Get Mystery Box with random crypto!

. . .. እኔ እንደ ፃፍኩላት እናትዬ... እንደምን ቆየሽልኝ... ዘመቻ ላይ ሁኜ ስለነበር ባ | ትዝታዊ🐣

. . .. እኔ እንደ ፃፍኩላት


እናትዬ... እንደምን ቆየሽልኝ... ዘመቻ ላይ ሁኜ ስለነበር ባለፈው የላክሽልኝ ደብዳቤ አሁን ወደካምፕ ስመለስ ነው የደረሰኝ። እድልዬ ስምንተኛ ክፍል በጥሩ ውጤት እንዳለፈች ሰማው። ደስ ብሎኛል የላክሽልኝ መፅሃፍም ደርሶኛል ብለሽ ሳሚልኝ።

እናትዬ አንቺ ለጤናሽ እንዴት ነሽ። ብቻሽን ጥዬሽ ... ልጆቹን እንዴት አረግሻቸው... አስቸገሩሽ ይሆን ... ናፍቀሺኛል እናቴ።

ወደቤት መመለሻዬን ቀን ስጠብቅ አለሁ።

ናፍቆትስ ነው መሰል አሁን እባባለሁ... በሞት ላንቃ ተላውሼ ስመለስ ... መች ያበቃል እላለው... ድካም አይገልም ... ጥሩ ነው ... ትስፋ ሲኖር...ድካም አይገድም... ምናልባት ጥሩ አይደለም... መቻልን ተስፋ አድርገን ከቆየን... ድካም ቢገድለን አይሻልም... ስለኔ አይደለም ማወራው እናቴ ... አይናቸውን ጨፍነው የገቡ ብዙ ጓዶች አይቻለው... ምናልባት በድፍረት... በጀግንነት ይሆናል... አላውቅም ...ወይም ፈሪ ነኝ ወይም ጀግንነት አልገባኝም...

እናቴ እዚህ ይደክማል ... ካንቺ ጋር ስሆን ሰላም ይዞ የሚነፍሰው ንፋስ... እዚህ ጫጫታ ይዞ ይመጣል...

የቀን አቆጣጠሬ ጠፍቶኛል... በፀህይ ፋንታ የመጀመሪያውን የተኩስ ድምፅ መጠበቀ ጀምሪያለው... ከቀልሃው እኩል እንደቅጠል የሚረግፉ ነፍሶች ላይ አይኔን እጨፍናለው... "ወንድሜ ነህ ይቅር በለኝ" አልልም... እስትንፋሳቸው አካላቸውን ለቆ በወጣበት ፍጥነት ከንቅ ሃሳቤ ይጠፋሉ... በመሃከላችን ያለው ልዩነት የቦታ ብቻ እንደሆነ አስባለው... ባልገዛነው ሃሳብ ታስረን ተፋጠን እንዋደቃለን... በእጃችን ከምንዳሣቸው ፍላጎቶቻችን ርቀን በአማላይ ሃሳቦች ቅዠት እንድንዋልል ላደረጉን ሰዎች እንሞታለን ... ይደክማል... ቢሆንም ድካም አይገልም...እሱም ጥሩ ነው ...ተስፋ ካለን...

በዚህ ድርጊቴን እጠይቃለው በዚህ አንቺን አስባለው... ነፍስ ለመብላት ስጋሽን መበደሌን... ብቸኝነትን ማስታቀፌን አስባለው... ዛሬ ላይሆን ልጅ ነፍስሽን ሳስረጅብሽ እየታወቀኝ ... ቀዝቃዛ ሃዘን እታመማለሁ... መቼ ልምጣ አልልሽ ነገር... መችህ ትመጣለህ መልስ የለው ነገር...ልቤ ይርዳል ልቀር መቻሌን ሳስብ። ሰግቼ ተስፋሽን ልገምሰው አልሻም ።

እነዚህ ሃሳቦች አንደበቴ ደጃፍ ያልሞቱት ... ካለሁበት አለም ውጪ... አንቺ ስላለሽ ነው... በለሆሳስ ያንሾካሸኩት... ኩልል ብሎ እንደሚሰማሽ ስለማውቅ ነው ... አንዳንድ ገፆች አሸናፊና ተሸናፊ የግድ ይፈልጋሉ... እዚህ ገፅ ላይ... ያሸናፊው ስም የኔ ይሆናል... ላንቺ ስል አሸንፋለው... ጀግንነትና ጀብዱ ፍለጋ አይደለም... ፈሪ ልቤን አንቺ ብቻ ንነሽና ምታውቂው... ያኔ እንዳጀገንሽ አሁንም ገስጪልኝ እናትዬ

ስትይልኝ እድልዬን አባትሽ ኮርቶብሻል በይልኝ። ግንባሯን ሳም አርጊልኝ። ሁላችሁንም እዎዳችኋለው።

ደህና ቆዪኝ እማ



. . . . እኔ እንደ ፃፍኩለት

ናፍቀከኛል

"መች ትመጣለህ . . . ?" አትልም የወታደር ሚስት! ጦርነት ማለቅያውን ቀን አይቆርጥም . .


ጥማተኛ መሬት ዝናብን ሚናፍቀው ለምን ይመስልካል ? አንዳንዴ ጥማትህን ለመቁረጥ ብቻ ውሃ አፈልግም . ... ውሃው ኖሮ ሊላው ሲጠጣው በማየትህ ብቻ ትረካለህ. . .

ከትራሴ ለመንተራስ አንተን ከፈለገው በላይ ነፍሴ ልጆቼ በእቅፎችክ አኩኩሉ ሲጫወቱ ማየት ጠምቶታል. . .

የወታደር ሚስት መሆን ያስፈራል . . . እንደ ሚሉት ጀግንነት አልተሰማኝም . . አብሶ ወንድሜን ለመማረክ ወይም ለመግደል እንደ ሄድክ ማወቅ ያማል . . . ኢላማውን ያላወቀ ፣ አላማ ያለውን ተንኮል ማገልገል ያስፈራል. . .

ሆኖም ቀረ በአንዱ ቤት ውስጥ ጀግና ትባላለክ ፣ ባለኽ ጎረቤት የነበሩት ከፈራሽ የተረፉት ነፍሶች ውስጥ ደሞ የጭካኔ ሃውልት ይቆምልካል . . .

የአፍቃሪ ነፍስ ግን እዴትም ይሁን ይሄን ትላለች
. . . ባሌ ሆይ በሰላም ናልኝ !

እኔና ልጆችህ ያለ በር ነን. .

በር ያላጣች ሃገርን ፣ በር ደብቀው ለላኩክ ባለወቅቶች . . . በስንት ደም ሁለቱን በር ገጥመው እንደ ምትመለስ ባላውቅም . . በፍቅራችን ለተበረከቱት ልጆቻችን ዓለም ከሚሰጣቸው እውቀት በላይ ከፈጣሪ በተሰጣቸው ጥበብ አሳድጋቸዋለው. . . ምን አልባት ለሃጥያታችን መዳኛ ይሆኑን ይሆናል . . ?

የምልካቸውን መፅሐፎች ከእሳት ግብግብ መሃል ታነባለክ ብዬ እርግጠኛ ሆኜ ሳይሆን ምን አልባት በአንዱ ቀን የገለጥካት ገፅ መሳርያህን ካስጣለችክ በሚል ተስፋ ነው . . . አዎ ታማኝ ወታደር ነህ ፣ አውቃለው ለዝና ሳይሆን ለክብር ምትሰዋ ፅኑ ነህ . . . ይሄ ለኔም ክብር ነው!

ግን ይሄ ከማን ጋር ነው ? ሙሴ ህዝቦቹ እያመፁበት ወደከንአን ምድር ሊያሻግራቸው ቻለ እንጂ እዲጠፉ አልፀለየም ወይም እዲጠፉም አላሸረበም . . .

መንፈሳዊ ወታደር ስትሆን ፍርኦንን ሚወጋልህ እውነት ትገነባለህ ፣ ወንድምህንም በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ጀርባህን አሰጠውም!

እንደ ሙሴ ያርገን የኔ ፍቅር. . .

ናፍቀከኛል . . .

"መቼ ትመጣለህ ?" ግን አልልህም. . . የወታደር ሚስት ይሄን አጠይቅም ተስፋ ታረጋለች እንጂ . .

በድል ተመለስም አልልህም . . . ድል የለውምና
ብቻ በሰላም ናልኝ !

እወድሃለው !

/ ዘካርያስ . . . . .ትዝታ /


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ