Get Mystery Box with random crypto!

የሆነ ምሉዕነት መንፈሱን አጥግቦታል... የቤቱ እያንዳንዱ ጥግ ብርሃን ይፈንጥቃል... ለሱ ብቻ የ | ትዝታዊ🐣

የሆነ ምሉዕነት መንፈሱን አጥግቦታል... የቤቱ እያንዳንዱ ጥግ ብርሃን ይፈንጥቃል... ለሱ ብቻ የሚሰማውን ዝማሬ ያዜማል... እርሱ ብቻ በሚያስተውለው መንገድ ዝማሬውን ተከትለው የቤቱ እቃዎች ያሸበሽባሉ ... ሁሉ ነገር ያጫውተዋል... ከመታጠቢያ ቤት የሱን ሸሚዝ ብቻ ለብሳ ስትመጣ ጎትቶ ወደ አልጋው አስቀመጣት... ልመና እና ጉጉት ኩራት በተቀላቀለው ደምፅ "ዛሬ አትሂጅ ..." አላት ካንገቷ ስር የሚፈልቀውን መአዛ እየማገ...
"ሂድ ሞዛዛ... " ብላው ካልገው ላይ ተስፈንጥራ ተነሳች...
"ምን አለበት?"
ስልኳን እየጎረጎረች "አይሆንማ "
"እባክሽ አለሜ"
"ተፌ ደሞ እያወክ"
ጉጉቱ ለሷ ፈተና እንደሚሆንባት ሲገባው ዝም አለ ...ገፁ ላይ ነፍስ ስታጣ አይኗ ሃዘን ለበሰ... ካልጋው ላይ ወጥታ እቅፉ ውስጥ ተወሸቀች... "ተፌ..."
"ወዬ አለሜ..."
"በነፃነት ውስጥ ላፈቅርህ እፈልጋለው..."


የሚለው አልነበረውም አጥብቆ አቀፋት አናቷን ሳማት ...ሲተቃቀፉ ከአካሏ ላይ ስሮች ሲበቅሉ ይታወቃታል... ቆዳቸው ሲገናኝ እርስ በርስ ሲዋዋጡ ታስተውላለች ካንደበቱ ቃል ባይወጣውም የልቡ ምት ስልቱን ሲቀይር ይሰማታል...ምንም አትለውም...እቅፉ ውስጥ እንዳለች ዝምታዋን ያዳምጣል... ዝምታዋ ላይ ትዝታ ይቀዳበታል... እና በትውስታዎቹ ልክ ደጋግሞ ይስማታል...


/ዘካሪያስ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ