሴሎ ሴት ልጆች አንዷ አይደለሁም
በአታሞ ድምፅ እዳልማርክህ ፣
እርቃን ስጋ ፣ ቀጫጫ ነፍስ ነው ያለኝ
እደገባሁኹ ቀስ ብለህ ሳለኝ . . . "!

/ትዝታ/

| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
2.4K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 21:08:41
...ምናልባት...በ ስንፍና እና በምርጫ መካከል ያለው ልዩነት ግልፅ የማይሆነው...በ ነፃነትኛ መኖር እስክትጀምር ይሆናል...

/ዘካሪያስ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
2.6K viewsedited  18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 18:33:18
" ተፈጥሮ ባንቺ በኩል ትዋባለች. .
ፊትሽን የመለስሽላቸው ነፍሶች
ይለመልማሉ. . .በፈገግታሽ ከሃዘን
ቁር ይላቀቃሉ . . .ከገፅሽ ብርሃን
ይፈልቃል. . .ከትንፋሽሽ ጋር
ሰላም ይነሰነሳል . . . የህይወት
ጠዋቴ ነሽ ዘውትር ምትነጊልኝ. . .
የምነፃብሽ ንሰሃዬ. . .የነፍሴን
እውነት የምኖርብሽ. . . የማፈቅርሽ "

/ዘካርያስ/

. . .

". . . የውቂያኖስ ውሃ በሙቀት እየተነነ
ነው ፣ በጨረቃ ፉጨት ፀሃይ አንቀላፍታለች
ከዋክብት ይተነፍሳሉ ፣ በዝች ቅዱስ
ውበት በወረራት ምሽት ልቤ ካንተ ልብ
ተንተርሳ እውነቷን ትሰማለች . .
ኦ . . . እንዴት ያለህ ፍቅር ነህ ?!. . . "

/ትዝታ/

| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
3.1K views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 21:16:32
". . . ዘናባማ ቀን አሳልፍለው ፣ ሰዎች
ፀሃይ እየሞቁ ነው . . እኔ ለብርዱ
'እትትትትት' ስል እነሱ ለሙቀቱ ያራግባሉ
. . ሙቀታቸው ላይ ምደርስ አይመስለኝም
ግን በጊዜዬ ደርሼም እንደምደርስም
አምኜ አውቃለው . . . "

/ትዝታ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
2.9K views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 19:16:25 የሆነ ምሉዕነት መንፈሱን አጥግቦታል... የቤቱ እያንዳንዱ ጥግ ብርሃን ይፈንጥቃል... ለሱ ብቻ የሚሰማውን ዝማሬ ያዜማል... እርሱ ብቻ በሚያስተውለው መንገድ ዝማሬውን ተከትለው የቤቱ እቃዎች ያሸበሽባሉ ... ሁሉ ነገር ያጫውተዋል... ከመታጠቢያ ቤት የሱን ሸሚዝ ብቻ ለብሳ ስትመጣ ጎትቶ ወደ አልጋው አስቀመጣት... ልመና እና ጉጉት ኩራት በተቀላቀለው ደምፅ "ዛሬ አትሂጅ ..." አላት ካንገቷ ስር የሚፈልቀውን መአዛ እየማገ...
"ሂድ ሞዛዛ... " ብላው ካልገው ላይ ተስፈንጥራ ተነሳች...
"ምን አለበት?"
ስልኳን እየጎረጎረች "አይሆንማ "
"እባክሽ አለሜ"
"ተፌ ደሞ እያወክ"
ጉጉቱ ለሷ ፈተና እንደሚሆንባት ሲገባው ዝም አለ ...ገፁ ላይ ነፍስ ስታጣ አይኗ ሃዘን ለበሰ... ካልጋው ላይ ወጥታ እቅፉ ውስጥ ተወሸቀች... "ተፌ..."
"ወዬ አለሜ..."
"በነፃነት ውስጥ ላፈቅርህ እፈልጋለው..."


የሚለው አልነበረውም አጥብቆ አቀፋት አናቷን ሳማት ...ሲተቃቀፉ ከአካሏ ላይ ስሮች ሲበቅሉ ይታወቃታል... ቆዳቸው ሲገናኝ እርስ በርስ ሲዋዋጡ ታስተውላለች ካንደበቱ ቃል ባይወጣውም የልቡ ምት ስልቱን ሲቀይር ይሰማታል...ምንም አትለውም...እቅፉ ውስጥ እንዳለች ዝምታዋን ያዳምጣል... ዝምታዋ ላይ ትዝታ ይቀዳበታል... እና በትውስታዎቹ ልክ ደጋግሞ ይስማታል...


/ዘካሪያስ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
2.6K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ